150.የተቀበረው የመጽሐፍ ገፅ ጥላሁን በላይ -TILAHUN BELAY
ከመጻሕፍት ጉባኤ
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣
በቅርቡ ክምችተ-አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ
አሳትሞ ያስመርቃል፡፡ ታሪካቸው በመጽሀፉ ውስጥ ከሚሰነድላቸው አሻራ ካኖሩ የሚድያ ሰዎች አንዱ የሚድያ ሰው አቶ ጥላሁን በላይ
ናቸው፡፡ አቶ ጥላሁን በላይ በተለይ በጠንካራ አንባቢነታቸው የተመሰከረላቸው በኢትዮጵያ ሬድዮ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትልቅ
ስራ ከሰሩት መካከል ቀዳሚው ናቸው፡፡ እዝራ እጅጉና አንተነህ ደመላሽ ታሪካቸውን እንደሚከተለው አጠናክረውታል፡፡
በፊደላት
ደማቸውን ለወሱ፤ በቃላት ስስ ሰውኛ ስጋቸውን ሰደሩ፤ በዓረፍተ-ነገር አካ
ላቸውን ገነቡ፤ በአናቅጽት ከበረዶ የነጣ አእምሯቸውን አበለጸጉ፤ ከ መጽሐፍት ጉባኤ
ተደባለቁ፤ የመቃብር አፈር የሚያፈርሰው የመጽሐፍ ገፅ የሆነው ቃል ኪዳን ተጋቡ፤ከመ
ጻሕፍት ጋር ማህበር ተጣጡ፤ ድንግልናቸውን ከመጽሐፍት ጋብቻ ህይወታቸውን ከንባብ
አቆራኙ፤ ፈቃደ ስጋቸውን በፈቃደ ማንበብ ደፈኑ ፡፡
በትህትና
ህልውናቸውን ለመጽሐፍት አስረከቡ ፤
የንባብ ፍላጎታቸው አስ
ተውሎታቸውን አስፍቶ ጠንቃቃ አድርጓቸዋል ፤ ምግባረ ማዕዛቸው ጥዑምነቱ ተወድ
ሶላቸዋል ፡፡ ከ ከንፈር ንባብ ተቃርነው ወደ ልዕለ ሰብ ዘልቀው የቁሳዊነት ነፍስን የመታ
በይ ትዕቢትን ! በ አከበሯቸው ገፆች ፣ በተሻገሯቸው ምዕራፎች ከልለዋል ፡፡
የቀን፣
የወር፣ የዓመትና የዘመን ስያሜ ¡ ተርጓሚዎች የቀኑን ስያሜ ስያሜነት የወሩን
መጠሪያ ወርነት ከተፈጥሮ ዑደቶች ጋር አዋህደው ለማሳመን ፡ ቋንቋዎችን ይከፋፍታሉ
ምልክቶችን ብራናዎችን ይዘረጋሉ ፤ ቅርፅ አልባ ድንጋዮችን ያነጥፋሉ ከዋክብትን
ይመለከታሉ ፤ ቁጥሮችን ይደረድራሉ ፤ ሐዋርያትን ያጣቅሳሉ ፡፡ እኒህ ትርጓሜ አሳሾች
ወርሃ ታኅሣሥን የመሻት፣ የመፈለግ ፣ የመመርመር ፣ ሲጨመቅ የፍለጋ ወራት ሲሉ
ይተርጉሙታል፡፡ ወራቶች የራሳቸው የመሻትና የማግኘት ወይስ የፈለጉትን የማበ
ጀት ቀመር ያላቸው??
የታኅሣሥ
ንጉሥ
ይሄኛው
ታኅሣሥ ግን ይለያል ! ራሱ ታኅሣሥ ወር ሁነኛ ሰው ሻተ ተመኘ ወ/ሮ
ፀዳል ፈጠነ እና አቶ በላይ ከልካይን በፍለጋ አጣመረ፡፡ ተፈጥሯቸውንም አመራመረ፡፡
በወርሃ ታኅሣሥ በ 1936ዓ.ም የንባብ ፔርሙዳውን የታኅሣሡን ንጉሥ አንጋፋ ጋዜ
ጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይ 'ን ወለደ ፡፡
በቀድሞው
ሸዋ ክፍለ ሀገር በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ አቶ ጥላሁን በላይ ተወለዱ፡፡
ወላጅ አባታቸው አቶ በላይ ከልካይ በሥራ ምክንያት በ ሀገራችን በሚገኙ አውራጃዎች
ሲዘዋወሩና ሲሰሩ አብረው ተዟዙሯል ፡፡ ልጅ ጥላሁን የመጀመሪያ ትምህርቱን በአምቦ
የጀመረ ቢሆንም ፡ ብዙም ሳይቆይ በ አባቱ በአቶ በላይ የሥራ ቦታ ወደ ደብረ
ብርሃን መለወጥ ምክንያት ከ ቤተሰቦቹ ጋር ወደ ብርዳማዋ ደብረ ብርሃን መጡ፡፡
ልጅ ጥላሁን ትምህርቱን በደብረ ብርሃን ባጠናቀቀ ማግስት በመሀል ወላጅ እናቱን
እና ወላጅ አባቱን በሞት መላዕክ ተነጠቀ ፡፡
ወደ
መዲናች አዲስ አበባ በመምጣትም የህይወት ጉዞውን ከ አክስቱ ከ ወ/ሮ
የንጉስነሽ ከልካይ ጋር መሸመን ጀመረ፡፡ አቶ ጥላሁን በላይ የጋዜጠኝነት ምዕራፋቸ
ውን በ 1956ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሪፖርተርነት ሀ ግዕዝ ብለው እንደጀመሩ
ይወሳላቸዋል ፡፡
የ ንባብ ሞገድ
እንደ
አንጋፋ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ አይነት አንባቢዎች ግልብ የትውልድን ልቦና
ያነባሉ ፤ ያሉበትን ዘመን ያንሰላስላሉ ፤ ያለበቂ ነጥብ አንደበታቸው አይላቀቅም ፤
ምላሳቸው አይላወስም ፤ተተኪ የዘመን ቀለሞችን ይለያሉ፡ እንዲህ አይነት በ ሀሳብም
በመፍትሄም የበሰሉ ሰዎችን አንድ ሀገር በ 100
አመት ልዩነት ተንፏቃ ትወልዳለች፡ በሌላ
የሀገር ገፅ ጠንቅቃ ካልተጠቀመችባቸው ትማስናለች ¡ ሀገራችን ኢትዮጵያም መሲና
የመሆን ጉዞዋ፡ ወደ ማረጥ እርጅና እያጋዳለች ይመስለኛል ፡፡
ከመጽሐፍ
ትይዩ መጽሐፍ የሆኑ ሁለንተናዊ አምዶቻችንን ፡ አለማመስገን ፣ አለመጠ
ቀም ፣ ለማየት መጠየፍ ፣ ለመስማት መዘግነን ፣ በ እቡይነት ማጥቃት ፣መነሻ ምንጫ
ቸውን ከመቅዳት ተቃርኖ ተገትረን፡ ለማድረቅ መገፍተር ምን ይሉታል ? ምን ይሉናል ?
