147. ሆደን
ኑር -የሶማሊኛ ጋዜጠኛ
ተወዳጅ
ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣ በቅርቡ ክምችተ-አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ
በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ አሳትሞ ያስመርቃል፡፡ ታሪካቸው በመጽሀፉ ውስጥ ከሚሰነድላቸው አሻራ ካኖሩ የሚድያ ሰዎች አንዷ ሆደን ኑር
ናት፡፡ ሆደን ኑር በሶማሊኛ ቋንቋ በሚተላፈው የሬድዮ ፕሮግራም ላይ
ባለፉት 20 አመታት በማገልግል የድርሻዋን የተወጣች ጋዜጠኛ ነች፡፡ አንተነህ ደመላሽና እዝራ እጅጉ የሆደንን አጭር ግለ-ታሪክ
እንደሚከተለው አሰናድተውታል፡፡
ከ ሶማሌ የሴት ጋዜጠኞች መካከል ከፈርቀዳጆች ረድፍ የምትቀመጠዋ
ሆደን ከ እናቷ ፋጡማ ሂርሲ ከ አባቴ ኑር አብዲ መቂ ከተማ ተወለደች፡፡መቂ
በ ኦሮማያ ክልል ምስራቃዊ ንፍቀ- ክፍል የምትገኝ ከተማ ናት ፡፡
የልጅነት ጊዜ አለፈና ወደ ትምህርት ተሰማራች፡፡ ከ 1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል
በ ካቶሊክ
ሚሺነሪ ተማሪ ቤት ትምህርቷን ጀመረች ፡፡ከ ስድስተኛ ወደ ሰባተኛ ክፍል በአመቱ
መጨረሻ የአለፈው
ተማሪ በዛ በሚል ሰበብ እንደገና እንዲፈተኑ ተደረገ ፡፡በወቅቱ
ፈተናውን ማለፍ
አልቻለችም ነበርና፡፡ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ድጋሚ የመማር ዕድል
ስለማይሰጥ ወደ መንግስት ትምህርት ቤት በመዛወር ትምህርቷን መቀጠል
ነበረባት፡፡ ወደ መንግስት ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርቷን ቀጠለች ፡፡
የ 7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትምህርቷን በመንግስት ተማሪ ቤት
ከተማረች በኀላ ወደ ዘጠነኛ ክፍል ስታልፍ በቀድሞ ትምህርት ቤቷ ከ ካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት ገባች ፡፡
ደስ የሚል የትምህርት ቤት እና የልጅነት ዘመኗንም በ ካቶሊክ ሚሽን ትምህርት
ቤት
አገባደደች፡፡
በልጅነቷ ለጥበቡ አለም
ፍላጎት አድሮባት ነበር ፡፡ እንደ ድራማ መስራት አይነት
ነገር! የ ኢትዮጵያን ሬዲዮ በጣም ታዳምጥ ነበር በተለይ እነ አርቲስት
ፈቃዱ ተክለ
ማሪያም ቅዳሜን ከሰዓት ከኛ ጋር በሚል ፕሮግራማቸው ትሳብ የነበረ ሲሆን
አርቲ
