146. አሸናፊ ተስፋዬ-ASHENAFI TESFAYE
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣
በቅርቡ ክምችተ-አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ
አሳትሞ ያስመርቃል፡፡
በዚህ ታሪክ ላይ ስራቸውና
ስማቸው ተሰንዶ መቀመጥ ይገባቸዋል ካላቸው እና በሙያቸው ሀገርና ህዝብ ካገለገሉ ሰዎች አንዱ ጋዜጠኛና የኦድዮቪዥዋል ባለሙያ አሸናፊ ተስፋዮ ይጠቀሳል፡፡ አሸናፊ ከ10
አመት በፋና ሬድዮ በርካታ ፕሮግራሞች አየር ላይ ያዋለ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአንጎላ ሀገር በማቅናት በኦድዮ ቪዥዋል ስራ
ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ያለፈባቸው መንገዶች አስተማሪ ገጽታ ያላቸው በመሆኑ ታነቡት ዘንድ የዚህ ግለ-ታሪክ አዘጋጆች አንተነህ
ደመላሽና እዝራ እጅጉ ይጋብዛሉ
በ
ኢትዮጵያ,, ሰኔ
ዳምኖ ዳምኖ
ነጠብጣብ ዝናብ
ብኩርናውን ይሰጠንና ለእፅ
ዋትም ለእንስሳትም ጉሮሮው ለነቃ መሬትም እርጥብ ያጎርሳል፡፡ እንዲሁ በተፈጥሮ
ዑደት ዘመን ይነጉዳል፡፡ ይሸኛኛል- ይተካካል- ይዋለዳል
፡፡ አቶ ተስፉ በላይ ተስፋ ፅዮንና
ወይዘሮ ትርንጎ ኃ/ ሚካኤልም ነሃሴ 27 /11/ 1976 ዓ.ም ልጅ አሸናፊን ወደ ዚህች
ዓለም አምጥተው ይሄውላችሁ ብለውናል ፡፡
ልጅ አሸናፊ
ተስፉም እንዲህ ይለናል ፡፡
‹‹ ውልደቴ እንደማንኛውም
ኢትዮጵያዊ በ አዲስ አበባ ሾላ ወይም ጋቦን ኤምባሲ
አጠገብ ነው ፡፡ እድገቴ
ግን 98% ቡታ ጅራ ነው ፡፡ ልጅነቴ የታሸው
እኔነቴ እኔ የሆነው ቡታ ጅራ ነው ፡ ቡታ ጅራ ሁለ ነገሬ ናትና የቡታ ጅራ ልጅ ብባል
ደስ ይለኛል ፡፡›› የቡታጅራው አሸናፊ ታሪኩን ይቀጥላል፡፡
የየኔታ ባርኮት
ለመዋእለ ህፃናት
አልደረሰም፡፡ ለአቅመ የኔታ ግን ደርሶ ነበር፡፡ በሳቸው ተማረ፡፡
እዚያው ሾላ ጋቦን ኤምባሲ አጠገብ የልጅነት ትንፋሹንና ፊደሌን
ሀ,,,,, ሁ
,,,,,ሂ,,,,ሃ ብሏል ፡፡
ለከፍተኛ
ትምህርት በሚደርስበት ሰዓት በ ቡታ ጅራ አነስተኛ መለስተኛ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ጁኒየር በሚባለው ትምህርት ቤት አንድ ብሎ ትምህርቱን
