ጥሩወርቅ ተካ 

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በየዘመኑ ድንቅ አሻራ ያኖሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ ለትውልድ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቀደም በሀምሌ 30 2014አ.ም የ180 የሚድያ ሰዎችን የሥራ እና የህይወት ታሪክ መዝገበ-አእምሮ በሚል 600 ገጽ በፈጀ ፤ በጠንካራ ሽፋን በተዘጋጀ መጽሀፍ አዘጋጅቶ ማሳተሙ እና ማስመረቁ ይታወሳል፡፡ በቀጣይ በቅጽ 2 ታሪካቸው በወጉ ከሚሰነድላቸው የሚድያ ሰዎች አንዷ ጥሩወርቅ ተካ ነች፡፡ ጥሩወርቅ በአፋን ኦሮሞ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በተለይ ባለፉት 21 አመታት ጉልህ አሻራ ካኖሩት ውስጥ በቀዳሚነት ስሟ ይነሳል፡፡ በፋና ሬድዮ ፤ በኦቢኤን እንዲሁም በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ ከምርመራ  ጋዜጠኝነት አንስቶ እስከ ዜና ድረስ ሙያዊ ብቃቷን ያስመሰከረች ናት፡፡ በመምህርነት ሙያ ለ18 አመታት የዘለቀችው ጥሩወርቅ ከአዘጋጅነት እስከ ስራ አስፈጻሚነት በዘለቀችበት የሚድያ ስራ ላይ ዛሬም በታላቅ ርካታ ውስጥ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ እዝራ እጅጉ የጥሩ ወርቅን ታሪክ እንደሚከተለው አጠናክሮታል፡፡   


ውልደት፤ እና ልጅነት

ጥሩወርቅ ተካ ፍሪሳ /አባ ሳንቢ/ መስከረም 5 1954 ዓ.ም  መስከረም 5 ተወለደች፡፡ አያቷ ፍሪሳ / አባ ሳንቢ አባዋሪ በሁለተኛው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ጊዜ አርበኛ ነበሩ፡፡  እርሳቸውም መጀመርያ ጂማ ዞን ጎማ ወረዳ ገንጂ ዳለቾ ቀበሌ ልዩ ስሙ መሰራ ተብሎ ከሚጠራው ቀያቸው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያም የዋንዛ ዋርካ ላይ የአገራቸውን ባንዲራ ሰቅለው ጣሊያንን ሲፋለሙ ነበር፡፡ አርበኛው ፍሪሳ ወይም ፊታውራሪ አባ ሳንቢ አባዋሪ በትውልድ ቦታቸው በሻሻ ቀዳማዬ እሚባለው አካባቢ ልዩ ስሙ መልካ ሰሪቲ/ ተበ ሰሪቲ/ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በባንዳዎች ሴራ በጣሊያን ተረሽነው ሳይቀበሩ የትም ቀሩ፡፡ የመምህርትና ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ  ወላጅ አባት  በጅሮንድ . ግራዝማች ተካ የአርበኛው ፍሪሳ ወይም የፊታውራሪ አባሳንቢ አባዋሪ ልጅ ናቸው፡፡

  እናቷ ደግሞ ወይዘሮ ጌጤ ዘረፋ ይባላሉ፡፡ አባ ዘረፋም  ሰሜን ሸዋ አሁን ደነባ ተብላ ከምትጠራው ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ኤጀርሳ ገንደጋራ ቀበሌ የማሪያም ቤተክርስቲያን መስራችና አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ ጥሩ ወርቅ ተካም ከግራዝማች ተካ  እና  ከ/ ጌጤ ዘረፋ የበኩር(ለሁለቱም) ልጅ ሆና ተወለደች። ህፃን ጥሩወርቅ ተካ ሁለቱ ወላጆቿ ባላቸው የሀይማኖት ልዩነት የተነሳ ጋብቻቸው በፍቅር ላይ ብቻ የተመሰረተ እንጂ የቤተሰብን ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ ትዳሩ ሲፈርስ እስከ  አምስት አመቷ ድረስ ብቻ ከእናቷ ጋር ቆይታ በአምስት አመቷ የከፋ /ግዛት /በጅሮንድ ሆነው የወቅቱን መንግስትና አገር እያገለገሉ ወደ ነበሩት አባቷ በጅሮንድ ተካ አባሳንቢ ዘንድ ጅማ ከተማ ተወሰደች።

 

 

 

             ጥሩወርቅ ተካ 

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በየዘመኑ ድንቅ አሻራ ያኖሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ ለትውልድ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቀደም በሀምሌ 30 2014አ.ም የ180 የሚድያ ሰዎችን የሥራ እና የህይወት ታሪክ መዝገበ-አዕምሮ በሚል 600 ገጽ በፈጀ ፤ በጠንካራ ሽፋን በተዘጋጀ መጽሀፍ አዘጋጅቶ ማሳተሙ እና ማስመረቁ ይታወሳል፡፡ በቀጣይ በቅጽ 2 ታሪካቸው በወጉ ከሚሰነድላቸው የሚድያ ሰዎች አንዷ ጥሩወርቅ ተካ ነች፡፡ ጥሩወርቅ በአፋን ኦሮሞ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በተለይ ባለፉት 21 አመታት ጉልህ አሻራ ካኖሩት ውስጥ በቀዳሚነት ስሟ ይነሳል፡፡ በፋና ሬድዮ ፤ በኦቢኤን እንዲሁም በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ ከምርመራ  ጋዜጠኝነት አንስቶ እስከ ዜና ድረስ ሙያዊ ብቃቷን ያስመሰከረች ናት፡፡ በመምህርነት ሙያ ለ18 አመታት የዘለቀችው ጥሩወርቅ ከአዘጋጅነት እስከ ስራ አስፈጻሚነት በዘለቀችበት የሚድያ ስራ ላይ ዛሬም በታላቅ ርካታ ውስጥ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ እዝራ እጅጉ የጥሩ ወርቅን ታሪክ እንደሚከተለው አጠናክሮታል፡፡      

 

         

                   ውልደት፤ እና ልጅነት

ጥሩወርቅ ተካ ፍሪሳ /አባ ሳንቢ/ መስከረም 5 1954 ዓ.ም  መስከረም 5 ተወለደች፡፡ አያቷ ፍሪሳ / አባ ሳንቢ አባዋሪ በሁለተኛው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ጊዜ አርበኛ ነበሩ፡፡  እርሳቸውም መጀመርያ ጂማ ዞን ጎማ ወረዳ ገንጂ ዳለቾ ቀበሌ ልዩ ስሙ መሰራ ተብሎ ከሚጠራው ቀያቸው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያም የዋንዛ ዋርካ ላይ የአገራቸውን ባንዲራ ሰቅለው ጣሊያንን ሲፋለሙ ነበር፡፡ አርበኛው ፍሪሳ ወይም ፊታውራሪ አባ ሳንቢ አባዋሪ በትውልድ ቦታቸው በሻሻ ቀዳማዬ እሚባለው አካባቢ ልዩ ስሙ መልካ ሰሪቲ/ ተበ ሰሪቲ/ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በባንዳዎች ሴራ በጣሊያን ተረሽነው ሳይቀበሩ የትም ቀሩ፡፡ የመምህርትና ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ  ወላጅ አባት  በጅሮንድ . ግራዝማች ተካ የአርበኛው ፍሪሳ ወይም የፊታውራሪ አባሳንቢ አባዋሪ ልጅ ናቸው፡፡