ለዚህ ድክመታችን
በጎ ምክንያት ይኖር ይሆን ??
ከ
ውዥምዥም ሰውነታቸው፣ ከ አይነ ግቡ መልካቸው ፣ከ ስርዓተ አለባበሳቸው
ተዋቅረን፡
ከ ቁጥብ አንደበታቸው የሚወጡ የቃላት ስብጥራቸውን ወደ ጆሯችን አን
ቆርቁረን ከልቦናችን አፍሰን፡ ከ ቀላ ሙያቸው የጋዜጠኝነት ልካቸውን ባንዳስስም !
ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ስለ አንጋፋ ጋዜጠኝነታቸው ፡ ከስራ ባልደረቦች ፣ ከሚያውቋ
ቸው ሰዎች ፡ ያሰባሰባቸውን ገላጭ አንደበቶች እስኪ አንድ ሁለት እያለን እንዝገን ፡፡
ጋዜጠኛ
ብርቱካን ሐረገወይን
/ የሥራ ባልደረባ /
ቤተ-
እውቀታችን
አንጋፋው
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይን የ የዜና ፋይል ክፍል ኃላፊ ሆነው ነው የማውቃቸው፡፡
አብዛኞቻችን ጋሽ ጥላሁን ነው የምንላቸው፡፡ በ 1985 ዓ.ም የዜና ክፍል ኃላፊ ሆነው ወደ
ኢትዮጵያ
ሬዲዮ መጡ ፡ለዜና ክፍላችን ጋሽ ጥላሁን እጅግ ወሳኝ
ነበር ፡፡
ዜናዎች
ምንም እንኳን ቶሎ ቶሎ በየጊዜው ተቀያያሪ ቢሆኑም በካበተ ልምዳቸው
ዜናዎችን በደንብ በመቅረጽና አርትኦት በማድረግ ዜና እንዴት እንደሚስተናገድ እንደ
ሚዘጋጅ ያሳዩን
ነበር፡በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በስፖርት አምድ ላይ ከፍተኛ ልምድ
ስለነበረው የትኛውም ዜና ለጋሸ ጥላሁን አዲስ አይደለም፡፡ ከቃላት አመራረጥ ጀምሮ
የጎደሉ ነገሮች እንዲሟሉ በማድረግ ዜናዎችን እንደየ ባህሪያቸው ነፍስ ይዘራባቸዋል፡፡
ከሥራው ጎን ለጎንም የመንገድ ቃላት እንዳንናገር እንድንጠነቀቅ ያግዘን ይረዳን
ነበር ፡፡
ምንም
ነገር ይቸግረን ከ ጋሽ ጥላሁን ነው የምናመሳክር የእውቀት ምንጫችንና
ቤተ- መጽሐፍታችንም ነበር፡፡ ከእጁ መጽሐፍ አይታጣም፡፡ ሙያውን በተመለከተ ራሱን
በአዳዲስ መረጃዎች ያድሳል ያበቃል ፡፡ ወደ ብሪቲሽ ካውንስል ሙያ ብሎ በመሄድ
BBC ምን ምን ፕሮግራሞች እንዳሉት በመጠቆም ይሄ ይሄ ፕሮግራም እንዳያመል
ጠን ተከፋፍለን መከታተል እንዳለብን ይመክረን ነበር፡ የዜና ክፍላችን የሚገጥመውን
የትኛውንም ችግር በመፍታት ረገድ ጋሸ ጥላሁንን የሚወዳደር አይገኝም ፡፡
ሴቶችን
በሚመለከት ጥናታዊ ጽሁፍ አዘጋጁ ተብሎ በወቅቱ ወ/ሮ ነፃነት አስፋው
ነበረች ከላይ ሆና የምትመራን፡ጋሽ ጥላሁን ያቀረበላትን ጥናታዊ ጽሁፍ ከተመለከትች
በኃላ፡"እንዲህ አይነት ሰዎች አሉ ወይ እዚህ አገር ላይ?" ምን አይነት እውቀት ነው? ነበር
ያለችው፡ ያልተደገመ ሌላ ቦታ ላይ የማይገኙ አዳዲስ ነገረ ሴት ጥንቅሮችን ነበር ጥና
ታዊ ጽሁፉ ላይ ያቀረበው ፡፡
መባከን የሌለበት ሰው. . .
