ጋዜጠኛ ሶስና
ተስፋዬ 1990ዎቹ
ተወዳጅ
ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን
‹‹መዝገበ-አዕምሮ›› በሚል
ርዕስ የ180 የሚድያ
ሰዎችን ታሪክ በመጽሀፍ
አሳትሞ ሀምሌ 30 2014 ማስመረቁ
ይታወቃል፡፡ በቀጣይ ደግሞ
መዝገበ-አእምሮ ቅጽ
ሁለት በሚል ርእስ
በቅጽ 1 ያልተካተቱ ሰዎች
በቅጽ 2 ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህም
አንዷ ሶስና ተስፋዬ ናት፡፡ እዝራ እጅጉና አንተነህ ደመላሽ ታሪኳን እነሆ ብለዋል፡፡
ውልደት- ልጅነት- ትምህርት
አዲስ
አበባ በዕለተ ቡሄ
ነሐሴ 13/ 12/ 1972ዓ.ም
መሿለኪያ አካባቢ ተወለደች፡፡
ወርሃ ነሐሴ የክረምት
ጎን መታጠቂያ
ነውና ሶስና ተስፋዬም
በዚህ ወር የህይወት
አንጓዋን ትለይ ትገነባም
ጀመር፡፡ብሔራዊ የህዝብ ትምህርት ቤት
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን
ከ 1ኛ
- 8ኛ ክፍል
ተምራለች::በመቀጠል የሁለተኛ ደረጃ
ትም ህርቷን
ሽመልስ ሀብቴ 2ኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት
ስታጠናቅቅ ወደ ኮተቤ
የመምህራን ኮሌጅ በመግባት
በ1991ዓ.ም በእንግሊዘኛ
ቋንቋ ዲፕሎማዋን አግኝታለች::ለአንድ
አመት ያህልም አዲስ አበባ በሚገኘው በ
አፄ ፋሲል
ትምህርት ቤት ከ
5ኛ-7ኛ
ክፍል በእንግሊዘኛ ቋንቋ
መምህርነት አገልግላለች፡፡በስራ ላይ እያለችም ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ በዉጭ ቋንቋና
ስነፅሁፍ ድግሪዋን
ተምራለች፡፡
የጋዜጠኝነት ጉዞ
የመምህርነትን
ሙያ ብትወደዉም
ቀድሞ የነበረዉ የመምህርነት
ክብር እና መምህርት
ሶስና የነበረችበት የተማሪዎች
ስነ-ምግባር
አለመታረቅ ምቾት ቢነሷት
ሌላ የሥራ
ዘርፍ ማፈላለጓን ቀጠለች፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው
ዕለታዊ ጋዜጣ የሚመሰረትበት
ወቅት ነበርና ይህ
መረጃ የደረሳት ሶስና
ለጀማሪ ጋዜጠኝነት በማመልከትና የሚፈለገውን
መስፈረት በማሟላት ለመቀጠር በቃች፡፡ "በእለታዊ አዲስ" ጋዜጣ በዜና
ክፍል ተመድባ የጋዜጠኝነት
ጉዞዋን ሀ ሁ
አለች፡፡በስራዉ ልምድ ካላቸዉ
የዜና ክፍል ጋዜጠኞች
ከጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተ
ወልድ፤ ከጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ
ዕቁባይ፤ከሙላት አለማየሁና/በአሁን
ሰአት ዶ/ር
ሙላት አለማየሁ/ ከተለያዩ
የሥራ ልምዴን ገነባሁ
የምትለን ጋዜጠኛ ሶስና
ተስፋዬ በእቅድ
ዜናዎችን በመስራት ቀጣይነታቸውን
በመፈልፈል በተለይ ሴቶች
