4. አቢይ አህመድ /ዶክተር/-abiy ahmed /dr/
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የመሪዎች ታሪክ የሚል ፕሮጀክት የዛሬ 7 አመት ነድፎ የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት በንጉስ ምኒሊክ ፤ በጸሀፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ፣በልጅ
እንዳልካቸው
መኮንን
ላይ የምርምር እና የስነዳ ስራዎችን ስንሰራ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በክፍል አንድ የዶክተር አቢይ አህመድን ታሪክ እነሆ ብለናል፡፡ ይህ ግለታሪክ በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግበትና የመሪዎችን በጎ ገጽታ ወይም ለሀገር የሰሩትን የሚያስተዋውቅ ይሆናል፡፡
የተተኪው ማንነት
ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት እኩለ ሌሊት እየተቃረበ እያለ የተሰማው ሰበር ዜና በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ያነጋገረ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ ተተኪያቸው ማን ይሆን? የሚለው በመላ አገሪቱ ዋነኛ መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በተለይ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተተኪውን የግንባሩን ሊቀመንበር ለመምረጥ ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ለአንድ ሳምንት በመቆየቱ፣ በርካቶች በመላ ምቶችና በሴራ ንድፈ ሐሳቦች እንዲጨናነቁ አድርጓቸዋል፡፡ የአገሪቱ ፖለቲካ ለትንተና እስከሚያስቸግር ድረስ የተለያዩ መረጃዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመሰማታቸው፣ የተተኪው ማንነት ብዙዎችን ቢያሳስብ አይገርምም ነበር፡፡ ሰዎች በአካል ተገናኝተው ከሚለዋወጡት ሐሳብ ጀምሮ፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የነበረው ውዝግብና ግራ መጋባት የተተኪው ማንነት ላይ ያነጣጠረም ነበር፡፡ ሰበር ዜናው ከተሰማ በኋላ ግን በርካታ ግምቶችና ትንተናዎች ፉርሽ ቢሆኑም፣ ውጤቱን በተለያዩ ስሜቶች በሚጠበቁት ዘንድ ግን መገረምን ፈጥሯል፡፡
ከበሻሻ እስከ አራት ኪሎ
የአብይ አህመድ (ዶ/ር) ወላጅ አባት አባ ዳብስ አባ ፊጣ (አህመድ ዓሊ)ልክ እንደ አብዛኛዎቹ የአገሪቱ ከተሞች በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በምትገኘው የገጠር ከተማ በሻሻ ኑሮው የሰከነና የተረጋጋ ነው፡፡ ከ6,000 በላይ ለሆኑ ነዋሪዎቿ መጠለያ የሆነችው የበሻሻ ከተማ፣ በአገሪቱ እየተካሄደ ካለው የፖለቲካ ውጥንቅጥ ርቃ የምትገኝ ትመስላለች፡፡
የበሻሻ ከተማ ላለፉት 3 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል የብዙኃኑን ሕይወት ቀጥፎ የበርካቶችን ንብረት ባወደመው ብጥብጥና ተቃውሞ ብዙም የተነካች አትመስልም፡፡ ሕይወት እንደ ወትሮ ቀጥሏል፡፡ ንግዱም እንደ ጦፈ ነው፡፡ ከሌሎች የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለየ ሰዎች በእርጋታ ወጥተው ቡናቸውን ሸጠው ይመለሳሉ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኘው በሻሻ ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያላትና የአገሪቱንም ሆነ የወጪ ንግዱን በዋናነት በሚያንቀሳቅሱት ቡናና ጫት የታደለች ናት፡፡ በዚህም ምክንያት አብዛኛው ማህበረሰብ ከእነዚህ ምርቶች በሚያገኘው ገቢ ነው የሚተዳደረው፡፡
በበሻሻ ወጣቶች ቀጣዩ ሀብታም የቡና ነጋዴ ለመሆን፣ መኪና ለመግዛትና ከአዲስ አበባ 497 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አጋሮ ከተማ ወጥተው ሌላ ንግድ ለመጀመር ያልማሉ፡፡
የበሻሻ ነዋሪዎች በአብዛኛው ሙስሊም ሲሆኑ፣ ልጆችም ቁርዓን እየቀሩ ያድጋሉ፡፡ ምንም እንኳን የክርስቲያንና የሙስሊም ማኅበረሰቡ ክፍሎች ተጋብተውና ተዋልደው የኖሩ ቢሆንም፣ በከተማዋ አሳዛኝ ክስተት ማጋጠሙ አይዘነጋም፡፡
በሻሻ በቡና ንግድ የታወቀች ብትሆንም ብዙዎች የሚያስታውሱት በሙስሊሙና በክርስቲያን ማህበረሰብ መካከል በጥቅምት 1999 ዓ.ም. ተፈጥሮ የነበረው ግጭት፣ የዚህችን ትንሽ የገጠር ከተማ ስም በተደጋጋሚ እንዲጠራ አድርጓል፡፡ በተለይ በአክራሪ ሙስሊሞች አነሳሽነት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ በተቃጣ ጥቃት በርካቶች መሞታቸው አስከፊ ትዝታ ነው፡፡
በጊዜው የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ጉዳዩን ካረጋጋ በኋላ ለዘመናት አብረው ከመኖር በላይ በሰላም የሚኖሩ፣ በድንገት ወደ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ የገቡትን የአካባቢውን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለማስታረቅ ዕቅድ ይነደፋል፡፡
በዚህን ጊዜ ነው ታዲያ ከ10 ዓመታት በፊት የፌዴራል መንግሥት የዕርቀ- ሰላሙ አስፈጻሚ በማድረግ፣ የ34 ዓመቱን አፍቃሬ ቴክኖሎጂ የሆኑትን ወጣት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከውጤት ጋር እንዲመለሱ ወደ አካባቢው የላከው፡፡
ይህም አጋጣሚ በወቅቱ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን ወጣቱን ዓብይ፣ በተወለዱበት ሥፍራ አስታራቂ ሆነው በመሄድ ባስመዘገቡት አርኪ ውጤት ትኩረት ውስጥ እንዲገቡ አደረጋቸው፡፡
‹‹……በወቅቱ ከተደረገው ዕርቅ በኋላ በሁለቱ ማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል ግጭት ቀርቶ በጠላትነት መተያየት የሚባል ነገር እንኳን የለም፤›› ሲሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩ የ76 ዓመት አዛውንቱ አቶ ብርሃኑ ሀብተ ማርያም ጉዳዩን ያስታውሳሉ፡፡ በወቅቱ በተፈጸመው ጥቃት ተጋላጭ የነበሩት አቶ ብርሃኑ በዕድል እንደተረፉም ይናገራሉ፡፡
‹‹ዓቢይ ነበር የዕርቁ ዋነኛ ተዋናይ፤›› ሲሉ የሚናገሩት ደግሞ፣ ኢማሙ አብዱልከሪም መሐመድ ናቸው፡፡