ጀምሮ እሰከ 8ኛ ክፍል አጠናቀቀ፡፡ በመቀጠል ቡታ ጅራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቴን አጠናቅቆ ፡በ
1994 ዓ.ም የመጣውን
ሀገር አቀፍ የመጨረሻውን ፈተና ወሰደ ፡፡
በ
1995 ዓ.ም እንዲሁ እንደ አጋጣሚ ማስሚዲያ የክረምት ኮርስ አቡነ ጴጥሮስ
አዲስ አበባ አገኘና ትምህርቱን መከታተል ጀመረ፡፡ አድቫንስ ዲፕሎማውን በሬዲዮ
ጋዜጠኝነት ወስዷል ፡፡ ከዚያ
በማስከተል ትርፍ የትምህርት ጉዞው ጋዜጠኝነት ከተመ
ረቀ በኃላ ልዩ የካሜራ ፍቅር ስለ ነበረው በካሜራ ማን የ6 ወር ኮርስ በመውሰድ በዚያው አመራ ፡፡
ከሁሉም
በፊት ግን,,! የፍቅር ጥማት ,,
ከሁሉም
በፊት ግን በ ቡታጅራ አማተር የጋዜጠኞች ማህበር ከመስራቾች አንዱ
በመሆን የጋዜጠኝነት የፍቅር ጥማቱን ይወጣ ነበር ፡፡
ክረምት በሚደርስበት
ሰዓት እንደማንኛውም ልጅ ወደ ቤተሰብ ወደ ዘመድ አዝማድ በሚሄድበት ሰአት
በአብዛኛው ወደ አዲስ አበባ ነበር የሚሄደው ፡፡
‹‹……በዚህም ክረምቱን
በ አዲስ አበባ " መታሰቢያ" የሚባል ፕሮሞሽን
እዚያ ውስጥ
በቡድን ሆኘ ከ እነሱ ጋር እሰራነበር ፡ ለትያትር ለስነ ፅሁፍና ለጋዜጠኝነት ፍላጎት ስለነበረኝ በጋዜጠኝነት ክበባቶችላይ
የመሳተፍ ፍላጎቴ ከፍተኛም ነበር ፡፡›› ይላል አሸናፊ፡፡
ሰርተፍኬት
ከእነ እውቀቱ
ለአንድ
አመት ያህል በ ቡታጅራ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ውስጥ በ አውቶ
መካኒክ ሰርተፍኬት ከ እነ እውቀቱ ወስዷል፡፡ ሆኖም ግን አልሰራበትም ፡፡
ከ
ፊት ለፊት የሚቀጠል ስም
ጋዜጠኛ አሸናፊ
ተስፉ በላይ
ተመርቆ
ስራ አጣና አንገቴን አስግጎ ፖሊስነት ለመግባት ተወዳደረ፡፡ እስከ
አርባ ምንጭ ሄዶ ፈተናውንም አለፈ፡፡
ግን ግን ዛሬ የማያስታውሰው ስሙን የማያ
ውቀው አንድ ፖሊስ " አንተ ለፖሊስነት
አትሆንም ወደ ጥበቡ ዓለም ገብተህ መክ
ሊትህን ብትፈልግ ነው የሚሻልህ " ብሎት ወጣ ፡፡ ከወጣ በኃላ ወደ ቡታጅራ
ተመለሰ ፡፡ ያን ጊዜ
መስቃርና ወረዳ የሚባል አዲስ ወረዳ እየተቋቋመ ነበር ፡
በጋዜጠኝነት
ዲፕሎማ ስለነበረው አዲስ በተቋቋመው ወረዳ ውስጥ በጋዜጠኝነት
ሙያ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ፡፡
የቅጥር
ማስታወቂያና ጋዜጠኛ አሸናፊ
በአዲሱ
