19. አሰፋ ጎሳዬ - ASSEFA GOSSAYE
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ሰዎች ታሪክ ከአንጋፋ እስከ ወጣት በሚል ሀሳብ ከ130 በላይ የሚድያ ሰዎችን ታሪክ ደረጃውን በጠበቀና ጠንካራ ሽፋን/hard
cover/ ኢንሳይክሎፒዲያ
ሊያሳትም
እንደሆነ
ይታወቃል፡፡
እስከዚያ
ድረስ
ታሪካቸው
በዚህ
ዊኪፒዲያ
እና በተወዳጅ ሚድያ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ከሚነገርላቸው መካከል የአዲስ አድማሱ ሰው አሰፋ ጎሳዬ ገዳ ይነሳል፡፡ አሰፋ ጎሳዬ ብዙ ውለታ የዋለ ለሚድያ ታላቅ ሚና ያበረከተ ነው፡፡ የዚህ የአማርኛ ዊኪፒዲያ መስራች ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ የቀድሞ አለቃውን አሰፋ ጎሳዬን መንገድ ያመላከተኝ ታላቅ መሪ ሲል ይገልጸዋል፡፡ ታሪኩንም በዶክመንተሪ እና በዊኪፒዲያ ያሰፈረ ሲሆን ታህሳስ 6 2014 አሰፋ ህይወቱ ያለፈበትን 17ኛ አመት አስመልክቶ ይህን አጭር ግለ-ታሪክ ሊያሰናዳ ችሏል፡፡
ንባብን ገና በልጅነት
‹‹የአዲስ አድማሱ ሰው›› አዳዲስ ነገሮች ይስማሙታል፡፡ ከተለመደው አካሄድ ወጣ ብሎ
ባልተሄደበት መንገድ ማሰብና ያሰበውን ማድረግ ይቀናዋል፡፡ምንም
እንኳን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ
ኢኮኖሚክስን ቢያጠናም ነፍሱ ግን ለጥበብ ታላቅ ጥማት ነበራትና ከጥበብ ደጃፍ ቆማ
ያላትን ለመስጠት ደግሞ ከሌሎች ለመቀበል ጉጉት ያድርባት ነበር፡፡
‹የአዲስ አድማሱ ሰው ለንባብ የዳበረ ማንነት ያለው ሰው በመሆኑ አብረውት ያሉ ሁለገቡን ባለራእይ
ደስ ብሏቸው ይሰሙታል፡፡ የአዲስ አድማሱ ሰው አሰፋ ጎሳዬ ጥበብ ላይ በቆየባቸው 17 አመታት
የራሱን የማስታወቂያ ድርጅት ከመክፈት አንስቶ አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን በማምጣት ፣ዘመናዊ
ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ብቃት ያለው መሆኑን አስመስክሯል፡፡አሰፋ ጎሳዬ ፡፡ የዛሬ 17 አመት
ህይወቱ ስላለፈው ስለዚህ በብዙዎች ስለሚወደድ ሰው ልንነግራችሁ ብቅ
ብለናል፡ የአዲስ አድማሱ ሰው አሰፋ ጎሳዬ -፡፡
አሰፋ ጎሳዬ ገዳ ፣ ለእናት ለአባቱ የበኩር ልጅ ነው፡፡አባቱ በጣም አስተዋይ መሆኑን ተመልክተው የሰፈር ልጆችን እንዲያስጠና ሃላፊነት ሰጡት፡፡ ትንሹ አሰፋ የሰፈር ጓደኞቹን ከማስጠናት ባለፈ ለራሱም እያጠና ጎበዘ፡፡ ገና በልጅነቱ በትምህርት ቤት በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር የቴሌቪዥንሽልማት