በእርግጥም ይህ ክስተት ነበር ዓቢይ የዶክትሬት ዲግሪ ጥናት የሠሩበትን ርዕስ እንዲመርጡ ያነሳሳቸው፡፡ ‹‹የማኅበረሰብ ካፒታልና በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ግጭቶችን ለመፍታት ያለው ሚና በጅማ ዞን በነበረ ሃይማኖታዊ ግጭት›› የሚል ነበር የጥናታቸው ርዕስ፡፡
ዓብይ አህመድ የ1966 ዓ.ም. አብዮት ከፈነዳ በኋላ ስለተወለዱ በልጅነታቸው ‹አብዮት› በሚል መጠሪያ ነበር የሚታወቁት፡፡ በርካታ ቁጥር ካለው ቤተሰብ የተገኙት ዓብይ፣ አራት ሚስቶች ካሏቸው አባታቸው 13ኛ ልጅ ናቸው፡፡ ዓብይ በአካባቢያቸው የተከበሩ ሽማግሌ የሆኑትና ለበሻሻ ክሊኒኮች እንዲገነቡና የስልክ አገልግሎት ይገባ ዘንድ፣ የቡና ተክል መሬታቸውን ለመስጠት ያላቅማሙት የአህመድ አባ ፊጣ ወይም አባ ደብስ አባ ፊጣ ልጅ ናቸው፡፡
አባ ደብስ አባ ፊጣ ለአካባቢያቸው እጅግ ብዙ አስተዋፅኦዎችን ማድረጋቸውን፣ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ አውቃቸዋለሁ የሚሉትን አቶ ብርሃኑን ጨምሮ በርካታ የበሻሻ ነዋሪዎች ይመሰክራሉ፡፡
የዓብይ እናት ወ/ሮ ትዝታ ወልዴ ይባላሉ፡፡ ከቡራዩ የተገኙት ወ/ሮ ትዝታ ለዓብይ አባት አራተኛ ሚስት ሲሆኑ፣ ስድስት ልጆች ወልደዋል፡፡ ዓብይ ደግሞ የመጨረሻ ልጅ ናቸው፡፡
‹‹ልጅ እያለ ቁርዓን ሲቀራ እጅግ ጎበዝ ነበር፣›› ሲሉ አቶ አህመድ ስለልጃቸው ያስታውሳሉ፡፡ ‹‹ሁሌም ቢሆን መማር፣ ማጥናትና ከታላላቆቹ ጋር መዋልን የሚወድ ነበር፤›› ይላሉ፡፡
ከመንፈሳዊ ትምህርቱ ጎን ለጎን ዓብይ ትምህርታቸውን በበሻሻ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ይከታተሉ ነበር፡፡ በሻሻ እስከ ስድስተኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ፣ 17 ኪሎ ሜትር ወደምትርቀው አጋሮ ከተማ ሄደው ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ዓብይ ወጣት እያለ ለጓደኞቹ ምሳሌ መሆን የሚወድ ነበር፣ እንዲያጠኑና እንዲማሩ ይገፋፋቸው ነበር፤›› ሲሉ ታላቅ እህታቸው ወ/ሮ ጥሩዬ አህመድ ያስታውሳሉ፡፡
ቡና በመሸጥ ሀብታም መሆንን ከሚያልሙት ጓደኞቻቸው ዓብይ ልዩ እንደነበሩ እህታቸው ያወሳሉ፡፡ ጓደኞቻቸው ሁሉ እንደሚሉት በትምህርት ነፃ አውጭነት በፅኑ ያምኑ የነበሩት ወጣቱ ዓቢይ፣ ወደ ፖለቲካው የተቀላቀሉት በለጋ ዕድሜያቸው ነበር፡፡ ወቅቱ አገሪቱ ከደርግ አገዛዝ ተላቃ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መራሹ መንግሥት ሥልጣን ለመያዝ ዋዜማ ላይ ነበር፡፡
ለ17 ዓመታት በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት የተሰላቹ የፖለቲካ ኃይሎችም፣ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን በጠረጴዛ ዙርያ የተቀመጡበት ወቅት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ እንደ ኸርማን ኮኸን ያሉ ታዋቂ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አገሪቱ ውስጥ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማምጣት የሚደረገውን ውይይት ከጀርባ ሆነው ይደግፉ ነበር፡፡
በወቅቱ በአገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን በዋናነት ይወያዩ የነበሩት አሁን ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን)፣ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነበሩ፡፡
ሆኖም በኦሮሚያ ክልል ሰፊ ተቀባናይነት ከነበረው ኦነግ ጋር የሚደረገው ድርድር ፍሬያማ መሆን ሳይችል ሲቀር፣ እንደ ኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ያለ አማራጭ ኦሮሚያን የሚወክል ድርጅት እንዲሆን ተቋቋመ፡፡
የወቅቱ ምስክር ሆነው ያለፉ ሰዎች ልክ እንደ ሌላዎቹ የኦሮሚያ አካባቢዎች፣ አሁን ከ37,000 በላይ ነዋሪዎች ያሉባት አጋሮ ውስጥም ኦነግ ከፍተኛ ድጋፍ ነበረው ይላሉ፡፡
በዚህ ወቅት የዓብይን ቤተሰብ ቀጥተኛ ተጠቂ ያደረገ ክስተት ይፈጠራል፡፡ የዓብይ አባት ከታላቅ ልጃቸው ከአቶ ከድር አህመድ ጋር ተይዘው ይታሰራሉ፡፡ ይሁንና አባትየው ሲፈቱ አቶ ከድር ግን ይገደላል፡፡ ግድያው በፖለቲካ ቂም ተነሳስተው ሌሎች ወገኖች የፈጸሙት ድርጊት እንደሆነም ለቤተሰቡ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች ይናገራሉ፡፡ በጊዜው አጋሮ ለኦነግ ፅኑ መሠረቱም ነበረች፡፡
‹‹የወንድሙ መገደል ለዓብይ ሕይወት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብዬ አስባለሁ፤›› ሲል የዓብይ የልጅነት ጓደኛ አቶ ሚፍታህ ሁዲን አባ ጀበል ይናገራል፡፡ ‹‹ወጣቶች ስለነበርን አንድ ማታ ዓብይ ጠርቶኝ ትግሉን እንቀላቀል አለኝ፡፡ እውነት ለመናገር የሚለውን ለመረዳት ለእኔ እጅግ ከባድ ነበር፤›› ብሏል፡፡ ከዚያ በኋላ ዓብይ በ1982 ዓ.ም. ደርግ ከመውደቁ ከጥቂት ወራት አስቀድሞ በ15 ዓመታቸው ኦሕዴድን መቀላቀላቸውን በርካታ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ድምፃዊ ጌትሽ ማሞ ከዓብይ ጋር ከልጅነት ጀምረው የሚተዋወቁ ሲሆን፣ ኦሕዴድን አብረው እንደተቀላቀሉ ይናገራል፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ በጣም ወጣቶች ነበርን፡፡ እኔ፣ ዓብይና አንድ ቆሚጣስ እያልን የምንጠራው ሾፌር ነበርን፤›› ሲል ቢፍቱ ኦሮሚያ የሚባለው የኦሕዴድ የሙዚቃ ቡድን አባል የነበረው ጌትሽ ያስታውሳል፡፡ ‹‹ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ጋርም እጅግ ቅርብ ነበርን፤›› የሚለው ጌትሽ፣ ዓብይ ያኔ የሬዲዮ ቴክኒሻን እንደነበሩ ያስረዳል፡፡
በፖለቲካውና በውትድርናው ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ምክንያት ዓብይ ወደ ሩዋንዳ የዘመተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ሠራዊት አባል ሆነው ተልከዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ በሩዋንዳ ከ1985 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. ሲዘልቅ በ1987 ዓ.ም. የተመለሱት ዓብይ፣ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከተሠለፉት የሠራዊቱ አባላት መካከል በሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያነት ነበሩበት፡፡