ወረዳ በጋዜጠኝነት ሙያ ተቀጥሮ እየሰራ እያለ የሥራ ማስታወቂያ
ወጣ : ደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 አዲስ የተቋቋመ ቴሌቭዥን ሬዲዮ ጣቢያ ነበር፡፡ በዚያ
ላይ ይህ ማስታወቂያ በየክልሉ ወጥቶ ስለ ነበር እርሱን መሰል ተወዳዳሪዎች ጋር ፡
የዞኑ ዋና ከተማ እንደመሆኗ መጠን ወልቂጤ ሄዶ ተወዳደረ፡፡ በሁለተኝነት ደረጃም
አለፈ ፡፡
የ
ደቡብ ክልል የወልቂጤ ቅርንጫፍ ኤፍ ኤም 100.9 ሬዲዮ ጣቢያ ገብቶ
መስራት ጀመረ ፡ የጉራጌ ዞንን የሚመለከቱ ማናቸውንም ክንውን ዜናዎችን ፕሮግ
ራሞችን በመስራት ህይወቱን መግፋት ቀጠለ ፡፡ ይህን በመሰለው ሁኔታ ውስጥ
እያለ ፡ በህይወት ምጣድ ላይ ካልተገላበጥህ ታራለህ እንዲሉ ! እርሱም ለመገለባበጥ
አሰበና ወደ አዲስ አበባ በእጥፍ ደሞዝ ቀንሶ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ- ከተማ በጋዜጠ
ኝነት ሙያ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ አለፈና በ 800 ብር የወር ደሞዝ
ተቀጥሮ ለ ➋ ዓመት
ያህል ሰራ ፡፡
በ
አቃቂ ክፍለ ከተማ እየሰራ እያለ ፋና ኤፍ ኤም 98,1 ባወጣው የስራ ቅጥር
ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሮ ለአራተኛ ጊዜ በዚሁ የጋዜጠኝነት ሙያ አልፎ ስራ
ጀመረ ፡፡2001 አ.ም፡፡
አ
ስ ከ ሬ ን ፈላጮች ,,,!
ፋና
ኤፍ ኤም በነበረበት የ ሁለት አመት የስራ መርሃ ግብር ውስጥ
በተለያዩ
ፕሮግራሞች እራሱን አሳትፎ ፡ነበር፡፡
በ ወቅቱ ከነበሩት ፕሮግራማዊ ዝግጅቶች
መካከል ፡ ህይወት በየፈርጁ፡ ቡና ጠጡ ፡ የተለያዩ ዶክመንተሪ ስራዎች ፡ ኒውስ
ከ NGO አጋር ድርጅቶች ከፋና ኤፍ ኤም 98.1 ጋር በመተባበር
የሚሰራውን ቅዱስ
ጴጥሮስ
ቤቶች ሆስፒታል ቲቢን በጋራ እንከላከል ሙሉ ፕሮግራም አሸናፊ ነበር የሚ
ቀምረው ፡፡
እቅዱን እና
ሀሳቡን ጋዜጠኛ ዘካርያስ ብርሀኑ ነበር ያመጣው ! በወቅቱ ዘካሪያስ
ዋና ሀላፊ እንደ መሆኑ መጠን ፡ ይህን ፕርግራም አሸናፊ ቢሰራው ጥሩ ነው ብሎ
ህይወት በየፈርጁን ፡ መቃብር ቆፋሪዎች አስከሬን ፈላጮች የታክሲ ወያላዎች
በአነስተኛ የስራ ክፍል ተሰማርተው የሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ህይወት የሚዳ
ስስ የሚያሳይ ፕርግራም ነበር ፡፡
ይህን ፕሮግራም አዘጋጀና
አመጣ፡፡ አሸናፊም እስካለ
ድረስ ሰራ፡፡ አብዛኛው ሰው ግን የሚያውቀው በዚህና በሰበር ዜና ነው፡፡ በአመዛኙ
ጥሩ የስራ ጊዜ ነበረው፡፡ በ ፋና ኤፍ ኤም ሲሰራበት በነበሩት ሁለት ዓመታት ፡፡
ለ ዚያች ከ ተ ማ
,,,
‹‹……. የልጅነቴ
ትዝታ ለሚንፎለፎልባት ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረው
ተዋደው የሚኖሩባት የአንድነት ተምሳሌት ለሆነች ለዚያች ከተማ ትልቅ ፍቅር አለኝ፡፡
በኮረና
ምክንያት ሁሉም ሰው ከ እለታዊ እንቅስቃሴ ለወራቶች ታቅቦ ነበርና በ ቡታ
ጅራ የነበሩ
የተማሩና የማውቃቸው
በዓለም ላይ ተሰራጭተው የሚገኙ አቻዎቼን በማሰባሰብ ፡ ምስኪኖችን የምናግዝበት ጊዜ በመሆኑ በፌስቡክ ቡታጅራ ህብረት ግሩፕ በሚል ተሰባስበን ይህንን በጎ ተግባር በማስተባበር ከአባላቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ገንዘብ በማዋጣት የአካባቢውን ማህበረሰብ እርዳታ እንዲያገኝ አድርገናል፡፡
ለዚህ
ቅን ስራችን መሳካት በዚሁ ከ አባላቱ ጀምሬ እስከ እውቅና ለሰጠን ለቡታጅራ
ከተማ አስተዳደር ድረስ ምስጋናየን እገልፃለሁ ፡፡
ፈተናዎቼ
የሕይወቴ ቁምነገሮች
እንደ
ማንኛውም ጋዜጠኛ የሙያው አምድ የሆነውን ያየሁትን እውነታ
ለማንፀባረቅ እሞክራለሁኝ፡ በህይወቴ ስንክሳር ብዙ ፈተናዎችን አይቻለሁ፡፡ አልፌያለሁ፡፡
ማንም ሰው ግን ተቸግሮ ማየት አልሻም፡፡ እንደ ችግር አስቀያሚና መጥፎ ነገር የለም
ከችግር ይሰውረን ፡ የበዙ መከራዎችን ስላሳለፍሁ ማንም ሰው ያንን ችግር ማለፍ
የለበትም ብዬ ስለማምን አቅሜ የፈቀደውን ማገዝ እፈልጋለሁ እያደረኩም ነው ፡፡
ከ
ሱዳን እ
ስ ከ
አንጎላ
ሱዳን
ውስጥ ያለ
ገንዘብ ስንዝር
መሬት መራመድ የማይሞከር ነው ! ሁሉ ነገረ
በገንዘብ
ይከወናል በህግ ውስጥም ከህግ ውጭም ይህ ነባራዊ ሀቅ ሙሉ የአፍሪ
ካን ምድር ያጠቃልላል ፡ ገንዘብ
የህጎች ሁሉ የበላይ
ገዥ ህግ ነው ያሰኛል ፡፡
ፋና
ኤፍ ኤም በምሰራበት ጊዜ ደሞዙ የኑሮ ውድነቱ ፈታኝ ሁኔታዎች ነበሩ!የህይወቴ
ትልቁ ቁምነገር የተሰናዳበት ክፍለ ጊዜም ነበር ፡ ከ አለቆቼ ጋር የነበረው አለመግባባት
ችግር በአንድ ቀን ውሳኔ ከስራ ተሰናበትሁ ፡፡ ወደ ሱዳንም ተንደረደርሁ፡፡ ብዙ ስቃይና
መከራ ተቀበልሁ ፡ ሱዳን ! ሱዳንኛ ቋንቋ አልችም ዶክመንት የሚባል መንቀሳቀሻ
ነገር
የለኝም፡ ሱዳን ላይ ዴም የምትባል አካባቢ ነበርሁኝ በዚሁ በዶክመንት ሳቢያ
እንዱርማን የሚባል መጥፎ እስር ቤት አላቸው እዚያ ወስደው አጎሩኝ ፡ ሦስት ወር
ያህል ታሰርሁ ፡፡
ሦስት
ወር የእስር ጊዜየን አገባድጄ የአባቴ
ቤተሰቦች ስለ ነበሩ ወደ ሚኖሩበት
አካባቢ በማቅናት ያሉበትን አድራሻ ለማግኘት ማጠያየቄን ቀጠልሁ፡ እህቴን ወይዘሮ
ፍርቱና ተስፉን ከ እነ ባለቤቷ ከ አቶ ኤፍሬም ገብረ እግዜርን አገኘኀቸው ፡
የ እህቴ ባል አቶ ኤፍሬም ገብረ እግዜር በዚሁ አጋጣሚ ላመሰግንህ ወደድሁ፡፡ የዛሬ
ህይወቴ መደላድል ወሳኝ ምዕራፍ ነህና፡፡አቶ ኤፍሬም ሰው መርዳት ይወዳል ለመር
ዳትም አቅም አለው ፡ ሱዳን እንድቀመጥ መረጃዬን አስተካከለልኝ የተወሰነ ጊዜ ሱዳ
ን እንድቆይም አስቻለኝ ፡ አጠቃላይ የሚያስፈልጉ መረጃዎቼን አሰናድቶ እና አሳድሶ
ወደ አውሮፓ ሊልከኝ አሰበ ፡፡ በአንድ ቀን አጋጣሚ አንድ ጓደኛው ለምን ወደ አውሮፓ
ትልከዋለህ ? አውሮፓ ምንም ስራ የሚሰራባቸው ሁኔታዎች የሉም ! መኪና ተደግፎ
ፎቶ እየተነሳ በፌስቡክ ከመለጠፍ በስተቀር ፡፡
እዚሁ
አፍሪካ አንጎላ የሚባል የስራ ሀገር አለ ወደ ዚያ ሄዶ ለምን ስራ አይሰራም
ሲለው ! የእህቴ ባለቤትም አቶ ኤፍሬም እዚያ ሄዶ እራሱን የሚቀይር ከሆነ ለምን
አይሄድም በሚል እይታ ከሱዳን ወደ አንጎላ ላከኝ ፡፡
ባቄላ
በእጅ ተቦክቶ
,,,
በሰፊው
የኖረ ! ጋዜጠኝነትን ያህል እንደውቅያኖስ የተዘረጋ ሙያ ውስጥ
ሲዋኝ አመታትን
የገፋ ሰው በድንገት የ እስር ቤት ሲሳይ ሲሆን ለዚያውም በሰው
ሀገር በሰው ቀየ ሁሉም ነገር ከ አንገት በላይ ይሆናል፡፡
በተለይ በተለይ
በእጅ ተቦክቶ
የሚቀርብልን የባቄላ ምግብ
ከ አስቀያሚ የምግብ ትዕይንቶች አንዱ ነበር ፡፡
መቼም
እስር ቤት ይወደኛል፡፡ ኬላ መሻገሪያው ቪዛ ፎርጅድ ነው በሚል ኬንያ ደግሞ
የ ➍ ወር እስር ገጠመኝ ፡፡ በዚያው እስር ቤት አምስት ልጆች
በጋራ ታስረን ነበር
ከ እስሩ መገባደድ በኃላ እንደምንም ብለን ወደ አንጎላ ገባን ፡፡
በጌታችን በመድሐኒታ
ችን እናት በቅድስት ድንግል ማሪያም አምናለሁና ከዚያ መከራ አውጥታ አንጎላ አስገባ
ችኝ ፡፡
ከ አንጎላ እ
ስ ከ
ሩዋንዳ ...