ከ
ስራ ባልደረባዬ ከአቶ
ፈቃደ የምሩ ጋር ተነጋግረን ጋሽ ጥላሁን ጡረታ ሲወጣ
ይህ ሰውዬ መባከን የሌለበት ሰው ነው እንጠቀምበት ብዬ ባቀረብሁት ሀሳብ ተስማ
ምተን ከ እኛ ጋር እንዲቀጥል ተደረገ፡፡ በ ኮንትራት መልክ ፡፡ ለ 7 ዓመታት ከሰራ በኃላ
የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜና አገልግሎት የበለጠ እንዲያጠናክር በሚል ወስደውት እዚያም አገልግሏል፡፡
ጋሽ
ጥላሁን እንደ አባት እንደ መምህር ሆኖ በጣም የሚያግዘን ትልቅ ሰው ነበር
በ 1996 ዓ.ም ግርጌ በ 1997ዓ.ም ራስጌ አካባቢ በኮንትራት የሚሰሩ ሰዎች መሄድ
አለባቸው ሲባል ከስራ ተሰናበቱ ፡፡
የ ኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር የተቋቋመው ጽ/ቤት የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ
ሆኘ ስመደብ ፡በርካታ የጽሁፍ ስራዎች ፣ ርዕሰ- አንቀጾችና ንግግሮች የሚፃፉ ስለነበሩ
የሚያግዝሽ ሰው አምጭ ስባል ጋሸ ጥላሁንን ነበር የወሰድሁት፡፡ ሁለት አመትም አገልግሏል ፡፡
አዳዲስ
ልጆች ሲቀጠሩ ሳይታክት ያሰለጥን ነበር፡ ጋሽ ጥላሁን ሩህሩህ ፤ ፀጥ ያለ
እንደ ሰው ብዙ የማይናገር ፤ ስራዎችን በስርዓት የሚመራ ፤ የሚገርመው አንዳንድ
ጊዜ የምሽት 4:00 ዜና ተነቦ እስኪያልቅ ይጠብቃል፡፡ የማንም ኃላፊ ይሄን አያደርግም፡፡
በነጋው ያው እንደተለመደው ነው በሰዓቷ ይገኛል- አይቀርም፡ ጠንካራ ከሚባሉ ሰዎች
አንዱም አርአያም ነበር፡ ሀብታም የመረጃ ምንጭም ነው ፡፡
አዳዲስ አሰራሮችን መትከል
በሀገራችን
ኢትዮጵያ በተለይ በድርጅት መዋቅር የአሰራር መስመር ውስጥ ከህ
ዝብ ጥቅም የበለጠ የቆዩ የቢሮ ዘየዮች ይከበራሉ ! የቢሮ መመሪያዎች በፈሰሱበት
የአሰራር
አድማስ ለብዙ ዘመን ተባጅቷል፡ በዚህም ለአዳዲስ ስራን መከወኛ ሀሳቦች
ማበረታቻም ማስተናገጃ ቦታም የለም፡፡ አብዛኞች በሁሉም እንቅስቃሴ ረገድ የተቆለ
ፈባቸው
ቢሮዎች ናቸው፡፡ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ይህንን የቁልፍ ድንበር ጥ
ሰዋል
ለ አሰራር የሚመቹ ሀሳቦችን ወደ መሬት በማውረድ ተግብረዋል ፡፡
ለረጅም
አመት የኖረው የዜና ፋይል ዳብሮ የቆየ ቢሆንም የበለጠ ተደማጭ እን
ሆን ለማድረግ ደግሞ ጋሽ ጥላሁን ካስተዋወቃቸው አዳዲስ አሰራሮች መካከል፦
፦
ምሽት ሁለትና አራት ሰዓት ዜናዎች በቀረፃ ነበር የሚተላለፉት በጋሽ ጥላሁን አማ
ካኝነት
የምሽት ዜናዎች
በቀጥታ/ live /እንዲቀርቡ ሆነዋል፡፡
፦ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ፈጥረዋል ለምሳሌ ፦ የሳምቱን ታላቅ ዜና ፤ የንዋይ ዘገባ፡፡
፥ ቋንቋን በተመለከተ ከ አማርኛ ቆንቋ ውጭ ያሉ እንደ ኦሮምኛ ፣ ትግርኛ ፤ አረብኛ ፤
አፋርኛ
፤ ሶማሊኛ እና ሌሎችም ተበታትነው ነበር በየክፍላቸው የነበሩት እናም ጋሸ
ጥላሁን ከእኔ ጋርና ከሌሎች የስራ ባልደረቦች ጋር በመመካከር " ዜና ማዕከል " በ
ሚል እንዲደራጅ በማድረግ ረገድ የዜና ክፍሉ የዜና ስርጭቱ ያማከለ እንዲሆንትልቅ
አስተዋፆኦ
አበርክቷል ፡፡
፦ ዜና ማዕከል ከ ዜና ፋይል ጋር ተዋህዶ ተበጣጥሶ የነበረው የዜና አሰራር የበለጠ
ወጥነት
እንዲኖረው ማኔጅመንቱ ይህንን እንዲያስተካክል ከፍተኛ ሚና ነበረው ፡፡
፦ የዜና አሰራር እንዴት ይሁን የሚሉትን በማማከር መመሪያዎችን በማዘጋጀት የ አን
በሳውን
ድርሻ ይወስዳሉ ፡ በጋሸ ጥላሁን ሞት
እንደ አጠቃላይ የዜና ክፍሉ ትልቅ
ነገር
እንዳጣ እቆጥረዋለሁ ፡፡
አውራ አድመኞች
ነገደ በረከት ስምዖኖች
አንጋፋ
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይን እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ያላቸውን የካበተ
ልምድ ዘርፈ ብዙ እውቀት እኛም ትውልዱም መጠቀም ይችል ነበር ! የኢትዮጵያ
ሬዲዮና ቴሌቭዥን ከተዋሃደና ወደ አንድ ከመጣን በኃላ ከ 2001 ዓ. ም ጀምሮ በ
ሚሰሩ ስራዎች ላይ ድክመቶችን ሳይ " እባካችሁ ልምድ ያለው ሰው ይምጣና ይደግፈን" ስል የበረከት ስምዖን ምልምል ነገዶች በየ ሚዲያው ከተዳቀሉ በኃላ ነገሮች
