]
174.ምንይችል እንግዳ
የአዊ ቋንቋን
ያሳደገ
ጋዜጠኛ ምንይችል እንግዳ በአገውኛ ቋንቋ ጋዜጠኞችን በማፍራትና በሙያውም ላይ የጎላ ድርሻ በማበርከት የራሱን ትልቅ
አሻራ ያኖረ ነው፡፡
ጋዜጠኛ፣ ደራሲና
የሙዚቃ ሰው ምንይችል እንግዳ ተወልዶ ያደገው በቀድሞው ጐጃም ክ/ሀገር መተከል አውራጃ ማንዱራ ወረዳ ነው፡፡ የመጀመሪያና
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከቤተሰቦቹ ጋር ተምሯል፡፡ ምንይችል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቲያትር ጥበባት የመጀመሪያ ዲግሪውን
ከጐንደር ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሶሻል ሳይንስ 2ኛ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡
ምንይችል እንግዳ
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከሪፖርተርነት እስከ መምሪያ ኃላፊነት በተለያዩ ክፍሎች ሰርቷል፡፡ ምንይችል እንግዳ ፀሀፊና ዘፋኝም
ነው፡፡
በተለይም ተወልዶ
ባደገበት አካባቢ የፅሁፍ ቋንቋ በዳበረበት የአገውኛ ቋንቋ ባህልና ወግ የሚያንፀባርቅ ‘’ድቑዊ ያቒንኩሲ’’የተሰኘ የግጥም
መድብል ለተደራሲያን አድርሷል፡፡ በአገውኛ ቋንቋ የዘፈን ግጥሞችን በመፃፍ ለድምፃውያን ሰጥቷል፡፡ እሱም ‘’እንዳርሼጊና’’
እና ‘’ዱንጊትጁና’’
የተሰኙ
ዘፈኖችን ለህዝብ አድርሷል፡፡
ጋዜጠኛ ምንይችል
እንግዳ የአገውኛ ቋንቋ እንዲዳብር በኪነጥበብ ዘርፍ እያበረከተ ካለው ጉልህ ተግባር በተጨማሪ አገውኛ ቋንቋ የአማራ ሬዲዮ
ስርጭት በጀመረበት ዓ.ም ጀምሮ በቋንቋ ጋዜጠኞችን በማሰልጠን አብሮ በመስራት ታላቅ አበርክቶ ነበረው፡፡ በተጨማሪም የአዊ
ልማት ማህበር ሲቋቋም የቦርድ አባል በመሆን ሰርቷል፡፡
ጋዜጠኛ፣ ፀሀፊና
ሙዚቀኛ ምንይችል እንግዳ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ከወጣ በኋላ በደቡብ ክልል ከንባታ፣ አላባና ጠንባሮ አካባቢዎች የባህል ባለሙያ
ሆኖ ሰርቷል፡፡
ወደ አካባቢው
ከተመለሰ በኋላም የአገው የሙዚቃ ባህል ቡድን ከመሰረቱ ቀዳሚውና የቡድኑ መሪ ሆኖ ለባህል ቡድኑ የጀርባ አጥንት ሆኖ
አገልግሏል፡፡
ጋዜጠኛ ምንይችል
እንግዳ ለሙዚቃ የተለየ ስሜት አለው፡፡ ቤተሰቦቹ ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር ያላቸውና በተለይ ከእርሻ ስራቸው ሲመለሱ ክራር በመጫወት
ራሳቸውን ያዝናኑ ስለነበር እርሱም ድምፃዊነት የጀመረው ከቤተሰቦቹ የሳት ዳር ጨዋታ ነበረ፡፡
የአገው የሙዚቃ
ባህል ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመሠረት በሙዚቃ መሣሪያና በአልባሳት የተሟላ እንዲሆን በወቅቱ የነበሩ ኃላፊዎች በትኩረት
እንዲሰሩ ሌት ተቀን በመጠየቅ ቡድኑ ጠንክሮ እንዲወጣ ጉልህ አሻራውን አስቀምጧል፡፡ የቡድኑ የሙዚቃ አልበም ለመጀመሪያ ጊዜ
ለህዝብ እንዲደርስና የአዊኛ ቋንቋ ባህልና ወግ ትውፊቱ እንዲታወቅ የመሪነቱን ሚና ተወጫቷል፡፡አንጋፋ ክሚባሉት የአማራ ሚዲያ
ኮርፖሬሽን ጋዜጠኞች አንዱ የሆነው ምንይችል በተለያዩ የሚድያ ዘርፎች ሲሰራ በ1997 አመተምህረት ሌላ አጋጣሚ