  እናቷ ደግሞ ወይዘሮ ጌጤ ዘረፋ ይባላሉ፡፡ አባ ዘረፋም  ሰሜን ሸዋ አሁን ደነባ ተብላ ከምትጠራው ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ኤጀርሳ ገንደጋራ ቀበሌ የማሪያም ቤተክርስቲያን መስራችና አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ ጥሩ ወርቅ ተካም ከግራዝማች ተካ  እና  ከ/ ጌጤ ዘረፋ የበኩር(ለሁለቱም) ልጅ ሆና ተወለደች። ህፃን ጥሩወርቅ ተካ ሁለቱ ወላጆቿ ባላቸው የሀይማኖት ልዩነት የተነሳ ጋብቻቸው በፍቅር ላይ ብቻ የተመሰረተ እንጂ የቤተሰብን ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ ትዳሩ ሲፈርስ እስከ  አምስት አመቷ ድረስ ብቻ ከእናቷ ጋር ቆይታ በአምስት አመቷ የከፋ /ግዛት /በጅሮንድ ሆነው የወቅቱን መንግስትና አገር እያገለገሉ ወደ ነበሩት አባቷ በጅሮንድ ተካ አባሳንቢ ዘንድ ጅማ ከተማ ተወሰደች።

 

                ታዳጊዋ ጥሩወርቅ

ወዲያውኑ በወላጅ አባቷ መኖሪያ አካባቢ ከሚገኘው በድሮ ስሙ ሚያዝያ 27 ከሚባል 1 ደረጃ /ቤት  1 ክፍል ገባች፡፡ ህፃን ጥሩወርቅ ተካ 5 ዓመት ዕድሜዋ ፊደል መቁጠርም ሆነ ማንበብና መፃፍ የምትችል የእንግሊዝኛ ፊደላትን ጠንቅቃ የምታውቅ ነበረች።

በሚያዝያ 27 1 ደረጃ /ቤት ተመዝግባ ወደ ክፍል ስትገባ ነይ ብላ አጠገቧ ያስቀመጠቻትና 6 ዓመታት ጓደኛዋ ሆና የዘለቀቸው ትንሿ በእናትዋ ኢትዮጵያዊ በአባቷ ጣሊያናዊ የሆነችው ህፃን ጁሰፒና ፓጋኖን መቼም አትረሳትም፡፡ ጥሩወርቅ እና ጁሰፒና ሌላም ሽታዬ ያደቴ የምትባል 3 ጓደኛም ነበራቸው፡፡  የሶስቱ አብሮነት እስከ 6 ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ዘለቀና ከሶስቱ ጥሩወርቅ ሚኒስትሪ አልፋ ወደ 7 ክፍል በመግባቷ የሶስቱ ታዳጊዎች ጓደኝነት ከጥሩ ወርቅ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠና ጥሩወርቅ ተካ ወደ ጅማ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት (ኮተቤ) ተመድባ ቀጠለች።

ጥሩወርቅ ተካ 1-6 ክፍል ተማሪ በነበረችበት ግብረገብ አማርኛ፣ፅሁፍ ፣ቅኔ፣ሰዋሰው፣ ክርክር፣እርሻ፣ሙዚቃ፣እጅሥራ፣ባልትና የሚባሉት ትምህርቶችን ለመማር ከታደሉ የዚያን ዘመን ተማሪዎች አንዷ ነች፡፡ እነዚህ 1 ደረጃ የተማረቻቸው ትምህርቶች ናቸው አሁን ላለችበት የጋዜጠኝነት ሙያ (የመፃፍ፣የመናገር) ለያዘችው የእጅ ሥራ ዕውቀት፣የግብርና ፍቅርና ሰዎችን አክብራና ሁሌም ለዕውነት ተሟጋች ሆና እንድትቀጥል ያስቻላት ብላ ታምናለች።

7 ክፍልን በጅማ መለስተኛ 2 ደረጃ(ኮተቤ) 8ኛ፣9ኛ፣10ኛን ደግሞ ወላጅ አባቷ በደርግ ሥርዐተ መንግሥት ከጅማ ክፍለሀገር ምክትል በጅሮንድነት ወደ ኢሉ አባቦራ /ሀገር ዋና በጅሮንድነት ከፍ ብለው በመመደባቸው (በመዛወራቸው) መቱ ከተማ 01 ቀበሌ ጤና ጣቢያው አካባቢ በሚገኘው 2 ደረጃ /ቤት ተከታተለችና 11 እና 12 ክፍል ትምህርቷን ደግሞ በልጅነት ዕድሜዋ ሳታስበው በገባችበት የትዳር ህይወት ምክንያት የመኖሪያ አካባቢዋ ወደ ከፋ ዞን ቦንጋ በማምራቱ 11ኛና 12 ክፍል ትምህርቷን ቦንጋ ከተማ በሚገኘው ሸታ 2 ደረጃ /ቤት 2 ልጆቿ አባት ከሆነው ባለቤቷ ወላጆች ዘንድ ሆና አጠናቀቀች።

 

                 መምህርት ጥሩወርቅ    

ተመላልሶ መማርና የልጅ እናት መሆን የነበረው አቅሟን ቀነሰው፡፡  በዚህ ምክንያት የጠበቀችውን የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ዕድል ባታገኝም በወቅቱ ጂማ በሚገኘው የመምህራን ማሰልጠኛ ስልጠናውን ተከታትላ 1 ደረጃ መምህርነት ትምህርቷን አጠናቀቀች፡፡  1975 ሀምሌ 1 ወደመምህርነት ሙያ ዘለቀች፡፡ በከፋ አውራጃ ዴቻ ወረዳ (የእድገት በህብረት ዘማቾች በእሳት የተቃጠሉበት አካባቢ) በሀ ጊዮርጊስ አካባቢ (ከቦንጋ ከተማ 3ሰዓት የእግር መንገድ) በሀ 1 ደረጃ /ቤት መምህርት ሆና  አማርኛ፣እንግሊዝኛ፣ህብረተሰብ ሣይንስ፣ሙዚቃና ስፖርትን ጨምሮ እጅ ሥራን በማስተማር የጀመረችውን ሥራ ለ1 ዓመት ያህል ቀጠለችበት።

በመቀጠል 1 ዓመት በኋላ ባለቤቷ ወደሚያስተምርበት ሻፓ አንደኛ ደረጃ (ለቦንጋ ከተማ 1 ሰዓት ርቀት ላይ የሚገኝ) ተዛውራ የአርሶአደር ልጆችን የማስተማር ሥራዋን 1 ዓመት ቀጠለች።በኋላም በዘመኑ ‘’ሙከራ’’ ተብሎ በተቀረፀው ስርዓተ- ትምህርት በከፋ አውራጃ /ቤቶች /ቤት ተመርጣ ከሌሎች የተመረጡ መምህራን ጋር ለማስተማር ለሥራው ዝግጅት ታስቦ የተሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ወደ ምስራቅ ሸዋ ቢሾፍቱ ከተማ ተጉዛ ጨርሳ ስትመለስ የአውራጃው ዋና ከተማ ቦንጋ በሚገኘው አንጋፋው የበዕደማርያም 1 ደረጃ /ቤት ተዛውራ 4 ተከታታይ አመታት 1 - 4 ክፍል ያሉትን ተማሪዎች ኮትኩታ ቀርፃለች።

ከዚያ ቀጥሎ 1981 . የሥራ ዝውውር በመጠየቅ ከባለቤቷ መምህር ታምሩ ሰቦቃ ጋር ወደ ጂማ ከተማ  ተዛወረች፡፡ ከጂማ ወጣ ብሎ . መንገድ ወደሚያስኬደውና በአንበሳ አውቶቢስ ተሳፍሮ ቀጥሎም 40 ደቂቃ በእግር ወደሚያስኬደው ‘’በላዋጃ’’ ወደተባለው አዲስ /ቤት ባለቤቷ በር/መምህርነት ጥሩወርቅ በመምህርነት ተመድበው 1 ዓመት አገለገሉ፡፡በኋላ ጥሩወርቅ ተካ  የኩላሊት ህመም ስለነበረባት  ወደ አጋሮ ከተማ በሚያመራው መንገድ ላይ ወደሚገኘው ‘’ቡጡሬ 1 ደረጃ’’ /ቤት በሀኪም ትዕዛዝ ትዛወርና ሥራዋን ቀጠለች፡፡ 1984 .  ጅማ ከተማ ወደሚገኘው ‘’ኪቶ 1 ደረጃ’’ ተዛውራ የተለመደውን 1 ደረጃ መምህርነቷን እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ በመምህርነት፣በዲፓርትመንት ኃላፊነት፣በዩኒት ሊደርነት /ቤቷን አገልግላለች።

ከፍተኛ የእውቀት ጥማት ያለባት መምህርት ጥሩወርቅ ተካ የቤተሰብ ኃላፊነቷ ፍላጎቷን እንድታሳካ ያላስቻላት ቢሆንም መማር እንዳለባት ግን ታምን ነበር፡፡  1989 በጂማ ከሚገኘው መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም  ለባዮሎጂና ኬሚስትሪ መምህርነትን የሚያበቃትን ትምህርት ለሶስት ዓመት ያህል ተምራ ሜጀሯን ባዮሎጂ ማይነሯን ኬሚስሪ አድርጋ በዲፕሎማ ተመረቀች።

ከኪቶ 1 ደረጃ ትምህርት ቤት እዚያው ጂማ ከተማ ማሪያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ወደሚገኘው ሀምሌ 19 መለስተኛ /ቤት በመዛወር 7 እና 8 ክፍል ክፍል ተማሪዎችን ሁለቱንም የትምህርት ዓይነት በማስተማር ላይ ሳለች  በህይወቷ ውስጥ ሌላ ምዕራፍ ተፈጠረ።

በዚህ ጊዜ በታዳጊነት ዕድሜዋ ያፈራቻቸው ልጆቿ ስምረት ታምሩና አፈወርቅ ታምሩም 1 ደረጃ ወደ 2 ደረጃ ምህርት ተሸጋግረው ነበር።

 

 

 

               ፋና ሬድዮ  በ1993 ቀጠራት

 ጥሩወርቅ፣ ለሥልጠና ወደ አዳማ፣ቢሾፍቱ፣አዲስ አበባ፣ወሊሶ ከሚመላለሱት መምህራን መካከል አንዷ ነበረች፡፡ መምህርት ጥሩወርቅ ተካ በአንዱ የሥልጠና ጉዞዋ ውስጥ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱን ትሰማና ልቧ ይነሳሳል።የዚህ መነሳሳት ምክንያት ደግሞ ጂማ ከተማ ውስጥ በዙርያዋ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ‘’አንቺኮ የቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ነው መሆን ያለብሽ’’ ይሏት የነበረው መልዕክት ነው።

በቀጣዩ የስልጠና ጥሪዋ የትምህርት መረጃዎቿን ሰብስባ በመሄድ በጣቢያው (ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን) ባሉትና በግል ለምታውቃቸው ሰዎች መረጃዋን እንዲያስመዘግቧት ትሰጥና ወደ ስልጠናው ታመራለች፡፡ በአካል ባለመገኘቷ ምዝገባው አልተሳካም። ስትመለስ ትቀበላቸውና ስሙን በወሬ ብቻ ወደምታውቀው ሬድዮ ፋና ታቀናለች።

ሬድዮ ፋና ያኔ እርሷ በሄደችበት ጊዜ ሳይሆን ለቀጣይ እንደሚቀጥሩና ማስታወቂያ እስኪወጣ እንድትጠባበቅ ነግረዋት የመረጃዋን ፎቶ ኮፒ ራሳቸው እዚያው አዘጋጅተው ይወስዱና ያሰናብቷታል። ስልጠናዋን አገባዳ በሳምንቱ ወደ ጂማ የተመለሰቸው መምህርት ጥሩወርቅ ተካ በተመለሰች በሳምንቱ ሬድዮ ፋና ደውሎ ለፈተና ይጠራታል። አላንገራገረችም፡፡ መጥታ 3:30 የሚሆን ሰዓት የተመደበላትን ፈተና ተፈትና ተመለሰች። በተፈተነች በሳምንቱ ወሊሶ ተመሳሳይ ስልጠና ላይ እያለች ትጠራና ስትሄድ የጠበቃትን ለማመን አልቻለችም፡፡ የቅጥር ደብዳቤ ተሰጣት። ደነገጠች፡፡ ምክንያቱም የትምህርት ጥማት ያለባት እርሷ በዚያን ሰዓት (ግንቦት አካባቢ 1993) በባዮሎጂ እና ኬሚስትሪ የዲግሪ ትምህርት ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል የሚያስችላትን ውድድር አልፋ በዝግጅት ላይ ነበረች። 2ኛው ምክንያቷ ደግሞ ተለይታቸው የማታውቃቸውን ሁለት ልጆቿንና ቤቷን ተለይታ ልትርቅ መሆኑ ነው።

