168 ይፍቱስራ ፋንታሁን
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣
በቅርቡ መዝገበ-አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ
አሳትሞ ያስመርቃል፡፡ ታሪካቸው በመጽሀፉ ውስጥ ከሚሰነድላቸው አሻራ ካኖሩ የሚድያ ሰዎች አንዷ ይፍቱስራ ፋንታሁን ናት፡፡ ይፍቱስራ
በአዊኛ ቋንቋ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ ስትሆን በአሁኑ ሰአትም በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን የቋንቋዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን እያገለገለች ትገኛለች፡፡ ታሪኳም
እንደሚከተለው ተጠናክሯል፡፡
ትውልድና ልጅነት
ጋዜጠኛ ይፍቱስራ ፈንታሁን
፤ ከአባቷ ከአቶ ፈንታሁን አስረስ እና ከእናቷ ወ/ሮ የሮም በየነ በቻግኒ በ1974 ነበር የተወለደችው። ወላጆቿ የስራ ስፍራቸው ወደ ደብረማርቆስ በመቀየሩም የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በድብዛ የመጀመሪያ ደረጃ
ት/ቤት እና በአብማ ትምህርት ቤት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በቻግኒ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትላለች፡፡
የዩኒቨርሲቲ ቆይታ
በ2001 ዓ.ም ከባህርዳር
ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ስነ-ጽሁፍ የመጀመሪያ ዲግሪዋን የያዘችው ይፍቱስራ ፈንታሁን በተጨማሪም እንግሊዝኛን ማይነር በማድረግ ተምራለች፡፡
አማርኛን በማስተማር ወይንም ቲም የማስተርስ ዲግሪዋን ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ በ2006 ዓ.ም የተቀበለች ሲሆን የተለያዩ አጫጭር
ስልጠናዎችንም ለመከታተል ጥረት አድርጋለች፡፡ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል
ወንበራ ወረዳ ቦለሌ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ የስራ አለምን የተቀላቀለችበት ጅማሮዋ ቢሆንም በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ለአራት
አመት አዊኛ እና አማርኛ ቋንቋን በማስተማር በመምህርነት ሙያ አገልግላለች፡፡
ሚድያ
ይፍቱስራ ለኪነ ጥበባት
እና የጋዜጠኝነት ሙያ በነበራት ልዩ ፍላጎት በ2000 ዓ.ም የቀድሞ
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የአሁኑ አማራ ሚድያ ኮርፖሬሺን ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው የአዊኛ ቋንቋ የቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድራ
በማለፍ ብቸኛ የአዊኛ ቋንቋ ሪፖርተር ሆና ስራ ጀምራለች። በቆይታዋ
በሪፖርተርነት ዜናዎችን እና ፕሮግራሞችን አጠናቅሮ ማስተላለፍ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዊኛ ቋንቋ መስክ ወጥቶ በአዊ ብሄረስብ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ
የፖለቲካ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ዘግቦ በማስተላለፍ በአዊኛ ቋንቋ ተቀጣሪነት የመጀመሪያዋ ሴት
ጋዜጠኛ ናት::
ከዚህ በተጨማሪ ይበልጥ
በሚድያ ሙያ በመዝለቅ ጋዜጠኛ ይፍቱስራ ፈንታሁን ግንቦት 2001 ዓ.ም ጀምሮ ከሪፖርተርነት በተጨማሪ በአዊኛ ቋንቋ የአርታኢነት ስራንም በተጨማሪነት እንድትሰራ በተሰጣት ኃላፊነት
መሰረት ስራን ደርቦ የመስራት ልምድንም አካብታለች፡፡ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቿ ጋር በመሆን ‹‹ቸርቤዋ›› የተሰኘችውን የአዊኛ
ጋዜጣ እና የአዊኛ ቋንቋ ቴሌቪዥን ፕሮግራም በመጀመር ረገድ የበኩሏን ድርሻ ተወጥታለች፡፡ ከ2006 በኋላም ተቋሙ በክልል ያሉ
ቋንቋዎችን ከህዝቡ ፍላጎት ተነስቶ የአየር ሰዓት እና የሰው ሃይል በመጨመሩ
ቋንቋዎችን በማደራጀት የአዊኛ ቋንቋ ዴስክ አስተባባሪ ወይንም ምክትል ዋና አዘጋጅ አድርጎ በሰጣት የስራ ምደባ ክፍሉን
በመምራት እና ዘገባዎችን ሰርቶ በማሰራት አገልግላለች ክፍሉንም በታታሪነቱ እና ተግባብቶ በመስራት እንዲሸለም አድርጋለች፡፡
