ጋዜጠኛ አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ

 ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን  የሚድያ ሰዎችን ታሪክ እያፈላለገ ለትውልድ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም በሐምሌ 30 2015 . ‹‹መዝገበ-አእምሮ›› በሚል ርእስ መጽሐፍ አሳትሞ ማስመረቁ ይታወቃል፡፡  በቅጽ ሁለት ታሪካቸው ከሚሰነድላቸው የሚድያ ሰዎች አንዱ አማኑኤል አብርሃም ነው፡፡ አማኑኤል በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ከምስረታ አንስቶ ከነበሩ ባልደረቦች አንዱ ነው፡፡ ዜና በብዛት በመስራት የሚታወቀው አማኑኤል አብርሃም 2 መጽሐፎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡ የአማኑኤልን ታሪክ አንተነህ ደመላሽ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡

 

የሚድያ ሰው አማኑኤል አብርሃም÷ በወርሃ ግንቦት በዕለተ- እሁድ ምሽት 12 ሰዓት 1961 . በቀድሞው አጠራር ዎላይታ አውራጃ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ቡጌ በምትባል መንደር ተወለዱ፡፡ ምጣኔ እድገታቸው ለአቅመ - ትምህርት ሲደርስም በመንደራቸው ወደሚገኘው ቡጌ ትምህርት ቤት 1 እስከ 6 ክፍል ተማሩ፡፡ በመቀጠል 5 . ርቆ በሚገኘው ‹‹ጋቼኖ›› በሚባል መንደር በማምራት 7 እና 8 ክፍል ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ በየ 2 አመት ልዩነት ትምህርት ቤት እየለወጡ የሚማሩት 9 እና 10 ክፍል ትምህርታቸውን ደግሞ ቦዲቲ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት አጠናቀቁ፡፡

 

በዚህ መሀል የተማሪ አማኑኤል ቤተሰብ ጠቅሎ አዲስ አበባ ሲከትም 11 እና 12 ክፍል ትምህርታቸውን ቦሌ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ቤት በመግባት ጨረሱ፡፡ 1983 . ወቅቱ የኢህአዴግ ሥርዓተ መንግስት ምስረታ ሂደት ላይ ስለነበር በዚህ የሽግግር ወቅት አቶ አማኑኤል በሚኖሩበት ገርጂ ሰኔ 1984 . በአካባቢው ህዝብ ይሁኝታ አግኝተው የቀበሌ አመራር በመሆን መስራት ጀመሩ፡፡ 6ወር የስራ ቆይታ በኋላ በጊዜው በነበረው አጠራር ዞን 3 በሚባለው የክፍለ- ከተማ ደረጃ  ኮሚቴ በመሆን 3 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

              ዋልታ እና አማኑኤል

‹‹…..አባቴ አብርሃም ባባንቶ የግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግኑኝነት ባልደረባ ሆነው ሲሰሩ በተለይ በልጅነቴ የግብርና ዜና ይጽፍና አንብበው ይለኛል፣ ቀጥሎም ስለ ዜና አፃፃፍ መርሆዎች ሲነግረኝ በልጅነት ልቦናዬ የጋዜጠኝነት ፍላጎቴ ተጠነሰሰ የሚሉት አቶ አማኑኤል፡ በጌጃ ቃለ -ህይወት ቤተክርስቲያን የሥነ- ጽሁፍ ኮሚቴ ሆኘ በመስራቴ ደግሞ መስመር ያዝኩ፡፡ በዚህም በቀበሌ አመራርነት ስሰራ የሥነ- ጽሁፍ ችሎታዬን ከመጠቀም ባለፈ አዳበርኩ፡፡ ዋልታ የኢንፎርሜሽን ማዕከል ደግሞ ጋዜጠኛ አድርጎ ቀረጸኝ…›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

 

አቶ አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ ከየ ክልሎች አንድ አንድ ሰው ተመርጦ 1987 . " ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል" ሲዋቀር ከተቀላቀሉ መስራቾች አንዱ ነበር፡፡ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ቅርንጫፍ ለማስፋፋት መጋቢት ወር 1987 . ወደ ደቡብ ክልል ሐዋሳ ሄደው ሪፖርተር ሆነውም ሰርቷል፡፡በ1989 . ወደ አዲስ አበባ በመመለስ "የመገናኛ ብዙኃን ኢንስትቲዩት" ሲቋቋምና ሥራ ሲጀምር ከመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች አንዱ በመሆን 1990 . ዲፕሎማውን አገኘ፡፡