ወደ
ሀገረ አንጎላ እንደገባ ከ ሰው ላይ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ፡ ካሜራም
ምንም እያለ ዛሬ አሁን " አሹ ስቱዲዮ " የሚባል ካሜራ ስቱዱዮ አለው ፡ የራሱን
ካሜራ ይሰራል ፡ ሰርግ ፡ ልደት ፡ ጥምቀት ፡ የተለያዩ ነገሮችን ይሰራል ፡ በተረፈ
በትርፍ ሰዓቱ ኖቭል ግሩፕ የሚባል ትልቅ ካምፓኒ
አለ ብዙ ሱፐር ማርኬቶች ፡ የተለ
ያዩ የምግብ ውጤቶች የሚያሽግ ፡ የኦሞ ፋብሪካዎችን ጠቅሎ የያዘ ካምፓኒ ነው፡፡
በዚህ
ኩባንያ ውስጥ የኮንቴነር ሽያጮችን ይቆጣጠራን ፡ አጠቃላይ የአንጎላ
ክፍለ ሀገሮችን የሩዋንዳን ጨምሮ የኮንቴነር ሽያጮችን እየተቆጣጠረ ይገኛል፡፡
የ አሸነፈው ቤ ተ ሰ ብ
ከልጅነት
ጀምሮ የማውቃት አብራኝ የነበረች ጓደኛዬ ፍቅረኛየ ፡ አሁን የልጆቼ
እናት ባለቤቴ
ወ/ሮ አዲስ ተሊላ አሊ እዚህ ከመጣሁ በኀላ ለፍቼ ጥሬ
ትዳር መስርቼ
ወደ ሀገረ አንጎላ አምጥቻት እኔንም የሁለት ልጆች አባት አድርጋ የመጀመሪያ ልጄን
ክርስቲያን አሸናፊን ፡ ሁለተኛ ልጄን
ሀሌ ሉያ አሸናፊን ሰጥታኛለች ፡፡ ባለቤቴ አዲስ
ተሊላም በ አንድ ትልቅ ድርጅት ውስጥ እየሰራች እየተጋገዝን በፍቅርና በደስታ እግዚ
ያአብሔርን እያመሰገንን ልጆቻችንን እያሳደግን እንገኛለን ፡፡
በ
እምነት በጥንካሬ
ና በተስፋ ከሄድን የማይቀየር የማይለወጥ የህይወት
መንገድ የለም የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ ፡፡ ዛሬ
ከሀገሬ ናፍቆት በስተቀር በጣም
ደህናነኝ ፡፡ በ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ሀገሬ ገብቼ በሙያዬ የካሜራ ሱቱድዮ ከፍቼ ለመስራት ፍላጎት አለኝ ፡፡
ጨርጨሮ
ቂጣ በሁለት ጎኑ ተገላብጦ በስሎ ነውና የሚጣፍጠው ፡ በትዕግስት
ሁሉም ነገር ያማረ ይሆናል፡ ክፋትን ምቀኝነትን ተንኮልን ከውስጣችን አስወግደን በትጋት
መስራት ፡ በመልካም ስራችን በጥረታችን በልፋታችን መሀል እንግዚያአብሔር
ጣልቃ
በመግባት ይሞላልናል ይባርክልናልም፡፡
ቴአትር
ለ
ትያትር ና
ስነ ፅሁፍ ባለው የተለየ የውስጥ ፍላጎት በ ተፈጠረው አጋጣሚ
የዳዊት እንዚራን ስክሪፕት በመውሰድ ከነ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ጋር በደቡብ የሀገ
ራችን ክፍሎች ተዟዙሯል ፡
ጥላሁን ዘውገ እና አለልኝ መኳንንት በሚሰሩት አጫጭር ድራማዎች ስንቅ በሚለው
ፕሮግራም የእነሱ 120 ፕሮግራም በሚቀርብበት ላይ ተሳትፏል ! እንዲሁ ከ አስረስ
በቀለ ጋር
አንድ ፊልም አብሮ ሰርቷል ፡
በ
ቡታጅራ "ቡታጅራ አማተር ጋዜጠኞች ማህበር " ከመስራቾች አንዱ ነበር !
