የፎቶ ባለሙያ ዳኜ አበራ

   

 

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያው ዘርፍ ጉልህ አሻራ የነበራቸውን ጋዜጠኞች፣ የቪድዮና የፎቶ ባለሙያዎች  የቴክኒክ ሰዎች ፣ የሚድያ መምህራን ፣ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሥራ መሪዎችን  እያፈላለገ የህይወት ታሪካቸውን እየሰነደ ይገኛል፡፡ ይህ የተሰነደ ታሪክ መዝገበ- አእምሮ መጽሀፍ ቅጽ 2 ላይ የሚወጣ ሲሆን ቅጽ 1 መዝገበ-አዕምሮ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወቃል፡፡  አሁን በዚህ ጽሁፍ  ታሪካቸው የሚዳሰሰው የፎቶ ባለሙያ ዳኜ አበራ ናቸው፡፡ እርሳቸውም በኢትዮጵያ የፎቶ ጋዜጠኝነት ታሪክ ላይ ላይ ደማቅ አሻራ ያኖሩ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰአት የ59 አመት ሰው ናቸው፡፡ ባለውለታን ማሰብ፣ ሰርቶ ደክሞ የራሱን ማንነት ያስመሰከረን ሰው መዘከር ዋናው ግባችን ነውና የፎቶ ሰው ዳኜ አበራን የህይወት ገጽ መፈተሸ እንጀምራለን፡፡  አንተነህ ደመላሽና እዝራ እጅጉ ታሪካቸውን እንደሚከተለው ሰንደውታል፡፡

 

39 ዓመት በላይ በልዩ የካሜራ ባለሙያነት ያገለገለው አንጋፋ

  የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ዳኜ አበራ ጥላሁን የፎቶግራፍ ህይወቱን እንዲተርክ አድርገነዋል፡፡

                              ጥር 11

       

               ወርሃ  ጥር 11 /05/ 1956 . እንጦጦ ሽሮ ሜዳ ተወለድሁ፡፡ እዚሁ ሽሮ ሜዳ ፖሊስ ሰፈር  አንደ ማንኛውም ህፃን ከመንደር አብሮ አደጎቼ ጋር አደግ

     ! ዛሬ እንዲህ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ባልሰፋበት በልጅነቴ አብሮ አደጎቼ ጋር

     እንጦጦ ጫካን በመውጣት ቤተሰቦቻችን ለማጎዶነት የሚውል እንጨት እናመ

     ነበር ፡፡ በዚህ አኳኀን በገፋነው  ልጅነት  ውስጥ በተለይ በክረምት ቀን ሥራ

     በመስራት በማገኛት ገንዘብ እራሴን ለመቻል እጥር ነበር ፡፡

 

 

 

 

               ትምህርት እና ዳኜ                            

 

                አንደኛ ደረጃ ትምህርቴን የድሮው አምሃ ደስታ አሁኑ እንጦጦ አንባ ትምህርት ቤት የተማርሁ ሲሆን በልጅነት ልቦናየ ወደ እግር ኳስ በማዘንበሌ

      8 ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናን ማለፍ አልቻልሁም ፡፡ ድክመቴን ተረድቼ በድጋሚ

     ወደ ጣይቱ ብጡል ቁስቋም ትምህርቴን ተከታተልሁ ፡፡፡ጥሩ ውጤት በማምጣት

    ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብቼ 2 አመት ያህል ትምህርቴን እየተከ

    ታተልሁ ሳለ በወቅቱ በነበረው ሀገሪቱ ሁኔታ ቀዩ ጦር በሚል የነበረውን ጅምላ

    አፈሳ ሽሽት ያዝኩ ፡፡

 

                                        የኢትዮጵያ ባህር ኃይል

 

            1975 .  የኢትዮጵያን ባህር ኃይል ተቀላቀለሁ፡፡ አስመራ የሚሰጠውን የመጀመሪያ ኮርሶች ወስጄ ባህር ኃይል ባሉት ሙያዎች ስመደብ እኔ የምፈልገው ሙያ በወቅቱ ባለመኖሩ ፍላጎት ባልነበረኝ መሪ/ቦስ/ ሙያ ተመድቤ ኢትዮጵያ የጦር መርከብ ላይ ከባዱን የመርከብ ህይወት ተጋፍጫለሁ ፡፡ መርከቧ ለረጅም ጊዜ ተበላሽታ ቆማ የነበረ ሲሆን እኔና ጓደኞቼ 1975 . ቅጥር መርከበኞች በተለያየ ሙያ 50 ሆነን ተመድበን ስንደርስ ቀድሞውኑ የነበሩት አንቱ የተባሉ መርከበኛ ባለሙያዎች ዋና ዋና ጥገናዋን ጨርሰው ነብርና የቀረውን ደግሞ በአዲስ ጉልበት እኛን ጨምረው ካስተካከሉ በኋላ ለሙሉ ጥገና ወደ የመን ኤደን ስትሄድ አብሬ በመሄድ ጥሩ ጊዜን አሳልፌያለሁ፡፡

 

                  የፎቶግራፍ ክበብ

 

                  የመን ኤደን እንደነበርሁኩ ቀድሞ እማርበት የነበረው ከተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት መልቀቂያየን ስወስድ የፎቶግራፍ ክበብ አባል መሆኔን የሚገልፅ ትንሽ ወረቀት ተያይዛ የነበረ ሲሆን በቅጥር ወቅት ከፅሁፍ ፈተና በኀላ የህክምና ምርመራ ጨርሰን በሚደረገው ቃለ- መጠይቅ ላይ የነበሩ ሦስት መኮንኖች ያችን ወረቀት አይተውና አንብበው  እጄ ካሜራ ነክቼ የማላውቀውን ሰውየ

    " ለመሆኑ ካሜራ ማንሳት ትችላለህ ?" ሲሉኝ በድፍረት " አዎ" አልኳቸው ከዚያም

    በራሽያኛ ቋንቋ መነጋገራቸው ትዝ ይለኛል ፡፡

 

             የመን እያለሁ ፎቶግራፍ ስልጠና ከመርከብ እንድወርድ መልዕክት እንደ

   መጣ ተነገረኝ ፡፡ የቅርብ አለቆቼም አንተ ምትክ ሰው ካልተተካ በስተቀር አትወርድም የሚል ውሳኔ ወሰኑ፡፡  የመርከቧ ዋና አዛዥ ካፒቴን  መርሻዬ በጣም ቅርብ

   ከሆነው አለቃዬ ወንዴ ጋር ተነጋግረው እኔ ምትክ ሌላ ሰው እስኪመደብላቸው

   ድረስ እሱና ጓደኞቼ  የእኔን ሥራ ድርሻ ደርበው እንደሚሰሩ ሲያረጋግጡላቸው

    የይሁንታ ፈቃዳቸውን ሰጡ ፡፡



















 

                                  የፎቶግራፍ ጅማሮ

                                       

               በወቅቱ የቪዲዮ ካሜራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በተለይም የመጀመሪያውን

       ባህር ኃይሉ ከየመን  ሲያስመጣ እዚያው ኤደን ስልጠና በመውሰድ ኤርትራ

       ውስጥ የመጀመሪያውን ካሜራ እኔ ነበርኩ የያዝኩሁት፡፡  አንድ አመት በኋላ

       አስመራ ላይ የነበሩት ሉፖኖና አፍሪካ ሙዚቃ ቤት እንዳስመጡት ትዝ ይለኛል

       በዚህ ሙያም ኤርትራ ላይ ታዋቂ እስከ መሆን በቅቻለሁ፡፡ በዚህም በርከት ያሉ

       ሽልማቶችን አግኝቻለሁ ፡፡ከጀማሪ መደብ እስከ ሴክሽን መሪነት 1976. ጀምሮ እስከ 1983 . ድረስ ባህር ኃይል ፎቶግራፍ ሙያየ አገልግያለሁ ፡፡     

 

 

 

                የሞት አይነት                              

             

                 በምፅዋ ጦርነት ወቅት የነበርሁበት ቢሮ በከባድ መሳሪያ ሲመታ 15 ቀን ጤዛ ልሼ ሞት ጋር ታግዬ አስመራ ስገባ የሞተ ሰው እንደተነሳ ነበር የተቆጠረው

    በመቀጠል አንዴ አስመራ፣ ዳህላክ ፣አሰብ፣አዲስ አበባ እያልሁ ስሰራ  መነሻዋን

       ከሶማሌ ያደረገች መለስተኛ የጭነት መርከብ 11 የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን

       የጦር መሳሪያ ስንቅ ጭና ለሻብያ ልታደርስ በምፅዋ ወደብ በድብቅ ስትጓዝ

       ፈጣንና ቆራጥ በነበሩ መርከበኞቻችን በቁጥጥር ስር ስለዋለች ይህንን ታሪክ

      በፎቶግራፍና በቪዲዮ ለመቅረፅ ነበር ግንቦት 2 ቀን 19 83 . አሰብ ዳህላክ

      ከምፅዋ ተፈናቅለን ያረፍንበት የባህር ኃይል ቤዝ ላይ የደረስኩ ፡፡

 

          ይህንን ክስተት በፎቶግራፍና በቪዲዮ ሰንጄ ሳበቃ የሰራሁት ሥራ በጣም ስለ

     ተፈለገ በየቀኑ አስመራ ዳህላክ በሚመላለስ ሄሊኮፕተር አስመራ ወደ አዲስ

     አበባ ለመሄድ ግንቦት 8 አስመራ ስገባ ሁኔታዎች ተዘባርቀዋል ፡፡

     ነገሮች ሁሉ ተቀያይረው ገጠመኝ ፡፡ የጉዞ ሰነድ አመቻችቶ ወደ አዲስ አበባ የሚሸኘኝም የሚያዳምጠኝም አልነበረም፡፡  ጦርነቱ አስመራ ዙሪያ መሆኑ ሁሉም በየፊናው ይራወጣል ፡፡ አልፎ  አልፎ ከጠላት የሚተኮሰው ከባድ መሳሪያ የቀድሞ ባህርኃይል ናብስታ ግቢ አካባቢ እና አስመራ ኤርፖርት አካባቢ መውደቅ ጀምሯል የማውቃቸውና ወዳጆቼ የነበሩ የአየር ኃይል አባላት ባሉት የጦር አውሮፕላን ለመውጣት ሲሯሯጡ ቀድሜ  የጉዞ  ዝግጅት /ፕሮሰስ/ ስላላደረኩ ሊረዱኝ አልቻሉም ነበር ፡፡

 

          ይሁንና አስመራ የገባሁ ዕለት ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ፈቃድ  አግኝቶ የነበረው ወንድሜ ፒኦ ሲሳይ ወርቁ ጥቂት የያዝኩትን እቃ በተለይም ዳህላክ ላይ የነበሩ

     ራሺያዎች የፖለቲካ ኃላፊው የሰጠኝን አነስተኛ የፎቶግራፍ ማተሚያ ለቤተሰብ እንዲሰጥልኝ ላኩት፡፡ እኔም የፒኦ ሲሳይን መኝታ ቤት ተረክቤ አምስት ቀናትን በጭንቅ አሳለፍኩ፡፡ በመጨረሻም ግንቦት 16 ቀን 1983 . ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሲሆን ሽሽት ሲጀመር እንደ እኔ ከዳህላክ ለህክምና መጥቶ የነበረው ከበደ ጋር ሽሽት ጀመርን ፡፡

 

          ከዚህ በፊት እዚያው አስመራ በሥራ ምክንያት እንተዋወቅ እንጅ በቤተሰብ

     ደረጃ ስለማንተዋወቅ አንዳችን ብንሰዋ እንኳን ብለን በማሰብ ለቤተሰብ ለመንገር

     አድራሻ ተለዋወጥን ቃልም ተገባባን፡፡ " በህይወት ተርፈን አዲስ አበባ ከገባን በቅድሚያ እመቤታችንን የእንጦጦዋ ኪዳነ ምህረትን ደጅ ወድቀን አመስግነን ነው

    ወደ የቤታችን የምንለያይ " ተባባልን ካሜራየን ይዤ ጉዞ ወደ ሀገረ ሱዳን ጀመርን፡፡

 

     እለቱ በነበርንበት አይፋ መኪና የባሬንቱን ከተማ አልፈን ምሽት ላይ ከነበርነው

  ብዙ መኪኖች መሃል የኛ መኪና ላይ  ሩምታ  ተኩስ ተከፍቶ ጥቂት ወንድሞቻችን

  ሲጎዱ እኛ እለተ ቀኗ በታአምር  ተረፍን፡፡ ግንቦት 16 ሌሊት ጀምሮ ቀን ከሌሊት+በ እግር በመጓዝ ባሬንቱ ከተማ ጫፍ ላይ ግንቦት 20 ቀን ተማረክን ፡፡

    

        በህይወቴ እንኳን ሲጋራ ላጨስ ….! ሲጋራ የሚያጨስ ጓደኛ የሌለኝ ሰውየ ጭንቅ

     ሆነብኝና " አቦ   "ብየ ስለምን 5 ድፍን ብርና 2 አንድ አንድ ብር ያየችንና ያዘነችልኝ ሻእብያ ሰጠችኝ፡፡ አለፍ ስልም የሚያውቀኝ የሻብያ ወታደር ሲጠራኝ ስሙን ጠርቼ ወደሱ ልጠጋ ስል መሳሪያውን ወደ እኔ ወድሮ " አንተ እዛው ፅና" አለኝ

     ምፅዋ ላይ በጣም አውቀው የነበረ ይህ ወጣት ታጋይ ኮዳ ፈልጎ ስኳርና በሶ

     አድርጎ ይህንን እየጠጣህ እዚያ ተራራ ላይ እደር ሲለኝ ! አብሮኝ የነበረውን ከበደ

     ጓደኛየን አብረን እንድንሆን ስጠይቀው ፈቀደልኝ እለቱ ከነበረው ሞትና እልቂት

     አተረፈን ፡፡

 

          ብዙ የሞት አይነቶችን የሰነድሁበት ፎቶግራፍ ካሜራ ፀሐዬን ከማግኘታችን

     በፊት በነበረው ከባድና ሰቅጣጭ ፍተሻ ባሬንቱ ላይ በትንንሽ ህፃናት የሻእብያ ወታደሮች ብዙ ታሪኮችን ያነሳሁበት ካሜራ ከነ ፊልሙ የፀሐዬ ባልደረቦች  ቀምተውኝ

     ስለነበር "ካሜራዬን" ስለው ,,"ዳኜ በህይወት ትረፍና አገርህ ገብተህ ታነሳለህ "

     ያለኝን ዛሬም አልረሳውም ፡፡

 

         በጥቅሉ 6 ወር የሱዳንን ስደትና መከራን አጣጥመን UNHCR በኩል ጥቅምት

     28 /02/ 1984 . ቀን ላይ አዲስ አበባ ስንገባ በቃላችን መሰረት እመቤታችን ደጀሰላም ለመሄድ ሽሮ ሜዳ ስደርስ መቼም የሚያውቀኝ ሰው አይጠፋም ከተማ ቆይተን በምሽቱ ለአይን ሲደበዝዝ ስደርስ እንደፈራሁት ወንድሜን ንጉሴ ከበደን አገኘሁት፡፡

      ዘሎ አቅፎ ሊስመኝ ሲል " ንጉሴ ቃል አለብንና መጀመሪያ ኪዳነ ምህረት አድር

     ሰን " ብየው  ቤተሰብ እንዳያገኘን በጨለማ በእንጦጦ ስላሴ በመቃብሩ ስፍራ አድርገን  እንጦጦ ኪዳነ ምህረት ደጀ ሰላሟ ደርሰን አመስግነን ጸሎታችንን አድርሰን ወደየ ቤተሰቦቻችን ተቀላቀልን ፡፡ወዳጆቼ ታሪኬ ብዙ ቢሆንም ለእኔ እመቤቴ ኪዳነ ምህረት ዓመት በወር በቀን በሰዓት በሰከንዶች ሁሉ አቅፋ ደግፋ ይዛኛለችና አመስግኑልኝ ፡፡

     ለእኔ እንደምትደርስና ከክፉ ሁሉ እንደሰወረችኝ ለእናንተም ጥላ ከለላ ትሁናችሁ

     ይለናል የካሜራ አርበኛው የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኘ አበራ አበራ ፡፡

 

      ሀገረ- ሱዳን ስደት እጅግ አስጨናቂና አስፈሪ ሞቶችን አልፌ  1984 .

 አዲስ አበባ እንደተመለስሁ በግል ስራ የጀመርሁ ሲሆን 1987. ጥር ወር

 ጀምሮ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በፎቶግራፍ ጋዜጠኝነት እያገለገልሁ እገኛለሁ ፡፡

 

                             

                            

                               ብላት  

 

        ጥር 13 ቀን 1999 . ደብረ ዘይት አየር ኃይል ዋናው ግቢ ጠዋቱ አንድ

   ሰዓት ደርሰናል የአየር ኃይል አባላትም በፍቅር ተቀብለው አስተናገዱን በኋላ

   አንቶኖቭ አውሮፕላን ጉዞ ጀመርን፡፡ የመጀመሪያ መዳረሻችን ድሬዳዋ ነበር፡፡

    ድሬደዋ አንደ ደረስን አንድ ሰዓት ያህል ካረፍን በኋላ ጉዟችንን ወደ ምስራቋ

   ጎዴ አደረግን፡፡ ለኢትዮጵያ ሀገራችን ባለ ውለታ በሆነው አውሮፕላን እኔ ለተደጋጋሚ

   ጊዜ የተጓዝሁበት በመሆኑ የለመድሁት ቢሆንም አየር ላይ ሲወጣ ግን ሁሌም

    አዲስ ነው የሚሆነው ፡፡

 

          ከኢቴቪ ካሜራ ማኖቹ ታምራት እና አሊ በስተቀር ሁሉም ለጉዞው አዲስ ስለ

   ነበሩ፡፡ የነበረው ጭንቀትና ሁኔታ መቼም አይረሳም ፡፡ እንደምንም ጎዴ ገባን፡፡  በመቀጠል ጎዴ ላይ ትጠብቀን የነበረች አነስተኛ የአየር ኃይል አውሮፕላን ውስጥ በመግባት ወደ ባይደዋ ጉዟችንን እናሳልጠው ጀመር የጉዟችን ዋናው ፍሬ ምክንያት

  ባሸባሪነት የተፈረጀው አልሻባብ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ለመዘገብ ነበር፡፡

  በዚህም መሰረት እኔም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በመወከል የፎቶ ካሜራየን ይዤ

  ወደ ቦታው ለመሄድ ከተመደቡ ባለሙያዎች አንዱነኝ ፡፡ ጉዞው በብዙ ፈተናዎች

  የታጀበ ነበር መጀመሪያ በአንቶኖቩ ሲሸበሩ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከእርሱ በመውረዳቸው

 ተመስገን ቢሉም ቀጥለው የገቡበት አውሮፕላን ግን ምነው የቅድሙ በቀጠለ የሚ

 ያስብል ነበር !፡፡ አሁን የገባንበት  አነስተኛዋ አውሮፕላን ነፋስ ከወዲያ ወዲህ

  ሲያወዛውዛትና ሲያላጋት እንኳን እነሱ እኔም ምነው አንቶኖቩ  በቀጠለና ይዞን በመጣ ብያለሁ ፡፡

 

       በጉዟችን ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳንበላ  ዘጠኝ ሰዓት ባይደዋ ደረስን፡፡ ይቀበሏችኀል

  የተባሉ አካላት ባለመኖራቸው እኔም ርሃቤን ለማስታገስ በፈራረሰው የባይደዋ 

  ኤርፖርት ውስጥ ካሜራዬን ይዤ መዘዋወር ያዝሁኝ ፡፡ በዚህ መካከል አንድ ህፃን

  በፈራረሰው የባይደዋ ህንፃ ውስጥ ትንሽዬ ልጅ ሬዲዮ ይዞ ዜና ይሁን ሙዚቃ ለመስማት የሬዲዮ አንቴናውን እየጎተተ ከወዲያ ወዲህ ሲል አገኘሁት የልጁ ሁኔታ አንጀቴን ስለበላው በካሜራዬ አስቀረሁት ፡፡ በአካባቢው የነበረው ሰራዊታችን ጥሩ ጥበቃ

  ያደረገልን ሲሆን አመሻሹ ላይ የባይደዋ ባለስልጣናት መጥተው በመጀመሪያ የኛ

  ሰራዊት አዛዥ ጋር አድርሰውን ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄዎች ምክር ለገሱን

  ከዚያ ወደ እንግዳ ማረፊያ ክፍል ወሰዱን አንድ ክፍል ለሦስትም  ለአራትም ተጋራን ፡፡

 

        የተሰጠን ክፍል ውስጥ ስንገባ በርካታ በራሪ ነፍሳት ከወዲያ ወዲህ ውርውር

    ይላሉ በተለይ የወባ ትንኝ አለች ተብሎ ስለተነገረን ፍራቻችን ከባድ ነበር ከጥቂት ቆይታ በኋላ የተቀበሉን አመራሮች በትንሽ ፌስታል የምን እንስሳ እንደሆነ የማናውቀው

   ጥብስና ፓስታ አመጡልን፡፡ ምግብ ከተመገብን 14 ሰዓት ያለፈን በመሆኑ ሁላችንም

    በሰከንዶች ልዩነት ተረባረብንበት ፡፡በዚህ ላይ የራበውን ታጠቃለች የምትባለውን

   ወባን ለማምለጥ ምን አማራጭ አለን ? በማግስቱ በዚያችው አነስተኛ አውሮፕላን

    ተጭነን ከህንድ ውቅያኖስ የሚመጣው ነፋስ ከወዲያ ወዲህ እያማታን ስድስት

   ሰዓት ሲሆን ሞቃድሾ ደረስን፡፡ እዚያም ይጠብቁን የነበሩት በኢትዮጵያ ኮማንዶዎች

   ታጅበን በቅርብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ገባን ፡፡፡  ካምፑ የሚገኘው ሰራዊታችንም የሚበላውን ኮቾሮና እስቃጥላ አቀረቡልን፡፡ እርሱን እየቀማመስን ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ወደ ቤተ- መንግስት በአጀብ ገባን ፡፡

 

           በቤተ- መንግስቱ ግንባሩ ዋና አዛዥ እና አስተባባሪ እንዲሁም የሶማሊያ

     መንግስት ቃል አቀባይ ተቀብለውን ከአነጋገሩን በኋላ የቡድን መሪ የሶማሊያ

     ቋንቋ የሚችለውን አብዱራማንን መርጠን በእሱ በኩል ግንኙነት እንደምናደርግ

     ተነጋግረን ስናበቃ  አዛዡ " ለመሆኑ አበል ስንት ስንት ይዛችሁ መጣችሁ? " ሲል

      ጠየቀን !፡፡ በቀን ሰባ ሰባ ነው የሚል ምላሽ ተሰጠው ወዲያው ቃል አቀባዩ

     ጋር ተነጋግረው ወደ ተያዘልን ላፍዎይን ፓላስ ሆቴል ገባን የሚገርመው በቀን

     ሰባ የኢትዮጵያ ብር የሚለው ውሎ አበላችን አሜሪካ 70 ዶላር ነበር      የመሰላቸው፡፡

   

       እንደዚያም መስሏቸው 54 ዶላር እየከፈልን እንድናድርና ምግብ እንድንመገብ

   ተነጋግረው ኖሮ ለሁለት ቀናት ካደርን በኋላ የሆቴሉ ሰራተኞች ሂሳብ እንድንከፍል

   ሲጠይቁን ያሰቡትን ዶላር አለመያዛችንን ሲያውቁ በጣም ተበሳጭተው ለአገሪቱ

   ቃል አቀባይ ደወሉ ፡፡ እኛ እንነጋገራለን በሚል ተግባቦት እስከዚያው ባሉበት ይሁኑ

    ተባልን ፡፡

 

       ይሁንና ሆቴሉ አገኛለሁ ብሎ የቋመጠለትን ዶላር ባለማግኘቱ ውጡ ባይሉንም

    በተለይ በምግብ መስተንግዶው በእጅጉ በመቀነሱ ተሻምቶ ወደ መብላት ተንደረደርን፡፡ አንዳንዴ ሙዝ በውሃ እየበላን ውለን የምናድርበት ቀን መጣ ፡፡ ደግነቱ

    ሙዝና ብስኩቶች በጣም ውድ ቢሆኑም በኢትዮጵያ ብር መገበያየት ይቻል ነበር፡፡

   የሆቴሉን ጥበቃዎች እያስላክን መጠቀም ስንጀምር ለደህንነታችሁ ጥሩ አይደለም

   በሚል ሆቴሉ ውስጥ በእኛው ብር በጣም  በውድ ዋጋ ሙዝና የሃይላንድ ውሃ ብቻ

    እየገዛን እንድንጠቀም ተደረገ ፡፡

 

        በሞቃድሾ በጣም  እርካሹ  የምባይል ካርድ ነው ገና የገባን ዕለት ወደ ሶስት

   የሚሆኑ የቴሌኮም ድርጅቶች ሆቴላችን ድረስ በመምጣት ሲምካርድ ተሻምተው

   በነፃ   አደሉን :፡ እኛም የተሻለውንና ርካሽ የአየር ሰዓት ያለውን መርጠን

    መጠቀም ጀመርን ፡፡ 20 ብር ካርድ ቤተሰቦቻችንን እንደልብ ደውለን እናወራ ነበር ፡፡

    

     ወደ ሆቴሉ በገባን ዕለት ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ አልሻባብ በደረሰው መረጃ

   መሰረት  ካለንበት ሆቴል እኛን ለማጥቃት ያልተኮሰው የመሳሪያ ዓይነት አልነበረም፡፡ መኝታ ክፍላችን ሳይቀር በጥይት ሲነዳደል አንዳችን ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ በእግዚአብሔር ቸርነት ተርፈናል ፡፡

 

         ሞቃድሾ የቆየንባቸው 12 ቀናት ለእኛ አንዷ ቀን አንድ አመት ያህል እስክትመሰለን ድረስ ከባድ ነበር በእያንዳንዱ ቀን ብዙ ገጠመኞችና አደጋዎችን እያሳለፍን የቆየን ሲሆን ጥር 14 ቀን /05/ 1999 . ባልጠበቀነውና ባላሰብነው ሁኔታ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ባለስልጣናትን ይዞ በመጣው አውሮፕላን እንድንመለስ ተደረገ፡፡

    እውነት አልመስል ያለንን ጉዞ ጀመርን ፡፡ አይሮፕላኑ አዲስ አበባ ሲገባ የነበረው

   ደስታና ጭብጨባ መቼም አይረሳኝም ፡፡ ምክንያቱም ሞትም ለካ በሀገር ያምራል

   በችግር ጊዜም መደበቂያ ወገንም  እንደሚናፍቅ ያየንበት አታካች ፈታኝ ከባድ ጉዞ ነበር ፡፡

   እኔ እንኳን  ቀደም ሲልም ጦርነትን ያየሁት እንደሌሎቹ ባይሆንም ከብዶኝ ነበር፡፡ በተለይም የአሁኑ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በወቅቱ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ አብረን ባሳለፍናቸው ቀናቶች የነበረው የስራ ፍቅር ድፍረቱ በጣም ይገርመኝ ነበር፡    

       ጉዟችን መልስም የተሰጠንን ውሎ አበል እንዲስተካከል ጠይቀን እኔንና ባል

  ደረባዬ ስንከለከል ነፍሱን ይማረውና አቶ አለማየሁ አቶምሳ የማስታወቂያ ሚኒስትር የሚመራው የሚዲያ ማኔጅመንት " እንዳይከፈላቸው " ብሎ የወሰነውን ውሳኔ

  አቶ አለማየሁ አቶምሳ የኢትዮጵያ ቴሊቭዥን ዋና ስራ አስኪያጅ " ባለሙያዎቼን ስልካቸው የህይወት መስዋትነት ጭምር ሊከፍሉ ነው "  በማለት እንዲከፈላቸው አደረገ ፡፡ ይሁንና አቶ አለማየሁ አቶምሳ

    በዚያች ስልጣን ብዙም አልቆዩም፡፡ በዚህ በሰሩት በጎ ስራ ምክንያት በወቅቱ በነበሩት ሰዎች ጥርስ ውስጥ የገቡ ይመስለኛል ፡፡ እኛም ከባልደረባዬ ጋር ከተቋማችን ቦርድ ሰብሳቢ ጀምሮ እስከ ሚኒስትሩ ድረስ በደብዳቤ አመልክተን ጥያቄያችሁ  ህገወጥ ነው በማለት ውድቅ ሲያደርጉብን ከእኛ በኋላ ለሄደው ጋዜጠኛ ግን ከበቂ በላይ የውጭ ምንዛሪ ሰጥተው እንደላኩት እናውቃለን፡፡ ነገርግን  መቼም ቢሆን  በሀገሬ  ኢትዮጵያ ቀልድ የለም፡፡

 

 

                  "  ካረርን በኀላ  መቀቀል "  የኛ  ,,!

 

              በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት እና ጥያቄያችንን ውድቅ ያደረጉት አበሉን ከተከለከልን ዓመቱ አግኝቻቸው የነበረውን ሁኔታ ሳስረዳቸው ሙዝ እየበላን ያደርንባቸው ቀናቶች እንደነበሩ በተጨማሪ የነበሩ ችግሮችን አክየ ሳስረዳቸው

    በወሰኑት ውሳኔ በጣም ተፀፅተዋል፡፡ ¡ ካረርን በሁዋላ መቀቀል ነውና የኛ የነገር

    ከእኛ መምጣት ማግስት የሄደው ጋዜጠኛ ስሙ ለጊዜው ስሙ ይቆይ ፡፡ 8 ቀን ቆይታው  15 ቀን በውጭ ምንዛሬ ነበር የተሰጠው ፡፡

 

                             

                                        ህግ    ማስከበር

 

            እለተ እሁድ ጥቅምት 29 /02/ 2013 .  አዳራችን ካደረግንበት ዳንሻ

    አምስተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር  በጠዋት እነ ጀነራል ሙሉአለም ጋር በመሆን

    በወታደራዊ አጀብ ታግዘን ትርካን ሁመራ ኤርፖርት ረፋድ ላይ ደረስን ፡፡በ አንደኛ

     ኮማንዶ ብርጌድ የሚመራው ኮማንዶ እና የምዕራብ ዕዝ 24 ክፍለ ጦርን

   ጨምሮ ሌሎች እግረኛ ሜካናይዝድ ጦሮች ጋር በመሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛነት  የተፈረጀውን ህወሃት ጦር ደምስሶ ኤርፖርቱን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ : ሌላ ተጨማሪ ጦር በኤርፖርቱ ዙሪያ ያሉ አካባቢዎችን ለመያዝ እና

  ተቆርጦ የቀረ ጦር ለማጽዳት እየተሰማራ ነበር የደረስነው ፡፡

 

        በቦታው ከደረስን በኀላ ካሜራችንን  ጠምደን ስለ ጠቅላላ ኦፕሬሽኑ  ዘመቻውን

   ከመሩት ወታደራዊ መኮንን መካከል አንዱ የሆኑት  አንደኛ ኮማንዶ ብርጌድ ምክ

   ትል አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል ምትኩን ቃለ- መጠይቅ አደረግን መልከ መልካሙ እና

   ደልደል ያለ ቁመና ባለቤት የሆኑት ቀይ ቦኔት ከነ ሙሉ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱት ኮሎኔል ሻምበል ምትኩ እልህና ወኔ በተቀላቀለበትና በሰረፀበት የጀግንነት መንፈስ  ከሶሮቃ ጀምሮ ትርካን ድረስ የነበረውን የሰራዊቱን የጦር ሜዳ ጀብዱ እና የዘመቻውን ዙሪያ ገባ መረጃ ሰጡን ፡፡

 

 

                                      ኮቪድ    ላምታ

 

       ኮሎኔሉ ቃለ መጠይቅ በኀላ የኤርፖርቱን ጠቅላላ ገጽታ ተዘዋውረን እየቀረ

   ጽን እያለ በቀጥታ ወደ ኤርፖርቱ አቅጣጫ የዝሆን ኩንቢ መሰል አፍንጫዋን ወድራ

   ጭንቅላቷ ላይ የጫነችውን መቅዘፊያ / rotor /  በፍጥነት እያሽከረከረች ከፍታ

   ዋን እየቀነሰች ኤርፖርቱ መንደርደሪያ  ላይ አረፈች ፡፡ ካሜራችንን ጠምደን ማን

  እንደሚወርድ መጠባበቅ ጀመርን፡፡ ቀይ ቦኔት ኮፍያ ከነ ሙሉ ወታደራዊ ዩኒፎርማቸው

  ያደረጉ ወታደራዊ ቁመናቸው የሚማርክ በደረታቸው ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ወታ

  ደሮች ቀድመው ወረዱ ፡፡ አሻግሬ ሳማትር የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል

   በላይ ስዩምን ከመሃል ሲመጡ በካሜራዬ ሥራዬን ቀጠልኩ ፡፡

 

        5 ሜካናይዝድ ክፍለ- ጦር ዋና አዛዥ / ጀነራል ሙሉአለም እና ሌሎች

   ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እነሱን ለመቀበል መጡ፡፡ በኤርፖርቱ  ተርሚናል እየተራመዱ ሲመጡ መሃል ላይ ሲገናኙ በድል አድራጊነት መንፈስ " ጀግኖች እንኳን ደስ

   አላችሁ " ብሎ / ጀነራል በላይ ስዩም / ጀነራል ሙሉአለምን ክንድ በመግ

  ጨት ኮቪድ ወለድ ሰላምታ ተለዋወጡ ፡፡ እኔም በተለያዩ ግዳጆች ላይ ስለሚያገኙኝ የኮቪድ ሰላምታ ተለዋውጠን አንተ ጀግና እዚህም አለህ ብለውኝ ወደመጡበት ሚስጥራዊ ጉዳይ ከጦር መኮንኖችና ጀነራሎች ጋር ለመምከር ለስብሰባ የምትመች ትልቅ ግራር ስር ካደረጉ በኀላ " በዚህ ጀግንነታችሁ ነገ ስድስት ሰዓት ላይ ሁመራ ከተማን መቆጣጠራችሁ እርግጥ ነው እሱን ግዳጅ ፈፅማችሁ አሳውቁን " በማለት የሰራዊቱን የማድረግ ብቃት በእርግጠኝነት ተናግረው በመጡበት ሁኔታ ተመለሱ፡፡ ከጀነራል በላይ ጋር በድጋሚ ሁመራ ከተማና አካባቢው ሲለቀቅ አብሪያቸው በመሄድ ጭር ያለቸውን ገና በሰራታችን ቁጥጥር ስር የገባችው የሁመራ ከተማን እየተዟዟርኩ ታሪካዊ ፎቶግራፍ አንስቻለሁ ፡፡

ጦርነት አውዳሚ እና አሰቃቂ መሆኑን እማኝና ምስክር የሚሆን ይመስለኛል ፡፡ ከዳንሻ እስከ አድዋ ቆላ ተንበይ በተዘዋወርኩባቸው ቦታዎች እና የጦር አውደ ውጊያዎች መከላከያ ሰራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እና የደረሰው ግፍ በቃላት ለመግለፅ  እንኳን ይሰቀጥጣል፡፡ በካሜራዬ ግን ለማስቀረት የምችለውን ሁሉ ከሞት ጋር እየተጋፈጥኩ አስቀርቻለሁ፡

የሆነው ሆኖ ጀግናው የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመግለፅ የሚከብድ ዘግናኝ ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ ቀልብሶ በአጭር ቀናት የጓዶቹ ደም ደመከልብ ሆኖ አንዳይቀር አንደ ንብ ተሞ በወሰደውአጸፋዊ ህግ የማስከበር  እና ሀገርን የማዳን እርምጃ ለተቀዳጀው አኩሪ ድል እንዲሁም በጀግንነቱ ክብር ተሰምቶኛል ፡፡ የዚህኛው ዘመን እና ታሪክ አካል በመሆኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ፡፡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለሀገሬ በሙያየ የበኩሌን የተወጣሁ ያህል ይሰማኛል ፡፡ ህወሃት በሰራዊቱ ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ ግን ዘወትር በታሪክ የማይረሳ ጥቁር ነጥብ ሆኖ ሲተረክ ይኖራል ፡፡፡

 

 

                             የሰሜን  ምዕራብ   የጋዜጠኞች ተጋድሎ

 

            ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ግንባር የዘመተው የጋዜጠኞች ቡድን መንፈሱ እና ወኔው ልዩ ነበር ፡፡ ከቀላል ክላሽ እስከ ከባዱ ታንክ መድፍና ቢኤም እሩም አልበገረውም ፡፡ ከባድ ውጊያ በነበረበት የበኸር ዛግር ውጊያ መሳሪያ ይዘን አንዋጋ እንጂ አውደ ውጊያው በተጠንቀቅ ከወታደሩ ጎን ቆመን አለኝታችንን አሳይተናል ፡፡

 

            ዳንሻ ጀምሮ እስከ አድዋ ተራሮችና ቆላ ተንበይ ሁሉም ጋዜጠኛ ለነፍሱ ቅንጣት ታክል ሳይሳሳ የእናንተን ድል አብረን እንይ ወደ ኋላ አትመልሱን ለህዝብም እውነተኛ መረጃ እናድርስ እያለ በጀግንነት አብሮ ወደ ፊት በቁርጠኝነት  ተጉዟል ፡፡

     ሽራሮ ከተገናኘን በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ አዲሀገራይ ወጣ ብላ በምትገኘው ዛግር

      ላይ ጀግናው / አበባው ታደሰ አገኘን " እናንተ ጋዜጠኞች ጠመንጃ አልታጠ

      ቃችሁም እንጅ እኛ እኩል አብራችሁ እንደተዋጊ ወታደር እየታገላችሁ ነው"

      ብሎን ነበር ፡፡ ጀግናው የጦር አበጋዝ / ጀነራል በላይ ስዩም ባገኘን ቁጥር

      " ያላችሁ ወኔና የድል መሻት ግሩም ነው" ይለን ነበር ፡፡

 

             አጠቃላይ በነበረን   ቆይታችን  አብረን  በመሬት

     ተኝተን ፣በቦቴ በሚመጣ ውሃ በጋራ ጠጥተን ፣እስቃጥላ እና ብስኩት ተሻምተን

     በልተን ፣በኒዶ ቆርቆሮ ቡና አፍልተን ጠጥተን ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች

     በአየር በመኪና ተጓጉዘን አቆራርጠን ግዳጃችንን ተወጥተናል፡፡ ከሙያችን ተልዕኮ

      ባሻገር ለሀገር ሰራዊቱ ያለንን አጋርነትም በገሀድ  አሳይተናል ፡፡

      

 

                                             

                                      ራስጌ እስከ ግርጌ

 

                                     ቅፅበቶችን  መንጠቅ

 

                                ውርድ  የልዩ ካሜራ ባለሙያነት

 

              ከስንጥርጣሪ  ሰከንዶች ጋር መተሳሰር  ቅፅበቶችን መንጠቅ  እንደገና

     ምልሰት በሌለበት ቅፅበቶችን ማስቀረት እና እንዲህ ነበርን ብለው እንዲያወጉ

     ማስቻል ድርጊቶችን የመጀመሪያ የመጨረሻ ፍፃሜ እጣዎችን በፎቶ ምልከታ

      አካላቸውን መወከል ከፍ ሲልም የአውደ ውጊያን አድማስ ማነፀር ! ያልወጡ

     ነፍሶችን ያልሞቱ አስከሬኖችን በአይነ ህሊና ተዳሳሽ ማድረግ ህም,,,,,,,ምም

    ይፈታተናል! የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኜ አበራ እንዲህ ይለናል ከድንገቶች መሃል፡፡

 

           በሙያየ ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተዘዋውሬ አይቻለሁ ይህ ቀረኝ

      የምለው ያላየሁት ቦታ የለም 1976 . ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ  የተቃጡ

      ጦርነቶች ላይ በሙሉ ተገኝቻለሁ ታሪካዊ ክስተቶች ላይ ተሰይሜያለሁ፡፡

      በታላላቅ ስብሰባዎች መንግስታዊ ስምምነቶች የኢትዮጵያና የኤርትራን

      የአልጀርስ ስምምነት ልብ ይሏል!/ ውስጥና ውጭ ሀገራት አለም

     አቀፍ ጉባኤዎች ላይ ተገኝቻለሁ ለካሜራ አስቸጋሪ የሆኑ ቅፅበቶችን

     በፎቶግራፍ ከትቤአለሁ ፡፡

   

    

             1988 . ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ የካሜራ ባለሙያ በመሆን

    የተለያዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሥራ እንቅስቃሴዎች በፎቶ ዘግቢያለሁ

    የግብፅ ፕሬዝዳንት  ሆሲን ሙባረክ በመዲናችን አዲስ አበባ የግድያ ሙከራ ያደረ

   ረጉባቸውን ግለሰቦች የመጨረሻ እጣ ፈንታ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆኘ ፎቶ አንስቻ

   ለሁ ፡፡ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅትም ዘለግ ያለውን የጦርነት ጊዜ በፆረና በባድመ

  ግንባር በመገኘት  አውደ ውጊያውን በካሜራየ አስቀርቻለሁ፡፡፡ ሠራዊቱ በባድመ ግንባር አሸንፎ ባንዲራውን ሲያውለበልብ እኔ ያነሳሁት ፎቶ ግራፍ በጊዜው በፖስተር ታትሞ ነበር ፡፡ እንዲሁም ሰራዊታችን ሶማሊያ  ሞቃድሾ ሲገባ አብሬ በመሄድ ታሪክ አስቀርቻለሁ ፡፡ የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ ሲጣል ከመኪና አደጋ ተርፌ ያነሳሁት ፎቶግራፍ እስከ ዛሬ ታሪካዊ ከፍታውን የጠበቀ ሆኖ ይገኛል ፡፡

 

                 

                                         ሦስቱ       ዎች

 

                      

 

            የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስረስ ፡ጠቅላይ ሚኒስትር

       ሆነው ሲሾሙ ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ፡ በህመም ላይ ሆነውሶማሌውን ፕሬዝዳንት ሲያናግሩ የህይወት ዘመናቸውን የመጨረሻ የሆነውን ፎቶግራፋቸውን አንስቻለሁ ፡፡

                           

                     ፪ኛ

    

              ጠቅላይ ሚኒስትር  ኃይለማሪያም ስልጣን ሲይዙ በተወካዮች ምክር ቤት

       ቃለ መሃላ ሲፈፅሙና፤ ሰኞ ስልጣን ሊለቁ አርብ የመጨረሻ ስራቸውን ፊርማቸውንና ስልክ አናግረው ሲወጡ  ፎቶግራፍ እንስቻለሁ ፡፡

 

                    ፫ኛ

 

                በጠቅላይ ሚኒስትር  መለስ ዜናዊ የጀመረው ልዩ የጠቅላይ ሚኒስትር

        ፎቶ አንሽነት  በአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አዳብሎ / አብይ አህመድ ሰልሷል በአሁኑ ሰዓትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ በቋሚ ፎቶ ዘጋቢነት እየሰራሁ እገኛለሁ ፡፡

 

               በሙያየ የተለያዩ አስደናቂ ቅፅበቶችን በፎቶ በማስቀረት ለወደፊት ለታሪክ ዘገባ በእማኝነት መቅረብ የሚችሉ ውድ ዋጋ ያላቸውን ፎቶ ግራፎች አስቀርቻለሁ

       በጥቅምት 24 /02/ 2013. በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት

      የተፈረጀው ህወሃት በሰሜን ዕዝ ሰራዊታችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለመመከት

      የተወሰደውን እርምጃ ጥቅምት 26 /02/ 2013 . ጀምሮ ከሰራዊታችን ጋር

      በመሰለፍ ቆላ ተንቤይ  ድረስ በመጓዝ ታሪክን በካሜራየ ሰንቄያለሁ

     በተለይ በቆላ ተንቤይ ላይ ከሞት ጋር ግብግብ እየገጠምሁ ባለ ከዘራውን ኮሎኔል ሻንበል በየነን የነሳሁት ፎቶግራፍ እውቅና አግኝቷል ፡፡

 

           በህልውና ዘመቻው ላይ ነሃሴ 10 /12/ 2013 . በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ መግቢያ ጀምሮ በሰሜን ወሎ ጋሽና ግንባር ላሊበላና ሰቆጣ ድረስ በመሄድ ታህሳስ 26 / 04/ 2014 . ነው የተመለስሁት በተጨማሪም በአፋር በኩል

    ያለውን ለመዘገብ ሲነየር እና ልምድ ያላቸው ይሂዱ ተብሎ ጥር 2/05/ 2014 . ጀምሮ ከምድር ድሮኖች ጋር ከርሚያለሁ ፡፡

      ቀደም ብሎም አሁን በተደረገው ጦርነት የትኛውም ሚዲያ ደፍሮ ገብቶ ያላገኘውን የአሁናችንን ትዕይንት እኔ በድፍረት ከሰራዊቱ ጋር በመግባት ህዝባችንናመንግስታችን እንዲያውቀው ማድረጌ ስራዎቼ ምስክር ናቸው ፡፡

     ለዚህም 2011 . የበጎ ሰው ሽልማት በሙያየ ለሀገር ባደረኩት አስተዋፆኦ

     ተሸልሜያለሁ፡፡ 39 ዓመታትን በሙያየ አገሬን በታማኝነት አገልግያለሁ፡ ከኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ጀምሮ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የሀገራችን መሪ የሆኑ ባለስልጣናት በእኔ ካሜራ ፎቶ ግራፍ ያልተነሳ የለም ፡፡

 

 

                             

 

 

             የሰራ አካላቱ ሁለንተናው   ከመምሰል ባለፈ  እራሱ ሙያውን የሆነ ሰው

     እንዴትስ  ልክ ይገለፃል  ? ሙያውን ከትህትና ጋር አዋህዶ ለዘመናት የዘለቀን

     ሙያ አደባባይ ከመብቃት ባሻገር የገዘፈን ምን አንደበት ሰልቶ ቃላት ቋጥሮ

      ይናገረዋል እስኪ ስለ አንጋፋ ፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኘ አበራ ለእማኝነት ከተሰየሙ አንደበቶች ቆንጥረን እንቃመስ ! ለመግለፅ አዳጋች ቢሆንም ፡፡

 

 

አቶ ጌትነት ታደሰ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋ/ሥራ አስፈፃሚ 

    የፎቶግራፍ ዘርፍ ውስጥ ምንም ስልጠና በሌለበት ምንም ማቴሪያል በሌለበት ጊዜ ምቹ ሁኔታ ባልነበረበት ጊዜ ከኪሱ በግሉ ካሜራ እየገዛ የሰራ ባለሙያ ነው።ይሄ ለሙያው ያለው ቀናይነት ነው የሚያሳየው የካሜራ ሙያውን ለእንጀራው ብቻ ብሎ የያዘው ሙያ አይደለም፡፡ ሃገር መውደድ አንዱ መገለጫ ሙያን መውደድ ነው በሙያ የሚታይ የሚጨበጥ ለነገ የሚተርፍ ስራን ሰርቷል፡፡

        

 

          ጋዜጠኛ ዘሪሁን ለማ

       10 ዓመታት በፊት 2004 .  በአንድ ፕሮጀክት ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ነው፡፡

    ዳኜ አበራን በአካል ያወቅኩት በስም ግን በየጋዜጣው አውቀው ነበር፡፡  ፡በምረቃው ሪቫን ቆረጣ ላይ በሰዓቱ ደርሼ እንዳልቀርፅ የተቀነባበረ ሴራ ተሰርቶ አልደረስኩም

    ያችን ሥነ ስርዓት አለመቅረጼ ደግሞ ሞቴን ወይ ሽረቴን ለደገሱልኝ ለእነዚህ ሰዎች

    የሚያስፈነድቅ ድል ነበር ፡፡

           በዚያ በረሃ በእግር አቆራርጨ ስደርስ  ሪቫን ተቆርጦ ቀጣይ ፕሮግራም ላይ

    ደረስኩ፡፡ አጋጣሚ ከዚህ በፊት በመልክ የማላውቀው ዳኜን ሰላም አልሁትና

    ሪቫኑን ፎቶ በእኔ ኮምፒውተር እንዲጭንልኝ ጠየኩት በፍፁም ቅንነት ያለሁበት

    ድረስ መጥቶ ጫነልኝ ፡፡

     በማግስቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ተጠራሁ አራቱም ሊበሉኝ የደረሱ ያሰፈሰፉ

     ጅቦች መስለው ታዩኝ " ለምንድን  ነው ሪቫን ቆረጣውን ያልቀረፅኸው ?" ቁጣ

     የተቀላቀለበት ጥያቄ  " ኧረ ቀርጨዋለሁ " የእኔ ፍራቻ የተቀላቀለበት መልስ,,

     እነሱ " እስኪ አምጣና አሳየን " ,,,

      

            ፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኜ አበራን  ፎቶ  አድርጌ አቀናብሬ ሙሉውን ፊልም

     አሳየሁዋቸው ! እርስ በእርሳቸው የግልምጫ አይነት ተያዩ የዳኜ ፎቶ ጥርት

    ከማለቱ የተነሳ ፊልምም ፎቶም መሆን ቻለ እንጂ ! ፎቶ መሆኑን ቢያውቁ ይበሉኝ

     ነበር ፡፡ አሁን አገራችንን ታላቅ ያደርጋታል የተባለ ፕሮጀክት እነዚያ ፕሮጀክቱን የገደሉ

    ሰዎችም አወዳደቃቸው ሳይምር ቀረ ፡፡

 

        መልካሙ ደጉ ሰው ዳኜ አበራ ግን የኛ የኛ ጸሎትና የኢትዮጵያ አምላክ ደግፎት

     እድሜና ጤና ሰጥቶት ለተደጋጋሚ ሽልማት በቃ ለሌሎችም አርአያ ሆነ ፡፡

 

                               የካሜራ  አርበኛ  ዳኜ አበራ ማለት

                                 ከተፍ ብሎልኛል በጨነቀኝ ሰዓት ፡፡

 

 

               

                                        / ሄኖክ ስዩም

 

                 /  የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ /

 

         ጥንቃቄ ፍጥነት ጥራት  ቁርጠኝነት የሚጠይቁ ስራዎች ሲኖሩና

    በተሻለ እንዲሰራልን ስንፈልግ በየትኛውም ሁኔታና በፈለግነው ደረጃ ስራዎችን

    መስራት የሚያስችለን የፎቶግራፍ ጋዜጠኛችን ነው ፡፡

 

           ጦርነቱም  በልማቱም ተሳትፏል ፡፡ የጦርነትንም  የልማቱንም ትሩፏቶች

    በጎውንም መጥፎውንም በፎቶ አስቀርቶልናል፡፡ ስለዚህ የታሪክ ሰናጅም ነው ልንለው እንችላለን  ዳኜ  አበራን ፡፡

 