ተፈጠረለት።ይሄውም በክልሉ ራዲዮ የአገውኛ ስርጭት መጀመሩ ነው።እናም ምንይችል የመጀመሪያው የአገውኛ ቋንቋ የራዲዮ ጋዜጠኛ
በመሆን ይታወቃል።በሂደትም ሌሎች ጋዜጠኞ ለቋንቋው እየተቀጠሩና የስራው አይነትም እየተስፋፉ ሄዶ በቴሌቪዥን በጋዜጣና
በኦንላይን/ በድረ-ገጽ/ ቋንቋው እንዲያድግ በመትጋት አይነተኛ ሚና ተጫውቷል።
ጋዜጠኛ ምንይችል
እንግዳ በአሁኑ ወቅት የስራና የህይወት ተሞክሮውን ለተተኪው እያስተማረ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋዜጣ፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥና
በኦንላይን በሚተላለፈው የአዊኛ ቋንቋ ዴስክ ኃላፊ በመሆን ተዝቆ ከማያልቀው የህይወት ልምዱ ለማህበረሰቡ እያካፈለ ይገኛል፡፡
ባለትዳርና ሶስት ልጆች አባትም ነው፡፡
ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ
ቻግኒ ከተማ ተምሯል፡፡
1982 አዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ገባ፡፡
1983 ዓ.ም
የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ ወደ ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ ገብቷል፡፡
ጋዜጠኛ ምንይችል
እንግዳ በዩኒቨርስቲ ቆይታው በወቅቱ በነበረው የደርግ አገዛዝ ይደርስ የነበረው ኢ-ፍትሀዊ አሰራር ከጓደኞቹ ጋር በመሆን
ተቃውሟል፡፡ በተለይም በ1981 ዓ.ም በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተሳትፈዋል የተባሉ ጀኔራሎች በመገደላቸው ከጓደኞቹ ጋር
ውሳኔውን በመቃወም በሰልፍ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም በ1985 ዓ.ም
የኤርትራን መገንጠል በመቃወም ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ስለኢትዮጵያ አንድነት ታግሏል፡፡ በዚህም ዩኒቨርሲቲው በመዘጋቱ
የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገዶ ነበር፡፡
ጋዜጠኛና የሙዚቃ
ሰው ምንይችል እንግዳ ከሙዚቃ መሣሪያ ለክራር ልዩ ፍቅር ያለውና የአዊ የሙዚቃ ቡድን ጋር ክራር በመጫወት ሙዚቀኞችን
አጅቧል፡፡
የአዊ የባህል ቡድን
ላይ አማተሮችን በቲያትር ጥበባት አሰልጥኗል፡፡አደራጅቷል።በአዊ ዞን በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የቲያትርና ስነጽሑፍ
ክበባት እየተዘዋወረ በማሰልጠን በርካታ ከያኒያንን አሰልጥኗል።
በሙዚቃ ስራዎች
በአዊ የባህል ቡድን “እንተዋወቅ” በተሰኘ የአካባቢውን ባህልና
ወግ በሚያስተዋውቅ አልበም ላይ ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ የአልበሙ ቁጥር 3 ደረጃ ድረስ የሙዚቃ ስራዎችን ለድምፃዊያን
ሰጥቷል፡፡ እርሱም በድምፅ ዘፍኗል፡፡
ጋዜጠኛ ምንይችል
እንግዳ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከእናቱ ወ/ሮ ስመኝ ኢያሱ የወረዳው አኢሴማ ም/ሊቀ መንበር ስለነበሩ ከስራ ቦታቸው ያመጡት
የነበረውን “አዲስ ህይወት” የተሰኘ መፅሄት ላይ ያገኘውን ፅሁፍ እንደ ጋዜጠኛ በማንበብ የጋዜጠኝነት ፍላጐቱ ከዚያ እንደጀመረ
ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ከሕጻንነቱ ጀምሮ ራዲዮ ይከታተል ስለነበር የታዋቂዎቹን ዜና አቅራቢዎች ቅላጼ በልጅ አንደበቱ
ለማስመሰል በመሞከር በተለይ ከእናቱ አድናቆት ይቸረው ነበር።
በ1ኛ እና 2ኛ
ደረጃ የትምህርት ቆይታው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይቋቋሙ በነበሩ የድራማና ስነ ፅሁፍ ክበባት በመሳተፍ የጥበብ ጥሪውን ገና
በለጋ ዕድሜው ተቀብሎ ጉዞውን ጀምሯል፡፡
ጋዜጠኛ
ምንይችል እንግዳ በልሳነ ብዙነቱም ይታወቃል። የጉምዝኛ፣
የአገውኛ፣ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ የአገውኛ
ቋንቋ ወደ ፅሁፍ ቋንቋ እንዲያድግ የመማሪያ መጻሕፍት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚዘጋጁበት ወቅት ወደ አገውኛ ቋንቋ በመተርጐም
ከተሳተፉ 21 ባለሙያዎች ውስጥ አንዱ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ተማሪዎች በሚያውቁት ስነ ልቦናዊ አመለካከትና የህይወት ፍልስፍና
እንዲያድጉ የአጋዥ መጻሕፍት እጥረት በመኖሩ የስነ ጽሑፍ ስራውን በአገውኛ ቋንቋ መፃፉንም ይናገራል፡፡
ጋዜጠኛ
ምንይችል ቋንቋ የሰው ልጅ ሁሉ ሀብት ነው የሚል ፅኑ እምነት
አለው፡፡ በተለይም ህፃናት የአካባቢያቸውን ሀብት ወግ ባህል አውቀው እንዲያድጉና የአስተሳሰብ አድማሳቸውን ማስፋት አለባቸው፡፡
ልጆች መታገዝ አለባቸው የሚል እምነት አለው ። የስነ ጽሑፍ ስራዎች ይህን ያግዛሉና ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ይላል ፡፡
የብሔር ፖለቲካና መናቆር ጥላ ያጠላበት የጥላቸው መንፈስ የቋንቋ ልዩነት መሆን የለበትም የሚለው ጋዜጠኛ ምንይችል አንድ ቋንቋ
ለተናጋሪው ብቻ ሳይሆን የሁሉም የሰው ልጅ ሀብት ነው ብሎ ያምናል፡፡ አንድን ቋንቋ ፖሊሲ ተቀርፆ መቀመጡ ብቻ ህያው
አያደርገውም፣ ሀገራችን አሁን ካለችበት የብሔር ፖለቲካና የቋንቋ ጥላቻ መንፈስ ወጥተን ለሁሉም ቋንቋ ዕድገት መስራት
እንደሚገባም ያምናል፡፡
መዝጊያ ፤ ይህ መዝጊያ
የመዝገበ አእምሮ ቦርድ አባላት አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች
ባለቤት ናት፡፡ ቋንቋውን ለማሳደግ የሚጥሩ በሳል ሰዎችም አሉ፡፡ የአዊ ቋንቋ በሀገራችን ከሚነገሩ ቋንቋዎች አንዱ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ምንይችልም ይህን ቋንቋ ለማሳደግ የጎላ ድርሻ
ካበረከቱ ባለሙያዎች አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ብቸኛም ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ብዙሀን መገናኛዎች ቋንቋን በማሳደግ የሚኖራቸው
ሚና ጉልህ በመሆኑ ምንይችልም ይህንን አውቆ ግላዊ አሻራውን ለማሳረፍ
ችሏል፡፡ ይህ ሚናው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ምንይችል በሀገራችን
ካሉ አንጋፋ የሚድያ ባለሙያዎች አንዱ ብቻ ሳይሆን ታሪክ የሰራ በመሆኑ መዝገበ- አእምሮ ላይ ታሪኩ ለመሰነድ በቅቷል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