ቢሆንም የምትፈልገው ዕድል በመሆኑ አላለፈችውም፡፡ 1993 . መጨረሻ(ግንቦት አካባቢ) በሬድዮ ፋና አፋን ኦሮሞ ክፍል የትምህርታዊ ፕሮግራም አዘጋጅ ሆና በመቀጠር የሚድያውን ዓለም ያለምንም ስልጠና በቀጥታ ተቀላቀለች። ከባዮሎጂ መምህርነት ወደ ጋዜጠኝነት። ቀጠለች። 

 ጥሩ ወርቅና የመገናኛ ብዙሀን ትምህርት

 ጥሩ ወርቅ ተካ በ1993 መጨረሻ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ  ሬድዮ ፋናን በተቀላቀለችበት ጊዜ  ክረምቱን በሀረማያ  ዩኒቨርሲቲ  በባዮሎጂና ኬሚስትሪ መምህርነት የዲግሪ ትምህርቷን ስትጀምር በሙያ ለውጥ ምክንያት   እድሉ የከሸፈ ቢመስላትም  ጋዜጠኝነት የመማር ህልሟ ግን እውን ሆኖ ነበር፡፡ ጋዜጠኝነትን በዲግሪ መርሀ-ግብር ተምራ በሬድዮ ጋዜጠኝነት ትምህርቷን አጠናቀቀች፡፡ፋና ሬድዮ እያለች የጀመረችውን  የጋዜጠኝነት የማታ ትምህርት  ኦሮሚያ ማስታወቂያ እና ህዝብ ግንኙነት ከተቀላቀለች በኋላ በ2000 አጠናቅቃ  ሙያዋን በእውቀት አደመቀችው፡፡  




 

         የምታመሰግናቸው-መልካሞች   

 

የአሁኗ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ምንም እንኳን አርበኛው አያቷን ሜዳ ላይ ረሽኖ ያለመቃብር ያስቀረውን ጣሊያን አሁንም ድረስ በጣም ብትጠላውም 1-6 ክፍል የልብ ጓደኛዋ በመሆን አብራት የነበረችውን የልብ ጓደኛዋ ጁሰፒና ፓጋኖን ከልቧ አስቀምጣለች። በተጨማሪም ከ1976 ጀምሮ ፤ በሙከራ ትምህርት የመምህርነት አጫጭር ሴሚናሮች ስትወስድ የተዋወቀቻት እና የልብ ጓደኛ እስከአሁንም በችግሯና በደስታዋ ሁሉ እንደጥላዋ አብራት የምትቆም መምህርት ጥሩወርቅ መኩርያ አየለ በተለየ ሁኔታ ማመስገን ትሻለች፡፡  የግብረገብ አስተማሪዋ አባ አምደብርሃን፣ የባልትና መምህሯ መምህርት ለተብርሃን (ታታ) T.T.I የኬሚስትሪ አስተማሪዋ የነበረው መምህር ታመነ፣ ፀሀይ በዙርያዋ ያሉትን ሁሉ (SOLAR SYSTEM) ይዛ እንደምትዞር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲናገር የሰማችው የጂኦግራፊ መምህሯ መምህር ዓሊ አህመድ፣ T.T.C የማታ ተማሪ የነበረች ጊዜ ሲያስተምራት የነበረው የባዮሎጂ መምህሯ (ጊዜውን ሁሉ ቆሞ ሲያስተምር የላቡ ብዛት ሸሚዙን የሚያርሰው እና ጥሩ ሞዴሏ እንደነበረ ሁሌም የምትመሰክርለት እና  አሁን በህይወት የሌለው) መምህር ዓለሙ ፈጠነን በዕደማሪያም /ቤት/ቦንጋ ንብረት ክፍል የነበረውና በረጅም ዓመት ኦዲቲንግ ውስጥ 15ሣንቲም ብቻ የጎደለበት አለሙ አድነው በጣም ከምታስታውሳቸውና በትጋታቸው፣በታታሪነታቸው እና በታማኝነታቸው እንደ አርአያ ፈለጋቸውን ከምትከተላቸው ሰዎች ውስጥ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ በጋዜጠኝነት ሙያዋ ውስጥ ሥራውን ስትጀምር የድምፅ መቅረጫ መሳሪያ አጠቃቀም፣የስክሪፕት አፃፃፍ፣ ኢንተርቪው እንዴት እንደሚደረግና ተያያዥ ሥራዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳያት ግርማ ሙሉጌታ(ጋዜጠኛ) በጣም ታመሰግነዋለች፡፡

ከአንድ ጊዜ እይታ በኋላ በቀጣይ ራሷን ችላ ወደ መስክ የተላከችው ለመጀመሪያ ጊዜ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሰለጠኑትን የዲፕሎማ ደረጃ ሰልጣኝ መምህራንን የአዳማ ከተማው T.T.C ሲያስመርቅ ነበር።

      የመጀመሪያ የመስክ ስራ

      የመጀመሪያ ኢንተርቪው

      የመጀመሪያ ዜና /በቀጥታ ስርጭት/

      የመጀመሪያ ትምህርታዊ ፕሮግራም

በተቀጠረች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በዚህ የመስክ ተልዕኮ የሰራችው ስራ ነበር።

በጣም ያስፈራ ነበር። ድምፁ ቢጠፋስ? ትክክል ባይሆንስ ... ሌላም ሌላም ስጋት ነበር፡፡ ግን ሁሉም ሥራ በጣም የተጨበጨበለት ምስጋና ያስቸራት ሥራ ሆኖ ተገኘ። በቀጣይ የጠዋት ብሪፍ ላይ በጣም ጥሩ ብሎ በወቅቱ የክፍሉ አለቃ የነበረው አቶ መስፍን ደረጀ የገለፀበትን የአድናቆት ቃል አትዘነጋም። ጎበዝ በዚሁ ቀጥይ ተባለች። ሞቅ አላት ሞራሏ ከፍ አለ፡፡ ከዚህ በላይ መሥራት አለብኝ ብላ ወሰነች፡፡ ቀጠለች ተሳካ።

 ‘’ቢፍቱ’’ የሚባል ምህርት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም፣ ሁበኖ የተባለ የሴቶች ፕሮግራም፣ HIV/Aids ኦሮሚያን እንቃኝ /ለተወሰነ ጊዜ/ ህዝቡ ምን ይላልና፣ እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? የሚሉ ፕሮግራሞችን በተሳካ ሁኔታ ለረጅም አመታት በአዘጋጅነትና በከፍተኛ አዘጋጅነት የሥራ ደረጃ ለአድማጮች እያዘጋጀች በየሳምንቱ 6 ፕሮግራሞችን ስታቀርብ ነበር፡፡ በየስድስት ወሩ በፋና የሚሰጠውን የሥራ ብልጫ ተሸላሚነት በነበራት የመጀመሪያ 5 አመት ቆይታ ያለምንም መቆራረጥ ከአንድ እርከን እስከ ሶስት እርከን የደረሱ የደሞዝ ጭማሪ እየተደረገላት ስትሰራ የነበረች ጋዜጠኛ ሆናም በትጋት አገልግላለች።