በተለይም የ15 ደቂቃ
የአዊኛ ሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራም ጀምሮ አሁን እስከአለበት እለታዊ ስርጭት የነበረውን የሚዲያ ጉዞ ፣ በዘጋቢነት፣ በመሪነት እና
አሁን እስከደረችበት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቋንቋች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርነት ደረጃ በሴቶች የሚዲያ መሪነት ሚና የበኩሏን
ድርሻ ተወጥታለች፡፡
በአሁኑ ስዓትም በሚዲያ
ተቋሙ አገልግሎት ከሚያደርስባቸው ቋንቋዎች መካከል አዊኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ህምጣና፣ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን በኃላፊነት እየመራለች
ትገኛለች፡፡
ቋንቋ አይገድባትም የምትባለው
ይፍቱስራ ከአዊኛ ቋንቋ በተጨማሪ በአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ ማቅረብ እና የሚዲያ መድረኮችን በመምራት ትታወቃለች፡፡
የጋዜጠኛ ሁለገብ ናት የሚሏት ባልደረቦቿ በስራዋ ታታሪነት ሁሉንም አይነት የሚዲያ ይዘቶች ማዘጋጅት እና የተደበቁ ባህሎች እንዲወጡ
ትልቅ ሚና ተወጥታለች፡፡
የውጭ
ጉዞ እና ስልጠና
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባመቻቸው እድል 15 የአማራ ብዙሃን መገናኛ
ድርጅት ጋዜጠኞች ቻይና ቤጂንግ ሄደው የ2019 የሚዲያ ሴሚናር እንዲሳተፉ ከተላኩት መካከል አንዷ ይፍቱስራ ፈንታሁን ነበረች።
ሴሚናሩ የተካሄደው እንደአውሮፓውያን
አቆጣጠር August 24-september 13/2019 ድረስ ነው። ጉብኝትና ትምህርታዊ ገለፃ ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘዴዎች ነበሩት።
በዚህም 3 የሚዲያ ተቋማትና 12 የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ከባልደረቦቿ
ጋር በመሆን ጎብኝታለች። በዋናነትም ከሲሲቲቪ (Cctv.com)፣ ጉዋንዡ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አስተዳደር እና ኔትዎርክ
(Guizhu radio and television Administration፣ Guizhu radio and television
networking) ሚዲያዎችን በአካል በመገኘት ተመልክታለች፡፡
በሚዲያ ጉብኝቷ
(Management and operation of TV, radio and convergence media) የሚዲያ ግንባታ (Construction and development of
Radio and TV industry at Provincial level)
የአዲሱን ሚዲያ ልማት (Development of new media in local TV station እውቀት ቀስማለች፡፡
በቻይና ታላላቅ የቱሪዝም
ስፍራዎች ታላቁን የቻይና ግንብ (Great wall)፣ የጎዋንዡን
ገጠራማ አካባቢዎች ፣ የህንፃ ምህንድስናወች፣ ጥንታዊ ከተሞች ፣ የጎብኝ ማዕከላት ጎብኝታለች፡፡ በተለይም ከቤጅንግ የወፍ ጎጆ
ስቴዲየም (Beijing Birds net Stadium) እስከ ተረሱት የቤጀንግ ከተሞች (Beijing Forbidden city) ፣
በሙያ ከተካኑት የቻይና የፊልም ስራ ማዕከል (China Film Production center) እስከ ቤጅንግ ግዙፉ የእንስሳት ፓርክ
(Beijing Zoo) እና ሌሎችንም በመመልከት ከቻይና ፈጣን እድገት ለተቋም ልማት የሚሆናቸውን ልምድ ከቀሰሙት ጋዜጠኞች ማዕከል
ናት፡፡
አቅምን አጎልብቶ ማውጣት እና ሽልማት
በነበራት የስራ ትጋትም
በተለያዩ ጊዜ በሚሰሩበት የሚዲያ ተቋም እውቅና ያገኙ ሲሆን የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶችን ከድርጅቱ አግኝተዋል፡፡ በግላቸው ባሳዩት ውጤት መሸለም ብቻ ሳይሆን በሚመሩት የሚዲያ ቲም ውስጥም
እንደቡድን ተሸላሚ እንዲሆን የነበራት ሚና የላቀ እንደነበር ጓደኞቿ ይመሰክራሉ፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባወጣው ዘገባም በተለይም ይፍቱስራ በምትሳተፍበት የመሪነት ደረጃዎች የመጡት ለውጦች አንዱ የተቋሙ አበይት ክንውን ሁኖ ተመዝግቧል፡፡