እጅ እግር ሆኑ ኤዲተር ተብለው ተቀምጠው አቅሙም ስለሌለ ምኑን ከምን ያድር
ጉት / በእነሱ አልፈርድም ! ከላይ ባሉት ሰዎች እንጅ,,/ እናም ልምድ ያለው ሰው
አለ ይምጣ ብዬ ስጠይቅ፡ሰለሞን የሚባል ስራ አስኪያጅ የነበረ " ያረጀ ያፈጀ ሰው
አንፈልግም
" በማለት ምላሽ ሰጠ ፡ ከዚያም ስራው እየሸረሸረ እየተቦረቦረ እየወደቀ
ሲመጣ ከስንት
ጊዜ ቆይታ በኀላ
አቶ ሰለሞን " ያንን ያልሽውን ሰውዬእባክሽን አም
ጭልኝ " በማለት ጠየቀየኝ ፡ በ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ልምድ ያለው ሰው እንዲመጣ
የማይፈልጉ
አውራ አድመኞች ስለነበሩ ጋሸ ጥላሁን በጡሮታ ተገልሎ እንኳን ገብቶ
የመስራት
እድሉን አከሰሙት ፡፡
ጋዜጠኛ ጌታሁን ንጋቱ
" ፅ ሁ ፍ
የጉልበት ሥራ አይደለም "
ከ
1993 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ስገባ አውቃቸዋለሁ እስከ መጨረሻው
እስከ ወጣሁበት ድረስ፡ጋሽ ጥላሁን አንጋፋ ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆኑ ጠንቃቃ አስተማ
ሪም ነበሩ የጋዜጠኝነት ሀ ሁንያስተማሩኝ እሳቸው ናቸው፡ አሁንም በጣም ትዝ የሚ
ለኝ! የመጀመሪያ ሪፖርቴን ወጥቼ ስመጣ ብርቱካን ሐረገወይን ኸላፊያችን ነበረችና
ኤዲት አድርጊኝ ስላት " ኣ ኣ ማንም ይህን ስራ አይሰራውም ጋሽ ጥላሁን በላይ ብቻ
ናቸው " አለችኝ፡ ወደ ጋሽ ጥላሁን አመራሁ ፡ ሪፖርቱን ስሰራ እኔ እንዳየሁት ፣ እኔ እንደተመለከትሁት፡ እያልሁ ነበር የፃፍሁት፡ ጋሽ ጥላሁንም " ጌታሁን ና" ሲሉኝ አቤት አልኀቸው፡ " ይሄ ዜና ያንተ አይደለም የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና ነው
እንዲህ እየተባለ አይፃፍም
"አሉኝ
፡፡ ጋሽ ጥላሁን አርትዖት ሲሰሩ ነግረውህ ነው ፡ እንደዚህ አይባለም ለምን?ከነ ምክንያቱ ይነግሩህና ያስረዱሃል ፡፡
በጣም
ጨዋ ልታይ ልታይ የማይሉ እውቀት ያላቸው ቀሪ ሀብታቸውም መጽሐ
ፋቸው ነበር፡፡ የህይወት ታሪካቸውን ለመስራት ብዙ ጊዜ ሞክረን እየሸሹ እንቢ ብለውን ፡ ከ እነ ትልቅነታቸው ከ እነ አባትነታቸው በመጨረሻ አጣናቸው ፡፡
ጋሸ
ጥላሁን እሳቸው ከአስተማሩኝና ከነገሩኝ ውጭ የሰጡኝ መጽሐፎች ብዙ ነገሮ
ቼን ሞልተውልኛል ፡አስተማሪዬአባቴ ነበሩ፡ ለተወካዮች ምክር ቤት ዘገባ ደርሰን ስን
መጣ ሊግ ለማውጣት በጣም ስንጨነቅ ይመጡና "ተነስ ቡና ልጋብዝህ " ይሉና ቀስ
ብለው ይዘውኝ ይወጣሉ እያወሩህ ይሄዳሉ፡" የት ውለህ መጣህ?" እዚህ ቦታ?" ምን
ምን ተባለ ?" እንደዚህ እንደዚህ ተባለ እያልን እያወራን እንሄዳለን ቡና እየጋበዙ ይሰ
ሙህና " ዜናውን እኮ ጨረስኸው ምን አስጨነቀህ ? ለእኔ የነገርኸኝን በል ፃፈው "
ይሉሃል እንደዚህ አይነት ሰው ነበሩ ፡፡
አንጋፋው
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ " ጽሁፍ የጉለበት ሥራ አይደለም " የሚል
በተግባራዊ እውቀት የተፍታታ ንግግር ነበራቸው፡ ዛሬ እኔም ጋዜጠኛ ሆኘ ጋዜጠኞ
ችን " ጽሁፍ የጉልበት ሥራ አይደለም " እላቸዋለሁ፡ መልካም ውርስ አይደለምን!!
ስታይል ቡክ
የትኛውም
ሚዲያ ያዘጋጀ እየመስለኝም፡ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ መርተውት
በተቋቋመ ቡድን ከ 300 ገፅ ባላይ ያለው ስታይል ቡክ ጽፈዋል፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ
እንዴት እንዳደረው አላውቅም ፡፡
ጋዜጠኛ የኔነህ ከበደ
በጣም ሰሩብኝ በአጭር ጊዜ አመኑብኝ
የኛ ዘመን ኢንተርኔት
በ
1989 ዓ.ም እሳቸውን ማወቅ ጀመርኩ፡፡ እዚህ አቡነ ጴጥሮስ ስቱዲዮ በያኔው በጥቂት ግለሰቦች ዝወራ ስር ተጠቅሎ የነበረ ቢሆንም በሙያ ብቃታቸው ፕሮግራሙን በህዝብ ተደማጭነት እንዲኖረው ዜና ፋይልን ከፍ አድርገዋል ፡ ከሌሎች የስራባልደረቦቼ ጋር ፈተና ወስደን በ ፍሪላንሰርነት ነበር የተቀጠርነው የመጀመሪያውን ስልጠና የሰጡን ጋሸ ጥላሁን ሲሆኑ ከመምህር በላይ ናቸው ፡፡
ጋሸ
ጥላሁን የልዩ ባህሪ ባለቤት ነበሩ አይታክቱም ፤ ጋዜጠኛው በሽፍት ሲሰራ