በዚህን ጊዜ ከፕሮግራም አዘጋጅነት በተጨማሪ የዜና አዘጋጅ ተርጓሚና የዜና መሪ (አንከር) በመሆን አገልግላለች። በዚህ ቆይታ ውስጥ የተሳካ የሥራ ባለቤት እንድትሆን ሲያግዟትና ሲደግፏት የነበሩ አለቃዋ መስፍን ደረጀን፣ ኤዲተሯ(አሁን በህይወት የሌለውና በጣም የምታከብረው) ኢብራሂም ሀጂ ዓሊ፣ ኢድራስ ጉደቶ፤ /ዋና ሥራ አስፈፃሚ /ፋና ሬድዮ/ የነበሩ አሁን የተከበሩ አቶ ተተካ በቀለና በጠንካራ መሪነቱ የምታደንቀው የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወልዱ ይመሰልን ጨምሮ ለመጀመርያ ጊዜ  በቀጥታ ሥርጭት የምሳ ሰዓት ዜናን አንከር ሆና ስታቀርብ ድምጿን በካሴት ቀርፆ ከስቱዲዮ ጨርሳ ስትወጣ ‘’አዳምጪ ጎበዝ’’ ብሎ የሰጣትን የአሁኑን የውጭ ጉዳይ / ቃል-አቀባይ እና የዛን ጊዜውን የሬድዮ ፋና ዜና ክፍል ኃላፊ  አቶ መለስ አለምን በፍፁም አትረሳም ታመሰግናቸዋለች።

 

 

       መርማሪዋ ጥሩወርቅ

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ የምርመራ ጋዜጠኝነትሰራ የነበረው (ህዝቡ ምን ይላል በተሰኘው ፕሮግራም አማካይነት ነበር፡፡ world Bank በዘርፉ የሰጠውን ሥልጠና ከተከታተለች በኋላ የበለጠ ለምርመራ ጋዜጠኝነት ተሳበች፡፡

በተፈጥሮዋ ለምን? እንዴት? እያለች መጠየቅ የምታዘወትረው ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ይህንን የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥልጠናና የህዝቡ ምን ይላል? ፕሮግራም አዘጋጅነት ዕድልን ስታገኝ በጣም መደሰቷን ትገልፃለች። ምክንያቱም ተፈጥሯዊ የጠያቂነት ባህሪዋ ከራሷ አልፎ የህዝብን ብሶት ነጋሪት ጎሳሚ እንድትሆን አስችሏታል። ድምጿን ከፍ አድርጋ በደል፣ ግፍና ብልሹ አሰራር ባለበት እየተገኘች እና እየመረመረች አቀናብራ  ለህዝብ ጆሮ ማድረሷን ተያያዘችው። በስኬትም ተወጣችው ታወቀችበት።

አንዴ ሰርታ በነበረው ፕሮግራም ችግራቸው የተፈታላቸው ግለሰቦች አባቷን አግኝተው ‘’ልጅዎ እኮ ..... ብለው ያገኙትን ፍትህ ሲንግሯቸው ቀድሞ ለህይወቷ በመሳሳትተይ ጥሩ !’’ ይሏት የነበሩ አባቷ ጠርተውተይ ብዬሽ ነበር አይደል? በይ መሞትሽ አይቀርምና ህዝብን እያገለገልሽ ብትሞቺም ምንም አይደለም በርቺ ቀጥይ !” ብለው ልቧን ያሞቋታል። ይህኛው የአባቷ መልዕክት ደግሞ የበለጠ አቅሟን እንዳሳደገላት ትናገራለች።በህዝቡ ምን ይላል?ዝግጅት የተነሳ የሚያከብሯትና የሚወዷት የሚያደንቋትም ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የሚጠሏት የሚፈሯትና የሚረግሟትም በርካቶች ናቸው። በየሄደችበት እጃቸውን ዘርግተው የሚቀበሏትና መረጃዎችን የሚሰጧት የመብዛታቸውን ያህል የጎሪጥ እያዩደግሞ ምን ልታደርጊ መጣሽ?የሚሏትም ቁጥራቸው ጥቂት አይባልም።

ጥሩወርቅ በሬድዮ ፋና በጣም እየወደደችውና እንደራሷ ጉዳይ እያየችው የህዝቡ ምን ይላልዝግጅትን እየተፈራረቁ አብሯት የሚሰራው ጋዜጠኛ አበራ ደገፉም ጥሩ አጋዥዋ እንደሆነ ታነሳለች። አንድ ጊዜ በአርሲ ዞን ጮሌ ወረዳ የመንግስት ገንዘብ መመዝበሩን ያሳዩበትና(8 ሺህ ብር የሶስት ውሾች ሬሳ ከመንገድ ላይ ተነሳበት የተባለበት) ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴየጮሌ ወረዳ ጮሌ ሹሞችብሎ እነሱ ያዘጋጁትን ዜና በአማርኛ ያቀረበበት መንገድ የሙስናን አሳዛኝ እና አስደናቂ ትርዒት አጣምሮ የታየበት ገጠመኛቸው ነበር።

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ በዚህ ዝግጅት በግሏ

1    የቡራዩ መሬት ችርቻሮ ስጋትና ጥልቀት እስከ ስልቱ

2.    ደኖችን እየቸበቸቡ የሚከብሩት እንዴትና እነማን እንደሆኑ

3.    በትራንስፖርት ዘርፍ የመንጃ ፍቃድ እንደተሰራላቸው የማያውቁና ከፍተኛ የአካል ጉዳት (ፖሊዮ) ባለቤት የሆኑ የኔቢጤዎች ሁላ እነሱ ሳያውቁ የመንጃ ፈቃድ ባለቤት ሆነው የነበረበት የብልሹ አሰራር ሚስጥር እና የተጠቃሚዎች ሰንሰለት

4.    የከተማ ማስተር ፕላኖች እንዴት ተጠምዝዘው በባለሙያዎችና ባለሀብቶች ያለ አግባብ ለግል ጥቅም እንደሚውሉ

5.    ለእርዳታ የሚሰራጨው የስንዴ ምርት እየተሸጠ የሙሰኞችና ደላሎችን ኪስ እንደሚሞላ እና መረጃ የሚሰጡ ሰዎች የሚደርስባቸው ግፍና በደል