 

1992 . እዚሁ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እየሰሩ በነበረው ሀገራዊ ምርጫ ዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ህዝብን በመወከል የፓርላማ ተመራጭ ሆኑ።ምንም እንኳን የፓርላማ ተመራጭ ቢሆኑም በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እስከ 1995. ድረስ ሰርተዋል፡፡እስከ ሶስት ዙር ድረስ በፓርላማ ተመራጭነታቸው የዘለቁት አቶ አማኑኤል 1993. ጀምሮ የባህል፤ቱሪዝም፤ የመገናኛ ብዙኃን በሙሉ የሚከታተል " የፓርላማ መገናኛ ብዙኃንና ባህል ጉዳዮች" ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሰርተዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስራ አመራር ቦርድ ሆነው ሰርተዋል፡፡

1995 እስከ 2004 . ባሉት አመታት የገዢው ፓርቲ ልሳን ዋና እና ምክትል አዘጋጅ በመሆን ሲሰሩ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ልሳን ላይ 4 ዓመት ያህል በምክትል ዋና አዘጋጅነት የሰሩ ሲሆን ይህ ጋዜጣ እስከ 8ሺህ ቅጂ ድረስ ይታተም እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡በመቀጠል 6 አመታት ደግሞ ደኢህዴን የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  ልሳን ዋና አዘጋጅ በመሆን ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን 186 ሺህ ቅጅ የሚሰራጨውን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን በስድስት ወር ውስጥ ያለበትን እዳ ከፍሎ ራሱን ችሎ እንዲደራጅ እና የከፍተኛ ሀብት ባለቤት እንዲሆን አስችለዋል፡፡

 


















            ዜና አምራችነት

 

ወደ ደቡብ ክልል ሀዋሳ በማምራት በሪፖርተርነት የጀመሩት ጋዜጠኛ አማኑኤል ዋልታ እሰከ ሰሩበት ድረስ በነበራቸው የስራ አፈጻጸም ግንባር ቀደም በመሆን በአመቱ መጨረሻ ላይ ተሸልመዋል፡፡ሙስናን፤ ህዝብን በሚበድሉ አመራሮች ላይ፤ የሥነ ምግባር ጥሰትን፤ ህዝባዊ እሮሮዎችን ከተለያዩ ተቋማት በማጠናቀር ቢያንስ በቀን አንድ ዜና ይሰሩ ነበር፡፡ በዚህም ‹‹ዜና አምራች የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ አማኑኤል የመጡባቸው ሂደቶች ከሚዲያ ጋር የተቆራኙ እንደመሆናቸው  በማህበራዊ÷ በፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና በስነ ምህዳር ላይ የሚያጠነጠኑ ትልልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ የውይይት መድረኮችን፤ በወጣቶች ላይ ህገ- መንግስትን ለማስረፅ በተጀመረውና ለረጅም ዓመታት የቆየው የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር፤ከፕሮጀክት ቀረጻ ጀምሮ ግንባር ቀደም ሆነው አስተዋጽኦዋቸውን አበርክተዋል፡፡ለሁለት ጊዜያት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/EBC/ የቦርድ አመራር በመሆን አገልግለዋል፡፡በተለይ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራር በነበሩበት ወቅት አጠቃላይ የመንግስት ሚዲያ የኢዲቶሪያል ፖሊሲ አልነበረምና በኢትዮጵያ የኢዲቶሪያል ፖሊሲ እንዲኖር ከሌሎች የቦርድ አመራር ጋር የግንባር ስጋ በመሆን ግፊት አድርገዋል፡፡ በሚዲያዎች Style book የጋዜጠኝነት ፀባይ /Code of conduct/ እንዲኖር አበርክቷቸው ሰፊ ነበር፡፡