ያገኘው
አሰፋ
ጎሳዮ
በተማሪ
ቤትም
ሆነ በሰፈር ልጆች ዘንድ ይከበር ነበር፡፡ ንባብን ገና በልጅነት የተለማመደው ትንሹ አሰፋ ታናናሽ እህት ወንድሞቹም የእርሱን ፈለግ እንዲከተሉ ይጥራል፡፡
ከሚቀጠር የራሱን ስራ መረጠ
አቶ ተፈራ ደንበል ከልጅነት አንስቶ አሰፋ ጎሳዬን የሚያውቅ የልብ ወዳጁ ሲሆን አሰፋ ተፈጥሮ የቸረችው ልዩ የሰው መውደድ ያለው ነው ሲል አሰፋን ይገልጸዋል፡፡
አሰፋ ከአባቱ ጋር በመሆን ከአስመራ ከተመለሰ በኋላ በወጣት ማህበር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ጀመረ፡፡ አሰፋ በዛን ወቅት በአመራር ችሎታው ለሌሎቸ አርአያ መሆን የሚችል ነበር፡፡
ነቢይ መኮንን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የአሰፋ የቅርብ ወዳጅ ሲሆን ስለ አሰፋ አሰብ ሲያደርግ
ጎላ
ብሎ የሚታይ ፣ በቀላሉ ተጽእኖ የሚፈጥር በሳል ሰው ነው ይለዋል፡፡
አሰፋ ጎሳዬ ፣ በሀገራችን በማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከአቶ ውብሸት ወርቃለማሁ በመቀጠል
የማስታወቂያ ድርጅት ለመክፈት የቻለ ሰው ነው፡፡አሰፋ የራሱን የማስታወቂያ ድርጅት ከመክፈቱ በፊት
በዘንባባ የካርቦን ፋብሪካ ለ4 አመታት ተቀጥሮ አገልግሏል፡፡ በዛን ወቅት የፋብሪካው ባለቤት የነበሩት
ቀኛዝማች ሀይሉ ቃለ-ወልድ እንደተናገሩት አሰፋ የተሰጠውን ስራ በአግባቡ የሚሰራና ብቁም ነበር ብለ
ው መስክረዋል፡፡ አሰፋ ተቀጥሮ ከሚሰራ ይልቅ የግሉን ስራ መመስረት እንዳለበት ያሰበው አባቱንና
ቀኛዝማች ሀይሉ ቃለ-ወልድን እንደመነሻ በማድረግ ነው፡፡ አሰፋ የራሱን ስራ ለመስራት ሲያስብ ልቡ
ጥበብን ወዶ ነበርና ኪነ- ጥበብን ከሚወዱ ሰዎች ጋር መዋል ጀመረ፡፡
ለሁሉም እኩል ወዳጅነት ያሳያል፡፡
ተወዳጁ አሰፋ ጎሳዬ ፣ሰውን ለመቅረብ አይቸግረውም ፡፡ ነገሮችን አክብዶ ከማየት ይልቅ ቀለል አድርጎ
ማየትን ይመርጣል፡፡ አሰፋ ሀሳብን ወደ ገንዘብ መቀየርን ያውቅበታል፡፡ የቅርብ ሰዎቹንም ሆነ በአንድ
አጋጣሚ የተዋወቀውን ሰው አዲስ ነገር ፈጥረህ ኑሮህን የተሻለ ማድረግ ትችላለህ ሲል ይመክራል፡፡
ደራሲ ዘነበ ወላ አሰፋን ሲገልጸው ‹‹በአካል ሳላየው የወደድኩት ሰው›› ብሎታል፡፡
አሰፋ ጎሳዬ ገዳ ከሰአሊው ፣ከቀራጺው ፣ከተዋናዩ ፤ከጋዜጠኛው ፣ከነጋዴው ከሁሉም ጋር በፍቅር ይግ
ባባል፡፡ ትንሽ ትልቅ ሳይል ለሁሉም እኩል ወዳጅነት ያሳያል፡፡