6     የአምቦ ውሃ ፋብሪካ ሠራተኞች በአመራሩ የሚደርስባቸው በደልና እንግልቶች

7     የጉጂ ወርቅና ወጣቶች ጉልበት ምዝበራ

8     የሙገር ሲሚንቶ ብናኝ የአርሶአደሮችን ምርታማነት በዜሮ የሚያጣፋበት ሁኔታና የአመራሮች ቸልተኝነት

      በሰሜን ሸዋ(ሱሉልታ) በጫንጮ የሚገኘው ቀደምት ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ የሚኖሩ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎች በዚህ ሁሉ ዘመን (የዚያን ጊዜ) ውስጥ መንገድ፣ ገበያ፣ /ቤት፣ ህክምናና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደማያገኙ ጥሩ ወርቅ በዘገባዋ አሳይታለች፡፡ በተቃራኒው በአካባቢያቸው በፈለቀ መርዛማ ውሃ እነሱ እና ከብቶቻቸውም ጭምር ከሞት እስከ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ነፍሰጡሮች እንኳን ችግር ሲያጋጥማቸው መንገድም መኪናም ባለመኖሩ ፋብሪካው ጥሬ ዕቃ በሚያመላልስበት የኬብል መስመር እንደሚጓጓዙ እና መብራት ሲጠፋ እስኪመጣ ድረስ አየር ላይ (ኬብሉ ላይ) እንደሚቆዩ  እና የተለያዩ አስደንጋጭ፣ አስገራሚና አንዳንዴም አስቂኝ የሙስናና ብልሹ አሰራር ስልቶችን እየመረመረች ስታጋልጥ ከርማለች። ይህ የኬብሉ ጉዞ ፕሮግራም ነበር በዚያን ጊዜ የነበሩ የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን ያስደነገጠና ፕሮግራሙ በተሰራጨ ማግስት በርካታ መኪኖቻቸውን አግተልትለው አካባቢውን ለመቃኘት የሄዱበትን ሁኔታ ፈጥሮ የነበረው። ቀድሞ በሬድዮ በፋና የአፋን ኦሮሞ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ የዚያኔ የህዝብ ተወካይ ሆነው የጨፌ አባል ነበሩናይህ ፕሮግራም እንዲህ ሳይሆን ሰፋ ብሎ ነበር መስራት የነበረበት እና ይደገምብለው ጣቢያው ድረስ የመጡበትን ሁኔታ መቼም አትረሳውም። በሬድዮ ፋና ከበርካቶቹ ሥራዎቿ እነዚህ ለአብነት ይጠቀሳሉ።

 

        የሰብዓዊ መብት ተሟጋች

 

የሬድዮ ፋናዋ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ከምታዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ውስጥ ሌላው ደግሞ ‹‹ሁብኖ›› የተባለ የሴቶች ፕሮግራም ነው። በርካታ የሴቶችን ያልታዩ ችግሮች እያነፈነፈች ታዘጋጅ ነበር። በዚህም የተነሳፌሚኒስትየሚባል ስም /ባትወደውም/ ይሰጧት የነበሩ ባልደረቦቿ ነበሩ ሉ።

ከእነዚህም መካከል አንድ ጊዜ መስክ በወጣችበት ሳታስበው ያጋጠማት ጉዳይ ከጋዜጠኝነት ይልቅ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ብሆን ይሻለኛል  ያስባላትን ጉዳይ አስተዋለች፡፡ ፕሮግራም አደረገችውም።

አንድ ማረሚያ ቤት ለመቃኘት አስፈቅዳ ትገባለች። ያሰበችውና ያጋጠማት የተለያዩ ነገሮች ነበሩ።

ማረሚያ ቤቱ ወንድም ሴትም ታራሚዎች አሉት። ወንዶቹ መደበኛ /ቤት አላቸው ይማራሉ፣ ላይብረሪም አላቸው፡፡ ገብተው ያነባሉ የእጅ ሥራ ሙያ ስልጠና ይሰጣቸውና የተለያየ ሙያ ባለቤት ይሆናሉ። በዚህ ሙያም ያመርታሉ፣ ጊቢው ውስጥ ገበያ አለ ያመረቱትን ይሸጣሉ ይለውጣሉ። ባገኙት ገንዘብ እዚያው ቁጭ ብለው የትም ያሉ ቤተሰቦቻቸውን በተልዕኮ ያስተዳድራሉ። የስፖርት ሜዳ አላቸው፣ ዘና ይላሉ ስፖርት ይሰራሉ ጥሩ ነገር ነው። ሴቶቹ ግን አይማሩም፣አያነቡም፣ የሙያ ሥልጠና አይሰጣቸውም አይሸጡም፣ አይለውጡም፡፡ በአንፃሩ እዛው ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ ሌላ አጥር ታጥሮ ያዘመመች ጎጆ ቤት ውስጥ አብረዋቸው ከታሰሩ ህፃናቶቻቸው ጋር  ኩርምት እና ጭብጥ ብለው ማረሚያ ቤት ውስጥ ይቀመጣሉ ፡፡ ታራሚ ሳይሆን እስረኛ ሆነው ይኖራሉ። የእውነት ታስረዋል ለምን ? ብላ የማረሚያ ቤቱን ኃላፊ ትጠይቃለች። ወንድና ሴቶች መቀላቀል የለባቸውም !የሚል መልስ ታገኛለች ለምን ሴቶቹ ለዚህ ተመረጡ ? እንዲህ የተደረጉት ለምን ወንዶቹ አልሆኑም ? ብላ ትጠይቃለች። መልስ የለም ፕሮግራም አደረገችው። የማይታመን ሳይታሰብ የተደረገ ሁሉንም የማረሚያ ቤቱን አመራሮችና ሠራተኞች ያስደነገጠ ጉዳይ ነበር። በቀጣይ ሌሎችንም ልትፈትሽ ፈለገች ግን አልተቻላትም። አልተፈቀደላትም እያዘነች ተወችው።

በዚሁ በሴቶች ፕሮግራም ሌላ የሰራችው ፕሮግራም ደግሞ የኦሮሚያን የቤተሰብ ህግ የተመለከተ ትልቅ ሥራም አለ።

የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ በፌደራሉ የቤተሰብ ህግ ውስጥ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ክልክል ነው  የሚለውን አንቀፅ አካቶ ይረቅና መጨረሻ ላይ ይህ አንቀፅ ተሰርዞ ወይም ሳያካትት ይፀድቃል። ጋዜጠኛዋ በየመድረኩ ይህንን ጉዳይ የተመለከቱ ሥራዎችን እየተከታተለች የመስራት ዕድሉን አግኝታ ነበር፡፡ እና ከፀደቀ በኋላ የተሰረዘውን አንቀፅ መዛ በማውጣት ዜና አደረገችው፡፡ በመደበኛ ፕሮግራሟ እናኢናንጊቲ ቦሬበሚለው የብዕር ስሟ ቅዳሜ ጠዋት ከሌሎች / ዝናሽ ኦላኒ፣ዳዲ ቱፋ፣ ታሪኩ ኦላናና እድሪስ ጉደቶ/ ባልደረቦቿ ጋር እየተቀያየሩ በሚያዘጋጁት መጣጥፍ ብቸኛ ተሟጋች ሆና ህጉ ለአንድ አመት ያህል ሥራ ላይ እንዳይውልና በድጋሚ ታይቶበጋብቻ ላይ ጋብቻ ክልክል ነውየሚለው አንቀፅ ተካቶበት እንደገና እንዲፀድቅ ታግላ አስፈፅማለች።