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  በጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ትምህርታቸውን ሲማሩ በወቅቱ የመጀመሪያ የሆነውን Freedom of Information act በሚል ርዕስ ብዙ ዋጋ ያስከፈላቸውን የመመረቂያ ጽሁፋቸውን አቅርበዋል፡፡ የመረጃ ትርጓሜን ከዓለም፤ ከአፍሪካ፤ ከሀገረ- ኢትዮጵያ አኳያ እንዴት እንደሚታይ በፖሊሲ በመርህ አንፃራዊነት እየፈተሹ በኢትዮጵያ ያለውን የተገደበ የመረጃ ፍሰት የሚያስከትለውን ችግር፣ችግሩም እንዴት መቀረፍ እንዳለበትና ምን ዓይነት ተቋም መገንባት እንዳለበት አመላክተውበታል፡፡ ጋዜጠኛ አማኑኤል "በህይወቴ የምቆጭበት ነገር  በተለይ በአመራር ደረጃ ስንቀመጥ ለመረጃ ያለን የተዛባ አመለካከት ነው፡፡ ዛሬም፣ ወደፊትም ህዝቡ በመረጃ ላይ ተመስርቶ ወደ ድምዳሜ የሚመጣበትን የሚዲያ ስርዓት ካልገነባንና ካልዘረጋን የሚመጣው ማዕበልና ውዥንብር ይዞን እየሄደ የተረጋጋ ሥርዓተ- መንግስት እንዳይኖረን ያደርጋል" በማለት የተስተካከለ የመረጃ ፍሰትን የመረጋገጥን አስፈላጊነት አስረግጠው  ይናገራሉ፡፡

ሀገራዊ ደህንነትን እና የመረጃ ተመጋጋቢነትን አጽንኦት የሰጡት ጋዜጠኛ አማኑኤል ለአመራሩ፤ለሚዲያው፤ ለአጠቃላይ ለህዝቡ መጽሐፍ አድርገው ጥር 2011 . አቅርበውታል፡፡ በነጻነት፤ በፈጠራ ሃሳብ፤በጋራ አመራር፤ በአብሮነት ስራ ላይ ያምናሉ፡፡ ከሌሎች የሙያና የህይወት ልምድን መጋራት ብሎም ካነበቡት አዲስ ሀሳብ ጋር ደብልቀው መተግበራቸውን በራሳቸው አንደበት ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል አብሮ ተዋቅሮ የነበረው የደቡብ ክልል ህዝብ ስነ ልቦናው፤ ያለበት የአየር ንብረት፤ የባህል መዳበር፤ ነገሮችን የመረዳት አውዱን በመተንተን እና ሰነድ አቅርበው በመሞገት፤ የደህዴን ልሳን የሆነው ጋዜጣን ለብቻው እንዲቋቋም አስችለዋል፡፡ ሙያ ነክ ማለትም የትምህርት፤ የግብርና፤ የጤና መጽሔቶችን እያዘጋጁ ለህዝብ እንዲዳረስ አድርገዋል፡፡ የምክርቤት ስብሰባዎችን፤ መግለጫዎችን እየተከታተሉ  አያሌ ዜናዎችን አምርተዋል፡፡

     

           የፓርላማው እንቅልፍ

 

ወቅቱ 1995 . ነበር በም/ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ የቴሌቪዥን ስክሪን የተገጠመ ሰሞን ነበርና በመደበኛ ስብሰባ ወቅት በርከት ያሉ አባላት እየተኙ እንደሆነ ካሜራው ማጋለጥ ጀመረ በዚህ ጊዜ አንድ ጋዜጣ እንቅልፋሙ ፖርላማ ብሎ ዘርዘር አድርጎ ያትማል ከዚያም ሸገር FM በዝርዝር ያቀርበዋል፣በዚህ ጊዜ አንዳንድ አባላት የም/ቤቱ ክብር እንደተነካ አድርገው ሚዲያዎቹ እንዲጠየቁ ሐሳብ ሲያቀርቡ፣መጠየቅ  ያለባቸው የህዝብን ኃላፊነት ዘንግተው የተኙ አባላት እንጂ ሚዲያ ሥራውን ነው የሠራው በማለትጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ በማድረግ ሚዲያን መከላከላቸውን ይጠቅሳሉ።በፓርላማ ቆይታቸውም አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ በሚዲያዎች ላይ መወሰድ እንደሌለበት" በጽኑ አቋም በልባዊነት በተለያዩ መድረኮች ሞግተዋል፡፡

"በዎላይታ ብሔር ታሪክ" ላይ ያተኮረ ሁለተኛ መጽሐፋቸውን ደግሞ በቅርቡ ለንባብ አብቅተዋል የትናንትናው ጋዜጠኛ የዛሬው ዲፕሎማት፣ በአሁኑ ወቅትም በውጭ አገር የኢትዮጵያ ሲኒየር ዲፕሎማት በመሆን አገራቸውንና ህዝባቸውን ማገልገላቸውን ቀጥለዋል፡፡