ላይ የሚደርሱ
አካላዊ፤ ሞራላዊና በስራ
ላይ የሚደርሱ
ተፅዕኖዎች ላይ ትኩረት
አድርጋ በመስራት ጉልህ
ሙያዊ አሻራዋን አስቀምጣለች፡፡
ሬዲዮ
ፋና
በ1993
ዓ.ም
መገባደጃ አካባቢ በተለያዩ
ተፅእኖዎች ምክንያት ህልውናውን
ማስቀጠል ያልቻለው ዕለታዊ አዲስ ጋዜጣ
ይዘጋል፡፡ብዙም ሳይቆይ ሬዲዮ ፋና ጋዜጠኞችን ለመቅጠር ይፈልግ ነበርና የወጣውን
ማስታወቂያ መሰረት በማድረግ ያመለከተችዉ ወጣቷ ጋዜጠኛ የጽሁፍና የቃል
ፈተናዎችን በመፈተን በ1994ዓ.ም
ሬዲዮ ፋናን ተቀላቅላለች፡፡በሬዲዮ
ፋና ለ5
አመታት ያህል በነበራት
የሥራ ዘመን ፍኖተ
ጤናና ተሰፋ ደወል
የተሰኘ በኤች አይቪ
ላይ የሚያተኩሩ
ሳምንታዊ ፕሮግራሞችን ከማዘጋጀት
በተጨማሪ፤ ከአርብ ምሽት
ጀምረው እስከ እሁድ
ምሽት በሚዘልቁ የመዝናኛና
የወጣቶች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ኃላፊነቷንና
ሙያዊ ግዴታዋን ትወጣ
ነበር፡፡
ከፋና ወደ"
ኤድስ መረጃ
ማዕከል
በማህበራዊ
የግንዛቤ ውስንነቶችና ክፍተቶች
ላይ ሙያዋን
ያሰረፀችው ጋዜጠኛ ሶስና
ከፋና ወደ" ኤድስ
መረጃ ማዕከል" ራሷን
አሰረገች፡፡ በወቅቱ በ"
John Hopkins University " አጋርነት
ህልውናውን የመሰረተው ይህ
ትልቅና አንጋፋ ድርጅት
ኤች አይቪ
ላይ ልዩ
የሬዲዮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት
እቅድ ላይ ነበር፡፡
የፕሮግራሙ አቀራረብ በግለሰብ
የእለት ተእለት የህይወት
ማስታወሻዎች ላይ ያጠነጠነ
ነዉ፡፡ ከ John Hopkins Universty በመጡ አሰልጣኞች
ስለ ሪያሊቲ
ሬዲዮ/Reality Radio/ አዘገጃጀት ጥልቅ
ስልጠና አገኘች፡፡በተለይም እንዴት
አድርገው የሰዎችን እውነተኛ
ታሪክ በተከታታይ ማዘጋጀትና
ማቅረብ እንደሚቻል /Radio Diary production/ ስልጠናውን ለሷና
በወቅቱ ለተመረጡ ጥቂት
ጋዜጠኞች ከሰጧቸው በኋላ
ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡
የስራ ባልደረቦቿ ጋዜጠኛ
መሰንበት ኃይሉ፤ ጋዜጠኛ
ነፃነት አሳየ፤ ጋዜጠኛ ሸዋዬ
አረጋና ሌሎችም ጋዜጠኞች ጋር በመሆን
በኤች አይቪ ኤድስ
በሽታ ላይ የማህበረሰቡን
አስተውሎት የገነባችው ጋዜጠኛ
ሶስና ተስፋዬ ለ
ፕሮግራሙ መጠሪያ " ቤተኛ
" የተሰኘውን ስያሜ የሰጠችዉም
እሷዉ ነች፡፡ይህ "ቤተኛ"
የተሰኘዉ የሬዲዮ ፕሮግራም
ኤች አይቪ
በደማቸዉ ዉስጥ የሚገኝ
ግለሰቦችን ታሪክ ከልጅነት
እስከ እውቀት ድረስ
በተከታታይ እያዘጋጀ
በአማርኛ፤ በኦሮምኛና በትግርኛ
ቋንቋዎች በሃገሪቱ በሚሰራጩ 7 የሬዲዮ
ጣቢያዎች ለአድማጮች
ያደርስ ነበር፡፡
በጋዜጠኛ
ሶስና ስያሜነትና ጉልህ
ሚና በአማርኛ
"ቤተኛ"፤ በኦሮሞኛ
"አንቴ" በትግሪኛ"መኧሙናይ"የተሰኘው ፕሮግራም
በወቅቱ ቫይረሱ
በደማቸዉ የሚገኝ ሰዎች
ለሌሎች ምሳሌ እንዲሆኑ
በማግባባትና የህይወት ተሞክሯቸውን
ለህዝብ እንዲያካፍሉ በማድረግ
ብዙ ስራዎችን
ሰርታለች፡፡በተለይም በአማርኛ ቋንቋ
በአዲስ አበባ በተለያዩ
ኤፍ ኤም
ጣቢያዎች ከሚተላለፉ ፕሮግራሞች
በተጨማሪ በአማራ እና
በደቡብ ክልል ለሚተላለፈው
ቤተኛ
ፕሮግራም ወደ ሁለቱም
ክልሎች በአካል በመሄድ
ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ
የሚኖሩና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎችን
በመመልመል፤ ስልጠና በመስጠት
ለማህበረሰቡ በራሱ የቋንቋ
ዘዬ፤ብሂል፤የትውልድ ቦታ፤ በሚያውቃቸውና
በሚውል በሚያድርባቸው ከተማዎች
የዳበረ ዝግጅት አዘጋጅታ
ታቀርብለት ነበር፡፡ ለስምንት
አመታት በዘለቀዉ በዚህ
ፕሮግራም ስለ ኤች
አይቪ ኤድስ በማህበረሰብ ዉስጥ የነበረዉን
ግንዛቤ በማስፋት ፤ ወጣቱ
እራሱን ከኤች አይ
ቪ እንዲጠብቅ
በማድረግ፤ ቨይረሱ
በደማቸዉ ዉስጥ የሚገኝ
ወገኖች የሚደርስባቸውን አድሎና
ማግለል በመቀነስ፤እንዲሁም የጸረኤች
አይቪ መድሃኒትን በአግባቡ
በመጠቀም ጤናማ ህይወት
እንዲኖሩ በማድረግ በጋዜጠኝነት ሙያዋ ችግሮችን
አቃላለች፤ትርጉም ያላቸዉ ስራዎችን
ሰርታለች ፤ እልፍ ነፍሶችን
ከ ወሲብ
ወረርሽኝ ታድጋለች፡፡በዚህ የስራ
ሂደቷም ጋዜጠኛ ሶስና
ከሲኒየር ፕሮግራም አዘጋጅነት
አስከ ፕሮግራም አስተባባሪነት
/coordinator/ ሰርታለች፡፡
"እርካብ
ሚዲያና ኮሚኒኬሽን"
በ2006
ዓ.ም
መንግስት በኤች አይቪ ላይ
ትኩረቱን ሲቀንስና ቀልቡን
ሲያሸሽ ፤ John Hopkins Universty'ም ድጋፉን
ሲያቋርጥ "የኤድስ መረጃ
ማዕከል" የቤተኛ ፕሮግራም አዘጋጆችን
የምስጋና
ምስክር ወረቀት እና
ዋንጫ በመስጠት ስለ
ነበራቻው ቆይታ አመስግኖ
አሰናበተ፡፡ተወዳጁ የሬዲዮ ፕሮግራምም ሊቋረጥ ሆነ፡፡ ጋዜጠኛ
ሶስና ተስፋዬ ፕሮግራሙን ከሚያዳምጡ
የማህበረሰብ ክፍሎች በሚደርሷት
የተለያዩ የስልክ መልዕክቶች
ፕሮግራሙ ከህብረተሰቡ
ጋር የጠለቀ
ትስስር እንደፈጠረ ስላወቀች
ብሎም ኤች አይቪ
በእያንዳንዱ የግለሰብ ህይወት ስር
የሰደደና ቢቋረጥ
የሚያስከትለዉን
ችግር ስለተረዳች በግል
ጥረቷና ትጋቷ "ቤተኛ"ፕሮግራምን የራሷን
ድርጅት "እርካብ ሚዲያና
ኮሚኒኬሽን" በማቋቋም ቀጠለች፡፡
ማታ
ያለፋቸው የሌሊት ሰዎች
Sex Workers in Addis
Abeba
Diaries of sex workers
ዛሬ በከተማችን አዲስ አበባና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተስፋፋ የመጣዉ የሴተኛ አደሪነት ሕይወት መነሻዉ ከጥንት ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡የቀን ሳይሆን የለሊት ሰዉ መሆን በአደንዛዥ እጽና አልኮል ደንዝዞ ህሊናንና ገላን መሸጥ በዚህ ሂደት ከሚደርሱ አካል ጉዳቶችና ከሞት ጋርም ጭምር ትንቅንቅ ዉስጥ መግባት የሴተኛ አዳሪዎቹ የየእለት ህይወት ገጠመኝ ነዉ፡፡ይህ ሁሉ ለገንዘብ ነዉ፡፡ገላን በገንዘብ መለወጥ፡፡የአንሶላና የብርድልብስ ኑሮን በሰቀቀን መፈጠምና መኖር፤ በበሽታ መያዝ፤ የአእምሮ መመረዝ፤ ሰውነትን ማጣት፤ እራስን ማጥፋት ...ቀባሪ ማጣት የእህቶቻችን አስቀያሚ ህይወት ነው፡፡
ጋዜጠኛ ሶስና
ኤች አይቪ ላይ ፕሮግራሞችን ስታዘጋጅ የሚገጥሟት የሴተኛ አደሪዎች ታሪክ ሁልጊዜም ዉስጧን ይረብሸዉ ነበር፡፡በተለይ አብዘኛዎቹ
ሴቶች ኤች አይ ቪ በደማቸዉ ዉስጥ የሚገኝ መሆኑና ይሕንንም እያወቁ አማራጭ በማጣት ምክንያት እዛዉ ሴተኛ አዳሪነት ውስጥ ተዘፍቀዉ
ስታይ መረበሽን ከመፍጠሩም በላይ ትርጉም ያለው ስራ እንድትሰራ በዉስጧ እልህ እንዲፈጠር አደረገ፡፡ ፈላጊና
ተፈላጊ ተገጣጠሙና ጋዜጠኛ
ሶስና በካዛንችስ
አካባቢ በራሳቸው በሴተኛ
አዳሪዎች የተቋቋመ ማህበር
አገኘች፡፡ ይህንን ስብስብ
እንደመነሻ አጋር ተጠቀመችና
የሴተኛ አዳሪዎችን የሚታይ
የሚጨበጥ እንዲሁም አሰቃቂ
የህይወት ጉድና ጎድጓዳዎችን
ታስስ ትበረብር ትጎለጉል
ገባች፡፡
ከቺቺንያ
እስከ ቦሌ፤ከካዛንቺስ እስከ
ዳትሰን ሰፈር እንዲሁም ከደሮ
ማነቂያ እስከ አዉቶቢስ ተራና
ካራ ቆሬ
ባጠቃላይ በአዲሰ አበባ
ከተማ ያለውን የሴተኛ
አዳሪዎች ህይወት በራሳቸዉ
አንደበት ቤተኛ ፕሮግራም ላይ እንዲናገሩ ከምልመላዉ ጀምሮ
ስልጠና በመስጠትና ፕሮግራሙን
በማዘጋጀት ህብረተሰቡ ስለሴተኛ
አዳሪዋ ህይወት በጥልቅ
እንዲገነዘብ አስችላለች፡፡
ፕሮግራሙን
ከደገፉ ድርጅቶች
ማለትም ንቃት በጎ
አድራጎት ማህበር ፤
ግሎባል ፈንድ፤ የአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር
ኤች አይቪ
መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት፤ ኤድስ
ሄልዝ ኬር ፋዉንዴሽን
ኢትዮጵያ/AHF ethiopia/ካናዳ ኤንባሲ
ኦሳድ ዲኬቲ ኢትዮጵያና
የመሳሳሉ ድርጅቶች ጋር በመሆን
በዚህ ህይወት ምክንያት
የሚመጡ የጤናና ማህበራዊ
ቀውሶችን የተመለከቱ በርካታ
የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ለተከታታይ 12 አመታት
አዘጋጅታለች፡፡ እያዘጋጀችም ትገኛለች፡፡
በዚህ
ፕሮግራም አማካኝነት ብዙ
በጎ ሰዎች
እጃቸውን ለሴተኛ አዳሪዎቹ
ይዘረጋሉ፡፡ በለስ
የቀናቸውና በዚህ ህይወት
ዉስጥ የሚገኙ እህቶቻችን
የገንዘብ
ድጋፍ በማግኘት የተለያዩ የግል
ስራዎችን በመጀመር ከህይወቱ
ተላቀዋል፤ አንዳንዶቹም ወደ ቤተሰባቸው
በመመለስ በዚያው
በቀያቸዉ የተለያዩ አዋጭ
ስራዎችን በመስራት ህይወታቸዉን
ቀይረዋል፡፡ ጋዜጠኛ
ሶስና በዚህ
ሴተኛ አዳሪዎች ላይ
በሚያተኩረዉ ፕሮግራሟ ብቻ
ከ25 በላይ
ሴቶች ከአስከፊዉ የሴተኛ
አደሪነት ህይወት ተላቀው
በማየቷ ትደሰታለች፡፡ ከስራዋ የምታገኘዉ ትልም እርካታዋ ነዉ፡፡ሴቶቹ
በሚያገኙት የስራ እድል
እንዲጠነክሩና ህይወታቸውን በጥሩ
መንፈስ እንዲቀይሩ የተለያዩ
ባለሙያዎችን በማነጋገር በበጎ
ፍቃድ የስነልቦና ድጋፍ
እንዲያገኙ ማድረጉ ላይም
ሶስና አልቦዘነችም፡፡
የኮቪድ ወረርሽኝ
ጊዜ
የኮቪድ
ወረርሽኝ ጊዜ ሁሉም
ከቤቱ ተከተተ፡፡ ለሴተኛ
አዳሪዎች የህይወት ስር
የሆነው መጠጥ ቤትና ሆቴሎች ከዛም አልፎ ጎዳናዎችም ጭምር ሰዉ አልባ እንዲሆኑ
ተወሰነ፡፡ጭፈራ ቤቶችና ፔንሲኖች የሞት
ዋሻቸውን ዘጉ፡፡ የሞት
ዋሻ ሲዘጋም
የሚቸገር ፍጡር ኖሯልና፡፡
የጋዜጠኛ ሶስና ስልክ
የጠኔ እዬዬውን ያቀልጠው
ጀመር፡፡ በዚህ ረመጥ
የሴተኛ አዳሪነት
ህይወት ቤተሰብ ተመስርቶ ጎጆ
ተቀልሷል፤ ልጅ ተወልዷል፤
ታዲያ ይህን ጊዜ ገላም ተሸጦ የሚመጣዉ ገንዘብ ከየት ይምጣ? እሷን የሚያውቁ
መገኛ መረጃዋ ያላቸው102
ሴተኛ አዳሪዎች በቤተኛ
ፕሮግራም አስተባባሪነት ግዜያዊ
የምግብ ፍጆታና የገንዘብ
ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የኮቪድ ወረርሽኝ ወደሃገራችን
በገባ ወቅትም ጋዜጠኛዋ እጇን አጣጥፋ መቀመጥ አልፈለገችም፡፡በተለይ አዲስ በሽታ እንደመሆኑ ስለቫይረሱ የነበረዉ የተዛባ አመለካከትና
በበሽታዉ የተያዙ ሰዎች የሚገጥሟቸዉ የአድሎና መገለል ችግሮች ትሰራበት ከነበረዉ ኤች አይቪ ጋር ተመሳሰለባት፡፡በመሆኑም ጥልቅ
ፕሮፖዛልና ዝርዝር የስራ ሂደት በጽሁፍ በማዘጋጀት ጤና ላይ ለሚሰሩ
አለማቀፍና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ታስገባ ጀመር፡፡ በመጨረሻም በአይነቱ ልዩ የሆነው በኮሮና የተያዙ ሰዎችን ታሪክ በገዛ
አንደበታቸዉ /Covid diary/በሬዲዮ ስለማቅረብ የሚያትተዉ ፕሮፖዛል በኢንተርኒውስ ግሎባልና ዩኤስ ኤ አይዲ
/Internews Global and USAID/ተቀባይነትን በማግኘቱ "አታሞ" የተሰኘዉን ሌላኛዉን ፕሮግራሟን በሸገር ኤፍ ኤም
102.1 ላይ ጀመረች፡፡በዚህ ፕሮግራም በርካታ ከኮቪድ ያገገሙ ሰዎች በሽታዉ ሲጀምራቸዉ ጀምሮ ከቫይረሱ ነጻ እስኪባሉ ድረስ ያሳለፉትን
ስቃይና ዉጣዉረድ ጥልቅ ከሆነ ሰዋዊ ስሜት ጋር አቀናብሮ አቅርቧል፡፡
ከ2009 ጀምሮ
ጋዜጠኛ
ሶስና ተስፋዬ ካለፍት
አምስት አመታት ወዲህ በድርጅቷ አማካኝነት
ከ ዲኬቲ
ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቤተሰብ
እቅድ አገልግሎትና ፤ የወጣቶች