 

 

       ጥሩወርቅ….. የኦሮሚያ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት

 

እንዲህ እንዲህ እያለች የቀጠለችው ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ከሬድዮ ፋና 5 ዓመት ቆይታዋ በኋላ ማለትም ከ1993-1998 የኦሮሚያ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ የራሱን የሬድዮና ቴሌቭዥን ጣቢያ ለማቋቋም ባቀደበት እና በወሰነበት ጊዜ የራሱ ካደረጋቸው የጋዜጠኝነት ባለሙያዎች መካከል የመጀመሪያዋ ሆና በቀረበላት ጥሪ መሰረት ወደዚያው አቀናች   ቢሮው ዕቅዱን ወደተግባር ሲቀይር የመጀመርያውን የቴሌቭዥን የቀጥታ ዘገባ አዳማ ቦሌ በተገነባው የጣቢያው ህንፃ ተገኝታ የመጀመሪያውን የቀጥታ ቴሌቭዥን ሥርጭት ተገበረችው። ቀጠለችሶነ ኦሮሚያ” “ሄሎ ዶክተር” “አርዳመሪ” “ሚሉ ቆረኖ” (የምርመራ ሥራ) እና ሌሎችም እንድትሰራ እንደአስፈላጊነቱ የሚሰጣትን ሥራ እየሰራች ከኤዲተርነት እስከ የትምህርታዊ ፕሮግራሞች ክፍል አስተባባሪነትና በመጨረሻም ፊንፊኔ FM 92.3 ሥራ (በዳይሬክተርነት ስርጭት እስከማስጀመር) በደረሱ የሥራ ደረጃ ከፍ ያሉ አሻራዋን በዛሬው OBN ላይ አሳርፋለች። ስለ OBN እና ባለሙያዎቹ ሲወሳ የጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ስም ከፍ ብሎ ይነሳል።

እዚያም እያለች ከምታዘጋጃቸው ዝግጅቶች ውስጥ በተለይ ሚሉ ቆረኖ በተባለው የምርመራ ሥራዋ የኦሮሚያ የውሃ ፓምፕ ፋብሪካ አሰራርና ምርት ስርጭት፣ የገቢዎች አሰባሰብና ችግሮቹ፣ የሀሰት ማስረጃና በፍትህ ሥርዐቱ ላይ እየተፈጠረ ያለው ሚናና የተገልጋዮች ሮሮ በተጨባጭ ማስረጃ፣ የጠበቆች አሰራርና የፍትህ መጓደል የደረሰበት ጫፍ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በየሳምንቱ የሚወጣው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአቋም መግለጫም  በዛሬው OBN በዛን ጊዜው STAVO የሚቀርበው በሷው ምስል እና ድምፅ ነበር።

በሌላ ዝግጅቶቿ ደግሞ የሀር ትል ምርት እና የአርሶ አደሩ ትግበራ የሩዝ ምርት አቅማችንና የጥራት ችግር መንስኤው፣ የአዋሽ ወንዝ ከመነሻው እስከ አፋር በረሃ ጉዞውና የፈንታሌ መስኖ ግድብ የአርብቶ አደሩ ተጠቃሚነት የፈጠረበት እውነታ(ዶክመንተሪ)

በሥራ ፈጠራ ዕድል ውስጥ የሚታዩ  የሙስና ትዕይንቶችና ለሥራ ወደ ቱርክ በተጓዘችበት ጊዜ የቱርክን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ስኬት ከአገራችን ወቅታዊ እንቅስቃሴ ጋር እያነፃፀረችና እያጣመረች ያዘጋጀቻቸው ትምህርታዊ ፕሮግራሞችና በመዝናኛው ዘርፍ ደግሞ በቱርክ ለአሮጌ ከተሞች የሚሰጥ ክብርና ጠቀሜታቸው፣ ከእየሱስ ማለፍ በኋላ የማርያም መኖርያ የነበረውን ቤትና ቦታ፣(ስፓርታኪያድ) ከእየሱስ ልደት በፊት ጌቶች ባሮችን ከአራዊት ጋር እያታገሉ የሚዝናኑበትን ስታድየም፣ የዚያን ጊዜ የግንባታ ጥበባቸውን ጨምሮ የአፋን ኦሮሞ እና የቱርክ ቋንቋ በርካታ የቃላት መመሳሰልና የትርጉም ፍፁም አንድነት ያሳየችባቸው ዝግጅቶቿ አድናቆትን ያስቸሩላት ነበሩ።

 

           ዳግም ወደ ፋና -ቀጥሎ ወደ አዲስ ሚድያ ኔትወርክ

 

በእንዲህ የቀጠለችው ይህች ባለሙያ ተቋሙ የደረሰበትን አስተማማኝ ብቃት ባረጋገጠችበት ጊዜ 5 ዓመት በላይ አገልግሎቷን አበርክታ ማለትም ከ1998-2003 ዓ.ም ወደ ቀደመው የሙያ ቤቷና ለሙያው ስትል አዲስ አበባ ትታቸው ወደ አዳማ የተጓዘችባቸው ልጆቿ ጋር አዲስ አበባ ተመልሳ ሬድዮ ፋና አፋን ኦሮሞ ክፍልን በዋና አዘጋጅነትና በዳይሬክተርነት እየመራች 4 ዓመት በላይ አገልግላለች።ከ2003-2007 ማለት ነው፡፡ በኋላም በአባቷ ህልፈት ምክንያት  ቤተሰባዊ ችግርን ለመፍታት ያጋጠማት የጊዜ ችግር የምትወደውን ሙያ ትታ ችግሩን ወደ ማቃለል ፊቷን እንድትመልስ ስላስገደዳት በራሷ ጠያቂነት ሥራዋን ለቃ 4 ዓመታት ከቆየች በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ ወደምትወደው ጣቢያዋና ወደምታከበራቸው ባልደረቦቿ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተመለሰችና ማገልገል ቀጠለች። ከ2011 በኋላ ማለት ነው፡፡በዚህም ምክንያት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቴሌቭዥን ጣቢያ የአፋን ኦሮሞ ስርጭት መጀመር ውስጥም አሻራዋን ለማስቀመጥ ዕድሉን አገኘች። አንድ ዓመት ያህል ሳታገለግልም አሁን ወዳለችበት የአዲስ ሚድያ ኔትወርክ እንድትቀላቀላቸው በቀረበላት ጥሪ ምክንያት ጥሪውን ተቀብላ የተፈለገችበትን የአፋን ኦሮሞ የሬድዮ ሥርጭት ለማስጀመር የተሰጣትን ኃላፊነት ለመወጣት በመጀመርያ በአማርኛ ቋንቋ የሬድዮ ዘርፍ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሆና ውጤታማ የሆኑ ወደ ሁለት ዓመት ሊጠጉ የደረሱ ጊዜያትን  አገለገለች፡፡ ቀጥሎም በሬድዮ ዘርፍ የቋንቋዎች ሥርጭት ሥራ አስፈፃሚ በመሆን ክፍል ለማደራጀትና ከሙያተኞች ቅጥር የጀመረ ሥራዋን ተያይዛ እንደጋዜጠኛም እንደሥራ መሪም ተቋሙን በማገልገል ላይ ትገኛለች።

          የማይደክማት ጋዜጠኛ 

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ፣ በጋዜጠኝነት የሙያ ቆይታዋ የዱከም አርሶአደሮች መሬት ላይ የተሰራ ደባን፣ የሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ ሽያጭን፣ የቡራዩ ከተማ መሬት ችርቻሮ፣ የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት ምዝበራንና የገቢዎች አሰባሰብ ላይ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን በተመለከተ ስትሰራ በነበረ ጊዜ በወቅቱ ከአንድ አንድ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላትና የችግሩ ባለቤቶች በህይወቷ በቤተሰቧ እና በሥራዋ ላይ አጋጥሟት የነበረወን ከፍተኛ አደጋ አትዘነጋውም።

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ መምህርት በነበረችበት ጊዜ ከጂማ ዞን መምህራን ማህበር ለአገር አቀፍ መምህራን ማህበር በአመራርነት ከነዶ/ ታዬ /ሰማያት ጋር ሆና የማገልገል ዕድሉንም አግኝታ ነበር።

የአሁኑ የአገሪቱ // / አብይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዝብ ተወካይነት በመጡበት ወቅት ላይ የቀረፁትን በጋራ አጋሮን እናልማፕሮጀክት በሚዲያው ዘርፍ በመሳተፍ የአጋሮን ከተማና አጎራባቾቿን ዶክመንተሪ በአጭር ጊዜ በመስራት አሁን አጋሮ ላገኘችው የኢንቨስትመንት ትኩረት ፕሮጀክቱ ውስጥ የራሷን ድርሻ አበርክታለች።

1 ደረጃ ምህርቷ ጀምሮ በየደረጃው የቋንቋና የንግግር አቅሟን እያሳደገች የቀጠለችው መምህርቷ እና ጋዜጠኛዋ ጥሩወርቅ ተካ ትላልቅ መድረኮችንም የመምራት ችሎታዋ የሚደነቅ ነው። ከመራቻቸው መድረኮች ውስጥም ከጋዜጠኛ ታሪኩ ኦላና ጋር ሆና የኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ህንፃ ምርቃት በህንፃው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሲካሄድ መድረኩን ስትመራ በነበረበት ጊዜ “Baga chaanaalii Ergiisaa kessaa bilisa baatani” ስትል ቋንቋውን የሚያውቁ ዕድምተኞችና የወቅቱን የክልሉ ፕሬዝዳንት ጨምሮ በቦታው የነበሩ የፌደራልና ክልል ባለስልጣናት ሁሉ ብድግ ብለው ያጨበጨቡበትን ሙቀትና የጊዜ ርዝመት በፍፁም አትረሳውም።

እንኳንም ከተውሶ ቻናል ተላቀቃችሁ !” ነበር መልዕክቱ፡፡ አባባሉ ወይም መልእክቱ ይህን ያህል የሰውን ስሜት ይኮረኩራል ብዬ አስቤው አልነበረም ብላ ትጠቅሳለች ዕለቱ ለእርሷበጣም አስገራሚ ዕለትብላ ታነሳዋለች።

ለዚህ አባባሏ ደግሞ ምክንያቷ ስትገልፅ ቢሮው (የኦሮሚያ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ) በወቅቱ የሚያዘጋጀው ዝግጅት የሚያሰራጨው በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ዕለት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻ የሚቆይ ዜናና ፕሮግራም እያዘጋጀ DV CAM እያሰራ ይልካል። ምንም እንኳን አንድ ሳምንት በወሰደ ድካም የተሠራ ዝግጅት ቢሆንም ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሰዓቱን ከፈለገው አዘጋጅተው የሚልኩት የአንድ ሰዓት ፕሮግራም ሳይሰራጭ ይቀራል። ዕድለኛ ከሆነ ለሳምንት ቀኑና አባባሉ ይቀየርና እንደገና ተቀርፆና ተደራጅቶ ይላካል፣ ይሰራጫል ካልሆነም ጊዜው ያለፈበት መረጃ ስለሚሆን ይቀርና ሌላ ሩጫ ለቀጣይ ይቀጥላል ያናድዳል። ሁኔታው ያናድዳት ስለነበር ሳታስበው መልዕክቱ ከአንደበቷ ወጣ፡፡ ዕድምተኞችን ሁሉ አስደነቀ አስደመመ -- ብለው እንዲያጨበጭቡላት ሆነ።

ጥሩወርቅ ተካ ተማሪ በነበረችበት ወቅት በተለይ 4-6 ባለው ክፍል ሁሌም ከሰዓት አርብ የክርክር ጊዜ ይካሄዳል በተማሪዎች መሀከል አንድም ቀን ተማሪዋ ጥሩወርቅ ተካ ያለችበት ቡድን ተሸንፎ አያውቅም።

የምትፅፋቸው ግጥሞች የሚነበቡላት ክፍል ውስጥ ሳይሆን ሰልፍ ላይ ነበር፡፡ ጋዜጠኛ ከሆነች በኋላ አንድ ቀን ስለስራዋና ስኬታማነቷ ቤተሰቦቿ አንስተው ሲወያዩ ራሷ ባለችበት ታናሽ እህቷና አሁን በመንግስት የንግድ ኮርፖሬሽን ውስጥ እያገለገለች ያለቸው ብርቄ ተካ ድሮ እኮጋዜጠኛ ብሆንአጋልጠው ነበርብለሽ ግጥም ፅፈሽ ነበር ብላ ስታስታውሳት በጣም መገረሟን ትናገራለች። በውስጧ ያለና ያደገ እሷ ግን የማታውቀው  ያጋዜጠኝነት ሙያ መሆኑ ነበር ያስገረማት።

ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ተካ ፈጣሪ ዕድሜና ጤና ሰጥቷት ለጡረታ ብትበቃ በጋዜጠኝነት ሙያዋ አገሯን እና ወገኖቿን እስከ መጨረሻው በግሏ እንደምታገለግል ደጋግማ ትናገራለች።

 

 



   

 

         

                  

















 

               



















 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች