88. ቅድስት
በላይ-kidist Belay
የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣
በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ
ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች
እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ
መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ
tewedajemedia@gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ
ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ
ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና
ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን
ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ
የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው ይዘከራል፡፡
በሚድያ ዘርፍ ባለፉት 22 አመታት በታላቅ ጽናት ከሰሩት መሀል
ከክልጆች አለም ጀምሮ-ዳይሬክተር የደረሰችው በአሁኑ ሰአት ስዊዘርላንድ ያለችው ቅድስት በላይ ናት፡፡
ትውልድ እና እድገት
ጋዜጠኛ ቅድስት
በላይ በአዲስ አበባ ከተማ ኃይለመለኮት መንገድ (መነን አከባቢ) ተወለደች።የአንደኛ ደረጃን - በፀሀይ ጮራ፣ መለስተኛ ሁለተኛ
ደረጃን በእንጦጦ አምባ( አመሀ ደስታ) ሁለተኛ ደረጃን በእንጦጦ የቀለም፣
የቴክኒክ እና የሙያ (ተፈሪ መኮንን) ት/ቤት አጠናቀቀች። ከጠንካራ ቤተሰብ እንደተገኘች የምትናገረው ቅድስት ፣
ቤተሰቦቿ ላዳበረችው መልካም ስነ ምግባር መሠረት በመሆናቸው ሁሌም አመሰግናቸዋለሁ ትላለች ።
የጋዜጠኝነት ሙያ ጉዞ
በወቅቱ የሀገሪቱ
ብቸኛ ብሔራዊ ጣቢያ በሆነው የኢትዮጵያ ራዲዮ የ “ከልጆች አለም” ፕሮግራም መግቢያ ላይ የሚሰማው ጣፋጭ የሁለት ህፃናት ድምፅ
(አቤሰሎም ታፈሰ እና ሉሊት ታፈሰ) ሲሆን የቅድስት የቅርብ ጓደኛዋ በሆነችው ሉሊት ታፈሰ አማካይነት እግሯ ወደ ታላቁ
የጋዜጠኝነት ሙያ ማምራቱን በትውስታ ትናገራለች። በነገራችን ላይ ነፍሱ በሰላም ትረፍና ዛሬ አቤሰሎም ታፈሰ በሕይወት
ባይኖርም፣ ታናሽ እህቱ ቀልጣፋዋ ሉሊት በጄኔቫ በUNHCR
በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰራች ትገኛለች፣ እናም በዚህች ጓደኛዋ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ራድዮ የከልጆች አለም ፕሮግራም
በ1980 ዓ.ም የተቀላቀለችው የያኔዋ ታዳጊ ወጣት ፣ በፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ በአቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ( ጋሽ ሰሌ) የራድዮ
ፕሮግራም አዘገጃጀት፣ በሙያ ስነ ምግባር ጭምር ተኮትኩታ ማደጓን
ትገልፃለች። በወቅቱ በልጅ አዕምሮዋ ለዚህ ታላቅ ሙያ መታጨቷ በእጅጉ እንደሚገርማት የምትናገረው ቅድስት በላይ ፣ የጋዜጠኝነት
መክሊቷን በዚያ ተወዳጅ አንጋፋ ጣቢያ መዘርጋቷን አጠናክራ ቀጠላ በፍሪላንስ ሠራተኛነት በሰራችበት እየተከፈላት መታተሯን
ቀጠለች፣ ቀጥላም ተቋሙ ባወጣው የሠራተኛ ማስታወቂያ ከ 10 አመት
የፍሪላንስ አገልግሎት በኋላ በአማርኛው ክፍል በ1990 ዓ.ም በሪፖርተርነት ተቀጠረች።
