139 .ደምሴ ዳምጤ
DEMiSE DAMTE
ለ 40 አመታት ያህል ስለ ሀገሩ ስፖርትና ስፖርተኞች ሲናገር ሲዘግብ ዘመናትን
ተሻግሯል ሁለንተናው
ሁሉ ስፖርት ነው ፍፁም ኢትዮጵያዊ ስፖርት፡ ጋዜጠኛ ደምሴ
ዳምጤ ፡፡ተወዳጅ ሚድያ
እና ኮሚኒኬሽን በሚድያው ዘርፍ ታላቅ አሻራ አሳርፈዋል ብሎ ያመነባቸውን ሰዎች በዚህ ድረ-ገጽ ላይ እያኖረ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከእነዚህ የማይረሱ ባለውለታዎች አንዱ ደምሴ ዳምጤ ነው፡፡ ህይወቱ ካለፈ 9 አመቱን ያስቆጠረው ደምሴ ከእያንዳንዱ ስፖርት አፍቃሪ ልብ ውስጥ እንደኖረ አለ፡፡ የተወዳጅ ሚድያ የግለ-ታሪክ
ረዳት ኤክስፐርት አንተነህ ደመላሽ የደምሴን ግለ-ታሪክ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡
ትውልድ እና
እድገት
በ1945 ዓ.ም ሐረርጌ ጋራ ሙለታ ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ተወለደ፡፡
አባቱ አቶ ዳምጤ
በድሬደዋ ስሚንቶ ፋብሪካ በወዝ አደርነት ይሰሩ ስለነበር
ልጃቸው ደምሴን ወደ ድሬደዋ ይዘውት መጡ፡፡
ህይወት ቀጠለች፡፡ ድሬደዋ ስሚንቶ ፋብሪካ የራሱ ድሬደዋ ሰሚንቶ የሚባል
የእግር ኳስ ክለብ ስለነበረው ፡ ክለቡ ጨዋታ ባለው ጊዜ አቶ ዳምጤ ልጃቸው
ደምሴን ወደ ድሬደዋ ስታዲየም ይወስዱት ነበር ፡ ከ አባቱ ጋር በመሆን ወደ
ስታዲየም የመግባት ዕድል
የነበረው ልጅ ደምሴ እግር ኳስንና የተለያዩ ጨዋታዎችን
እየተመለከተ አደገ፡፡
ስፖርት የመውደድ ጅማሬውም ሆነ ፡፡
ደምሴ ፣ በልጅነቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ከእኩዮቹ ጋር ልጅነታዊ ጨዋታዎችን
ተጫውቶ አድጓል ፡፡
አንድ ቀን የአዲስ ከተማና የገንደ- ቆሬ ሰፈር ልጆች የእግር
ኳስ ግጥሚያ ሲደረግ
ባለ ቅልጥማሙ ልጅ ደምሴ አዲስ ከተማን ወክሎ ወደ
ሜዳ ይገባል ፡፡ ጨዋታው
ከተጀመረና እየተጫወቱ እያለ ደምሴ ይጎዳና ይወድቃል፡፡
በወቅቱ የደረሰበት ጉዳት
ለእድሜ ልክ ከ እግርኳስ ተጫዋችነት ዓለም አገለለው፡፡
ደምሴ በጉዳት ከተጫዋችነት
መድረክ ቢወገድም እራሱን ወደ ጥሩ ተመልካችነት
አሸጋገረ ፡፡
የጋዜጠኝነት ዝንባሌ በልጅነት
ገና በ 13 ዓመቱ ደምሴ የ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ
በነበረበት
በወቅቱ የኢትዮጵያ ሬዲዮ
የስፖርት ዘጋቢዎች ሰለሞን ተሰማና ነጋ ወ/ስላሴ
የሚያቀርቡትንና ሌሎች
በድሬደዋ አካባቢ የተካሄዱ የስፖርት ውድድር ክንውኖችን
አሰባስቦ በተማሪዎች
የእረፍት ጊዜ ሲያቀርብ ፡የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መም
ህራኖች በአርምሞ ያደምጡት
ነበር ፡ አንዳንዶቹ ስፖርታዊ ዜናዎቹ በኢትዮጵያ
ሬድዮ ስፖርት ፕሮግራም
የቀረቡ ቢሆኑም ደምሴ መልሶ ሲያቀርባቸው እንደ
አዲስ በተመስጦ ያደምጡት
ነበር ፡፡
ድሬደዋ ስሚንቶ ክለብ ሲያሸነፍ የፋብሪካው ሰራተኞች ሰብሰብ ብለው የምጣድ
ጥብስ ግብዣ ያደርጉ
ነበር ፡፡ በስነ ስርዓቱ የሚዘጋጀው የምጣድ ጥብስ ሳበኝ፡፡
በዚያው እግር ኳስን
እየወደድሁት መጣሁ ፡፡ ከልጅነት የጥሬ ስጋ ፍቅር ጋር ሲል
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ተደምጧል ፡፡
የሀረርጌ የስፖርት መምሪያ ባልደረባ የሆኑት አቶ መላኩ ወልደማሪያም ግን
ደምሴ የሚያጠናቅረውን
የስፖርት ዘገባ ሰምተው ዝም አላሉም፡፡ ተሰጥኦውን
ተመልክተው ከጋዜጠኛ
ሰለሞን ተሰማ ጋር አገናኝተውታል ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ
ተማሪ እያለ በ13 ዓመቱ
የምስራቅ በረኛ ፖሊስና ድሬደዋ ሲሚንቶ ያደረጉትን ጨዋታ
ተመልክቶ ያዘጋጀው ዘገባ
ለሰለሞን ተሰማ በፖስታ ቤት በኩል ተልኮለት ፡መስከረም
12/01/ 1962ዓ,ም
በኢትዮጵያ ሬዲዮ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜናው ተላለፈለት ፡፡
የትምህርት አለም
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ የመጀመሪያ ትምህርቱን ድሬደዋ በሚገኘው
በራስ መኮንን ትምህርት ቤት የተከታተለ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
ደግሞ በከዚራ ትምህርት ቤት ተምሯል ፡፡
በ ነ ፃ
ፅናት እስከ 7 አመት
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ በትምህርት ቤት ውስጥ በ ሚኒሚዲያ ክፍል
ስፖርታዊ ክዋኔዎችን
ለተማሪዎችና ለመምህራኖች ቢያቀርብም ለዋና
ጋዜጠኝነት ሙያዊ ፍላጎት
መጠንሰስ ግን አባቱን አቶ ዳምጤን ከመጀመሪያ
ረድፍ ያስቀምጣቸዋል
፡፡
የኢትዮጵያ ሬድዮ ስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅ የሆኑት ጋዜጠኛ ይንበርበሩ
ምትኬ
ነሐሴ 26 ቀን
1968ዓ,ም ለ ኢትዮጵያ ሬዲዮ መምሪያ ተጠባባቂ ሀላፊ ለነበሩት
ለ አቶ ከፋለ ማሞ አንድ ደብዳቤ ጽፈዋል ፡፡ አቶ ይንበርበሩ ምትኬ በወቅቱ
በስፖርት ክፍሉ ውስጥ
ብቻቸውን ይሰሩ ስለነበር ፡ የሰው ሀይል እንዲቀጠርላቸው
ቀደም ሲል ጠይቀው የነበረ
ሲሆን " በሥራው ላይ ልምድና ዝንባሌ ያለው ሰው
ጠቁመን " ተብለው ደምሴ ዳምጤን ጠቁመዋል ፡፡
ጋዜጠኛ ይንበርበሩ ምትኬ ስለ ደምሴ ዝንባሌና ልምድ በጠቆሙበትና
በፃፉት ደብዳቤያቸው
የሚከተለውን ጠቅሰው ነበር ፡ ቃል በቃል እነሆ,,,
"
ከ ➐ ዓመታት በፊት በንፁህ አማተርነት መንፈስ የመንግስት አባል
ለሆኑት
ለዜና ማሰራጫዎች ለጋዜጣ ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን የሐረርጌ ክፍለ ሀገር
ስፖርት እንቅስቃሴ ሲያቀርብ የነበረው ደምሴ ዳምጤ ለዚህ ስራ ይበቃል
ብዬ መርጨዋለሁ ፡፡
ደምሴ ዳምጤ፣ የሁለተኛ ትምህርቱን በ 1964ዓ,ም ጨርሶ በአሁኑ
ሰዓት
በመምህርነት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ነው ፡ ደምሴ ዳምጤ
ከ አሁን በፊት ራሱን ለማሻሻል ብዙ ሥራ የማግኘት እድል ገጥመውት
በ
ዝንባሌየ በስፖርት ሪፖርተርነትና ተቺነት ካልተሰማራሁ ብሎ ያሳለፈ
ወጣት
ነው ፡፡ ወጣቱ ለዚህ ሥራ መብቃቱን የሚያረጋግጡት ለ ➐ አመታት
ያህል
በሬዲዮ በጋዜጣና ቴሌቭዥን ለህዝብ እንዲተላለፉ ያደረጋቸው መል
ዕክቶች ናቸው ፡፡ ወጣቱ ለሥራው ባለው ዝንባሌና ልምድ ለዘለቄታውም
ብቁ
ሆኖ እንደሚቀርብ ሙሉ እምነቶች አለኝ " በማለት አስፍረዋል
፡፡
ደምሴ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከመቀጠሩ በፊት ለ ➐ አመታት በነፃ የተለያዩ የስፖርት
ውድድሮችን እየተመለከተ
ዜናዎች ይዘግብ ነበር ፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ባልደረባ ያደረ
ገውም ይህ የስፖርት ፍቅሩና አንድም ሳንቲም ሳይከፈለው በፅናት ለ 7 አመታት
በነፃ ዘገባዎችን መዘገቡና
መላኩ ነበር ፡፡፡
መሠረት መትከል
በ 13 ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ወደ ሊቢያ ቤንጋዚ ያመራውን የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ
ለመከታተል አንድ የጅማ ሬዲዮ አድማጭ ለጋዜጠኛ ደምሴ
ዳምጤ ደውሎ
" ቴሌቭዥን የሌለን ሰዎች ምን ይዋጠን? " ይለዋል ጋዜጠኛ ደምሴ
በጥያቄው ብዙሃንነትና
አንገብጋቢነት ተጨንቆ አሰበ አሰላሰለ ፡፡ የበዛ ጭንቀቱም
መላ ወለደ " እግር ኳስን በሬዲዮ ይመልከቱ " ፅንሰ ሀሳብን
መሠረት ተከለ ፡፡
በእርግጥ በጊዜው ቴሌቭዥን በጥቂት ከበርቴ ግለሰቦች ቤት የሚገኝ ስለነበር
የስፖርት ቤተሰቡ የብሔራዊ
ቡድኑን ውድድራዊ ሂደት የማወቅ ዕድሉ የመርፌ
ቀዳዳ ያህል የጠበበ
ነበር ፡፡ በዚህ የገዘፈ አመክንዮ ነው ጋዜጠኛ ደምሴ
የተጨነቀው ፡ ተጨንቆ
ግን አልቀረም፡፡ የእግር ኳስን በሬዲዮ ይመልከቱ ፅንሰ- ሀሳብ
አፍልቆ ለአለቆቹ ለወ/ሮ
አሰገደች ይበርታና ለሙሉጌታ ሉሌ ንድፋዊ ይዘቱን
አበሰራቸው፡፡
" ቴሌቭዥን እዚህ ስቱዲዮ ላስገባና በቴሌቭዥን እየተመለከትሁ ጨዋ
ታውን ለህዝቡ በሬዲዮ
ላስተላልፍ " አለ ፡፡ አለቆቹ ግራ ተጋቡ፡፡ ሀሳቡ ያልተለመደና
እንግዳ በመሆኑ
" እንዴት ይሆናል ?" አሉት ፡፡ " ችግር የለውም የእኛን ተጫዋቾች
በተክለ- ቁመና ስለማውቃቸው
ስማቸውን እጠራለሁ ፡ የእነሱን ተጫዋቾች በቁጥር
እጠራለሁ" አላቸው
፡፡ ተደነቁ፡፡ ተደንቀውም ዝም አላሉም፡፡ ወይዘሮ አሰገደች ይበርታ
ሳሪስ ከሚገኘው ቤቷ
ባለ ጥቁርና ነጭ ቴሌቭዥኗን ጭና አመጣችለትና ስቱዲዮ
ተቀመጠ ፡፡
ለስፖርት ቤተሰቡ ጋዜጠኛ ደምሴ አስቀድሞ በሬዲዮ ጨዋታውን እንደሚያስተ
ላልፍ አሳውቆ ነበርና
ሰዓቱ ሲደርስ ልክ በስፍራው እንዳለ ጋዜጠኛ ሆኖ ጨዋታ
ውን አስተላለፈ ፡፡በተፈጥሮና
በሰው ሰራሽ ሁነት ያልተስተካከሉ የሞሉና የጎደሉ
እይታዎች በጋራ እግር ኳስን በማዳመጥ እኩል ሆነው ይመለከቱ ጀመር ፡፡
በ አንድ የጅማ ሬዲዮ አድማጭ በጎ ጥያቄ እግር ኳስን በሬዲዮ ይመልከቱ
ፍልስፍና ተተከለ፡፡
የሚሊየኖች ስሜት ምላሽ አገኘ ፡፡ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ
እግር ኳስን በሬዲዮ
በሀገራችን ኢትዮጵያ እንድንመለከት በማድረግ መሠረት የጣለ
ግንባር ቀደም ባለሙያም
ሆነ ፡፡
ነባራዊ ምስክርነት
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ለ 40 አመት ከሁለት ወር ያህል የ ኢትዮጵያ እግር
ኳስና
አትሌቲክስ ነባራዊ ምስክር
ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምሥራቅና በመካ
ከለኛው አፍሪካ ዋንጫ
ድል ሲያደርግ ጋዜጠኛ ደምሴ በውስጣዊና ውጫዊ ደስታ
ረስርሷል ፡ በአትሌቲክሱም
ዘርፍ በጀግኖች አትሌቶች ድል የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ
ብሎ ሲውለበለብ የደስታ
ሳግ እየተናነቀው ድሉን በልዩ የስሜት የበላይነት ዘግቧል፡፡
ከ ሞስኮ እስከ ባርሴሎና
፡ከ አትላንታ እስከ ሲድኒ ፡ ከ አቴንስ እስከ ቤጂንግ ደምሴ
የ ሀገር ኩራቶች አብሪ
ከዋክብቶች የደመቁበትን ደማቅ ድል ለሚወደው ህዝብ
በአይረሴና ተናፋቂ ድምፁ
አስተጋብቷል ፡ ታሪክ ሲሰራ ከታሪክ ቀማሪዎች ጋር
ተገኝቷል፡፡ ታሪካቸውን
ሰንዷል እነሆ አብሮም ታሪክ ሆኗል ፡፡፡
ስነ - ምሳሌ
ጋዜጠኛ ደምሴ በ 40 ዓመታት የኢትዮጵያ ስፖርት ውጣ ውረድ ውስጥ
ደሙ
እስኪንተከተክ ድረስ
ተችቷል፡፡ ጮኋል ገምግሟል ፡፡ ስፖርትና ስፖርትን ብቻ ዘግቧል፡፡
ስነ- ስፖርትን ዘምሯል፡፡
ለብዙ ወጣቶች በተለያዩ ስፖርቶች መሳተፍና የስፖርት ጋዜጠ
ኞች መፈጠር ከፍላጎት
መቀስቀሻ ምንጭነት ያለፈ የሙያ ስነ ምሳሌ ሆኗል ፡፡
እ ር ዛ ት
የባዶነታችን ጥግ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ መታየት ባለመቻሉ
አንጀቱ
በግኗል ፡፡ ህዝብ ጀሮው
ህውው እስኪልበት ድረስ ጨዋታቸውን ብቃታቸውን ያደመ
ጠላቸው ፡እጁ እስኪላጥ
ያጨበጨበላቸው ፡ እይኑ እስኪፈጥ አንገቱ እንስኪጣመም
ተቆልምሞ የተመለከታቸው፡
በ አበባ ዘመናቸው የሳሳላቸው ለብሔራዊ ቡድን
ተጫውተው የነበሩ ኮኮብ ተጫዋቾች፡የእለት ጉርስ የአመት ልብስ የጎን ማሳረፊያ
ጎጆ አጥተው ፡ ከስታድየም
ደጃፍ እራፊ ጨርቅ አንጥፈው ሲለምኑ ፡ጋዜጠኛ ደምሴ
በማየቱ ምርር እርር ብሎ አልቅሷል ፡፡
የ እግርኳስ ፌዴሬሽኑ አመራሮች መሀከል በተፈጠረው ሰጣ ገባ ሳቢያ ብሔራዊ
ቡድኑ በፊፋ ቅጣት ሲጣልበት
ቆሽቱ አሯል ፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ድልድል
ወቅትም በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ብድን ከግብፅ ጋር የሚደለደልበትን ደባ
አይቷል ታዝቧል ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ➎ በላይ ጎሎችን ሲያስተናግድ በብ
ስጭት ነዷል፡፡ ከ
70 በላይ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በየተራ ሲጠፉና ሲሰደዱ
እህህ ብሏል ፡፡ ስለ ሀገሩ ስፖርት ቆስሏል ደምቷል ፡፡፡
በስፖርትጋዜጠኞችና
አትሌቶች አድማስ
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ከ ስፖርት ዓለም ባሻገር በሀገር ፍቅር
መንቀልቀል
በፅኑ ታማኝነት ዘመናትን
ማገልገል ፡ ከራስ በላይ ለህዝብ ክብር መስጠት መገለጫ
ባህሪዎቹ ነበሩ ፡፡በታሪካዊ
ድምፁ ሞገዶችን እየሰነጠቀ በወጣቶች አይነ- ህሊና ውስጥ
ስዕሉን ስሏል
እያደር የሚገለጥ ከ አለት የጠነከረ ከ እሳተ ገሞራ ነበልባልነት
የተስ
ተካከለ መሻት ቀስቅሷል
፡፡ ከ አትሌቶቻችንና ከስፖርት ጋዜጠኞች ጀርባ የሙያ አባት
አምድነቱን ተክሏል ፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ የበዙ አካላዊ ፡ ሙያዊና ሀገራዊ ምስ
ክርነቶች ባለቤት
" አንቷችን " ነው ፡፡
ተቆርቆሪ ነው !