በውትድርናው ዓለም እስከ 2000 ዓ.ም. የቆዩት ዓቢይ፣ የሻለቅነት ማዕረግ እስከ ማግኘት ደርሰዋል፡፡ በ2008 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ካቢኔ አባል ሆነው ሲቀርቡ አጭር የሕይወት ታሪካቸው ላይ ይህ ማዕረግ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ በተለያዩ ዘገባዎች ደግሞ ሌተናል ኮሎኔል መድረሳቸው ይነገራል፡፡
በ2000 ዓ.ም. ነበር የአገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመው የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተቋቋመው፡፡ ባላቸው የሬዲዮ ግንኙነትና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እውቀት ዓብይ ከመሥራቾቹ አንደኛው እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በኤጀንሲው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች የሠሩት ዓብይ፣ የለውጥ ኃይል እንደነበሩም ይነገርላቸዋል፡፡
እስከ 2002 ዓ.ም. ዓብይ በኤጀንሲው የቆዩ ሲሆን፣ በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት በተጠባባቂ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡ በ2002 ምርጫም ተሳትፈው አጋሮ ወረዳን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠዋል፡፡
ትምህርት
አዲስ አበባ የሚገኘው የአመራር ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም፤በእንግሊዝ ለንደን ከሚገኘው ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ጋራ በጥምረት በሚሰጡት Transformational Leadership and Change with Merit የትምህርት ዘርፍ፣ የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ተከታትለው፣ሁለተኛ
ዲግሪያቸውን
ያገኙት
ዶ/ር አብይ አሕመድ፥በ2013
ደግሞ
አሽላንድ
ሊድስታር
ከተባለ
ዩኒቨርሲቲ
ተጨማሪ
የድህረ
ምረቃ
ትምህርታቸውን
(management of Business Administration) በMBA በመከታተል ሌላ የሁለተኛ ዲግሪ ማግኘት ችለዋል። በመጨረሻም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከInstitute for Peace and Security Studies የዶክትሬት ድግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ከበሻሻ እስከ አራት ኪሎ
ዓብይ ለአጋሮ ወረዳ ዕድገት ኢንቨስተሮችን በማሰባሰብ አስተዋፅኦ ያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ በሸራተን ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ጭምር እንዲዘጋጅ ማድረጋቸው ይነገራል፡፡ ዶ/ር ዓብይ በተመረጡባቸው በእነዚህ ጊዜያት በሻሻ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሠራ ሲሆን፣ አጋሮ ደግሞ ሆስፒታል አግኝታለች፡፡
‹‹ብዙ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ፈጽሟል፤›› ሲሉ በአጋሮ ኢንቨስተርና የሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ደበላ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ ጅማና አጋሮን ለሚያገናኘው መንገድ ቃል ቢገባም እስካሁን አልተሳካም፤›› ብለዋል፡፡
የሚድያ ሰዎች በሥፍራው ተገኝተው መታዘብ እንደቻሉት ምንም እንኳን አካባቢው በግብርና ምርቶችና በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ቢሆንም፣ ምቹ የሆኑ መንገዶች ባለመኖራቸው መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የሚመጡ ሰዎችን ተስፋ ያስቆርጣል፡፡
‹‹አካባቢው
ደካማ
የመንገዶችና
የኤሌክትሪክ
ኃይል
መሠረተ-
ልማት
ስላለው
ችግሮች
ይገጥሙናል፤››
ሲሉ የጎማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሬይስ ዓሊ ይናገራሉ፡፡ የአካባቢው ማኅበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲገባለት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ቢከፍልም፣ ሰባት ዓመታት ሙሉ በጥበቃ ላይ መሆኑም ይነገራል፡፡
ምንም እንኳን ዓብይ ለቴክኖሎጂ ፍላጎትና ቅርበት ቢኖራቸውም፣ በእነዚህ ጊዜያት ከሌሎቹ የምክር ቤት አባላት በተለየ ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን አብጠልጥለው በማንበብ፣ የተድበሰበሱ ሪፖርቶችን በመተቸትና የሰላ አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ፡፡
ከዚህ በመቀጠል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ዓብይ፣ ከሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው በለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሆኑ ተሾሙ፡፡
በሚኒስቴሩ ለአንድ ዓመት ያህል ቢቆዩም፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲን እንደገና በማዋቀር በሚኒስቴሩ ሥር በማድረግ የኤሮ ስፔስ ኢንስቲትዩት ብለው ሰይመውታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ዶ/ር ዓብይ ሚኒስቴሩን በፖለቲካ ብቻ ከሚነዳ ተቋምነት ወደ ምርምር ማዕከልነት አሳድገውታል የሚሉ አሉ፡፡
ዓቢይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ የማዕከሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ዋሲሁን ዓለማየሁ፣ ‹‹ዓብይ ለትምህርት ያላቸው አመለካከትና ቆራጥነት ውስጤ የቀረ ማንነታቸው ነው፤›› በማለት ያስታውሷቸዋል፡፡
አቶ ዋሲሁን እንደሚሉት በአገሪቱ ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሽፕ) እንዲኖር በማድረግ፣ ሠራተኞች መማር የሚችሉበትን ዕድል ያመቻቹ ናቸው፡፡ ‹‹ሁሌም ቢሆን እንድንማርና ራሳችንን እንድናሳድግ ያበረታቱን ነበር፤›› ይላሉ አቶ ዋሲሁን፡፡