እሳቸው በቀን ከ8:00 ሰዓት በላይ ይሰራሉ ፤ ሁለገብ ችሎታ አላቸው፤ አርትኦት ሲያ
ደርጉ በዚያን ጊዜ ቴፕ ሪከርደር ነበር ፡፡ከወጣት በጣም በፈጠነ ይከተክቱት ነበር ፤
ስምሪት ውለህ ስትመጣ እንዲሁ እንደዘበት አዋዋልህን ይጠይቁሃል የሪፖርትህን
አስኳል ፈልገው ያገኙና አቅጣጫ ያመላክቱሃል፤ ቅዳሜ ሰንበት የሚባል ነገር የለም
ከ እሁድ እስከ እሁድ ስራ ነው፤ ሥራ በሌላቸው ጊዜ ደግሞ ከጠዋት እስከ ማታ
መጽሐፋቸውን ዘርግተው ታገኛቸዋለህ ፡፡
ጋሸ
ጥላሁን ውስብስብ አፃፃፍን ይችሉታል ሆኖም ግን " አፃፃፍህ ውስብስብ
መሆን የለበትም ሬዲዮ የጀሮ እንደመሆኑ መጠን አጭርና ግልፅ በሆነ ቋንቋ መገለፅ
አለበት" ሲሉ ያመላክቱኛል፡ በጣም አስገዳጅ ካልሆነ ውስብስብ አፃፃፍ አትጠቀም
ይላሉ ፡፡
ተ ቋ ም
ጋሸ
ጥላሁን በላይ ይመክሩሃል ያስተምሩሃል የዚያን ጊዜ እንዲህ ኢንተርኔት አልተ
ስፋፋምና ግራ የገባንን ነገር ከነ ምሳሌው፣ ከ እነ ታሪኩ፣ ከነ ምዝሩ ዝርግፍ ያደርጉ
ታል፡፡ የእኛ ዘመን ኢንተርኔት አንጋፋ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይ ነበሩ፡፡
እኔ
ከ አንድ ዩኒቨርስቲ ማስተርሴን በኢንተርናሽናል ሪሌሽን / አለም አቀፍ ግኑኝነት/
አግኝቻለሁ ፡ አስተማሪየ ተቋሜ የምለው ግን ጋሽ ጥላሁን በላይን ነው ፡፡ በራሳቸው
የሙሉ ትምህርት ቤት ተቋም ናቸው ያልተዘመረላች አይነት ሰው ፡፡
በ
እሳቸው ልክ የሥራ ባህል ያለው ማግኘት ያደክማል የማይታክታቸው ታላቅ ሰው
በ ስራቸው ያሉ ሰራተኞችን በደንብ ይመራሉ ያበቃሉ፡ የዲሲፕሊን ግድፈት አይፈቅዱም
ወጣ ያለ ባህሪ ያለው ከተገኘም ወዲያው ረድፉን ይይዛል፡ በመጀመሪያ በጣም ሰሩብ
ኝ በአጭር ጊዜ አመኑብኝ ከአንጋፋዎቹ ተርታ የከተተኝ የእሳቸው ልፋት ነው ፡፡
ጥሮታ
ከወጡ በኀላም መጽሐፎች የሚሸጡበት የአርከ ሱቆች የሚባሉት ላይ
ነበር ውሏቸው ፡፡
ቤተሰባዊነት
ጋዜጠኛ
ጥላሁን በላይ ዘላለማዊ የጋዜጠኝነት ኪዳን የሆነው የማንበብን መልክ
ለጋዜጠኞች እድሜ ልካቸውን ሲያስተጋቡ ኖረዋል ፡፡ በምድራዊ ህይወታቸው የማንበብ
ን ድንቅ አላማ ለማሳወቅ ተግተዋል፡፡ለዚህ ደብዛዛ ክፍለ- ህዝብ በተለይ ለመጪው ተተ
ኪና ወራሽ ትውልድ የማንበብን ስፋትና ርዝመት ከፍታና ጥልቀት አሳይተዋል ፡፡
አንጋፋ
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይን ለመግለፅ፡ ሰብአዊ ቋንቋ ቢቸግርም
ከ ቤተሰባቸውና ከረዥም ጊዜ የሥራ ባልደረባ ጓደኛቸው አንደበት ጋዜጠኛ ጥላሁን
በላይን እንደዚህ ነበር ይሉናል ፡፡
ተሾመ ንጋቱ
/ የሥራ ባልደረባ የነበረ /
አንድን
የጭነት መኪናን ስንት በየአይነት መጽሐፍ ይሞለዋል
,?
ጋዜጠኛ
ጥላሁን በጣም ጠንቃቃ አንድ ዜና ከመቅረቡ በፊት ደግሞ ደጋግሞ የሚ
መለከት፡ የሚተማመንበት ሰው ካለ ሰልሶ የሚያሳይ ነበር ፡ ወቅቱ ደግሞ የደርግ ዘመ
ነ መንግስት ነውና ፡ የደርግ ዘመነ መንግስት ባህሪው ይታወቃል ትንሽ ሳት ካለህ አፀፋ
ው ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡ የጋሸ ጥላሁን ባህሪን በዚህ ዘመን አገኘዋለሁ
ተብሎ የሚገመት አይደለም፡ ሌሎችም
ከ እሱ እንዲማሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ፡፡
ከ
ጥንቃቄ ባሻገር እያበሳጨኸው እሱን በማይመች ሁኔታ እየሰራህ እንኳን ታግሶ
ስህተትህን ለይቶ ስለሚያውቅ ውስንነትህን ሊያስተምርህ የሚተጋ ሰው ነው፡ አንዳንድ
ኤዲተሮች አሉ የሞተ ዜናን ነፍስ ሚዘሩ! ጋሽ ጥላሁን በላይ ግን ከሁሉም ቁንጮ ነው
የሞተ ዜና ላይ ነፍስ ዘርቶ ህይወት አዋህዶ ያስውበዋል ፡፡
ከሁሉም
በላይ ግን ጋሽ ጥላሁን በጡረታ ከተገለለ በኃላ በ አብዛኛው አገኘው የነ
በረው መጽሐፍ ተራ ነበር ፡ እጅግ እጅግ አንባቢ ከሚባሉ ሰዎች ተርታ ይሰደራል፡እኛን
ምን ምን መጽሐፍ ማንበብ እንዳለብን ይጠቁመናል፡፡ አንድ ጊዜ ከረጅም አለመተያየት
በኃላ አራት ኪሎ አግኝቸው ዳግማዊ አፄ ሚኒልክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያሉ ካፌዎ
ች ተቀምጠን ስንጫወት፡ያነሳልኝ የነበሩ ነጥቦች እጅግ የሚገርሙ ናቸው፡የሰዎችን አእ
ምሮ የሚያነብበት መንገድ ፤ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልፅበት አተያይ ፡ በእርግጥም
ጋሽ ጥላሁን አንባቢና በጣም ጥሩ ተገንዛቢ ነበር ብያለሁ ፡፡ እንደተነገረኝ ሁለት አይ
ሲዙ መኪና ሙሉ መጽሐፍት ከቤቱ ተሰብስበው ተጭነው ነው የወጡት ፡፡
እሙሀይ የንጉስነሽ ከልካይ
/ አክስት /
ጥላሁን
ጥሩ አመል ያለው ትንሽ ትልቅ የማይል የሁሉንም ጥያቄዎች አክብሮ የሚመ
ልስ፡ መጽሐፍ ይዞ ይመጣል፡፡ ከመጽሐፍቶቹ ጋር ያወጋል እንጅ ከ አዋቂ ጋር አያወራም
ከ ትንንሽ ልጆች ጋር በመጠኑ ይጫወታል አንብቡ መጽሐፍ እገዛላችኀለሁ ይላቸው
ነበር ፡፡፡
ምሥራቅ ግዛው
/ የአክስት ልጅ /
ሁለተኛ አባቴ
በጣም
ነው ሰው የሚያከብረው፡፡ አክብሮቱ ደግሞ ትንሽ ትልቅ አይልም፡ ትንሽ ልጅ
ቢጠይቀው የሚሰራውን አቋርጦ ጥያቄውን በሚገባ አብራርቶ ይመልሳል ፡፡መቆጣት
አይፈልግም፡፡ ካጠፋህ ደግሞ ለምን ድርጊቱን እንደፈፀምህ ምክንያቱን ይጠይቅሃል
የቤተሰብ አክብሮቱ ድንቅ ነበር ፡፡
ጋሸ
ጥላሁን ለእኔ ሁለተኛ አባቴ ነው፡፡ በምንም መልኩ እኛን እንዲለየን አይፈልግም
በደስታችን በሀዘናችን ጊዜ አብሮን አለ፡፡ ልጅ ማድረግ የሚፈልገውን ሁሉ አባቱን እን
ደሚጠይቀው እኛም ጥላሁንን ጠይቀን ይህ ቀረብን የምንለው የለም ፡፡ ሁሉንም እኛ
ን በሚጠቅም መልኩ አድርጎልናል ፡፡
አንድ
አንድ ነጥቦች ላይ ስናወራ በደንብ አብራርቶ ያስረዳናል፡፡ የማናውቀው ግልፅ
ያልሆነልንን ስንጠይቀው በደንብ ጠለቅ ብሎ ትንታኔ ይሰጠናል ፡፡ ከቤተሰብ ጋር ጨዋ
ታ ሲኖር ይጫወታል፡፡ እንግዳ ከቤት ከመጣ ግን ሰላምታ ካቀረበ በኃላ መጽሐፉን ይዞ
በኃላ ቤት ይወጣና በረንዳላይ በመሆን ያነባል፡፡ ከሌላ ሰው ጋር ደብለቅ ብሎ የመጫ
ወት ባህሪይ አልነበረውም ፡፡ወደ ቤቱም ሲሄድ ደስ ብሎት ነበር የሚለየን ፡፡
ህመሙ
ይህን ያህል ተገማች ጠንካራ አልነበረም፡፡ እንደውም እነሳለሁ የሚል ተስፋ
ነበረው፡፡ እንዲህ ለሞት ያደርሰኛልን አላሰበም፡፡ መጨረሻ አካባቢ እየደከመ
ሲሄድ
ያስቀመጠው መጽሐፍ አሳሰበው ፡፡
ፍሬ ህይወት ግዛው
መልከ ፀዴቅ, [27-Feb-22 10:09 PM]
/ የአክስት ልጅ /
ዋናው
አንች አንብቢ እንጂ. . .
ከ
ልጅነቴ ጀምሮ ስሄድ ሲመጣ እኛ ልጆችን ነበር በጣም የሚቀርበን ከቤቱ ወደ
እኛ ቤት ሲመጣ ከትልልቅ ሰዎች ጋር ሳይሆን ከህፃናት ጋር ነበር ተግባቦቱን ያዘነብል
የነበር፡፡ የምማርበት መጽሐፍቶች ይሰጠኛል" ምን ያስፈልግሻል ? የሚያስፈልግሽን
ጠይቂኝ ይመጣልሻል ዋናው አንቺ አንብቢ እንጂ " ነበር የሚለኝ ፡ እዚህ ወደ እኛ
ከመጣ በኃላ እንደ ከዚህ ቀደሙ አንብቡ አንብቡ ይለን ነበር፡፡
አሁን
መጽሐፍቶቹን ሳያቸው ያላነበበው የመጽሐፍ አይነት የለም፡ ከ ሀይማኖቱ ፤
ከፖለቲካው ፤ ከፍልስፍናው ፤ ከኢኮኖሚው፤ ከ ስርዓተ ፆታው ፤ . . . የሌለው
ነገረ
የለም ለእኛም ያወረሰን ነገር ቢኖር" መጽሐፍትን አንብቡ" የሚለውን ነው ፡፡
ቤዛዊት አብርሃም
/ የአክስት ልጅ /
የ
ንባብ ን ህልውና ማስረፅ
ከ
ልጅነታችን ጀምሮ እቤት ሲመጣ መጸሐፍ ይዞልን ይመጣል ፡ በመጽሐፍ ነው
የምናውቀው ፡ ከ እድሜና ከአእምሮችን እድገት ጋር የተማጠነውን መጽሐፍ ይዞ
ልን ይመጣል ፡፡
በመጣ
ቁጥር አንድ አንድ መጽሐፍ ይመግበናል፡፡ እኔንም እህቶቸንም እንድናነብ
ይገፈትረን ነበር ፡እዚህ መጥቶ ከ እኛ ጋር መኖር ከጀመረ በኃላ ከ ትምህርታዊ እገዛ
ዎች ተያያዥ የምንከራከርባቸው ነጥቦች ነበሩ ፡ ያስረዳኛል ያሳምነኛልም ፡ የሚያ
ነባቸው መጽሐፍቶች ጥልቅ ግንዛቤ በውስጡ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ እንደነገረኝ
ከሆነ መጽሐፍ ኤዲት ያደርግ ነበር እናም አንዳንዴ የእኔንም መጽሐፍ ኤዲት ታደርግ
ልኛለህ ስለው!" ደክሞኛል አሁንኳ አልችልም ዝቅ ብሎ መፃፍ" ይልና ይመልስልኛል
አንድ ነገር ላይ እምነት ስትጥሉ ጭፍን ነገር እንዳይኖር በትክክል ፈልጋችሁ ማግኘት
አለባችሁ ይለን ነበር፡፡፡
ከዚሁ
ማየት ስንጀምር በእኛ አእምሮ ላይ የመጽሐፍን ትልቅነት አሳውቆናል፡ ይህ
ማለት እሱ ቢያልፍም የእሱ ምኞት ከንቱ አልቀረም በ ተተኪ ትውልድ ላይ የንባብን