ስት አብርሃም አስመላሽ የሚያነባቸውን ግጥሞች ከመስማት ባለፈ ግጥሞቹን
በቃሏ ይዛ ለክፍሏ ተማሪዎች ታቀርብላቸው ነበር፡፡የአርቲስት አብርሃም አስመላሽ
ግጥም ግን ከመውደድ
የበለጠ ግጥሞችን እንድትፅፍ ከፍተኛ ጥበባዊ ተፅእኖ
እንደ አሳረፈባት ተናግራለች ፡፡
በጊዜው የሚማሩበት ትምህርት ቤት ጥበባዊ ፍላጎትን መግለጫና ማጎልበቻ
እንደ ሚኒሚዲያ አይነት ክበብ አልነበረውም ፡፡ ይሁንና ትምህርታዊ የሆነ የክርክር
መድረክ የሚባል
መከራከሪያ ርዕሶች ተመርጠው በ ርዕሶቹ መካከል የሚደ
ረግ ክርክር ስለነበር በሱም ተሳትፊ ነበረች፡ ብቻ ውስጧ የነበራትን ስሜት
ልትገልፀው
የማትችለው ከጥበባዊ አለም ጋር ያቆራኛት ነገር እንደነበራት ገልፃለች ፡፡
በሙስሊሙ
ማህበረሰብ በተለይ በእሷ ቤተሰብ እንዲህ አይነት ጥበብ ነክ ተሳትፎዎች
ፈፅሞ
የተከለከሉ ቢሆኑም እድሎችን ከመጠቀም አላቀቧትም ፡፡
BBC እና ሶማሌዎች
ሶማሊኛ ቋንቋ በአፍሪካ በአምስት ሀገሮች ይነገራል ! የሶማሌ
ማህበረሰብ
ደግሞ ወሬ ወይም ዜና በጣም ይወዳል፡፡ በወቅታዊ መረጃዎች እራሱን ያደራጃል
በዚህም በ BBC የሚቀርበው የሶማሊኛ ዝግጅት ከ 11:00 - 11 :
30 በቤተሰቧ
በጉጉትና በስርዓት ይደመጣል፡፡ በልጅነቷም ልትገልፀው የማይቻላት ስሜት ተጠንስሶ
አሁን ለደረስችበት ማንነቷ እርሾውን ጥሏል ፡፡
በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመን በኢትዮጵያ ሬዲዮ ይሰራ የነበር የ ሶማሌ ጋዜጠኛ
መሀመድ
ሁሴን ጅሬ ከመታወቁ በላቀ ጅግጅጋ ከተማ በስሙ ትምህርት ቤት የተሰየ
መለት
፣ጋዜጠኛ አብድል ቃድር ፋራህ ኮሎምቦ፣ጋዜጠኛ ኢብራሂም፣ ከሴት ጋዜጠኛ
ደግሞ
ጋዜጠኛ ደሀቦ ሺደን እና ከ ወደ BBC ጋዜጠኛ አብደላሂ አል የሱፍ ወደ ጋዜጠ
ኝኘቱ አለም ከመግባቷ በፊት ተጠቃሽ አርአያዎቿ ጋዜጠኞች ነበሩ
፡፡
ፍልሰት
የ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ፈተና ተፈትና ወደ መካነ- አእምሮ/
ዪኒቨርሲቲ/ የሚያስገባ የተተመነውን ውጤት ባለማምጣቷ ወደ አረብ ሀገር ሄደች ፡ አረብ ሀገር ሆና እየሰራች እያለ! ወንድሟ ደውሎ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ካምብሪጅ ኮሌጅ በርቀት መማር እንደሚፈልግና
ክፈይልኝም ብሎ ጠየቃት፡ወንድሟ የሚማርበትን ክፍያ ካመቻቸች በኀላ እሷም የመማር ስሜት ተቀሰቀሰባት እና ከካምብሪጅ ኮሌጅ ጋር
በመፃፃፍ
በርቀት ትምህርቷን ቀጠለች፡፡ ሆደን "ቋንቋ ላይ የተለየ ችሎታ አለኝ
አዲስ ቋንቋ ለመል
ልመድ ቋንቋውን የሚችሉ ሰዎችን ለጥቂት ጊዜ መስማት በመቀጠል ትንሽየ ልም
ምድ ማድረግ ነው የሚጠበቅብኝ፡፡ በቀላሉ በተወሰነ ድግግሞሽ እለምደዋለሁ
"
ስትል ያላትን ብርሃናማ ፍላጎት ገልፃለች ፡፡
አራት አመት ባህሬን በሚባል ሀገር ስትቆይ በ እንግሊዝኛ ቋንቋ ከ ካምብሪጅ
ኮሌጅ
ዲፕሎማዋን ያዘች ፡፡ ወንድሟ ናስር ኑር በፓርላማ ላይ የአማርኛን ቋንቋ
ወደ ሶማሊኛ
ሶማሊኛን ወደ አማርኛ እየተረጎመ በአስተርጓሚነት በህዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት
ይሰራ ነበር፡ ከ አዲስ አበባ መካነ አእምሮ ትምህርት ቤት በእንግሊዘኛ ቋንቋ
የመ
ጀመሪያ ዲግሪውን ወስዷል፤፡ እሷም ሳላውቀው የወንድሜን ፈለግ እከተል ኖሯል
በማለት አግራሞቷን አክላለች ፡፡
ምልሰት
ወንድሟ ናስር ኑር ሬዲዮ ፋና ገብቶ በሬዲዮ ፋና ብዙም ሳይሰራ ሆደን
ወደ ሀገር
ከመመለሷ በፊት በድንገት አረፈ ፡፡ ወደ ሀገር ከተመለስች በኀላ ሬዲዮ ፋና
በሶማ
ሊኛ ቋንቋ የሬዲዮ ዝግጅት ክፍላቸው ሰው እንደሚፈልጉ ሰማች ፡፡ በ ጊዜው
በነበረ
ው የሶማሊኛ ቋንቋና አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኛ ማግኘት ይቸግር ነበር፡፡በዚሁ
አጋ
ጣሚ ይህን
መስፈርት አሟላችና ከልጅነቷ ለሙያው ፍላጎቱም ምኞቱም ስለነበራት
በ 1994 ዓ.ም ፋና ሬዲዮን ተቀላቀለች፡፡ ተቀጠረችም ፡፡ይሄው እስከ ዛሬ
ድረስም ከፋና
መስሪያ ቤቷ ትገኛለች ፡፡
የ ልምድ ፍሰት
ወደ ፋና ሬዲዮ ስራ ስትገባ በመጀመሪያ ቀጥታ ወደ ፕሮግራም ጥቅል
ዝግጅት
አልገባችም ! አስፈፃሚ መሆን ፡ ፕሮግራሞችን መምራት ላይ ነው የጀመረችው "ወደ
ማይክ
ውስጥ ስገባ በጣም እፈራ ነበር " የምትለን የዛሬዋ ጋዜጠኛ ሆደን ኑር "ከርቀት
ሲያዩት
ቀላል ይመስላል ሬዲዮም ቢሆን ፕሮግራሞችን ሳቀርብ ሰዎች ተደብቀው
የሚያዩኝ
ነበር የሚመስለኝ " ስትል የልምድ ፍሰቷን አጋርታናለች ፡፡
የተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች የፕሮግራም ተሞክሮዎች የራስ ልምዶች ተዳምረው
ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን የመዝናኛ ፕሮግራሞችን የዘፈን ምርጫ ፕሮግራሞችን
በሶማሊኛ ቋንቋ ክፍል ውስጥ በራሷ እንድታዘጋጅ አስቻሏት፡ በተጨማሪ ለረጅም
አመታት ጤና ፕሮግራም ላይ ሰርቻለች ፡ ጤና ነክ ግንዛቤን በተመለከተ አበርክቶዋን ሰጥታለች !