በዓብይ አህመድ በተጀመረው የትምህርት ዕድል መሠረት 1,500 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች፣ በተለያዩ አገሮች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ ይላሉ፡፡ አቶ ዋሲሁን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በውጭ ቋንቋዎች ክፍል ትምህርት ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡ ‹‹እኔ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቴን ስጀምር ከ3.5 በታች ካመጣሁ ደስተኛ እንደማይሆኑ ገልጸውልኝ ነበር፤›› ሲሉ አቶ ዋሲሁን ያስታውሳሉ፡፡
ዶ/ር ዓብይ ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሄዱ አቶ ዋሲሁንም ተከትለዋቸው በሚኒስቴሩ በሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርነት ተሾሙ፡፡ ‹‹በእርሳቸው አበረታችነት ተነሳስቼ 3.7 ነጥብ አምጥቼ ተመረቅሁ፤›› ይላሉ አቶ ዋሲሁን፡፡
ይሁንና የዶ/ር ዓብይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቆይታ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው መጠነ ሰፊ ተቃውሞና ብጥብጥ ምክንያት በአጭሩ ተቋጨ፡፡ በርካታ የኦሕዴድ የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ክልል ሲሄዱ፣ እርሳቸውም ክልሉን ለማረጋጋት ወደ እዚያው አቀኑ፡፡
ዶ/ር ዓብይ ከሌሎች የኦሕዴድ አባላት ጋር በመተባበር በክልሉ ተንሰራፍቶ የነበረውን ተቃውሞና አመፅ ማርገብ ችለዋልም ይባልላቸዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች አሁን ኦሕዴድ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የሕዝብ ተቀባይነት ማግኘት ችሏል ይላሉ፡፡
ዶ/ር ዓብይ ከሚኒስትርነታቸው ከለቀቁ በኋላ የኦሮሚያ ክልል የከተማና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ከሠሩ በኋላ፣ አቶ አብዱላዚዝ መሐመድን በመተካት የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊም በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከ3 አመት በፊት በተካሄደ የኦሕዴድ ምክር ቤት ምርጫም፣ ዶ/ር ዓብይ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን አቶ ለማ መገርሳን በመተካት ተመርጠዋል፡፡
ምንም እንኳን በስኬቶቻቸው የሚመሠገኑ ቢሆኑም፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲፀድቅ በምክር ቤቱ ሳይገኙ በመቅረታቸው በእጅጉ ሲተቹ ነበር፡፡ ይህም በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ተንፀባርቆ ነበር፡፡
የ45 ዓመቱ ዓብይ በጋብቻ የተሳሰሩት ከወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጋር ነው፡፡ ዶ/ር ዓብይና ወ/ሮ ዝናሽ የተገናኙት ዓብይ ውትድርና ውስጥ በነበሩበት ወቅት ሲሆን፣ ወ/ሮ ዝናሽ የወታደራዊ የሙዚቃ ቡድን አባል ነበሩ፡፡ ዶ/ር ዓብይና ወ/ሮ ዝናሽ ሦስት ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡
ዶ/ር ዓብይን በቅርበት የሚያውቋቸው ለስፖርትና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትኩረት የሚሰጡ እንደሆኑና ወደ ጂምናዝየሞች በመሄድ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ያወሳሉ፡፡ በብዛትም በአዲስ አበባ በቦዲ ዋይዝ ዌልነስና ፊትነስ ሴንተር፣ ቀጥሎም በጥላ ኸልዝ ክበብ ስፖርት ይሠሩ እንደነበር ማወቅ ተችሏል፡፡
ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆን የተመረጡት ዶ/ር ዓብይ፣ አቶ ኃይለ ማርያምን በመተካት ሦስተኛው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡
ዶ/ር ዓብይ በብሔርና በፖለቲካ አመለካከት የተከፋፈለውን ሕዝብ ወደ አንድ በማምጣት ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን መሥራት ትልቁ የቤት ሥራ ይሆንባቸዋል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ዶ/ር ዓብይ የሚሄዱበት የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን መጋቢ ተመስገን ብርሃኑ አንዱ ናቸው፡፡
መጋቢ ተመስገን ተቋማቸውን ሳይወክሉ በግላቸው ስለ ዶ/ር ዓብይ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ዶ/ር ዓብይ እግዚአብሔርን የሚወድ ቅንና ትሁት ሰው ሲሆን፣ ባገኘው ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል መማር የሚወድና ዕድል ሲያገኝም ቃሉን የሚያስተምር ነው፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ዶ/ር ዓብይ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ከመሆኑ በፊት የመንግሥት ሥልጣን ላይ የቆየ ነው፤›› የሚሉት መጋቢ ተመስገን፣ ‹‹ልዩ ትኩረት የማይፈልግና በሥልጣኑም የማይኩራራ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ከእዚያም በላይ ሕዝቡንና አገሩን የሚወድና ከበላይም ሆነ ከበታቹ ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የማይቸገር ነው፤›› ብለዋል፡፡
አገሪቱ ከገባችበት ቀውስ እንድትወጣና ሰላም እንዲመጣ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ሁሉም ቤተ ክርስቲያኖች ሲፀልዩ ነበር ያሉት መጋቢ ተመስገን፣ አሁን እግዚብሔር ፀሎታቸውን ሰምቷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ መጋቢው አክለውም ዶ/ር ዓብይ ብቻቸውን ለአገሪቱ ሰላም ማምጣት ስለማይችሉ፣ አብረዋቸው ያሉት ባለሥልጣናት በአንድነትና በመግባባት እንዲሠሩ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ዶክተር አቢይና ቤተሰባዊ
እይታቸው
በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እይታ ሀገር የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው፡፡ ሀገር ሲባል የቤተሰብ ስብስብ ነው፡፡ ሀገርን የሚመራ ሰው መቼም ከአንድ ቤተሰብ ነው ሊወጣ የሚችለው፡፡ ያ ቤተሰብ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ ቢሆን ቤተሰብ ያው ቤተሰብ ነው፡፡ መጋቢት 24
2010 የሀገራችን
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ሆነው
የተሾሙት
ዶክተር
አቢይ
አህመድ ስለ ቤተሰብ አንድ መልካም እይታ የያዙ ስለመሆኑ በስፋት ይነገራል፡፡ ይህ እይታ በሌሎችም ቢኮረጅ ስል አስባለሁ፡፡ ይህ በጎ እይታ ምንድን ነው? አንድ የሀገር መሪ ስለቤተሰብ ማሰቡ ፣ማውራቱ በቤተሰብ ጉዳይ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ማድረጉ ምን ፋይዳ አለው? እንዲሁም ዶክተር አቢይ በንግግራቸው ቀረብ ስላለው የግል ቤተሰባዊ ህይወታቸው ማውራታቸው ምን የአስተሳሰብ ለውጥ አመጣ? የሚለውን ብዙዎችን ሊያነጋግር የሚችል ይመስለኛል፡፡
ከ1923 ወዲህ የመጡ የሀገራችን መሪዎች ስለሀገራቸው አሊያ ድል አድራጊ ስለመሆናቸው ወይም ደግሞ ስለህዝባቸው ምን እንደሚያስቡ ይናገሩ ነበር እንጂ ቤተሰባዊ ህይወታቸውን እያነሱ በዛ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ብዙም አልተለመደም፡፡
በቤተሰብ
ላይ ያላቸው ፍልስፍና ምን እንደሆነ ለማሳወቅ ብዙም ሀሳባቸውን ለመስጠት አይፈልጉም፡፡ በደፈናው ህዝብን ያስባሉ ወይም ስለ ህዝብ ጥቅም ሲባል ሲሉ እሳቤያቸውን ለማስተጋባት ይሞክራሉ፡፡ ምናልባት ከ1923-2010፣ ከዶክተር አቢይ በፊት የነበሩ መሪዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተናግረው ከሆነ መረጃውን ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡ ብዙዎቹ እናቴ እንዲህ ነበረች፣ ባለቤቴ ልትመሰገን ይገባል ብለው የማውራት ባህሉን አለመዱትም፡፡ ወይም የግል ህይወታቸውን ማውራታቸው በተመሪው ዘንድ የሚፈጥረውን በጎ ተጽእኖ አይረዱትም፡፡ ይልቁንም መሪ ከእናት ከአባት ያልተፈጠረ እስኪመስል ድረስ ራሳቸውን እንደ ልዩ ፍጡር የሚመለከቱ መሪዎች ሲመሩን አመታት አልፈዋል፡፡ ያለፉበትን መንገድ መናገርን ወይም የግል ጉዳያቸውን ማብራራትን ገበናን እንደማሳየት አድርገው ያስቡታል፡፡ ወይም ከግለሰብ ታሪክ ይልቅ የድርጅት ታሪክ መቅደም አለበት የሚለውን መርህ ያራምዳሉ፡፡ ምናልባት የባህር ማዶ መሪዎች ቀረብ አድርገው ስለቤተሰባዊ ጉዳያቸው ሲነግሩን ሰምተናል ፡፡ እንደ ባራክ ኦባማ ያሉ መሪዎች በቤተሰባዊ ጉዳይ ለማውራት ደስ የሚላቸው ሰው ናቸው፡፡
በአደባባይም
የቤተሰባቸውን
አባላት
ይዘው
ይታያሉ፡፡
መጋቢት 24 2010 ዶክተር አቢይ በበአለ - ሲመታቸው እለት ያደረጉት ንግግር ለምን ብዙዎችን ሳበ? ተብሎ ጥናት ቢደረግ ለሁላችንም ቅርብ ስለሆነው ቤተሰባዊ ጉዳይ በማንሳታቸው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ምናልባት ቀላል ወይም የአንድ ሰው ጉዳይ ሊመስለን ቢችልም የ100ሚልዮን ሰዎችን ቤት ለማንኳኳት የቻለ ነው፡፡ እናቱን የማይወድ ማን አለ? ለሚስቱ ክብር የሚሰጥ በርካታ ሰው ባለበት ሀገር ይህን ጉዳይ ከማንሳት በላይ ዋና ጉዳይ የለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም መጣ ፤ አልመጣ ሀገር አደገ አላደገ ሁሉም የሚደክመው ቤተሰቡን ከፍ ወዳለ ስፍራ ለማድረስ ነው፡፡ ስለሆነም የቤተሰብ ጉዳይ ዋና ርእሰ-ነገር ቢሆን ላይደንቀን ይችላል፡፡
ብዙ ጊዜ መሪዎቻችንን ልንረዳቸው ወይም ያሉበትን ሁኔታ ልናውቅ የምንችለው እንደኛ ሰው መሆናቸውን ስናውቅ ፣ ቤተሰባዊ ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ስንገነዘብ ብቻ ነው፡፡ አሊያ ግን እንደፈራናቸው ሳንወዳቸው እንዘልቃለን፡፡
አንድን
መሪ ልወደው ወይም ይምራኝ ብዬ ልታዘዘው የምችለው እኔም እንደሆንኩት እርሱም መሆኑን ሳውቅ ነው፡፡ እኔ ትዳር አለኝ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ትዳር አለው ብዬ ማሰብ እንድችል ያደርገኛል፡፡ አንድ መሪ ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ አንድ መሪ ግላዊ ነገሩን በደንብ ስናውቅለት አብረነው ለመተባበር እጃችንን ለማንሳት ከባድ አይሆንብንም፡፡
መጀመሪያ
ዶክተር
አቢይ
በቀላሉ
ሊወደዱ
የቻሉት
በአቀራረባቸው
ብቻ ሳይሆን በሀሳቡ ይዘትም ጭምር ነው፡፡ ይህ ንግግራቸው ትልቅ ግብ ሊመታ እንደሚችል ተገንዝበዋል፡፡
የሰውን
ትኩረት
ስበዋል፡፡
ከአሁን
በኋላ
ምንም አይነት የሚሰለች ነገር ቢናገሩ እንኳን ዋናውን ጥበብ ስለያዙ ህልማቸው ግቡን ይመታል፡፡
ዶክተር አቢይ ስለ ወላጅ እናታቸው ሲያስረዱ 3 ቤተሰባዊ ጉዳይን እንድናስብ አድርገዋል ፡፡ ይህም የእናት ፍቅር ፣ ለእናት የሚሰጥ ምስጋና እና ጠንካራ እናት ምን አይነት መሆኗን አሳይተውናል፡፡ በአለ- ሲመታቸው በመላ ሀገሪቱ ብሎም በባህር ማዶ በቀጥታ የሚተላለፍ ስለነበር ሰዎች ወይም የቤተሰብ አባላት ተሰባስበው ሲከታተሉት ነበር፡፡ በጥሩ አገላለፅ ሀገር ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን ቤተሰብ መሆኑን በንግግራቸው አስቀምጠውታል፡፡
የእናት ፍቅር
ለእኔ ተምሳሌታዊ አገላለጽ ነው፡፡ እናታቸውን ይወዳሉ ማለት ሀገራቸውን ይወዳሉ ማለት ነው፡፡ እናታቸውን ይወዳሉ ማለት ለቤተሰባዊ ግንኙነት ትርጉም ይሰጣሉ ማለት ነው፡፡ ይህን ሰፋ አድርገን ስናየው ሰውን እንደ ወዳጅ እንደ ቅርብ የቤተሰብ አባል የማየት አቅማቸው ትልቅ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ የአመራር ፍልስፍና ቀደም ሲልም በሰሩበት መስሪያ ቤት ስኬታማ አድርጓቸዋል፡፡
ቀደም
ሲል ሀገር ማለት ቤተሰብ ነው ካልን በርካታ ቤተሰቦችን የሚመራ ደግሞ ሆደ- ሰፊ ሆኖ ቤተሰባዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ክህሎት ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ ከዚህ አንጻር ጉዳዩ ይበልጥ የገባቸው ይመስላል፡፡ እናም እናታቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ይኖሩ እንደነበር ቢያውቁም ፍቅራቸው ጥልቅ መሆኑን ከንግግራቸው ድምጸት መገንዘብ ይቻላል፡፡
እናም
የራሳቸውን
ቤተሰብ
ወይም
እናታቸውን
በዚህ
መልኩ
ተረድተው ካቀረቧቸው ቀሪውን እናት ምን ያህል ይረዱታል ብለን መጠየቅ እንችላለን፡፡
ታዲያ
እናቱን
የወደደ
ሀገሩን
እንዴት
አይወድም?
ነገሮች
በደግ
አባት
አይን
ያያሉ
ማለት
ነው፡፡
አለም
በአሁኑ
ሰአት
ያጣችው
እንደ
ደግ አባት የሚቆጠር መሪ ነው፡፡ ምንም ቢሆን ደግ መሪ ደግ ነው እንዲሉ እናቱን ደግሞ ደጋግሞ ያመሰገነ መሪ ወንድሙን እህቱን ምን ያህል ከልቡ ሊወድ እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡
ለእናት የሚሰጥ ምስጋና
በጎ ስፋራ ላይ ስንደርስ ምን ያህሎቻን የቤተሰብ አባሎቻችንን እናመሰግናለን? በተለይም አባት እናት አጎት አክስት ብሎም አሳዳጊ የቅርብ ዘመዶች ለፍተውና ጥረው አሳድገው ሲመሰገኑ ደስ ይላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህንኑ ነበር ያደረጉት፡፡
እናታቸውን
አመስግነዋል፡፡ ከእርሳቸው ቤተሰብን ማመስገን
ምን
ያህል
አስፈላጊ
እንደሆነ
እንማራለን፡፡
ብዙ ህዝብ በጎ ነገር ሊማር የሚችለው ከመሪው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወላጅ እናታቸው ክብር ሰጥተው ሲያመሰግኑ
ቤተሰብ
ለአንድ
ሰው ዋና መሰረት መሆኑን መገንዘብ እንችላለን፡፡ ይህን ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ስንመለከተው
ምን
ያህሎቻችን
ሀገራችንን
እናመሰግናለን?
በተለይ
የተማርንበትን
ተማሪ
ቤት፣
ያስተማሩንን
መምህራንን
ብሎም
ቀዬ መንደሩን ያሳደጉንን ጎረቤቶች ምን ያህል ክብርና ምስጋና እንሰጣለን? ዶክተር አቢይ አህመድ በሚያዝያ 8 2010 ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ አንድ ቁምነገር ጣል ማድረጋቸው አልቀረም፡፡ በባህር ማዶ ያሉ ሀበሾችን ሲናገሩ ‹‹ እናት ታማ ዝም ብሎ ማየት ከዛም ስትሞት ለቀብር መምጣት ምን ማለት ነው?›› ሲሉ በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ በጥሩ አገላለጽ ለእናት ሀገራችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ ብለው ነገሩን ከወላጅ እናት ጋር ማዛመዳቸው ብዙዎችን የሚነካ ይመስለኛል፡፡ በባህር ማዶ ያሉ እናታቸውን የሚወዱ ሁሉ ይህን ነገር ቆም ብለው ቢያስቡበት፡፡ እናት መመስገን ያለባት መረዳት ያለባት በሕይወት ሳለች ነው፡፡
ጠንካራ እናት
ብርቱና ለመከራ ፈጽሞ የማትበገር እናት በየቦታው አለች፡፡ ይህች እናት ጥንካሬዋ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስክሯል፡፡ ይህም በተለይ ብዙ እናቶችን ያስደሰተ ጉዳይ ነው፡፡
ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመሰገኑት ወይም ክብር የሰጡት ለባለቤታቸው ነበር፡፡
አንድ
ወንድ
የቤተሰቡ
መሪ ነው ከተባለ ሚስቱን እንዲወዳትና አክብሮት እንዲሰጣት መጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሯል፡፡ 100ሚልዮን ሰው እየሰማ ለዚያውም በአለ-ሲመታቸው ላይ የባለቤታቸውን ስም እየጠቀሱ ማመስገን ቀላል አይደለም፡፡
ለሚሰማው
ሰው ትልቅ ትርጉም ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው ቤተሰቡን ሲመራ ፍቅርና አክብሮት መስጠቱ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ዶክተሩ አሳይተዋል፡፡ እርሳቸው የአንድ ሀገር መሪ ስለሆኑ ተጽእኖ የማድረግ አቅማቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ሰው በእርሳቸው ንግግር ከመነቃቃት ባለፈ አንዳች ቁምነገር መማሩ አይቀሬ ነው፡፡ ልጆች በቤተሰብ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና ፤ ሚስት በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚሰጣት ስፍራ እነዚህ ሁሉ ቦታ እንዳላቸው እርሳቸው ነግረውናል፡፡
የዶክተር አቢይ አስተሳሰብ በሌሎች ሲሰርጽ
አንዱ ከአንዱ በጎ ነገር መማሩ አይቀርም፡፡ ሲጀመር የሚኮረጀው በጎ ነገር ነው፡፡ በመሰረቱ ዶክተር አቢይ የልጅ የሚስት የእናት ጉዳይን ያነሱት እንዲያው ትኩረት ለመሳብ ፈልገው አይመስልም፡፡ ይልቁንም አንድ ባህል እያሰረጹ ነው፡፡ ይህም ቤተሰብን የመውድድ ባህል፡፡ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በተደረገው የሽኝት ስነ-ሰርአት ላይ አንድ ስሜት በግልጽ ይነበብ ነበር፡፡ አቶ ሀይለማሪያም ዶክተር አቢይ ባለቤታቸውን ባመሰገኑበት ሁኔታ እርሳቸውም ስለ ቀዳማይ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ወይም ስለ ባለቤታቸው ተናገሩ፡፡ ተናገሩ ከምል እምባ እየተናነቃቸው አመሰገኗት፡፡ አቶ ሀይለማሪያም 6 አመት ሀገሪቱን ሲመሩ ስለ ቤተሰባዊ ህይወት እንዳላወሩ ያንንም ባህል እያወገዙ ነበር ሀሳባቸውን የገለጹት፡፡ ለዚህ ባህል መሰበር ደግሞ ፣ በቀዳሚነት ዶክተር አቢይ በጎ ባህል አስጀምረውናል ሲሉ ምስጋና ቸረዋቸዋል፡፡ ይህ ነው በጎ ባህል፡፡ ታላቅ ከታናሹ ሲማርና በተጽእኖው ሲማረክ፡፡
መሪ
ስለ ልጆቹ ሲያወራ እስከዛሬ ሰምቼ አላውቅም፡፡ አቶ ሀይለማሪያም ግን ባለቤታቸውን ከማመስገን ባለፈ ልጆቼ የጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ ነን ሳይሉና ሳይኩራሩ በታክሲ ተማሪ ቤት መሄዳቸው ሊያስመሰግናቸው ይገባል በማለት ልጆቻቸውን በህዝብ ፊት አሞግሰዋል፡፡ ይህ ቀላል አይደለም፡፡ አባት ልጆቹን ወይም የቤተሰቡን አባላት በእንዲህ መልኩ ካመሰገነ ትውልዱ ከማማረር ይልቅ የተሰጠውን አሜን ብሎ መቀበልን ይማራል፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በህዝብ ዘንድ መወደድ የቻሉት የቤተሰብ ጉዳይ በማንሳታቸው ነው ፡፡ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ያነሱበት ቦታ እና ጊዜ ወሳኝነት ነበራቸው፡፡ በሀገራችን ሰላም በሚያስፈልግበት
ወቅት
እንደ
ግለሰብ
ሳይሆን
እንደ
ቤተሰብ
መዋደድ
ባለብን
ጊዜ ነበር ያንን ንግግር በበአለ ሲመታቸው ያደረጉት፡፡ ይህ ንግግራቸው ደግሞ ቤተሰባዊ ፍቅርን የሚያመጣ ነው፡፡
ከእኛ ምን ይጠበቃል?
በተለይ ቤተሰብ የመሰረትን ሰዎች አንድ አደራ እንዳለብን ማወቅ አለብን፡፡ የነገ ሰው ከእኛ ቤተሰብ ይወጣል፡፡ የነገ መሪ አንዱ የቤተሰባችን አባል ሊሆን ይችላል፡፡
ዛሬ
የወደድነው
የቤተሰባችን
አባል፣
ዛሬ ክብር የሰጠነው ልጃችን ነገ በተራው ያመሰግነናል፡፡
ስልጣን
ላይ መውጣት ቤተሰብን ፣ወላጆችን በፍጹም እንደማያስረሳ ከዶክተር አቢይ መማር ይቻላል፡፡ ሰው በቀዳሚነት ስለ ሰው ማሰብና ሰውን እንደ ቅርብ ቤተሰቡ መመልከት ሲችል ነው ሀገሩን ይወዳል የሚባለው፡፡ ሀገር ማለት ሰው ነውና፡፡
አቢይ በመከላከያ
ሻምበል አበበ ብርሀኑ እስከ 2000 ድረስ በመከላከያ ውስጥ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ከዚያም
አልፎ አልፎ ይገናኛሉ፡፡ሻምበል
አበበ
ብርሀኑ
ሲኒየር
ናቸው፡፡
እንዲህ
ይላሉ
‹‹…… በማህበራዊ ህይወቱ ከላይም ከታችም ያለው ቁርጠኝነት ጤናማ ነበር፡፡ ሰራዊቱ ውስጥ ስንቆይ ብዙ ነገር አለ፡፡ አንዱ ሊመችህ ይችላል፡፡ ሌላው ደግሞ ላይመችህ ይችላል፡፡ ዶክተር አቢይ ግን በጣም አስተዋይና ተወዳጅ ነበር፡፡ ትልቅ ነው ትንሽ ሳይል ይመክርሀል፡፡ ከስራ ግንኙነት ውጭ መረብ ኳስና ቴኒስ ቴብል ሲጫወት ሲጫወት አውቃለሁ፡፡ ያኔ አቢይ ጠንካራ ሰራተኛ ነበር፡፡ለነገ ብሎ የሚያሳድረው ስራ የለም፡፡ አዲስ አበባም ይሁን ግንባር እያለ አውቀዋለሁ፡፡
ግንባር
እያለም
ድንኳን
ውስጥ
ተቀምጦ
ስራውን
በጥንቃቄ
ይከውናል፡፡
የሚመጣውን
መልእክት
ይቀበላል፡፡
የመጣውን
መልእክት
ማድረስ
ለሚገባው
ሰው ያደርሳል፡፡ ከዚያ ውጭ አጠገቡ ላሉ የሰራዊት አባላት የቀለብ ችግር ቢያጋጥም ፤ ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች እጥረት ቢፈጠር፤ ባለው የዲፕሎማሲ ችሎታ ከሌሎች አጎራባች ሀይሎች ጋር ተነጋግሮ የመርዳትና የመደገፍ ዝንባሌ ነበረው፡፡ እንደ እኔ ከጅምሩ የነበረው ትጋትና ታታሪነት ለዚህ አድርሶታል› የሚል እምነት አለኝ ›› ሲል ሻምበል አበበ ብርሀኑ ምስክርነት ሰጥቷል፡፡
አቢይ ኢንሳ ውስጥ
ከ12 አመት በፊት አቢይን የሚያውቀው ሰው ከዚህ በታች ያለውን ምስክርነት ሰጥቶ ነበር
‹‹…ሳውቀው እኔ ተራ ሰራተኛ እርሱ ደግሞ ተወክሎ ዋና ዳይሬክተርነት ያገለግል ነበር፡፡ ስለእርሱ ሳስብ በጣም ትዝ የሚለኝ ሰራተኛውን ሁሉ ሰብስቦ የጉባኤ ንግግር ያደርግ ነበር፡፡ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ‹‹ ተቃቀፉ›› ብሎ ስለ ፍቅር ይናገራል፡፡ በተለያየ እምነት ያሉ ሰዎችን ያቀራርባል፡፡ልዩነትን ይነቅፋል፡፡ አንድነትን ይሰብካል፡፡ ወታደሩንና ሲቪሉን ያስተቃቅፋል፡፡ በጣም ደስ የሚለው በአመት ሁለቴ ይሰበስበን ነበር፡፡ ያኔ ታዲያ በዋነኛነት የሚናገረው ስለ ፍቅር ነበር፡፡ ሁሉም ሰው በሚሰራው ስራ አይነት ይለያይ እንጂ ሁሉም እኩል እንደሆኑ ይነግረን ነበር፡፡ ›› በማለት የኢንሳው ሰው ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
አቢይን ኢንሳ ሳለ ጀምሮ የሚያውቀው ሰው አሁንም መመስከሩን ቀጥሏል
‹‹…..አቢይ በግል ባህሪውም ቢሆን በጣም ቸር ነው፡፡ የመማር አቅም የሌላቸውን ሴቶች ከራሱ ኪስ ገንዘብ አውጥቶ ያስተምራቸዋል፡፡ ለሰራተኛ መብት ተቆርቋሪም መሆኑን እዚህ ጋር መናገር ያስፈልጋል›› በማለት ሀሳቡን ገልጾ ነበር፡፤
ዶክተር ያእቆብ ሀይለማሪያም አለም አቀፍ የህግ ባለሙያ ሲሆኑ በተለይ ደግሞ አሰብ የማናት ? በሚለው መጽሀፋቸው ይታወቃሉ፡፡ ከ 3 አመት በፊት ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በዶክተር አቢይ ላይ ሊሰራ ለታሰብ ዶክመንተሪ ቃለ-ምልልስ አድርጎላቸው ነበር፡፡ ዶክተር ያእቆብ ያኔ ዶክተር አቢይ ይዘው የመጡትን የይቅርታ ሀሳብ አድንቀዋል፡፡ ጊዜውን ጠብቆ የመጣ ለውጥ ውስጥ የመጡ ሰው ናቸው ሲሉ ዶክተር ያእቆብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይገልጹዋቸዋል፡፡
ዶክተር ያእቆብ ያኔ በሰጡት ሀሳብ የሀገራችን የአገዛዝ ታሪክ የጉልበት ታሪክ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ሀገርን በፍቅር መምራት እንደሚቻል ዶክተር አቢይ አሳይተዋል ሲሉ ዶክተር ያእቆብ ታላቅ አድናቆታቸውን ይገልጻሉ፡፡
ዶክተር አቢይ አህመድ ከመጡ ምን በጎ ነገር መጣ
ዶክተር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ 3 አመት ከ6 ወር ሆናቸው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ብዙ ህዝብ የሚፈልጋቸው ብቻ ሳይሆኑ ለህዝብ በመሰረታዊነት የሚያስፈልጉ እሴቶች ተገንብተዋል፡፡
እነዚህ
በጎ እሴቶች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አቅም የሚሆኑ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያዊነት
ስሜትን
ማስረጽ
ከ1983-2010 በነበረው የኢህአዴግ አገዛዝ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በፍቅርና ከፍ አድርጎ መጥራት እንደ አሳፋሪ ነገር ይቆጠር ነበር፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ አድዋ ላይ በመሪነት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ እንደ አጤ ምኒልክ አይነት አለም የኮራባቸውን ጀግኖች ማወድስ ክልክል ነበር፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ በብሄር መከፋፈል የአንድ ብሄር የበላይነት ነግሶ ከአንድ ብሄር የመጡ ሰዎች በሙስና እና በሌብነት የተሰማሩበት ጊዜ ነበር፡፡ ታዲያ በዚህ ሰአት ኢትዮጵያን እወዳለሁ ብሎ ደፍሮ መናገር የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ነህ ተብሎ የሚያስፈርጅ ነበር፡፡ ስለ ካራማራ ጦርነት ማንሳትና የሶማሌን ጦር በእንዴት ያለ መልኩ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳስወጣው ማውሳት በዚያን ጊዜ ከቶ የማይቻል ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ግን በመጋቢት 24 2010 የበአለ ሲመታቸው እለት የካራማራውን ጀግና ስሙ በሞቀ ስሜት ተሞልተው ጠርተውታል፡፡ ይህ ቀድሞውኑ ኢትዮጵያን በሚወደው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ የደስታ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማንም በላይ ስለ ሀገሩ ቢተርኩለት ፤ ሀገሩን ቢያሞግሱለት ደስ ይለዋል፡፡ ዶክተር አቢይም ራሳቸው በኢትዮጵያ ፍቅር ተቃጥለው ይህን ፍቅር ህዝቡ ላይ ለማጋባት ችለዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም የህዝብ ተቀባይነት ያገኙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
ሀገራዊ መግባባት መፍጠርና ይቅርታ
ዶክተር አቢይ አዲስ ብሂል አምጥተው ነበር፡፡ ይህ ባህል በሀሳብ አለመስማማት ጫካ የነበሩ እንዲሁም በተቃዋሚነት ጎራ በባህር ማዶ ተሰልፈው የነበሩ ሰዎች ኢትዮጵያ ሀገራቸው ናትና እንዲመጡ ጥርጊያ መንገዱን ከፍተዋል፡፡ ውጭ ሆነው ኢህአዴግን ሲቃወሙ የነበሩ ፓርቲዎች ሳይቀሩ ሀገር ቤት በሰላም ገቡ፡፡ በኋላ ላይ ለራሱ ለዶክተር አቢይ ችግር ቢፈጥሩም ዋናው የዶክተር አቢይ ግብ በፍቅርና በይቅርታ የህዝቦችን ግንኙነት ማሻሻል ነው፡፡
ያለፉ መሪዎችን ማክበር
ዶክተር አቢይ ገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቤተ-መንግስት የገቡ እለት የቀደሙ የኢትዮጵያ መሪዎች የራሳቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው መሆኑን መስክረዋል፡፡ ከ2 አመት በኋላ የአንድነት ፓርክ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለእነዚህ መሪዎች ትውልድ የማይረሳው ማስታወሻ እንዲሰራላቸው አድርገውላቸዋል፡፡
ይህም
አሰራራቸው
ፍጹም
ከቂም
በቀል
የጸዳ
አሰራር
በመሆኑ
በብዙዎች
ዘንድ
መደነቅን
አስገኝቶላቸዋል፡፡
ያለእረፍት በመስራት የጠንካራ ተምሳሌት መሆን
ዶክተር አቢይ ስልጣኑን የተረከቡ ሰሞን አንድም እረፍት አልነበራቸውም፡፡ በቀን ውስጥ የሚተኙበት ጊዜም አልነበራቸውም፡፡ በየክልሉ እየሄዱ መንግስታቸው ያሰበውን ለማስረዳት የተቻላቸውን ያህል ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ በየጊዜው መንግስታቸው ፈተና የሚገጥመው ስለነበር ያንን ሁሉ በድል እያለፉ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማስማማት ህዝቦቹንም ለማቀራረብ ተነሱ፡፡ ይህ መነሳሳታቸው በ2012 የኖቤል ሽልማትን ቢያስገኝላቸውም በዋናነት ግን ከ20 አመት በላይ ተለያይተው የነበሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች መገናኘት ችለዋል፡፡ አንድ አባት ለ20 አመት የተለያት ሚስቱን ማግኘት ችሏል፡፡ ይህ ቀላል ስሜት አይባልም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በአረብ ሀገር ስደት ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በአንድ አውሮፕላን አብሮ ይዞ የመጣ ነው ዶክተር አቢይ ፡፡
ዶክተር አቢይ ያለአንዳች እረፍት 3 አመት ከ6ወር ብዙ ለውጦች ለማምጣት ጥረዋል፡፡ እኒህ መሪ ሰኔ 2013 በተደረገው ምርጫ ፓርቲያቸው ብልጽግና አሸናፊ ሆኖ በመስከረም 24
2014 ጠቅላይ
ሚኒስትር
ለመሆን
ችለዋል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