አሰፋ ሁለተኛ ደረጃ ሳለ ለሂሳብና ለፊዚክስ ልዩ ፍቅር ነበረው፡፡የደረጃም ተማሪ ነበር፡፡ አንደኛና ሁለተኛ እየወጣ ነበር ትምህርቱን ያጠናቀቀው፡፡ አሰፋ በ1973 ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ኢኮኖሚክስን ፈልጎ ነበር ያጠናው፡፡ በበርካታ ተማሪዎችም ዘንድ በመጽሀፍ ወዳድነቱ ይታወቅ የነበረው አሰፋ ከእጁ መጽሀፍ አይለይም፡፡
አሰፋ ጎሳዬ ፤ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በዘንባባ ካርቦን ፋብሪካ ተቀጠረ፡፡ አሰፋ በዘንባባ ካርቦን ፋብሪካ ሲቀጠር የራሱን ድርጅት የመክፈት ራእይ እንዳለው ይናገር፡ ነበር፡፡አሰፋ ጎሳዬ በ1981 የዛሬ 33 አመት ‹‹አድማስ አድቨርታይዚንግ››
የተሰኘውን
የራሱን
ድርጅት
ከከፈተ
በኋላ
አዳዲስ
ነገሮችን
ይዞ ብቅ አለ፡፡በአማርኛ
ቁዋንቁዋ
ያዘጋጀው
የአለም
ካርታ
ለሽያጭ
እንደቀረበ
አሰፋ
ልዩ የፈጠራ ብቃት እንዳለው ታወቀ፡፡ ከ15-20ሺህ ኮፒ የታተመው እና የአለም ውቅያኖሶችን አህጉራትን ስም በአማርኛ ያቀረበው ይህ ካርታ ከ15-20 ብር ለመሸጥ የበቃ ነው ፡፡ አሰፋ በዚህ መልኩ በርካታ ሀሳቦችን እያፈለቀ ብዙ ተግባራትን ማከናወን ችሏል፡፡ከአሰፋ ጋር ለረጅም አመት በጓደኝነት የዘለቀው አቶ ተፈራ ደንበል አሰፋ ስራ ፈጣሪነትን ያበረታታ እንደነበር ያስታውሳል፡፡
አሰፋ ጎሳዬ፣ ለአዳዲስ ነገሮች ሁልጊዜም ክፍት ነው፡፡ ሜጋ ኪነ- ጥበባት ከተመሰረተ በኋላ በ1984 አንድ ነገር አሰበ፡፡ የደጋ የመኪና እሽቅድምድም በሚል ከሜጋ ጋር በመሆን የቀረጻ ስራውን መርቶ ነበር፡፡አሰፋ ለዚህ ውድድር 4 ካሜራ አስወጣ ፡፡እንደ ዳይሬክተርም ፤ እንደፕሮዲውሰርም ሆኖ ስራውን በብቃት አከናወነ፡፡ የኤዲቲንግ ስራውንም አጠናቅቆ ውድድሩን ላዘጋጀው አካል ፊልሞቹን አስረከበ፡፡ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ አሰፋ ሀሳብን መሸጥ የሚያውቅ ባለ ታላቅ ተሰጥዖ ሲል ይገልጸዋል፡፡
አሰፋ የቤቱ የበኩር ልጅ ስለነበር እህት ወንድሞቹን ይመክራል፡፡ ያወያያል፡፡ አሰፋ ለእህት ለወንድሞቹ ሁልጊዜ አሳቢ ነው፡፡ ትልቅ ቦታ ደርሰው ማየትን ሁልጊዜም ይመኛል፡፡ ገነት ጎሳዬ ይህን የወንድሟን አሳቢነት ዛሬ ድረስ አትዘነጋውም፡፡ አሰፋ እህት ወንድሞቹ ጋር ከተገናኘ ሳቅ እና ደስታ አለ፡፡
አሰፋ የሰው ደስታ ያስደስተዋል፡፡
ከሰው
ጎን ለመቆም ሁልጊዜም ዝግጁ ነው፡፡በተለይም
በኪነ-ጥበቡ ላይ ላሉ ሰዎች የሚያሳየው ቀረቤታ በስራው እንዲገፉበት የሚያደርግ ነበር፡፡ ለዚህ እንደ ዋና ምስክር ሆና የምትቀርበው ድምጻዊት ጸደንያ ገብረማርቆስ ናት፡፡
……..