ህልውና አስርፆብናልና፡ ፡
ቴዎድርስ ግዛው
/ የአክስት ልጅ/
ህያዋን
ናቸው በ እርግጥሞ
ጋሸ
ጥላሁን ለእኛ አንደ አባት እንደ ወንድም እንደ ጓደኛችን ነበር ፡ ለእኛ የነበረው
ቀረቤታ መጫወት ከፈለግህ ያጫውትሃል መቆጣትም ከፈለገ ከዳበረው እውቀቱ መዞ
በምክንያታዊነት ያስረዳሃል ፡፡
ጋሸ
ጥላሁን እኛ በጣም ህፃን እያለን ነበር ትምህርቱን የጨረሰው ግን በልጅነት ል
ቦናየ የማስታውሰው ቡልጋሪያና ጀርመን ሄዶ ሲመለስ ፡ እኛ እንደ ልጅ ፍላጎት ለህፃና
ት የሚገባ ነገር ይዞልን ይመጣል ብለን ነበር ፡ የሆነው ግን ሌላ ነው ኤርፖርት ልንቀ
በለው ስንሄድ በፌስታሎች ሙሉ መጽሐፍቶችን ይዞ መጣ ፡ ምነው ለእኛ ለልጆች የሆ
ነ ነገር ይዘህልን ያልመጣህ ስንለው ፡ ይሄው! "ይህ መጽሐፍ ማለት እኮ የማያልቅ ነው
ልብስ ጫማ ባመጣላችሁ ወራቶችን ሳይሻገር ያልቃል " ይለን ነበር ፡ በእርግጥም
ያለው ነገር ዛሬ ሆነን በማስተዋል ልቦና ስናየው ትክክል ነው፡ ያኔ ልብስ ጫማ ቢያ
መጣልን ኖሮ ዛሬ የት እናገኛቸው ነበር? መጽሐፎቹ ግን ዛሬም አሉ ህያዋን ናቸው፡፡
ከመጽሐፍ
ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ ዝም ብላችሁ ከምትቀመጡ ከምታወሩ
አንብቡ ቢያንስ በቀን አንድ መስመር ብታነቡ በወር ሲጠራቀም 30 ረድፍ ይሆናል የወ
ራቶች ሲጠራቀሙ ወደ መጽሐፍ ይቀየራል ፡ የግድ መጽሐፍ ስላልወደዳችሁ ሳይሆን
ባነበባችሁ ቁጥር በንባቡ ውስጥ የምታገኟቸው አዳዲስ ሃሳቦች መጽሐፍ ማንበብ እ
ንድትወዱ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፡ ያገኛችሁትን ነገር የሚነበብ ከሆነ ብታነቡት አይጎ
ዳችሁም ይለን ነበር ፡፡
ከ
ጋሸ ጥላሁን ትዕግስቱን ክፉ አለመናገሩን የቀሰምን ይመስለኛል ከመጽሐፍቶቹ
ጎን ለጎን ፡ በታምር ከ አፉ ክፉ አይወጣውም ነበር፡፡
መጽሐፉን
እኔ እና እህቴ ከቤቱ ሄደን ስናመጣው ከዋናው ሳሎን ገብተን ወደ መኝታ
ክፍሉ የሚሄድበት መንገድ የአንድ ሰው መተላለፊያ ጠባብ መንገድ ነበር ያለችው፡፡
ሌላው ክፍት ቦታ ፣ ሶፋው ፣ ብፌው ፣ቁም ሳጥኑ ፣ በሙሉ መጽሐፍ ነው የደረደረበት
የሚገርመው ልብሶቹን መሬት አስቀምጦ ቁም ሳጥኑን በመጽሐፍ ነበር የሞላው ፡፡
3,500 መጽሐፍቶቹን
አምጥተን ስናያቸው፡ አይደለም መቀደድ አንድ ገፅ እንኳን
አልታጠፉም፡ መጽሐፍቶቹ ብል የበላው የለ የቆሸሸ የለ በሙሉ አዲስ ናቸው ፡፡
መጨነቅ መጠበብ
እድሜ
ዘመኑን ያጠራቀመው መጽሐፍ ለ ጋሽ ጥላሁን ቀሪ ሀብቱ ነው! ብዙ ገንዘብ
ወጥቶባቸዋል ፡ አንዳንዶች መጽሐፍትም የማይገኙ ናቸውና ይህን ሁሉ መጸሐፍ ምን እና
ድርገው ብለን ተጨነቅን፡ እንደውም ብዬ መጽሐፍ ሻጮች መደብር አከፋፍለን ሽያጭ
ባልሆነ መንገድ መጽሐፍ ሻጮች በሚመቻቸው አቅጣጫ ለህዝቡ እንዲያከፋፍሉ የሚ
ል ሀሳብ ሁሉ አሰብን፡የአክስቱ የእሙሃይ የንጉሥነሽ ከልካይ አንድ ነገር ሳልሆን መጽሐ
ፎቹ መላ ይበጅላቸው ውትወታ የጠዋት ማታ ማሳሰቢያነትን አልፎ መጠበብን ወልዷል፡፡
ዘለግ
እንበል
ስንጠብ
ከ ኢትዮጵያ፤
እጃችንን ስንከነዳ ከምስራቅ አፍሪካ፤ አንቧትረን ገደም
ስንል ከ አፍሪካ ወደ ደመና ስንመጥቅ ከ ዓለም አንጋፋ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይን
ብናተያያቸው ከ አለም የበጎ እውቀት መዝገብ ላይ ይሰፍሩ ነበር ፡፡
ግለሰብ
ለተቋሞች ተቋም
ሲሆን
የ
አንጋፋ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይ ቤተሰቦች ከ ጥብቅ ጓደኞቹ ጋር ሆነው
መከሩ
! ተዘካከሩ በመጨረሻም በቁጥር
ከ 3500 በላይ የሚሆኑ መጽሐፎችን
ለተቋማት
ለማከፋፈል ተስማምተው ወሰኑ፡ መጽሐፎችንም በየ ፈርጅ ፈርጃቸው
ሰትረው
መጽሐፉ ለሚገባቸው ተቋማት አከፋፈሉ፡ ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ለተቋ
ሞች ተቋም
ሆናቸው ፡፡
መስተዋወቂያ
/ መጽሐፍትን
እንደ ሰብል መሰብሰብ /
አክብረው
መጽሐፍ ከለገሱት ፤ ነገን ይጠቅማል ብለው ቀልቡን አንብበው ከመረ
ረቁት ፤ የንባብ ህልውናን ለማስቀጠል ለልጆች ካበረከቱት መጽሐፎች ውጭ ከቤታቸ
ው እንደ ሰብል የተሰበሰበ ሙሉ ቤቱን የተጠመጠመ 3,500 የመጽሐፍ ተራራ ተገኝቷል
ይህ እውቀትን የመጠማት! ሙያን የማስከበር ተጋድሎ የምኝታ አልጋቸውን ሳይቀር
ተጋርቷል ነገረ ሄዋንንም ተክቷል ፡፡
አንጋፋው
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይ ፡ የጋዜጠኝነት ምዕራፋቸውን
ታኅሣሥ
19/04/ 1956ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሪፖርተርነት የጀመሩት ፡ የካቲት 11 /06/
1961 ዓ.ም ስፖርት ፋና ሳምንታዊ ጋዜጣ በአዘጋጅነት ሰርተዋል ፡፡
በኢትዮጵያ
ዜና አገልግሎት በአዲስ አበባ ዜና ዝግጅት ክፍል ዋና አዘጋጅ ሆነው ካ
ገለገሉ በኀላ መስከረም 25 /01/ 1986 ዓ.ም
ጀምሮ በኢትዮጵያ ድምጽ መምሪያ በ
ኢትዮጵያ ሬዲዮና
ቴሌቭዥን ድርጅት በዜና ፋይል በቅንነትና በታማኝነት በጡረታ እስ
ከወጡበት ድረስ አገልግለዋል ፡፡
ከ
የካቲት 1974 እስከ ሰኔ 1974 ዓም
በ ሀንጋሪ ፤ ከ ሚያዝያ 1978 እስከ ግንቦት
1978 ዓ.ም
በዲሞክራቲክ ጀርመን የጋዜጠኝነት ስልጠና ወስደዋል ፡፡
አንጋፋ ው
ጋዜጠኛ ጥላሁን በላይ ከልካይ ባደረባቸው ህመም ምክንያት መጋቢት
17/ 07/ 2013
ዓ.ም በ 77 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ለዚህ ትውልድ ስነ አርአያ ሙያዊ ሰብዓዊ ጉዟቸውን እናስተዋውቅ እናወርሳለን ፡፡
መዝጊያ ይህ መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ሀሳብ የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ጋሽ ጥላሁን በደቀመዝሙሮቻቸው የተመሰከረላቸው ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ ሰውነታቸው ከአንባቢነታቸው አሀዱ ይላል፡፡
ስለሚያነቡና ስላነበቡ አይስቱም ነበር፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ያላቸው ግንዛቤ የሰፋ ስለነበር ለሚጠየቁት ጥያቄ አንድም መልስ አያጡም፡፡
በ77 አመታቸው ህይወታቸው ያለፈው አንጋፋው የሚድያ ሰው ጋሽ ጥላሁን ኢትዮጵያ ሬድዮ እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሰሩ ሰዎች
ሁሉ ግዜም ይመሰገናሉ፡፡ እንደ ቀዳሚ ባለውለታም ይቆጠራል፡፡ በቀላሉ የማይጠፋ አሻራ ያኖሩ በመሆናቸው አዲሱ ትውልድ በኩራት ያነሳቸዋል፡፡ አቶ ጥላሁን በላይ ከሁሉም በላይ ከመናገርና
ከመጻፍ አስቀድሞ ማንበብ ግድ ነው የሚለውን የጸና ኣቋማቸውን በሰፊው ሲያንጸባርቁ ኖረዋል፡፡ በዚህም እምነታቸው ብዙዎች ላይ በጎ
ተጽእኖ ፈጥረዋል፡፡ ስለ ጋሽ ጥላሁን ግን ብዙ ሲጻፍ አናይም፡፡ ሚድያዎች የሄዱበትን መንገድ አልነገሩንም፡፡ የሚድያ ሰው የአቶ
ጥላሁን በላይ ስራ ግን ዛሬም የብዙዎችን የአስተሳሰብ እየቀየረ ይገኛል፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እንደ አቶ ጥላሁን በላይ አይነት ሰዎች መዘከር አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም አክብሮታችን ለአዲሱ ትውልድ ለማሻገር
እነሆ ታሪካቸውን ለክብር መዝገብ ላይ አስፍረነዋል፤፡
/ ይህ ግለ-ታሪክ የአዲስ ሚድያ ኔት ወርክ ስለ አቶ ጥላሁን በላይ የሰራነው ዘገባ መነሻ በማድረግ የተሰራ ነው፡፡
በተጨማሪም የአቶ ጥላሁንን ቤተሰቦች በማነጋገር በቂ ሰነዶችን በማየት
የቀድሞ ባልደረቦቻቸውን በማነጋገር የተሰናዳ ግለ-ታሪክ ነው፡፡ ይህ ግለ-ታሪክ በጋዜተኛ እዝራ እጅጉ በጋዜጠኛ አንተነህ ደመላሽ
የተጠናከረ ሲሆን በተለይ ጋዜጠኛ ብርቱካን ሀረገወይን አቶ ጥላሁን በላይ ታሪካቸው እንዲሰራ ያደረገችው ጥረት ሊበረታታ ይገባል፡፡
ዛሬ ሮብ የካቲት 23 2014 በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የአቶ ጥላሁን በላይ ታሪክ ወጣ፡፡ አስፈላጊው ማሻሻያ ተደርጎበትም በየጊዜው
ተስተካክሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
መጰሀፉ ቢታተም በጣም ጥሩ ነው ተቀብለናል
ምላሽ ይስጡሰርዝ