ጋዜጠኛ ዳንኤል ጋሻው
ከደምሴ ጋር በ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ አብሬ መስራት ከመጀመሬ በፊት በፍሪላንሰርነት
ዜናዎችን በነፃ እየሰራሁ
ለእሱና ለጎርፍነህ እሰጥ ነበር ብዙ ጊዜ የሥራ ስምሪት ሲደረግ
የተለያዩ የስፖርት ውድድሮችን
እንድዘግብ ይልከኝ ነበር ፡፡በወቅቱ በጣቢያው
ለምሰራው ዜና ክፍያ
አይደረግልኝም ፡፡ደምሴ ከራሱ የትራንስፖርት ይሰጠኝ ነበር፡፡
እኔ ለሙያው ፍቅር ስለነበረኝ
የራሴን ትራንስፖርት ራሴ ችየ ነበር የምሰራው፡፡ ደምሴ
ግን "አልቀበልም
" ስለው ይቆጣኝ ነበር ፡፡
ደምሴ በሀገር
ውስጥ ዘገባው ነው የሚታወቀው፡፡ ለስፖርቱ በጣም ተቆርቋሪ ነው፡፡
በጣም የሚያስገርመኝ
የደምሴ ባህሪይ ስንሸነፍ ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ በተደጋጋሚ
በእግር ኳሳችን መውደቅ
በጣም ነው የሚናደደው፡፡ የስፖርት ሰዎች እንኳን እንደእርሱ
የሚቆጩ አይመስለኝም
፡፡
ብሔራዊ ቡድናችን አዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ሲኖረው ለ ➎ ጊዜ ያህል እኔ
ደምሴና ጎርፍነህ እየተቀያየርን
ጨዋታዎችን በቀጥታ አስተላልፈናል፡፡ ለእኔ ትልቅ
እድል ነው የሰጠኝ፡፡
ብዙዎቻችን ወጣት ጋዜጠኞች ከደምሴ ልምድ ብዙ ነገር
የተማርንና የቀሰምን
ይመስለኛል ፡፡
ደምሴ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መስራች ሲሆን ከ
ቤጂንግ
ኦሎምፒክ መልስ የኢትዮጵያ
ኦሎምፒክ ኮሚቴ በኦሎምፒክ ዘገባ ከፍተኛ አስተዋ
ጽኦ ያበረከተ አንድ
መርጠን እንድንልክ በሰጠን ዕድል ደምሴን መርጠን ለረዥም
አመታት ላበረከተው አስተዋፆኦ
ተሸልሟል ፡፡
ከ እግርኳስም ባ ሻ ገ ር ,,,,,,,!
ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው
ጋዜጠኛ ደምሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት በ 1996 ዓ.ም ባህር ዳር
ከተማ ውድድር ሲያካሄድ
ለመዘገብ የመጣ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በፊት እንደማንኛውም
ሰው በሬዲዮ በድምፅ
ብቻ ነበር የማውቀው ፡፡የዚያን ጊዜ እሱ በኢትዮጵያ ሬዲዮ
እኔ ደግሞ በአማራ ክልል
ሬዲዮ ዜናዎችን ለመዘገብ ነበር የሄድነው ፡፡
በወቅቱ በጣም የማደንቀው ሰው በአካል ለማየት በመቻሌ መንገድ ላይ
እየተከ
ታተልሁ የሚያወራውን
ነገር እሰማው ነበር፡፡ አዲስ አበባ መጥቼ ኤፍ ኤም 97.1
ሬዲዮ ከገባሁ በኀላ
ያንን ገጠመኝ አስታውሼ ነግሬው አስቄዋለሁ ፡፡
ደምሴን እኔ
እንደ ሙያ አባቴ ነው የምቆጥረው፡፡ማንኛውንም ዘገባዎቼን እየሰማ
አስተያየት ይሰጠኛል ፡፡ በተለይ ብዙዎቻችን በስፖርት ፕርግራም ላይ ወደ ውጭ
ሀገር እግር ኳስ ስናጋድል
፡የሀገር ውስጥ ስፖርትን መዘንጋት እንደሌለብን ይነግረን
ነበር፡፡ በተለይ ከ
እግር ኳስ ሌላ ቦክስ፡ ቴኳንዶ ፡ የሜዳ ቴኒንስ ፡ ቴኒስና፡ ብስክሌትም
አጠቃላይ ስፖርታዊ ክንውኖች
መሰራት እንዳለባቸው ይነግረናል ፡፡
ደምሴ ፣ በስፖርት ዘገባዎች በጣም የሚታወቀው በቀጥታ በሚያስተላልፈው ዘገባው
ነው ፡ ከእርሱ ጋር
የተወሰኑ ጨዋታዎችንም አብሬ የማስተላለፍ እድል ገጥሞኛል፡፡ ብዙ
ጊዜ በቀጥታ ስርጭት
ላይ " እንደእኔ ስሜታዊ እንዳትሆን እኔ ስሜቴን መቆጣጠር
እያቃተኝ ነው የምጮኸው
፤አንተ ግን በተቻለ መጠን ስሜታዊ መሆን የለብህም፤ እንደ
ውም እንደ ጎርፍነህ
ብታቀርብ ጥሩ ነው " ይለኝ ነበር ፡፡
ከ አንጋፋ ባለሙያነት እስከ ስታዲየም በህዝብ መሙላት !
ጋዜጠኛ አለም ሰገድ ሰይፉ
/ የ ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ /
ጋዜጠኛ
ደምሴ በስፖርት ዘገባዎች አንደ አርአያ የምቆጥረው አንጋፋ ባለሙያ
ነው፡፡ ደምሴ ብዙ ኳሊቲዎች
( ሙያዊ ብቃቶች ) አሉት፡፡ ከሁሉም ግን በሀገር ውስጥ
ስፖርት ያለው ተቆርቋሪነት
ዋናው ነው፡፡
በሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ትችት መሰንዘር ፡ የራሱ የሆነ ችግር የሚያመጣ
ቢሆንም ደምሴ ግን በድፍረት
ያየውን ነገር የሚተች ሰው ነው ፡፡ በሀላፊነት መንፈስ
የሚሰራ በመሆኑ ብሔራዊ
ቡድናችን ስታዲየም ጨዋታ ሲኖረው ህዝብ ግጥም
እንዲል ያደርገዋል ፡፡
ከ 15ኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ድል በኀላ
የህዝቡን ስሜት እንዴት
አነሳስቶት እንደነበር የሁላችን የጋራ ትውስታ ነው ፡፡፡
ከ አክብሮት
የመነጨ ፍርሀት ውስጤን ይሰማኛል
ጋዜጠኛ አበበ ግደይ
ከልጅነቴ ጀምሮ የስፖርት ዘገባዎቹን እየሰማሁ ነው ያደግሁት ፡
በተለይ
ጨዋታዎችን ተመልክቶ
የሚሰጣቸው ግምገማዎች በጣም ይመስጡኝ ነበር ፡
ለ ጋዜጠኛ ደምሴ አክብሮት
አለኝ፡፡ ሁልጊዜም ደምሴን ቃለ- መጠይቅ ላደርግ
ስል ፡ የማላውቀው ስሜት
ይሰማኛል፡፡ ልቤም በከፍተኛ ሁኔታ ይመታል፡፡ ከ አክብሮት
የመነጨ ፍርሀት ውስጤን
ይሰማኛል ፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ የሀገር ፍቅር ያለው ባለሙያ ነው ፡፡ የሀገር ፍቅሩንም
በስራው
ላይ ባሳየው ትጋት አስመስክሯል፡፡ ለሙያውም ዋጋ ከፍሏል ፡፡ ለምሳሌ ደራርቱ ቱሉ
በባርሴሎና ኦሎምፒክ
ያሸነፈች ጊዜ ሌሊት በእግሩ ከቤቱ እስከ ሬዲዮ ጣቢያ ድረስ
