ሰሎሞን ሞገስ
በደብረብርሀን ከተማ የተወለደው ነገር ግን የህጻንነት እና የወጣትነት እድሜውን ከወላጅ እናቱ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈው ገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ / ፋሲል / በተለይም በሀገር ጉዳይ ላይ ባተኮሩ መሳጭ ግጥሞቹ ይታወቃል፡፡ ባለፉት 26 አመታት በገጣሚነቱና በጋዜጠኝነቱ የሚታወቀው ሰሎሞን 4 የግጥም መጽሀፎችን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በተጨማሪም በቪሲዲ ‹‹የሀገር ልጅ ጨዋታ›› የተሰኘ የኮሜዲ ስራንም ለተመልካቾች አቅርቧል ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ በመይሳው ፣ በገናናው፣በሩህ ፣በኔሽን እና በአውራ አምባ ታይምስ ጋዜጦች ላይ የሰራ ሲሆን በ2007 አ.ም ዳሸን ቢራ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ ውድድር በስነ-ግጥም ዘርፍ ተወዳድሮ አንደኛ ለመሆን የቻለ ነው፡፡በወቅቱም‹‹ ህልሞቻችሁን ፈልጉ!›› በተሰኘው ግጥሙ ከዳሸን ቢራ የአንድ መቶ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በ2001 አ.ም‹‹እውነትን ስቀሏት!››፤ በ2004 አ.ም ‹‹ከፀሀይ በታች››፤በ2006 አ.ም ‹‹ጽሞና እና ጩኸት›› ፣በ2009 አ.ም ‹‹የተገለጡ አይኖች›› የተሰኙ የግጥም መጽሀፍትን አሳትሞ ለንባብ ያበቃ ነው፡፡ሰሎሞን እነዚህም ስራዎቹ በአንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የቻሉ ነበሩ፡፡ሰሎሞን ሞገስ በስነ-ግጥምና በጋዜጣ ጽሁፎቹ የህዝቡን እውነት በመናገር ፤ ማህበራዊ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት ይታወቃል፡፡ በዚህም በወቅቱ በነበረው የኢህአዴግ ስርአት ከፍተኛ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም፣ በ2010 አ.ም ከሚወዳት ሀገሩና ከሙያው ተለይቶ በስደት ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰአት ገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ በጀርመን ሀገር ኑሮውን በስደት እየገፋ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ምንጭ ተወዳጅ ሚድያ አዘጋጅ እዝራ እጅጉ

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