የሰነተዋልዶ ጤና ላይ
የሚያተኩሩ ፕሮግራሞችን በተጨማሪነት እያዘጋጀች
ትገኛለች፡፡በሸገር ኤፍ ኤም
ከሚተላለፉ ቤተኛና አታሞ
ፕሮግራሞች በተጨማሪ ተመሳሳይ
ይዘት ያላቸዉን ፕሮግራሞች በ
ፋና ሬዲዮና
፤ በኢትዮጵያ
ሬዲዮ ብሄራዊ
አገልግሎት በሁለት የተለያዩ
ቋንቋዎች ማለትም በኦሮምኛና
በሱማልኛ ቋንቋዎች ጋዜጠኞችን ቀጥራ ታሰራለች ክትትል
ታደርጋለች፡፡
የምታዘጋጃቸዉ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቶች የተለያዩ ቤተሰቦችን ታሪክ እንድታዉቅ ረድቷታል፡፡በተለይም
የልጆችን ቁጥር መወሰንና የእርግዝና መከላከያ ዘዴን በተመለከተ የባሎች
ሚና እጅግ አናሳ መሆኑን የተረዳችዉ ጋዜጠኛዋ ጥቂት የትዳር አጋሮች ግን ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ተሞክሮ እንዳላቸዉ ተገነዘበች፡፡በመሆኑም
በአይነቱ ልዩ የሆነና በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ "የምርጥ ባሎች" ዉድድር ማዘጋጀት ጀመረች፡፡ለአራት
ተከታታይ ዙሮች ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር አጋርነትን በመፍጠር ይህ የምርጥ ባሎች ዉድድር ተከሂዳል በርካታ ተወዳዳሪ ምርጥ ባሎች
ተሞክሯቸዉን ለሌሎች በሬዲዮ አካፍለዋል፡፡ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
ጋዜጠኛ
ሶስና ከዚህ ስራ
ጎን ለጎንም
የአፈር ለምነትን በተመለከተ
በአማራ እና በኦሮሚያ
የተመረጡ አካባቢዎች በመሄድ
"አፈርም ይታመማል" በሚል
የተፈጥሮ ቁርቋሬ ብሎም
የአርሶ አደሩን ችግር
በመረዳት የተለያዩ ፕሮግራሞች ሰርታለች፡፡የአፈር አሲዳማነትን በተመለከተ
በኖራ ማከም እንደሚቻል
ለ አርሶ
አደሩ ግንዛቤ ለመፍጠር፡
ከ GIZ፤
Agree Pro Focus ፤ Ministry of
Agriculture . . . መሰል
አጋር ድርጅቶች ጋር
በመሆን በአማርኛ፤ በኦሮሞኛና
በትግርኛ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን ሰርታለች፡፡
በተለይ በአማራ ክልል
በምስራቅ ጎጃም አጫጭር
መልእክቶችን በማዘጋጀት፤ በገበያ
ቀን ከ
6 በላይ መድረኮችን በመቀመር
ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን
ትምህርት ከመዝናኛ ፕሮግራሞች
ጋር ከሽና
አቅርባለች፡፡
የማህበረሰብ
መልክ የሆነችው ጋዜጠኛ
ሶስና ተስፋዬ፡፡ "እርካብ
ሚዲያና ኮሚኒኬሽን" በተሰኘ
የግሏ ሚዲያ ከአስር በላይ
ለሆኑ ሰዎች የስራ
እድል ፈጥራለች! ባለ
ትዳርና የሶስት ልጆች
እናት ናት፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