መሄዱ ትልቅ ምስክር
ነው ፡፡ ጥርሱን በስፖርት ዘገባ ነቅሏል ለማለት ይቻላል ፡፡ ለአንድ
ባለሙያ በህዝብ ዘንድ
መወደድ ከባድ ነው፡፡ ደምሴ ግን ፍቅሩን አግኝቶታል ፡፡
ደም
ያለው ጋዜጠኛ
ጋዜጠኛ
መሰለ መንግስቱ
አንዳንድ የሀገራችን ስፖርት ጋዜጠኞች እግር ኳስ በሬዲዮ ማስተላለፌን አድምጠው
ኢትዮጵያዊው
"ጋሪ ብሉ" ብለውኛል ፡ " ጋሪ ብሉ " የታወቀው እንግሊዛዊ የእግር
ኳስ ኮሜንታተር ነው
፡፡ ለተሰጠኝ አክብሮት እጅግ አድርጌ እያመሰገንሁ ፡እኔ ግን
ይሄ ክብር የሚገባው
ለ ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ነው ባይ ነኝ ፡፡ ደምሴ ስሜት ያለው
ጥሩ የቋንቋ ችሎታ ያለው
፡ እግር ኳስን መግለፅ የሚችል ደም ያለው ጋዜጠኛ ነው፡፡
ለእኔ "ሮል
ሞዴሌ " ነው ፡ የእሱን የእግር ኳስ ዘገባዎች እየሰማሁ ነው ያደግሁት ፡አንድ
ቀን እንደሱ ባቀርብ
እያልሁ እመኝ ነበር ፡ ደምሴ ለብዙዎቻችን የስፖርት ጋዜጠኞች
በር የከፈተ ሰው ነው
፡ ከአትሌቶቻችን ጀርባ ሁሌም ያለ ሰው ነው ፡ከ ጅብ ጋር እየተጋፋ
የደራርቱን ድል ለኢትዮጵያ
ህዝብ ያበሰረ ጋዜጠኛ ነው ፡፡
በጆሮ ማየት
ጋዜጠኛ
ኤርሚያስ አማረ
/ በኢንተር ስፖርት
ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ /
የስፖርት ጋዜጠኝነት እንዲህ እንደዛሬው ቀላል ባልነበረበት ጊዜ
ደምሴና
ጎርፍነህ ከፍተኛ መስዋዕትነት
የጠየቀ ስራ ነው የሰሩት፡፡በተለይ ደምሴ ስታዲየም
የተመለከተውን የእግር
ኳስ ጨዋታ ሰኞ ማታ 2:30 ላይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሲዘግበ
ው እንደገና የማየት
ያህል ነበር ፡ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችንም ማታ በቴሌቪዥን
አይተነው በአዲስ መልክ
ነው ጠዋት የሚያቀርብልን ፡ ለብዙዎቻችን መሠረት የሆነ
ጋዜጠኛ ነው ፡በግሌም
ከ ደምሴ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ፡ እንደ እስፖርት ሌጀንድ
ልንቆጥረው የምንችለው
ነውም ፡፡
ከ ጭላሎ ተራራ ግርጌ
ሻለቃ
አትሌት ኃይሌ ገ / ስላሴ
ጋዜጠኛ ደምሴ ከሀገራችን አትሌቶች ጀርባ ሁሌም አለ ፡ ድላቸውን እግር
በእግር እየተከተለ ዘግቧል
፡፡ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ አደባባይ
በ5ሺህ ና በ10 ሺህ ሜትር ድርብ ድል ሲቀዳጅ ፡ደምሴ ድሉን ለኢትዮጵያ ህዝብ
ያበሰረው ሲቃ እየተናነቀው
ነበር ፡፡ይህ የደምሴ ድምፅ ከጭላሎ ተራራ ግርጌ
እኔን ወደ ሩጫው ዓለም በወደር የለሽ ፍላጎት ጠርቶኛል ፡፡
ተስፋፊ መንገድ የጎረሳት ቤት
ጋዜጠኛ ደምሴ 40 ዓመት ከ ሁለት ወር ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት
ሲጮህ
የመኖሩን ያህል በጡረታ
መውጪያ ዋዜማው ላይ ይህ ነው የሚባል ጥሪት
አልነበረውም ፡፡ የሚኖረው
በቀበሌ ቤት 3 ክፍል ቤት ውስጥ ነበር፡፡ከጀርመን ኤምባሲ
አካባቢ የሚገኘው ቤቱ
፡ መንገድ ዳር በመሆኑ ተስፋፊ መንገድ አንዷን ክፍል ልሷታል፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ከስፖርቱ ጋር በተየያዘ ብዙ ውጣውረዶችን አልፏል ፡፡ ብሔራዊ
ቡድኑ በተደጋጋሚ ሲሸነፍ
ታሟል ፡፡ በስኳር ህመም ተጠቅቷል ፡፡ ለደም ግፊት ተጋልጧል፡፡
ኳስ ያንቀረቀቡ አይኖቹ እንደበፊቱ የማየት አቅማቸው ተዳክሟል ፡፡ በመጨረሻም
በሀገር ውስጥ ህክምና ፈፅሞ መዳን እንደማይችል የዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል
የ ህክምና ቦርድ ወስኗል ፡ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ህክምና ከሙያ ልጆቹ እስከ
ስፖርት ቤተሰቡ በጎ
አስተዋፆኦ ተደርጓል ፡፡
የቤተሰብ ህይወት
ለ 26 ዓመታት በዘለቀው ትዳሩ አንጋፋው ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ከባለቤቱ
ከ ወ/ሮ ፀሀይነሽ መንግስቱ
ሦስት ልጆችን ማፍራት ችሏል ፡፡ ተወዳጁና አንጋፋው
የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ
ዳምጤ የ እድናለሁ ተስፋ ቢያዝልም ከ 1945 ዓ.ም እስከ
2005 ዓ.ም በተወለደ
በ60 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በአካለ ስጋ ተለየን ፡፡
መዝጊያ፤ ይህ መዝጊያ
የተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ደምሴ ለስፖርት ጋዜጠኞች ጥሩ ተምሳሌት ነው፡፡ ለሀገሩ ትልቅ ፍቅር ያለው
40 አመት ያለአንዳች ድካም ያገለገለ ድንቅ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ሰናጆች እምነት ደምሴ ለሙያው ጥልቅ ፍቅር ያሳደረ በመሆኑ
ሙያው ሊስከብረው ችሏል፡፡ ደምሴ ከውስጥ በመነጨ ስሜት የሚሰራ ሰው ስለነበር ነገር ያምርለታል፡፡ ለዚህ ነው በስፖርት አፍቃሪያን
ልብ ውስጥ ወለል ብሎ የገባው፡፡ በተለይ በ1980ዎቹ እና በ1990ዎቹ የነበሩ የስፖርት ወዳጆች የስፖርት መረጃ ረሃባቸውን ደምሴ
ያረካላቸው ነበር፡፡ በዚህ ትጋቱ እንደታላቅ ባለውለታ ይቆጠራል፡፡ ደምሴ በዚህ ሙያ ለ40 አመታት እንደማሳለፉ በሙያው ላይ በቂ
ልምድ አካብቷል፡፡ በ1978 ላይ ጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ በኢትዮጵያ ቲቪ ስለ አለም እግር ኳስ ዋንጫ ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ደምሴም ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር አንድ ላይ በመሆን ይጠይቅ ነበር፡፡ ደምሴ ሬድዮ
ላይ ያለአንዳች መቋረጥ 40 አመት መስራቱ ራሱ ስሙን ከፍ ያደርገዋል፡፡
ከ20 አመቱ ጀምሮ በዚህ ሙያ ላይ የደከመ ሰው ስለነበር ኢትዮጵያ ውለታውን እንዲህ በቀላሉ የምትዘነጋው አይሆንም፡፡ ስለ ደምሴ
ይህን ግለ-ታሪክ ስንሰንድ ደምሴ ለስፖርት ጋዜጠኝነት ተፈጥሮ እሱኑ ሲሰራ የኖረ ታላቅ ሰው ብለን ልንጠራው ይገባል፡፡ አዲሱ ትውልድም ደምሴን ሲያስብ የሙያ ፍቅርን አብሮ እንዲያስብ
እንሻለን፡፡ / ይህ ግለ-ታሪክ በተወዳጅ ሚድያ የግለ-ታሪክ ረዳት ኤክስፐርት በአንተነህ ደመላሽ የተጠናከረ ሲሆን ከቁምነገር መጽሄትም ሀሳቦች ተወስደዋል፡፡
የቁምነገር መጽሄት መስራች አቶ ታምራት ሀይሉ ይህ ታሪክ በዚህ መልኩ
እንዲሰራ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናችን ይድረሰው ›፡፡ ይህ ግለ-ታሪክ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 28 2014 አ.ም በተወዳጅ ሚድያ የግለ-ታሪክ
ገጾች የተጫነ ሲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ እየተደረገበትም ተስተካክሎ ለአንባቢያን የሚቀርብ ይሆናል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