1987 . እስከ 1994 . መጨረሻ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሪፖርተር፤ ፕሮግራሞችን በመቅረጽና እስከ ኤዲተር ሆነው ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ 1995 . እስከ 2004 . ከፓርላማ ተመራጭነት እስከ ቋሚ ኮሚቴ አባልና አማካሪ ኮሚቴ ብሎም 10 አመት የፓርቲ ልሳን በምክትል እና ዋና አዘጋጅ በመሆን፤ 2005 . እስከ 2008 . የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ደኤታ፤ 2008 . መጨረሻ እስከ 20011. ድረስ በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ደኤታ፤ ከግንቦት 20011. ጀምሮ ደግሞ ሲኒየር ዲፕሎማት በመሆን ሀገራቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ወደ ፊትም ሶስተኛ መጽሐፋቸውን ለማበርከት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አብስረዋል፡፡

 

 

         አብረው የሰሩት ምስክርነት

 

ከጋዜጠኝነት እስከ ፖለቲካ አመራር ድረስ የዘለቁት የዛሬው ዲፕሎማት አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ ፡ከቀድሞው ጋዜጤኛ፤ ከአሁኑ ዲፕሎማት ጋር የምንተዋወቀው 1989 .. ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃን ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የጋዜጠኝኘት ዲፕሎማን ለማግኘት ስንማር ነው፡፡ በዲፓርትመንትም የህትመት ተማሪነታችንም እንቀራረብ ነበር፡፡ 1990 .. ደግሞ ልንመረቅ አንድ ሴሚስተር ሲቀረን ጀምሮ፣ ‹‹ትጋተህ እና የሚዲያ ተሳትፎህ ጥሩ ስለሆነ ዋልታ እንድትቀጠር አደርግሃለሁ›› ቢለኝም በወቅቱ የድርጅት እና የግል ሚዲያ ላይ የመሥራት ፍላጎት ስላልነበረኝ ከተመረቅሁ በኋላ ‹‹አሻፈረኝ›› ባይነት የተወሰኑ ወራት ያለሥራ ቆየሁ፡፡ ሥራ ማጣት ሲያማርረኝ ግን አቋሜን መቀየሬን ነግሬው ዋልታ ያስቀጠረኝ እርሱ ነው፡፡

በዋልታ የአራት ዓመት ተኩል ቆይታዬ ለሙያው አዲስ ባልሆንም እስክለምድ የቅርብ እገዛው አልተለየኝም ነበር፡፡ በወቅቱ ዋልታ ውስጥ ቅንነት እና ግልጽነት የነበረ ሲሆን እርሱም እንዲያ ነበር፡፡ በዘጋቢነት መረጃ ሰብስቦ ሲዘግብም፣ ሪፖርተሮችን በዴስክ እያስተባበረ ሲያርምም ሆነ ከማኔጅመንቱ ጋር ሆኖ ሲሠራ በእርጋታ ከማስረዳት እና ከማሳመን አቅሙ ጋር ተዳምሮ ድፍረቱ እና ትህትናው በራስ የመተማመን ብቃቱን ያሳየበት ነው፡፡    እስክንድር መርሀ-ጽድቅ / የቀድሞ የዋልታ ባልደረባ/

….

መሠለ አዳነ እባላለሁ፡፡ በሙያዬ ጋዜጠኛ ስሆን፣ የሶራ ማስታወቂያና ህትመት ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ነኝ።

አማኑኤል አብርሃምን  የማውቀው 1989 . ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል  ነው።የሥራ ባልደረቦች ነበርን።

አማኑኤል 1989 .  የበጀት ዓመት የዋልታ ኢንፎርሜሽን የሀዋሳ  ቅርንጫፍ ሪፖርተር እያለ ተሸላሚ እንደነበር አስታውሳለሁ።

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ደግሞ የተለያዩ የምርመራ ዘገባ ዜናዎችን ይሠራ ነበር። በተለይም በወቅቱ ግብርና ሚኒስቴር የነበረ ብልሹ አሠራርን በማጋለጥ ረገድ አንድ ወቅት መነጋገሪያ የሆነ ዜና መሥራቱን አስታውሳለሁ፡፡ እሱ የገለጠው ዜና ምእንያት በወቅቱ የነበሩት ሚኒስትር ወዲያውኑ ከኃላፊነት መነሳታቸውን አስታውሳለሁ።በ1993 . የፓርላማ አባል እስከሆነበት ጊዜ ድረስ አያሌ ብልሹ አሠራርን የሚያጋልጡ ዜናዎችን በመሥራት በወቅቱ አይነኬ የሚመስሉ ዘገባዎችን በመሥራት አማኑኤል ይታወቃል፡፡ 

                    


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች