አለም ብርሀኔ ደስታ
ተወዳጅ
ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያው ዘርፍ ጉልህ አሻራ የነበራቸውን ጋዜጠኞች፣ የቴክኒክ ሰዎች ፣ የሚድያ መምህራን ፣ የማስታወቂያ
ሚኒስቴር የሥራ መሪዎችን እያፈላለገ የህይወት ታሪካቸውን እየሰነደ
ይገኛል፡፡ ይህ የተሰነደ ታሪክ መዝገበ- አእምሮ መጽሀፍ ቅጽ 2 ላይ የሚወጣ ሲሆን ቅጽ 1 መዝገበ-አዕምሮ ከፍተኛ ተቀባይነት
ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ ታሪኩን የምናቀርብለት ሰው አለም ብርሀኔ ደስታ ይባላል፡፡ በአለም በኢትዮጵያ
ሬድዮ በቴክኒክ ዘርፍ ላይ ከማገልገሉ በላይ የጣቢያው የቆየ ታሪካዊ የስቱድዮ እና የመስክ መሳሪያዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረጉ ስሙ ይነሳል፡፡
በተለይ ኢትዮጵያ ሬድዮ የሬድዮ ቀንን ባከበረ ጊዜ ለኤግዚቢሽን የሚሆኑ የድሮ እቃዎችን በማሰባሰብ አለም የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡
እንደ አለም አይነት ብርቱ ሰዎች ያለፉበት መንገድ ያስተምራል በሚል እሳቤ የህይወት ታሪኩን እዝራ እጅጉ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡
ከልደት እስከ ዕድገት
መምህር አለም ከአባቱ ከአቶ ብርሃኔ ደስታ ፣ ከእናቱ
ወ/ሮ ሄዋን ተድላ የካቲት 25 1969 ዓ.ም በቀድሞ ትግራይ ክፍለ ሃገር በምስራቃዊ
ዞን ደብረ ዳሞ ገዳም አካባቢ እንትጮ ወረዳ ጉሎ ምካዳ መንደር ተወለደ ፡፡ መምህር
አለም በተወለደ በ2 ዓመቱ ከእናቱ ጋር ወደ ኤርትራ ክፍለ - ሃገር
አስመራ ከተማ በመሄድ ዕድገቱ ገና ሀ ብሎ ጀመረ
፡፡ በመስከረም ወር 1975 ዓ.ም
ወደ ትምህርት አለም ተቀላቅሎ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርቱ በአግአዚያን ት/ቤት ፤ ሁለተኛ
ደረጃ ከ7ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ደግሞ በዶግዓሊ ት/ቤት እንዲሁም 9ኛ ክፍል በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ( ቀ.ኃስ ) ( ቀይሕ ባሕሪ ) ት/ቤት
ተምሯል ፡፡ በወቅቱ ከባድ ጦርነት ስለነበረ
ከእናቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ ነሐሴ
22 / 1982 ዓ.ም በታላቅ ወንድሙ መልካም ሁለተኛውን
ምዕራፍ ኑሮውን ለመኖር በመምጣት ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ትምህርቱን
በአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (
ጂሲኤ ) ተምሯል፡፡
ከልጅነት ዕድሜ እስከ ወጣትነት ዕድሜ ድረስም እግር ኳስ በሰፈር በመጫወትና ወወክማ በመሰልጠን
፤ በመመልከት እና በስነ- ስዕል ጥበብ ፤ በዕደ
ጥበብ ሙያና በፈጠራ ሥራዎች ክህሎትና ችሎታ ነበረው ፡፡
አለም በሥራ ዓለም
1985 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዶ ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃ ውጤት ስላልነበረው ፣ ታላቅ ወንድሙ ድንገት በሞት ሲለየው ፤ ደካማ
አይነስውር እናቱን ለመርዳት ፤
ኑሮውን ለማሸነፍ ሲል መርካቶ ጎማ ተራ በግለሰብ ንግድ ተቀጥሮ የመኪና ጎማ በመሸጥ በሚከፈለው
ዕለታዊ ክፍያ እናቱን ቤት ተከራይቶ በመርዳት
፤ በማታ
ክፍለ - ጊዜም በኤሌክትሮኒክስ በአዲስ አበባ ተግባረ - ዕድ
ት/ቤት በመማር በከፍተኛ ውጤት በማዕረግ ሀምሌ 1992 ዓ.ም በዲፕሎማ ተመርቋል
፡፡ ከዚህ በኃላ በተማረበት
ሙያ ሥራ ለማፈላለግ
ለአንድ ዓመት ያህል ከቆየ በኃላ ሀምሌ
01 /1993 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሬድዮ ድርጅት በቴክኒክ ሙያ ዘርፍ ተቀጥሮ ሥራውን ጀመረ
፡፡ በቀጥታ ስርጭትና መስክ ቀረጻ ክፍል ተመድቦ ፣ በተለያዩ
ማህበራዊና ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁነቶች ከጋዜጠኛ ጀርባ በመሆን ፤ በተንቀሳቃሽ
ሬድዮ ስቱድዮ ቀጥታ ስርጭትና እና በመስክ ቀረጻ በከተማና ገጠር በናግራ ሪል ቴፕ ቀረጻን በጥራት ይህም በፓርላማ መደበኛ ስብሰባዎች
፤ በከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮችን
ንግግርና ጋዜጣዊ ወቅታዊ ሁነቶች
፣ የበአላት ሙዚቃ ቀረጻዎች በተለይም በሳምንት ዓርብ ቀን የሚተላለፈው የሊቀ- ናይል የተማሪዎች
ጥያቄና መልስ ውድድር በጀማሪነት ከሪል ቴፕ
ቀረጻ ጀምሮ እስከ አዶቤ እና ፍላሽ ቀረጻ ድረስ በግንባር ቀደምትነት
እንዲሁም በሬድዮ ስቱድዮ በቴክኒክ ቀረጻና በሲስተም ቴክኒክ ጥገና ባለሙያነት
አገልግሏል ፡፡
ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቴሌቪዥን ሲስተም ላይም በርካታ ሥራዎችን በመስራት ውጤታማ የነበረ ሲሆን ይህም በስቱድዮ ኢንስታሌሽን
ሥራዎች ማለትም የኢቢሲ ባህርዳር ጊዜያዊ ስቱድዮ ኢንስታሌሽን
ሥራ ፤ ዲያግራም ስራ ፤ የተለያዩ
የአርክቴክት ሥራዎችን ሰርቷል ፡፡ በተጨማሪም በስቱድዮ ሲስተምና ሳተላይት ዘመናዊ የቴክኒክ ጥገና ማዕከል እንዲኖር ከፕሮፖዛል
ጀምሮ እስከ ጥናታዊ ጽሁፍ በማዘጋጀት
ባለሙያዎችን በማስተባበር የልምድ ልውውጥ እንዲወስዱ
ሁኔታዎችን በማመቻቸትና በተለያዩ የመስክ ቀጥታና ቀረጻ ሥራዎችን በማከናወን
፣ የተለያዮ የቴክኒክ ጥገና ስራዎችን በመሳተፍና
በመስራት ውጤታማ ተግባራትን
አበርክቷል ፡፡
ታሪካዊ ሙዚየም
ከየካቲት 2008 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ በተቋቋመው
የኢቢሲ ሚዲያ ታሪካዊ ሙዚየም ከጽንሰ- ሃሳቡ
ጀምሮ ባደረገው ጥረት የሙዚየም ቡድን መሪ በመሆን በተሰጠው ኃላፊነት በርካታ ቅርሶችን በማሰባሰብ
፤ ለግንባታ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን
በማሰባሰብ ፕሮፖዛልና የመዋቅር ፕላን በማዘጋጀት
የግንባታ ሥራዎችን ጀምሮ በተግባር በመጨረስ በሬድዮና በቴሌቪዥን
ኮርነር የተለያዮ ተቋሙን በይዘትና በሚዲያ ቴክኖሎጂ የሚዘክሩ ሁነቶችን በፎቶግራፍ
፣ በቴክኒክ መሳሪያዎች ፤ በኦዲዮ ቪዥዋል እና በስክሪን በማዘጋጀት ለዕይታ አቅርቧል
፡፡ ባለው የወደፊት ዕቅድና ራዕይም ሙዚየሙን ለማሳደግ ከብሔራዊ ሙዚየም ጋር የሥራ ግንኙነት በመፍጠር
ሙያዊ እገዛ
ማግኘት ችለዋል ፡፡
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በሙዚየምና
ቤተ-መጻህፍት ቡድን መሪ በኃላፊነት በመስራት ከሙዚየም ጎን ለጎን ቤተ-መጻህፍትንም
ለማደራጀት ዕቅድን በመንደፍ በከፍተኛ ሞራል ዘመናዊ ቤተመጻህፍት
አውቶሜሽን የመረጃ ማዕከል እንዲኖር ፕሮፖዛል በማዘጋጀት
፤ ስራውን ሳይንሳዊ በሆነ ጥናት እንዲደገፍ
ከተለያዮ ተቋማት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፤ ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና
ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ፤ ከስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር ሙያዊ ግንኙነት በማድረግ ጥናታዊ ጽሁፍ ፤ ዝርዝር
የበጀት ስፔስፊኬሽን ሰነድ በማዘጋጀት
ስራውን ለመጀመር በሂደት ላይ እያለ በበጀት እጥረት ምክንያት ስራው ሳይሳካ ቀርቷል ፡፡
ከሰኔ 01 / 2010 ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ በተሰራው አዲስ የአደረጃጀት
መዋቅር በዋና ላይብረሪያን
የሥራ መደብ እስካሁን ድረስ በማገልገል
ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤ የተሰጠውን
ኃላፊነት ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ለመምራት ታህሳስ 2011 ዓ.ም ከብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት
ኤጀንሲ የቤተ-መጻህፍት ሙያ የአሰልጣኞች ስልጠና ተከታትለው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል ፡፡ ባገኙት ሙያዊ ክህሎት ስራቸውን ውጤታማ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ
፡፡ በአጠቃላይ 17 ዓመት በከፍተኛ
ቴክንሽያን ፤ ለ5 ዓመት በሙዚየምና
ቤተመጻህፍት በቡድን መሪነትና በዋና ላይብረሪያን
በማገልገል ላይ ይገኛል ፡፡
መንፈሳዊ
ህይወትና ግልጋሎት
መምህር አለም ብርሃኔ ከልጅነቱ ጀምሮ ከቤተሰብ ባገኘው የክርስትና እምነት ታንጾ በማደጉ ምክንያት ከልጅነቱ ጀምሮ አሁን ለደረሰበት ከፍተኛ መንፈሳዊ ደረጃ መሠረት ጥለው ለልጆቻቸውና ለመጪው ትውልድ አብነት ለመሆን መልካም ጅማሮ በመሆኑ በእግዚአብሄር ቃል በጥበብ ታንጾ በጥበብ በዕውቀት ለማደግ በነበረው ህልምና ራዕይ ገና መንፈሳዊ ትምህርት በነሃሴ
1984 ዓ.ም በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውልደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በአባልነት
ተመዝግበው ፤ የ8ኛ ዙር ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት በሚገባ ተከታትሎ
፤ በሰ/ትቤቱ በተለያዩ የኮሚቴ አደረጃጀት በሰባሳቢነትና
በአባልነት ከማገልሉ በተጨማሪ በሰ/ትቤቱ በሚሰሩት የኪነጥበብ ስራዎች በራሄል ዕንባ ፤ በደም
ድምጽ በመሳሰሉት ትልልቅ የመድረክ ድራማዎች ላይ
በተዋናይነት ሰርቷል ፡፡ እንዲሁም በሚሰጠው መንፈሳዊ ተከታታይ ኮርስ በአስተማሪነት
አገልግሏል ፡፡
ፈጣሪውን ለማገልገል በነበረው ከፍተኛ እሳቤ ከአባ ልብሰ ወርቅ ዘንድ የአብነት ትምህርት ውዳሴ ማርያም ፤ ከአባ
ክፍለ ዮሃንስ ንባብ በመማር ፤ በታህሳስ
1991 ዓ.ም ከሊቀ ጳጳስ አቡን እጅ የዲቁና ማዕረግ ተቀብሏል
፡፡ አሁንም እግዚአብሄር ለማገልገል
ትልቅ ራዕይ ስለነበረው
መንፈሳዊ ዕውቀት በስፋት ተምሮ ለማስተማር
ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሃምሌ 3
/ 1996 ዓ.ም በዲፕሎማ እና በሰኔ
05 / 2002 ዓ.ም ባችለር ዲግሪ በስነ መለኮት ( ቲኦሎጂ )
በብቃት ትምህርቱን ተከታትሎ ከፓትሪያሪክ ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እጅ ዲግሪና ዲፕሎማ ከነሙሉ ክብሩ አግኝቷል
፡፡
መምህር አለም ብርሃኔ ባገኛው ባለ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ ዕውቀት ቅድስት ኦርቶቶክስ
ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለማገልገል ፤ ምዕመናንን በመንፈሳዊ
ትምህርት ለማነጽ ለተከታታይ
አስር ዓመታት በተለያዩ ገዳማትና አድባራት ፤ በማታ
መርሃ ግብር ፤ በመንፈሳዊ
ማህበራትና ሰንበት ትምህርት ቤቶች
፤ በመንፈሳዊ ጉዞዎች በማስተማር
በስብከት በትሩፋት አገልግሏል ፡፡
የትዳር
ህይወት ፡
ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት በእግዚአብሄር
መልካም ፈቃድ ጋብቻውን ከወ/ሮ ለምለም ስለሺ በስርዓተ ቤተክርስቲያን በተክሊልና
በቅዱስ ቁርባን ህዳር 07
/ 2001 ዓ.ም በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን
ፈጽሟል ፡፡ በትዳር ህይወትም አራት ሴት ልጆች ሶሊያና አለም
፤ ኑሃሚን አለም ፤ ዮስቲና አለም እና አሜን አለም ወልዷል ፡፡
ልጆቻውም ወደፊት ሀገርንና ቤተክርስቲያንን ለማገልገል
በፈሪሃ እግዚአብሔር በመንፈሳዊ
ጥበብ ዕውቀት እያሳደገ ይገኛል
፡፡
አለማዊ ትምህርትን በተመለከተ ፡
Ø በሃምሌ 1992 ዓ.ም
በኤሌክትሮኒክስ ሙያ ዘርፍ ዲፕሎማ ከአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ት/ቤት
Ø ሰኔ 2001 ዓ.ም
በአድቫንስድ ኤሌክትሮኒክስ ዲፕሎማ ከአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ኢንዱስቲሪያል ኮሌጅ
Ø በመስከረም 2014 ዓ.ም በማኔጅመንት
ባችለር ዲግሪ ከኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ
Ø በአሁኑ ጊዜም በማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ የ5ኛ ዓመት ኮምፒውተር ኢንጀሪንግ
በመማር ላይ ይገኛል ፤
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