                    

                                      ፈቃዱ ከተማ

                                /  የስራ ባልደረባ  /

         

             የህዳሴ ግድቡን ከጅምሩ ከመሠረት ድንጋዩ ጀምሮ አሁን ድረስ የሚታዩ

        ትልልቅ ፎቶዎችን በዳኜ የተነሱ ናቸው ፡፡

 

 

                                        አርአያ  ጌታቸው

                                    / የስራ ባልደረባ /

      

                   ዛሬም ድረስ በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚዞሩት የሚዟዟሩት ፎቶዎች

       ዳኔ አበራ  ፎቶዎች ናቸው ፡፡

 

                

                                            አበረ  አዳሙ

                                     /   የስራ ባልደረባ /

 

             ዳኜ  ፎቶግራፈር ብቻ አይደለም ለሙያውም የተሰጠ እንጅ ! የአዲስ አበባ

        ማዘጋጃ ቤት ነባር የከተሞችን ፎቶ ቢጠየቅ የለውም : ዳኜ ግን ጽዳት ጀምሮ

        አስከ መጨረሻ ለውጣቸው ድረስ ታሪካቸውን / መልካቸውን /  እድገታቸውን

         ጠብቆ  በፎቶ ያስቀምጣል ፡፡

 

 

                                    ጋዜጠኛ  ጌታቸው ለማ

 

                 ዳኜ ቢሮ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን  በጦር ሜዳም ተገናኝተናል በተለይ

        በባድመ ሽራሮ ግንባር ያነሳቸው የሰራቸው  ፎቶዎች በጣም ውብና የማይረሱ

       ነበሩ ! ገና ፎቶውን ስናይ ይሄ  የዳኜ ፎቶ ነው ብለን እንለየዋል ፡፡፡

 

                                          አስቴር ኤልያስ

                                      / የስራ ባልደረባ  /

    

           እጁ የማያርፍ ሰው ታውቂያለሽ በሚንቀሳቀስበት ሁሉ  ሁሉንም ማንሳ

      ደስ የሚለው ሰው ነው ፡፡

   

                                              ፀሐይ  ንጉሴ

                                          / የስራ ባልደረባ /

                 ዳኜካሜራ  አይን  ነው  ማለት ትችያለሽ  አንች ያላየሽውን ዳኜ ቀድሞ ነው የሚያየው ፡፡

 

 

                                     ወለተ ማሪያም ሰይፉ

                                      / የስራ  ባልደረባ  /

 

            በአብዛኛው  ፎቶግራፎችን  የፊት ገፅ ላይ የምንጠቀማቸው  የዳኜ አበራን ፎቶዎች ነው ፡፡

 

 

 

                                               አስራ ስድስት

          

                                                           

 

        የበዙ ሞቶችን አምልጫለሁ፡፡ በአይኔ እያየኀቸው በእጄ እየዳበስኀቸው ሁሉንም

    የሞት አዚም አንጋዳዎች 16 የኪዳነ ምህረት እለት ነው ያለፍኀቸው በዚህ

    በሚዳበሰው ፎቶግራፍ ህይወቴ ውስጥ ሦስት " " ህጎች አሉኝ ! እነሱም

    መፍጠር መፍጠን መፍጠጥ ፡፡

 

        በአሁኑ ዘመን ግን በግልባጭ ነው መፍጠጥ መፍጠን መፍጠር አንድም ለሀገራቸው ሳይሰሩ ምላሰ ጮሌና አፍጣጮች የሚከበሩበት ሀገር አየሆነች ሳይ ይደንቀኛል መንግስትም ለሀገር የሰሩትን አይፈልጋቸውም ! ሀቀኞችም ለሃገር ታሪክ የሰሩ ይህን ሰርተናል ብለው አይወጡም እንጂ ብዙ ጀግና በየቤቱስ አለ ፡፡

 

          የቀድሞ ባህርኃይል ባልደረቦቼ እና አለቆቼ ጀግኖች ምፅዋ ጦርነት ላይ ቃል የገባነው እጅ ልንሰጥ አይደለም በማለት መይሳው ካሳ ጥይቱን ሲጠጣ በተሳለ ትልቅ ስዕል

   ላይ እራሳቸውን ሰውተዋል ፡፡ ዛሬ በሴራና ተንኮል እድገቷን በማይፈልጉ ሃገራትና ባንዳዎች  ሀገራችን ፈተና እየገጠማት ብትሆንም  

  ለወደፊት የልጅ ልጆቻችን ተዋደውና ተከባብረው በፍቅር የሚኖሩባት ኢትዮጵያ እንደምትሆን አልጠራጠርም ያን ጊዜ ለሀገር መስዋት የከፈሉ የሚታወሱበት ጊዜ ይሆናል ፡፡

 

        ይህ የተሰባጠረ በክስተት የተሞላ የኔ ብቻ የሚመስል ግን የብዙ ጓዶች ጥምር ነው፡፡  እንዲሁም ለሃገሬ በፎቶ ታሪክን እንድሰንድ ለአደረገኝ ለቀድሞ ባህር ኃይልና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እናም በየአመቱ ለኢትዮጵያ በሙያቸው በጎ ለሰሩ ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት ላይ 2011 . እጩ ሆኜ እንድሸለም ላደረጉኝ እና  እንዲሁም ለሀገሬ በፎቶ ታሪክ እንድሰንድ ላደረገኝ  2000 . ለስራ ትጋቴ በክብር ለሸለመኝ  ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ካሜራቸውን እንዳነገቱ  ለተሰውት ባልደረቦቼ ዘውዱ ኃይሉ እና ዋሲሁን መታሰቢያነቱ

 ይሁንልኝ ፡፡

  

          እስትንፋሴ  እስካለች  ፎቶግራፍ ህይወቴ ይቀጥላል .........

                አንጋፍ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ዳኘ በላይ አበራ

 

              

                                      ፈትለ ቤተሰብ

 

    22 ዓመት ያህል ያከበርነው አሁንም የቀጠለው ከውዷ ባለቤቴ / ትርንጎ ሃይሉ ጋር የመሰረትነው ትዳር እግዚአብሔር አክብሮን የአብራክ ትሩፋት ለግሶናል፡፡

ለባለቤቴ / ትርንጎ ሃይሉ ምስጋናየን ማቅረብ እገደዳለሁ ፡፡ የስራ ባህሪየን

አስማምታ ቤተሰባችንን ጠብቃለች ተንከባክባለች እናም እግዚአብሄር እድሜና ጤና

ይስጥልኝ ልጆች ሄለን ዳኜ አበራን ፍፁም ዳኜ አበራን እና ናሆም ዳኜ አበራን፡

አፍርተናል . . . 





























 

 

አስተያየቶች

  1. ድንቅ ስብእና ከሞያ ብቃት ጋር ያለው የኢትዮጰያ ጀግና ❤️ ለአዳዲስ ባለሞያዎች የምታደርገው ድጋፍ ደግሞ የማይረሳ ነው በርታልን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. ዳኜ ፈጣሪ ለክብር ያብቃህህህ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. ዳኙ ትልቀ ሰብዕና ያለህ ስራ ወዳድ የሙያ ፍቅርህ ጥግ የደረሰ፣ታታሪ ነህ።ስለተዋወቅን አብረን ስለሰራን ዕድለኛ ነኝ!

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

አስተያየት ይለጥፉ

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች