ንጋት በቃና
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ሰዎችን የህይወት
እና የሥራ ታሪክ በመሰነድ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡ ቅዳሜ ሀምሌ 30 2014 ዓ.ም ‹‹መዝገበ-አዕምሮ›› በሚል ርእስ የ180 የሚድያ ሰዎች ታሪክ በጠንካራ ሽፋን በተዘጋጀ መጽሀፍ ታትሞ መመረቁ
ይታወቃል፡፡ በቅጽ 2 ታሪካቸውን ከምንሰንድላቸው የሚድያ ሰዎች መካከል
ንጋት በቃና አንዷ ናት፡፡ ንጋት በቃና በፋና ሬድዮ በጋዜጠኝነት
፣ በኢቲቪ በዜና አንባቢነት፤ እንዲሁም በፖሊስ ፕሮግራም ያገለገለች ሲሆን አሜሪካን ሀገር ከሄደች በኋላም ደግሞ በውጭ ሀገር የሚደረጉ
ክንውኖችን በፕሮግራም እና በዜና በመስራት ለኢቲቪ እየላለች ትገኛለች፡፡ የንጋት በቃናን የህይወት ታሪክ ዕዝራ እጅጉ እንደሚከተለው
ሰንዶታል፡፡
1963 ዓ.ም በወርሃ መጋቢት ከአባቷ ኮ/ል በቃና አራርሶ ከእናቷ ወ/ሮ ትዝታ ሙሳ ነጌሌ ቦረና ውስጥ ተወለደች። እድገቷ አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ነው።
የመጀመሪያው
ደረጃ ትምህርቷን በየተባበሩት መምህራን እና - ዮርዳኖስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በሽመልስ ሀብቴ እና ንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኮሌጅ ትምህርቷን ደግሞ በዮኒቲ ዮኒቨርሲቲ አጠናቃለች።
ገና
ከማለዳው አባቷ ኮ/ል በቃና አራርሶ ልጆቻቸው እንዲያነቡት በቤት ውስጥ የሚያኖሯቸው ዳጎስ ያሉ የታሪክ እና ልቦለድ መፅሃፍቶች የሥነ- ፅሁፍ እና የንባብ ፍቅሯን ይበልጥ እንዳጫሩት ትናገራለች።
ለጋዜጠኝነት
ያላት ፍቅር ገና በልጅነቷ እንደጀመረ የምትናገረው ጋዜጠኛ ንጋት በቃና በኢትዮጵያ ሬዲዮ የምትሰማቸው አንጋፋዎቹ ጋዜጠኞች እነ መአዛ ብሩ ፣ደረጀ ሀይሌ፣ኢሳያስ ልሳኑ እና ሌሎችም በ70ዎቹ መጨረሻና በሰማንያዎቹ አጋማሽ የነበሩ ተወዳጅ ጋዜጠኞች ምሳሌዎቿ እንደነበሩ ታስታውሳለች።
ከአንድ
ወንድሟ እና አራት እህቶቿ መካከል በአንድ ወቅት እርሷም ጋዜጠኛ የነበረችው እና በኋላም ወደ ህክምና ሙያ ያዘነበለችው
ታላቅ እህቷ ፍሬህይወት በቃና በ1985 አ.ም ጋዜጠኝነትን አንድ ብላ ለጀመረችበት ለገዳዲ ሬዲዮ ጣቢያ መግባት ምክንያት ነበረችና አርአያነቷን ሁሌም ከምስጋና ጋር ታስበዋለች።
በለገዳዲ
ሬዲዮ ጣቢያ በነበራት የሁለት አመት ቆይታ በወቅቱ በጉጉት እየተጠበቀ በሚደመጠው "እሁድን ላንዳፍታ" የተሰኘው ዝግጅት ላይ ሰርታለች።
ጋዜጠኝነትን
በተለያዩ የሥነ- ፅሁፍ እና የጋዜጠኝነት ኮርሶች አዳብራ በ1987 ህዳር ወር ሬዲዮ ፋናን ተቀላቀለች። ቅዳሜ "አብረን እናረፋፍድ" አርብ ምሽት በነበረው መዝናኛ ላይ በፕሮግራም አቅራቢነት ፣ ታዋቂና ዝነኛ ሰዎችን ቃለ-መጠይቅ በማድረግ እንዲሁም በብዙዎች በሚወደደው የዜና አቀራረብዋ በጣቢያው በነበራት የአምስት አመት ቆይታ ከፍተኛ ተደማጭነትን አትርፋለች። ፋና የጋዜጠኝነትን ሀሁ የቆጠረችበት ጋዜጠኝነት ከሥራዎቿ አንዱ ሆኖ እንዲቀጥል ምዕራፍ የተጣለበት ጊዜ እንደነበር ታስታውሳለች።ንጋት በቃና ፋና በነበረችበት ጊዜ
በዜና አቀራረቧ ተወዳጅ እንደነበረ የፋና ጋዜጠኛ ዮናስ አብርሀም ይናገራል፡፡ ዮናስ አብርሀም፣ ንጋት ፋና ሲጀመር አንስቶ የነበረች በመሆኗ የራሷን ቀለም ያበጀች ናት ይላል፡፡
የዚህ ግለ-ታሪክ ጽሁፍ አዘጋጅ ከዚህ ቀደም ንጋት አየር ላይ ታውላቸው የነበሩትን መሰናዶዎች በማየት እንደተረዳው ጋዜጠኛዋ የዚያን ዘመን ጠንካራ እና ብርቱ ነበረች፡፡
ጋዜጠኛ
ንጋት በቃና ከትዳር አጋሯ ዶ/ ር መላኩ ግርማ ጋር 4 ልጆችን አፍርታለች። ከ1992 ዓ.ም እስከ 1996 ዓ.ም ያለውን ዘመኗን በትምህርት እና ልጆችን በማሳደግ ማሳለፏን ትናገራለች።
ንጋት በቃና፣
በህግ ትምህርት ከዩኒቲ ዮኒቨርሲቲ ከተመረቀች በኋላ
ወደ ጋዜጠኝነት ሙያዋ በመመለስ በፓሊስ እና ህብረተሰብ ሬዲዮ የህግ ፕሮግራም አዘጋጅ ሆና ለአንድ አመት ሰርታለች።
በ1996
ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለዜና አቅራቢነት ባወጣው ማስታወቂያ ይህንንም ተከትሎ ካወዳደራቸው 856 ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ ካለፋት 3 ዜና አንባቢዎች መካከል አንዷ ሆና መመረጧን ዛሬም ጋዜጠኝነትን ስታስብ በኩራት የምታስታውሰው ትዝታ ነው።
ከ1997
አ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው ጋዜጠኛ ንጋት በቃና ባህር ማዶም ተሻግራ ሙያዋን አልተወችም።
ዋሽንግተን
ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ በርካታ የሚባሉ የተለያዩ የሚዲያ ሥራዎችን ሰርታለች።
የኤምባሲው
ሥራዎች ላይ ያተኮሩ ዝግጅቶች " በአገራዊ ጉዳይ ላይ የዲያስፖራው ተሳትፎ" በሚል ርዕስ በአርአያነታቸው የሚጠቀሱ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሞክሮዎችን በማቅረብ ሰፊ ሥራ ሰርታለች።
በተለይም
ከብዙ የሚዲያ ዕይታዎች ውጪ የሆኑ በርካታ ዜናዎችን ሰርታለች።
በኮሙዩኒቲ
ደረጃ የኢትዮጵያውያንን እንቅስቃሴዎች የቃኙ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን በአለም መድረክ ስለአገራቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎችን ተከታትሎ እና በቦታው ተገኝቶ በመዝገብ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአየር ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ በሙያው ለአገር ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች።
በጋዜጠኝነት
ህይወቴ በኢትዮጵያ ውስጥ በአገሬ ሆኜ ከሰራሁት ጊዜ ይልቅ ውጪ ሆኜ የሰራሁት በቁጥር ይልቃል የምትለው በዜና አዘጋገብ ብቃት የተካነችው ጋዜጠኛ ንጋት በቃና ዛሬም ድረስ ሙያዋን አክብራ ስራውን ቀጥላለች።ንጋት በቃና አየር ላይ ካዋለቻቸው መሰናዶዎች
አንዱ ስለ እማሆይ አጥናፍወርቅ አባተ የሰራችው ይገኝበታል፡፡ ይህ
መሰናዶ የ80 ደቂቃ ዘጋቢ ስራ ሲሆን በባህር ማዶ ለረጅም አመታት የኖሩትን የእማሆይ አጥናፍወርቅ የህይወት ገጽ የሚፈትሽ ነው፡፡
ንጋት ይህን ዶክመንተሪ ለመስራት ብዙ ለፍታለች፡፡ የዚህ ግለ- ታሪክ አዘጋጅ እንዳጤነው ለዘጋቢ ፊልሙ የተጠቀመቻቸው ማልበሻ ምስሎችም
ተገቢነት ያላቸው ነበሩ፡፡ ሙሉ ዘጋቢ ፊልሙን ለማየት ጽሁፉ ሲያልቅ ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡፡
ንጋትን በቅርብ የሚያውቁ የሰጡት ምስክርነት
ጋዜጠኛ ንጋት በባህር ማዶ ሲካሄዱ የነበሩ ሁነቶችን በአግባቡ ትዘግብ ነበር፡፡
ካሜራ ማን ቀርጾ የሚያመጣው ፕሮፌሽናል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አሰነድታ አየር ላይ ታውል ነበር፡፡ ትልቁ የንጋት ችሎታ የእቅድ
ችሎታዋ ነው፡፡ ምን አይነት ጉዳዮች መሰራት አለባቸው ወይም የለባቸውም በሚለው ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤ አላት፡፡ በራሷም ተነሳሽነት
ባለፉት 7 አመታት የሰራቻቸው መሰናዶዎች ትልቅ ለውጥ ያመጡ እና በባህር ማዶ ያለውን የኢትዮጵያውያን ንቅናቄ ለማሳየት የሞከረችበት
ነው፡፡ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ ንጋት ትዘግብ ነበር፡፡ከ30 በላይ በሚጠጉ ግዛቶች እየዞርን የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ስናከናውን ንጋት
በሚድያ ታሪክ የማይዘነጋውን ጉልህ ተግባር አከናውናለች፡፡ የኢትዮጵያ ቲቪም ያለቀለት ፕሮግራም ስለሆነ የምትልክላቸው ደስተኛ መሆናቸውን
በየጊዜው ይናገራሉ፡፡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም እንግዶችን በማነጋገር የንጋት ሚና ትልቅ ነበር፡፡ ንጋት መዘገብ ያለበትን እና የሌለበትን
በሚገባ ታውቃለች ፡፡ በዚህም ሙያዊ አደራዋን ተወጥታለች ብዬ ገምታለሁ፡፡
አቶ ፍጹም አረጋ -በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩ
ንጋት በባህር ማዶ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በማሳወቅ የጎላ አስተዋጽኦ ነበራት፡፡
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብረን መሆናችንን በወጉ ለማሳየት የቻለች ጎበዝ ጋዜጠኛ ነች፡፡ ዳያስፖራው በሀገሩ ጉዳይ ያለውን ምልከታ
ለማሳየት ችላለች፡፡በዩቲዩብ ላይም ክሊፖችን በመጫን ለሙያዋ ያላትን ፍቅርና ታማኝነት እንድናውቅ አድርጋለች፡፡ በዚህ ጥረቷ ሁላችንም
አድናቆታችንን እንቸራታለን፡፡
ማርታ ገብረስላሴ/
አሜሪካ
ከ ወ/ሮ ንጋት
በቃና ጋር እንደ አውሮፓ ቀመር ከ 2015-2018 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አብሮ የመስራት ዕድሉን ያገኘሁ ሲሆን፥ በቆይታየም
ወ/ሮ ንጋትን በጋዜጠኝነት ሙያዋ አገሯን ስታገለግል የሚታይባት ወኔ፣ፍጥነት፣ ትጋት፣ ሰዓት አክባሪነት፣ ሰዎችን የማግባባት፣ የማነሳሳትና
የማስተባበር ችሎታዋ እጅግ የሚደነቅ ነበር፡፡ ከሌሎች የኤምባሲው ባልደረቦች፣ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን ጋር የምታሳየው አክብሮትን የተጎናጸፈ መግባባትና አንድነት ለብዙዎቻችን የሥራ
ተነሳሽነትን የፈጠረ ነበር፡፡ በተለይም አገር ወዳድነትን፣ ግልጽነትን እና ቅንነትን የተላበሰው ስብዕናዋ የምትጠይቃቸውን ብቻ ሳይሆን
ያልጠየቀቻቸውን ተጨማሪ መረጃዎች በማስገኘት ለጋዜጠኝነት ሙያዋ ተጨማሪ ብቃትና ስኬትን ሲያጎናጽፍላት ለማየት የቻልሁባቸው በርካታ
አጋጣሚዎች ነበሩ ፡፡ አብረን የታደምናቸውን ኩነቶች በምታዘጋጀው ዜና እንደ አዲስ በተመስጦ ለመስማት/ለማየት መገደዳችንን ሳስብ፥
የ ወ/ሮ ንጋትን የጋዜጠኝነት ብቃት ለመመስከር ሁነኛ አስረጂ ሆኖ አገኘዋለሁ።
ንህነ
መሠረት
አደመ
(በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቀድሞ ባልደረባ)
መዝጊያ
ጋዜጠኛ ንጋት በቃና ከ28 አመት በፊት አንድ ብላ የሚድያ ስራን ጀምራ ዛሬም በጽኑ ፍቅር እየሰራች ትገኛለች፡፡ በተለይ
በባህር ማዶ በአሁኑ ሰአት ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በዲፖሎማሲው መስክ መወጣት ያለባትን አደራ እንደ ጋዜጠኛ ተወጥታለች፡፡
ይህም በተወዳጅ ሚድያእና ኮሚኒኬሽን ትልቅ አክብሮትን የሚያሰጥ ነው፡፡
ለሀገር የሰራ ታሪኩ ይከተባል፡፡ ተረካቢ ትውልድ ሲመጣም ይማርበታል፡፡
ንጋትም በዚህ መልኩ ወደፊት ለምታደርገው ጥረት ተወዳጅ ሚድያ የሙያዊ እና ሌሎች እገዛዎችንም ለማድረግ ቃል ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን
ከሚወዱ ጋር ሁሌን እናብራለን፡፡ ንጋት አየር ላይ ያዋለቻቸውን መሰናዶዎች ለማየት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡፡
1.
2. https://fb.watch/g1nTTh3VXq/
3.
4. https://youtu.be/0PMd7dJcZGA
5.
6.
7. https://fb.watch/c795aTj3w4/
8.
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