58 ሻማዎች ክፍል አንድ / በእዝራ እጅጉ
ውድ ክቡራት እና ክቡራን የዚህ ገጽ ተከታታዮች ‹‹58 ሻማዎች›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን 58ኛ አመት በኦን ላይን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለማክበር የተነሳሳነው አንድም ጣቢያው የሁላችንም ስለሆነ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ኢቲቪን ስንመለከት አድገናል፡፡ከሚተላለፉት ምክር አዘልና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ተጠቅመናል፡፡ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችንም
ቃርመናል፡፡ ጣቢያው በ4 መንግስታት እንደማለፉ ስለ ሁሉም መንግስታት የሚናገረው አለው፡፡ ኢቲቪ የኢትዮጵያን ታሪክ በቪድዮ የያዘ ፣ የወቅቱ ሁኔታዎችን የሚገልጽ መረጃ ያከማቸ እና ብዙዎች የደከሙለት የባለሙያዎች ቤት ነው፡፡ ልበ-ብርሀን እና እንደ ብረት የጀገኑ ታታሪ ባለሙያዎች ለፍሬ ያበቃ አንጋፋ ቤት ነው፡፡ ባለፉት 58 ዓመታት ኢቲቪን 22 የሥራ መሪዎች
መርተውታል፡፡ የዚህን
አንጋፋ ጣቢያ ልደት ልናከብር ሀሳብ ስናፈልቅ የእስከዛሬዎቹ የተቋሙ ባለሙያዎች እስከ ህይወት መስዋእትነት የከፈሉበትን ልክ ለማሳየትና የባለሙያዎቹንም እውቅና እና ትጋት በደማቅ ብእር ልንከትበው ፈልገን ነው፡፡
አንድ ተቋም ያለ ብቁ ባለሙያ ተቋም ሊባል አይችልምና
እነሆ ይህ ጣቢያ
በሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ደክመውለት፤ ሮጠውለት ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ይህን ግማሽ ክፍለ-ዘመን የቆየ ጣቢያን እንኳን ለበአለ-ልደቱ አደረሰው እንላለን፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ባለሙያዎችን እና የሚድያ ተቋማትን ታሪክ በምርምር መልክ እየሰነደ እና ለትውልድ እያስቀመጠ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ኢቲቪም ካሉት ሚድያዎች ከአንጋፋዎቹ ተርታ የሚመደብ እንደመሆኑ የያዛቸው የቪድዮ ሰነዶች ስለ ቀደመችው ኢትዮጵያ በሚያሳምን መልኩ የሚናገሩ ናቸው፡፡ እነዚህ የቆዩ ሰነዶች
አዲሱን ትውልድ የማስተማር አቅም ስላላቸው ከወዲሁ ለህዝብ እይታ የሚቀርቡበት ስልት ቢነደፍ ጠቃሚ ነው እንላለን፡፡
የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን አባላት
በራሳችን ተነሳሽነት ባለፉት 7 አመታት የሀገራችን አንጋፋ ሚድያዎች አመሰራረት ፤ እድገትና አሁናዊ ሁኔታላይ
መለስተኛ ዳሰሳዊ ጥናት ስናሰናዳ ቆይተናል፡፡ እንዲሁም
በሙያቸው ላይ ጉልህ አሻራ ያኖሩ ባለሙያዎች ወደየት አሉ? ምን የተለየ ነገር ከወኑ? ስንል የህይወት ታሪካቸውን በብዙ ጥረት ስናሰባስብ ቆይተናል፡፡ 180 ያህሉን የሚድያ ሰዎች ደረጃውን በጠበቀ ጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ ‹‹መዝገበ-አእምሮ ››በሚል ርእስ አሳትመን አስመርቀናል፡፡
የባለሙያዎቹ ታሪክ በአንድ በኩል በከፊል የመስሪያ ቤታቸውን ታሪክ የሚነግር ነው፡፡
እስከዛሬ የህይወት ታሪካቸውን ከጻፍንላቸው ባለሙያዎች ውስጥ 50 ያህሉ ኢቲቪ በአንድ ወቅት ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ ይገኙበታል፡፡ብዙዎች በታሪካቸው ላይ እንዳቀረቡትና
ለእኛም በተደጋጋሚ እንዳጫወቱን
ኢቲቪን እንደ ቤታቸው ከማየታቸው የተነሳ ለእድገቱ ይቆረቆራሉ፡፡ ምንም ቢሆን ምን የተማርንበት ፤ አይረሴ ትዝታ ያሳለፍንበት ቤት ነው በማለት የኢቲቪን መልካም ቦታ መድረስ እንደሚመኙ ነግረውናል፡፡ኢቲቪ በ58አመት ውስጥ ማደግ የሚገባውን ያህል አድጓል ወይ? በዘመናት ውስጥ ያሉት ውጣውረዶች ምንድናቸው ?የሚለውን ወደፊት በጥናት መልክ የምናየው ሆኖ አሁን ግን ስራችን የልደት ሻማ ከመለኮስና ባለሙያዎችን ከማውሳት አያልፍም
፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽንም ኢቲቪን የሚያስታውሱ የቀድሞ ቪድዮዎችን
ለእይታ በማቅረብ ፤ የባለሙያዎችንም ትዝታ ከኢቲቪ አመሰራረት ጋር አንድ ላይ በማድረግ 58ቱን ሻማ ለመለኮስ አስበናል፡፡ በተጨማሪም ለጣቢያው እዚህ መድረስ ጉልህ ሚና የነበራቸውን ሰዎች በደምሳሳው እናነሳለን፡፡ ይህ ማለትግን እዚህ ባለሙያዎች
በተጨማሪም ሌሎች የሉም ለማለት ሳይሆን ለእኛ ለመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ፈቃደኛ ሆነው ታሪካቸውን የሰጡንን ብቻ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ለማካተት ወስነናል፡፡ ከዛሬም ጥቅምት 21 2015- ጥቅምት 30 2015 ተከታታይ ጽሁፎችን እያወጣን የኢቲቪን 58ኛ አመት የልደት በአል እናስባለን፡፡
በመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ታሪካቸው የተካተተ የኢቲቪ ባለሙያዎች
1.አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ
2.ኢንጂነር ገሰሰ አባይ
3. አባባ ተስፋዬ ሳህሉ
4.አቶ ሰለሞን ተሰማ
5. ተክሉ
ታቦር
6. አሳምነው ገብረወልድ
7.እሌኒ መኩርያ
8.ጌታቸው ኃይለማርያም
9.ህሊና ተፈራ
10. ብርቄ ወልደገብርኤል
11. ተሾመ
ብርሀኑ
12.ታዬ
በላቸው
13. አማረ
አረጋዊ
14. ኢሳያስ
ሆርዶፋ
15. ዜናነህ
መኮንን
16. ጸጋዩ
ሀይሉ ተፈራ
17 . ስለሺ
ሽብሩ
18. ሮማን
ተገኝ
19 . አስካለ ተስፋዬ
20. አዲስ
አለም ሀድጉ
21. እሸቴ አሰፋ
22 ዘሩ በላይ
23. ገነት አየለ
24. መሳይ ወንድሜነህ
25. መቲ ሸዋዬ ይልማ
26. ተገኝ ጃለታ
27. አሸብር ጌትነት
28. አንድነት አማረ
29. እመቤት ደመቀ
30. ዮሀንስ አያሌው
31. ደረጀ ገብረማርያም
32. ጌጡ ተመስገን
33.ፍጹም ጌታቸው
34. መስከረም ጌታቸው
35.መአዛ መላኩ
36.መኳንንት በርሄ
37. አንተነህ
ደግፌ
38. ጀማል
አህመድ
39 ከብካብ
አስፋው
40. ሺበሺ
አለማየሁ
41. ዘላለም
ቱሉ
42. አስናቀች ጸጋዬ
43. አይናለም ባልቻ
44. ሻምበል አክሊሉ ዘለቀ
45. ሰብለወንጌል አሰፋ
46. ብዙወንድም አገኘሁ
47. ሀብቴ ገመዳ
48 ሰላማዊት ካሳ
49 . ሳሙኤል ፍቅሬ
በነገራችን ላይ እስከ ህዳር 17 2015 ዓ.ም
ታሪካቸው የሚጠናቀቅ 28 የኢቲቪ ሰዎች ታሪካቸው እጃችን ላይ አልቆ ባለመድረሱ ምክንያት
በዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም፡፡ ታሪኩ ሲገባ ዝርዝሩን አፕዴት የምናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡
በዚህ
አጋጣሚ በኢትዮጵያ ቲቪ ሰርተው ጉልህ አሻራ አኑረዋል የምትሏቸውን በቴክኒክ ፤ በጋዜጠኝነት እና በሚድያ አመራርነት ላይ ያሉ ሰዎችን በtewedajemedia@gmail.com ብትጠቁሙን
ስራችንን የተሟላ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ለኢቲቪ ያላችሁንም የእንኳን አደረሰህ መልእክት ማድረስ ትችላላችሁ፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