በ ኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቲቢን በጋራ እንከላከል ህብረት ማህበርን አቋቁ
ሟል፡ ለአንድ አመትም በሊቀ መንበርነትም መርቷል ፡፡
የመዝጊያ ሀሳብ ፤ ይህ
መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የኢንሳይክሎፒዲያ ቦርድ አባላት አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
አሸናፊ በሚድያ እና ስነ-ጽሁፍ አካባቢ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጡን እያዳመጥ
ጋዜጠኝነት በፍቅር ሊሰራ የሚቻለውን አድርጓል፡፡ ምንም እንኳን ህይወት በውጣ ውረድ የሚታለፍባት መስክ ብትሆንም ለታገሳት ብዙም
አትጎዳም፡፡ አሸናፊ በሚድያው አካባቢ በቆየባቸው ጊዜያት በተለይም ደግሞ ፋና በሰራባቸው 2 አመታት የራሱን አሻራ ያሳረፈባቸው
መሰናዶዎችን አየር ላይ አውሏል፡፡ እነዚህ መሰናዶዎች እንዲህ በቀላሉ የሚሰሩ ሳይሆን የጋዜጠኛውን ድፍረት ፤ እውቀትና ፍላጎት
የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ አሸናፊ ደግሞ ሶስቱንም ሰንቆ ሙያዊ አደራውን ሲወጣ ነበር፡፡ ይህ ትልቅ ርካታን ይሰጠዋል፡፡ ያኔ አሸናፊ ይሰራቸው
የነበሩትን አየር ላይ የዋሉ መሰናዶዎችን ከአርካይቭ አውጥተን ስናደምጥ የጊዜው መልክ ምን እንደነበር ይነግረናል፡፡ አሸናፊ አየር
ላይ ያዋላቸው ን ወደ 20 የሚጠጉ መሰናዶዎች ስናደምጥ የጋዜጠኛው የሚድያ ፍቅር እምን ድረስ እንደሆነ መገመት አያቅተንም፡፡ የአሸናፊ
ታሪክ እንዲሰራ ከውሳኔ ላይ ስንደርስ በ2000 ዘመን የነበረውን
የጋዜጠኝነት አካሄድ እንዲነግረን በማሰብ ነው፡፡ አሸናፊ ኑሮውን በአፍሪካዊቷ ሀገር አንጎላ ካደረገም በኋላ የሚድያ እና የኦድዮቪዥዋል ፍቅር ውስጡ እንደሰረጸ ነው፡፡ በዚህ ሙያ ብዙ
የማደግ እቅድ አለው፡፡ እኛ የአሸናፊ ታሪክ በብዙ መልኩ ያስተምራል፡፡ ከአዲስ አበባ ሱዳን ከሱዳን በብዙ ውጣ ውረድ አልፎ አንጎላ
ውስጠ የቪድዮ መቅረጫ ተቋም መክፈት ቀላል አይባል፡፡ መከራ የማይገድል ቢሆን ሊያደረስ የሚችለው ከጥንካሬ ጎዳና ነው፡፡ከዚህ የጥንካሬ
ጎዳና ላይ ለመድረስ ግን አሸናፊ ባለቤቱን ወይዘሮ አዲስ ተሊላን ከልብ ማመስገን ይወዳል፡፡ ትናንት በአለቆቹ ተማርሮ የነበረው አሸናፊ ዛሬ ደግሞ ችግርን ተጋፍጦ ማለፍ
ከምን እንደሚያደረስ ሊያሳይ እነሆ ታሪኩን ተረከ፡፡
/ ይህ ጽሁፍ ባለታሪኩን በማነጋገር ፤ አየር ላይ ያዋላቸውን የሬድዮ መሰናዶዎች በማድመጥ የተጠናከረ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ እና በአንተነህ ደመላሽ ተሰናዳ፡፡ አስፈላጊው ለውጥ እና ማሻሻያ እየተደረገለት በየጊዜው በዚህ ድረ-ገጽ ላይ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ ይህ ጽሁፍ ዛሬ የካቲት 20 2014አ.ም በተወዳጅ ሚድያ የፌስ ቡክ ገጽ እና በተወዳጅ ሚድያ የብሎግ ገጽ ላይ ወጣ፡፡
አሹ ወንድሜ ከአአ ከወጣህ በዃላ ያለው ታሪክ አዲስ እና ማወቅ የሚፈልገው ነበር አመሠግናለሁ ጸሃፊው
ምላሽ ይስጡሰርዝእኔም አክብራችሁ ታሪክ አስተማሪ ነው ብላችሁ ስለ ጋበዛችሁኝ. ክብረት ይስጥልኝ🙏🙏🙏
ሰርዝ