በአሰፋ ጎሳዬ የተመሰረተው አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ስኬታማ መሆኑ የተረጋገጠው በአንባቢ ብቻ ሳይሆን በመንግስትም ተቀባይነት ማግኘት መቻሉ ነው፡፡ ‹‹አዲስ አድማስ›› ጥሩ ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት፣ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡ በጋዜጣው መስራች ለጋዜጣው ከተቀመጡት መድረሻ ግቦች አንዱ፣ የጋዜጣውን ቅጂ 50ሺህ ማድረስ ነበር፡፡ ‹‹አዲስ አድማስ›› መታተም ከጀመረ ከአንድ አመት በኋላ የኮፒው ቁጥር ከሳምንት ሳምንት እያደገ መጥቶ አሰፋ ካለመው በላይ ቅጂው ከ50ሺህ በላይ ሊታተም ችሏል፡፡አሰፋ ለዚህ ስኬቱ በዋናነት አብረውት የሚሰሩትን ጋዜጠኞችን ያመሰግናል፡፡ ቀድሞውኑ አሰፋ ከማን ጋር ሊሰራ እንደሚችል ስለሚያውቅ በሰው ሀይል በኩል ብቃት የነበራቸው ሰዎች አጠገቡ ነበር፡፡
አሰፋ ጎሳዬ፣ ለማነጋገር ይቀላል፡፡ሁሉም ጓደኞቹ ስለ አሰፋ ሀሳብ ስጡ ሲባሉ ፣ያቺን ፈገግታውንና ቀለል ማለቱን አይረሱም፡፡ በዚህ ምክንያት አሰፋ የፈለገውን ተግባራዊ ለማድረግ አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮለታል፡፡ ላለፉት 18 አመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣን በመስራችነትና በዋና አዘጋጅነት ያገለገለው ገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን ይህን የአሰፋን ቀለል ብሎ መገኘት ያደንቃል፡፡
‹‹አዲስ አድማስ›› ሲመሰረት ከነበሩ ጋዜጠኞች አንዱ ሰለሞን ገብረእግዚአብሄር በቁጥር በርከት ያሉ ጽሁፎችን ‹‹አዲስ አድማስ›› ላይ ጽፏል፡፡ ብዙ በመጻፉም ብዙ መማሩን ያውቃል፡፡ ለዚህ ደግሞ አሰፋ ትልቅ ምስጋና ሊቸረው ይገባል ይላል ሰለሞን፡፡
ሸራተን ሆቴል በተመረቀ ማግስት፣ ህዝቡ የነገስታትና የባለስልጣናት ማረፊያ ነው ብሎ ድምዳሜ ላይ በደረሰበት ሰአት አሰፋ በዚህ አዲስ ሆቴል ውስጥ አንድ ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት ሀሳብ ያደርጋል፡፡ የሆቴሉን አዳራሽ ተከራይቶ ከሀምሌ 1-5
1990 ያቀረበው
የኮምፒውተርና
የኮምፒውተር
እቃዎች
ኤግዚቢሽን
የአሰፋ
ጎሳዬ
ልዩ ሰው መሆን የታየበት ሌላው ስራ ነበር፡፡ የአሰፋ የፈጠራ ስራዎች የሚመነጩት አንድ በአንባቢነቱ ሲሆን ሌላው በተፈጥሮ ከተቸረው የአእምሮ ስጦታ ነው፡፡
ይህ ታላቅ ሰው ታህሳስ 6 1997 የዛሬ 17 አመት በተወለደ በ46 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡
መዝጊያ ይህ መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን መስራችን አቋም የሚያንጸባርቅና የተወዳጅ ዊኪፒዲያ ቦርድ አባላት ያመኑበት ነው፡፡
አሰፋ ጎሳዬ በተለይ ለሰው ልጅ ልዩ ክብርና ፍቅር ያለው ቸር ሰው መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ በሚድያው ኢንዱስትሪ ላይ ደግሞ የንባብ ፍቅር ያሰረጸችውን አዲስ አድማስ ጋዜጣ የፈጠረ ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ አሰፋ ሰው መፍጠር ይችላል፡፡ ልዩ ክህሎትንም ማጋባት ይችላል፡፡ አሰፋ ከምንም በላይ ያልተጀመረ ነገርን በመጀመር እና ለስኬት በማብቃት ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ታላቅ ሰው ከ 7 አመት በፊት ታትሞ ለንባብ የበቃው መጽሀፍ ብዙ ሀቆችን የያዘ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ስለ አሰፋ ገና ይጻፋል፡፡ / ይህ ጽሁፍ በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ዛሬ ታህሳስ 4 2014 ተጻፈ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