በዚህም የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በብሔረሰብ ቋንቋዎች የሰዓት ለውጥ እንዲያደርግ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፡፡
ይፍቱስራ በይዘት ዝግጅት፣
በፎርማት ቀረፃ የተለየ ችሎታ አላት የሚሏት ባልደረቦቿ፡ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቋንቋዎች ዳይሬክቶሬትን ከአማራ ቴሌቪዥን በተጨማሪ
፣ አሚኮ ህብር ቻናልን እንዲያቋቁም በመሪነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች፡፡ ከሕዳር 8/2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የዜናና የፕሮግራም ሰዓት ማሻሻያ
ጣቢያው ሲያደርግ በሚዲያ መሪነት ዘመኗ ከመጡ የለውጥ አጋጣሚዎች የሚጠቀስ ሁኗል፡፡
በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የቋንቋዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ
ይፍቱስራ ፈንታሁን የዓየር ሰዓታቱን ለመከታተል ምቹ ባለመሆናቸው የህብረተሰቡን ጥያቄ መሠረት በማድረግ የሰዓት ለውጥ እንደተደረገ
ለጣቢያ የሰጠችው መረጃ ያሳያል፡፡
በዚህ መሠረትም ሰኞ
(የኽምጣጞ) ፣ ማክሰኞ (የአዊጚ) እና ረቡዕ (የኦሮምኛ) ዜናና ፕሮግራሞች ከቀኑ 7፡00 - 8፡00 ይተላለፋሉ፡፡ በቀኑ መርሀ
ግብር የተላለፉት ዜናና ፕሮግራሞች በድጋሜ ምሽት ከ5፡00-6፡00 እንዲሁም ጠዋት ከ12፡00-1፡00 እንደሚተላለፍ በዳይሬክተሪነት
ባለችው ኃላፊነት ካሳካቻቸው ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
በአሁኑ ስዓት የሁለት
ወንድ ልጆች እናት እና የሚዲያ መሪ በመሆን በቤተሰብ እና በሙያ ኃላፊነት እያገለገለች ትገኛለች፡፡
ስለ ይፍቱስራ ፋንታሁን
የስራ ትጋት ምስክርነት እንዲሰጡን የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚን አቶ አንተነህ መንግስቴን አነጋግረን ነበር፡፡
አቶ አንተነህ መንግስቴ ስለ ጋዜጠኛ ይፍቱስራ ሲናገሩ በተለይ አዊ ቋንቋ ላይ ያበረከተችው አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡ እንደ መሪም
ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ በቶሎ እና በሙያዊ ብቃት ከመጡት ውስጥ አንዷ ናት ሲሉ የስራ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
‹‹ የአዊ ቋንቋ አድማጮች በደንብ ያውቋታል፡፡ያከብሯታል፡፡ የመጀመሪያዋ የአዊ
ቋንቋ ጋዜጠኛም ነች፡፡ ይህም ታሪካዊ ያደርጋታል፡፡ በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ታሪክ ከፍተኛ የአመራር ደረጃ በመያዝ ከሴቶች ብቸኛዋ ናት፡፡ ከአለቆቿ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም ጠንካራ ከሰው
ጋር ያላት አጠቃላይ ተግባቦትም በብዙዎች የሚደነቅ ነው፡፡ ሰውን ስለምታከብር ሰውም በጣም የሚያከብራት ሰው ናት፡፡ የእርሷ ታሪክ
በተወዳጅ ሚድያ ብሎግና በኢንሳይክሎፒዲያ መውጣቱ አዲስ ለሚመጡት የሚድያ ሰዎች የሚያበረታታ ነው፡፡›› በማለት ምክትል ዋና
ስራ አስፈጻሚው ነግረውናል፡፡
መዝጊያ ፤ ይህ መዝጊያ
የተወዳጅ ሚድያ የኢንሳይክሎፒዲያ ቦርድን አቋምን የሚያንጸባርቅ ነው
ጋዜጠኛ ይፍቱስራ በአንድ በኩል በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ናት፡፡ በሌላ
ደግሞ በአዊ ቋንቋ ጋዜጠኝነት በማካሄድ የጎላ ሚና ያበረከተች ናት፤፤ ጋዜጠኝነት በሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች መሰራት እንደሚችል
በተግባር ያስመሰከረች ናት፡፡ ጋዜጠኛ በእንዲህ መልኩ ሁለገብ ሆኖ ሲሰራ ትልቅ አሻራ ማኖር ይችላል፡፡ ይፍቱስራ የፕሮግራም ፎርማት ቀረጻ ላይ የጎላ ሚና ነበራት፡፡ እንዲህ አይነት
ሰዎች ወደ ፊት መጥተው ታሪካቸውን ቢያካፍሉ ብዙዎች ይነቃቃሉ፡፡
በተለይ የሀገር ውስጥ ቋንቋን በመጠቀም የሚድያን ስራ እያከናወኑ
ያሉ ባለሙያዎች በክብር ሊያዙ ይገባል፡፡ ስራቸውንም በብቃት ለማከናወን ሁኔታዎች ሊመቻቹላቸው ይገባል፡፡ የእኛ ዋና አላማ መሰነድ
ስለሆነ ግለ-ታሪኳን በዚህ መልኩ ለትውልድ እንዲቀመጥ አድርገናል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