በተለይ በሶማሌ ክልል የሴት ልጅን ግርዛት በተመለከተ ግርዛቱን በሙሉ ማስቀረት
ባይቻልም ቢያንስ
በግንዛቤ ብዛት እንዲቀንስ በጎ አስተዋፆኦ አድርጋለች፡፡ ዘመን
ወለድ የሆኑ የጤና ትምህርቶችን የሚያሳልጡ ማስታወቂያዎችን ድራማዎችን እንደ
አዘጋጅ ፣ተዋናይና አርታኢም በመሆን ተሳትፋለች ጋዜጠኛ ሆደን ኑር ፡፡
ቤተሰብ
ፋና ስትገባ ጋዜጠኛ መሀመድ ሀሰን የሶማሊኛ የሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ሃላፊ
ነበር
እዚያው በሥራ ምክንያት መተዋወቅን ተሻግረው ተጋቡ ፡፡በኮንትራት መልክ የተጀመ
ረው የጋዜጠኛ ሆደን የሬዲዮ ፋና ህይወት በ 1200 ብር የወር ደሞዝ ዳዴ
ብሎ ለ20
ዓመታት ዘልቆ ይኸው ለዛሬ በቅቷል! በዚህ መካከል የተለያዩ ስልጠናዎችን
በመ
ውሰድ በረዳት አዘጋጅነት የምትወደውን የጋዜጠኝነት ሙያዋን በሶማሌኛ ቋንቋ
ክፍል ውስጥ ታሳልጠዋለች ፡፡
ባለቤቷ መሀመድ ሀሰን ሬዲዮ ፋና በገባች ከ 7 ወር በኃላ ብዙም ስይቆይ
ወደ ጅግጅጋ
ሌላ ሥራ ቀይሮ ሄደ፡፡ አሁንም እዚያው እየሰራ ይገኛል፡፡ ባስቆጠሩት
የ
20 ዓመት የትዳራቸው ቆይታ ውስጥ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የመጀመሪያ
ልጃቸው
የ 19 ዓመት ሁለተኛው ልጃቸው ደግሞ 11 ዓመት ልጆች ሆነዋል ፡፡
ጋዜጠኛ ባልሆን ,,,,,,,,,, !
የ ኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚኒኬሽን ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በድምፅ ተወዳድራና
ውድድሩንም
አሸንፋ ፡ በሶማሌኛ ቋንቋ ለሚገለገሉ ማህበረሰቦች "ያለዎት
ቀሪ ሂሳብ "
የምትለው
ድምፅ ባለቤት ጋዜጠኛ ሁደን ናት፡ አሁንም ይህ ሥራዋ በሶማሊኛ ቋንቋ
አገልግሎት
እየሰጠ ይገኛል፡በዚህም ደስተኛ ነኝ ትላለች የሶማሌዋ ፈርጥ ጋዜጠኛ
ሆደን
ኑር አብዲ " ጋዜጠኛ ባልሆን ዕድሉን አላገኘውም ነበርና" በማለት፡፡
የመዝጊያ
ሀሳብ ፤ ይህ መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የኢንሳይክሎፒዲያ ቦርድ አባላት አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ሆደን
ኑር ዛሬ በፋና ሬድዮ በሶማሊኛ ዝግጅት ክፍል በከፍተኛ ሃላፊነት እያገለገለች ትገኛለች፡፡ ዛሬ ሆደን በዚህ ሙያ ላይ ከመሰማራቷ
አስቀድሞ ለሙያው ከፍተኛ ፍቅር ነበራት፡፡ የኪነጥበብ የሚድያ ፍቅሩ ያደረባት ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ነበር፡፡ ታዲያ
ያኔ የጀመረው ጥረት ዛሬ ሚድያ ገብቶ የመስራት እድሉ ሲገኝ በእድሉ መጠቀም ችላለች፡፡ ሆደን ኑር በ1990ዎቹ በጋዜጠኝነት ዘርፍ
በተለየ ደግሞ በሶማሊኛ ጋዜጠኝነት የራሷን ጉልህ አሻራ ለማኖር በቅታለች፡፡ ለዚህ ደግሞ ቀዳሚ ምስክር የሚሆኑት በሚሊዮን የሚቆጠሩ
የሬድዮ አድማጮቿ ናቸው፡፡ ሆደን በሙያዋ ከዚህ በላይ የማደግ እና ለሀገሯ በተለይ ደግሞ የሶማሊኛ ጋዜጠኝነት እንዲያድግ የበኩሏን
ጥረት ማድረጓ አልቀረም፡፡ / ይህ አጭር ግለ-ታሪክ ባለ-ታሪኳን በማነጋገር ፤ እንዲሁም የቅርብ ሰዎቿን በመጠየቅ የተሰራ ነው፡፡
ይህ ጽሁፍ በጋዜጠኛ አንተነህ ደመላሽና በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ተጠናክሮ የቀረበ ሲሆን ዛሬ ሰኞ የካቲት 21 2014 በተወዳጅ ሚድያ
የፌስ ቡክ ገጽ እና የግለ-ታሪክ ድረ-ገጽ ላይ ወጣ፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