የጋዜጠኛ ቅድስት በላይ በኢትዮጵያ ራድዮ፣ ከሪፖርተርነት እስከ
ዳይሬክተርነት ጉዞ
በ ከልጆች አለም
ፕሮግራም ረዳት አዘጋጅ ሆና እየሠራች ባገኘችው እድል በሪፓርተርነት እንደ አዲስ ስትቀጠር፣ ለሙያው ባላት ከፍተኛ ፍቅር፣ በ
ፍሪላንስ አገልግሎቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከፈላት 50.00 ብር ስራ ግብር ተቆርጦ 45.00 ብር ኋላም ብር 100.00 ሲከፈላት
ቆይታ፣ በብር 672.00 ወርሃዊ ደሞዝ በቋሚነት መቀጠልዋ፣
የበለጠ ትጋትዋን እንድትቀጥል እንዳደረጋት
ታስታውሳለች። ንፁህ የሙያ ፍቅር፣ ከፍተኛ የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር በነበረበት ወቅት በሙያው ማለፏ በእጅጉ
እንደሚያስደስታት የምትናገረው ቅድስት ፣ በአዲስ አበባየጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ተቋም ሲመሠረት ከመልካም አለቆቿ ባገኘችው ቀና
ትብብር ተወዳዳሪ ሆና በጋዜጠኝነት እና ኮምዩንኬሽን በራድዮ ጋዜጠኝነት በዲፕሎማ በ1994ዓ.ም ተመርቃ፣ በተቋሙ የውስጥ
የእድገት ማስታወቂያዎች በመወዳደር ከ1995 ዓ. ም ከፍተኛ ሪፖርተር ፣ ከዚያም አዘጋጅ ሆና መስራቷን ትገልፃለች።
በሙያው በተቋሙ
ውስጥ ራሴን ማሳደጌ ያኮራኛል የምትለው ጋዜጠኛዋ፣ በነበራት
ቆይታ፣ የጤና፣ የህግ እና ህብረተሰብ ፣ የ ምን እንጠይቅልዎ፣ የካነበብነው ፕሮግራሞች አዘጋጅ እና ኤዲተር ሆና
ስትሰራ ቆይታ፣ በነበራት መልካም ስነ ምግባር እና የሙያ ብቃት
፣በምክትል ዋና አዘጋጅነት፣ የመዝናኛ ዲፓርትመንት የአማርኛ ፣ ኦሮምኛና እና ትግሪኛ ቋንቋዎች የእቅድ እና ክትትል ክፍል
ኃላፊ በመሆን አገልግላለች። በመጨረሻም ከተቋሙ እስከወጣችበት ቀን ድረስ የኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የመዝናኛ
ዲፓርትመንትበአማርኛ ቋንቋ ማስተባበርያ ፣የፊልም እና ድራማ ምክትል ዳይሬክተር በመሆን ሠርታለች። ከአዘጋጅ ወደላይ
ባሉየእድገት ደረጃዎች ባገለገለችበት ወቅት ከሙያዋ ጎን ለጎን ከልጅነቷ የጀመረችውን ይህን ክቡር የጋዜጠኝነት ሙያ በእውቀት
ለማዳበርም፣ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተመሳሳይ በጋዜጠኝነት እና ኮምዩንኬሽን በራድዮ ጋዜጠኝነት በ2002 ዓም በዲግሪ
ተመርቃለች።
ጋዜጠኝነት እጅግ
የተከበረ ሙያ ነው የምትለው ቅድስት በላይ ፣ እንደ እርሷ በሚዲያ ተቋም ውስጥ የማደግ እድሉ ለገጠማቸው ሰዎች ባማረ
ስነምግባር ሕይወታቸውን መምራት ያስችላል ብላ ታምናለች። እንደ ዛሬ የመገናኛ ብዙሀን ባልበዛበት ዘመን በጥራት እና በብቃት
የሙያው ትሩፋቶች አየተመረቱ በሚወጡበት ፣ ተቀባዮች በሚከበሩበት፣ የጋዜጠኛው ሰብእና በአለቆች እይታ ስር በሚያልፍበት፣ መከባበሩ መተሳሰቡ፣ ቤተሰባዊ ፍቅሩ
በነገሰበት ወቅት ሀገሯን ያውሞ በዚህ ክቡር ሙያ በማገልገሏ በእጅጉ እንደምትኮራ አልሸሸገችም።
የቤተሰብ ትስስር በኢትዮጵያ ራድዮ
ለጋዜጠኛ ቅድስት
በላይ የኢትዮጵያ ራዲዮ ሌላው ያደገችበት ቤት በመሆኑ በልቧ በደማቅ ብእር ታትሞ የሚኖር መሆኑን በአፅንኦት
ትገልፃለች።ከ”ከልጆች አለም ፕሮግራም” ጀምሮ በተለያዩ በሠራቻቸው ፕሮግራሞች አብረዋት የተጓዙትን በርካታ የሙያ አጋሮቿን በሙሉ ሁሌም እንደምታመሰግን እየገለፀች፣ በተለይ
ግን በሙያው የተበላሸውን እያቃኑ ለመብቷም አየተከራከሩ ንፁህ ፍቅራቸውን የለገሷትን አለቆቿን ማመሰገን ትሻለች፣ እናም
በተለያየ ግዜ በሀላፊነት የመሯትን ፣ አቶ ሰለሞን ገ/ ስላሴ፣ ወ/ሮ ትሩፉት ገብረየስ፣ ወ/ሮ ስርአት አስፋው፣ ወ/ሮ
አባይነሽ ብሩ፣ ወ/ሮ ፀሀይ ተፈረደኝ፣ ወ/ሮ ሰሎሜ ደስታ ፣ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ አቶ ደጀኔ ጥላሁን፣ አቶ ወንድሙ
ከበደ(ነብስ ይማር)፣ አቶ ዋጋዬ በቀለ ፣ አቶ ፈቃደ የምሩ(የኢትዮጵያ ራድዮ ስራ አስኪያጅ) አቶ ሰለሞን ተስፋዬን፣
እግዚአብሔር ያክብርልኝ ብላለች።
የጋዜጠኝነት ሙያ በእጅጉ በጥንቃቄ የሚሰራበት ጊዜ ነበርና ያኔ በእኛ
ዘመን በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ለመምራት በብዙ ስልጠና እና ልምምድ ነው የወጣነው የምትለው ቅድስት፣ በጊዜው ከበርካታ አመታት
በኋላ በእለተ ረቡዕ የኢትዮጵያ ራዲዮ የምሽት ስርጭት ለመጀመሪያ ግዜ በቀጥታ ስርጭት እጄን ይዞ የወጣውን ልዩ እና ተወዳጅ
የኢትዮጵያ ራዲዮ የወርቃማው ግዜ ምርጥ ጋዜጠኛ የነበረውን ታምራት አሰፋን ግን መቼም አልረሳውም ትላለች። (ታሜ ነፍስህ
ከፃድቃን ሰማእታት ጋር በሰላም ትረፍ! ) በነበረኝ ቆይታ ንፁህ ፍቅራቸውን ለለገሱኝን የዜና፣ ክፍል፣ የትምህርታዊ እና
የመዝናኛ ማስተባበርያ ሠራተኞች በሙሉ አክብሮቴ ይድረስልኝ ትላለች።
በኢትዮጵያ ራዲዮ
፣ ከጋዜጠኞቹ
ባሻገር አንቱ የተባሉ የቴክኒክ ክፍል ሙያተኞችም ቅንነታችሁ፣ ትእግስታችሁ የሙያ ስነ-ምግባራችሁ እና ፍቅራችሁ
በልቤ ታትሞ ይኖራልና፣ ባላችሁበት ሰላም ሁኑልኝ፣ በአፀደ ስጋ የተለዩንን ደግሞ ነብስ ይማር ስትል አክላለች። በኢትዮጵያ
ራዲዮ በመጀመሪያው የአገልግሎት ዘመኗ በጣቢያው በሚተላለፉ
የተለያዩ የማህበራዊ እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ጠንካራ የብዕር ትሩፋቶች
ተሳትፎ የነበራት ቅድስት፣ በአድማጮች ዘንድ በጣም ስሟ በመለመዱ በወቅቱ ከ 150 በላይ የብዕር ጓደኞች
እንደነበሯት በጥሩ ትውስታ ትናገራለች። በጊዜው ከነበሯት የብእር ጓደኞች መካከልም 80% የቀድሞ ሠራዊት አባላት በመሆናቸው
ክብር ይሰማኛል ትላለች።
ጋዜጠኝነት እና የዘር ውርስ፣
ጋዜጠኝነቴን በዘር
የወረስኩት ይመስለኛል የምትለው ቅድስት በላይ፣ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ “ አሐዱ ሳቡሬ፣ አጠገበኝ ወሬ” ሲሉ የተናገሩለት
የእውቁ ጋዜጠኛ እና ዲፕሎማት አምባሳደር አሐዱ ሳቡሬ አጎትዋ በመሆናቸው ሙያውን በዘር የወረስኩት ያህል ይሰማኛል በተለይ
ከዘመናት በኋላ እኔም ከምወደው ሙያዬ የተገፉሁበት ታሪክ ግጥምጥሞሽ የዘር ውርስ ያደርገዋል ትላለች። አሐዱ ሳቡሬ የመጀመሪያው
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ፣ የራድዮ ተናጋሪ፣ኤዲተር፣ ኋላም የማስታወቂያ ሚንስቴር -- ሚንስትር ህኖ ሲያገለግል
በአንድ ወቅት በፃፈው ሀተታ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ፣ ተደፈርኩ ብለው በማሰባቸው ለ ስድስት ወራት በግማሽ ደሞዝ ከ አዲስ አበባ
ወደ አሰላ እንዲጋዝ አድርገውት ነበር ያለችው ቅድስት በላይ፣
እሷም ከዘመናት በኋላ ከምትወደው ተቋም፣ ከሙያዋም ጭምር በግፍ መሰናበቷን አጋጣሚ ወደኋላ መለስ ብላ በማስታወስ
ነው።
ዛሬ ሁሉን ትታ
በይቅርታ ልብ ከ2006 ዓም በሀገረ ስዊዘርላንድ ኑሮዋን የምትመራው ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ፣ ይህ በዘር የወረሰችው ያህል
የሚሰማትን እና አብዝታ የምትወደውን የጋዜጠኝነት ሙያ ከተቋረጠበት የማስቀጠል ፅኑ አላማ እንዳላት ትናገራለች። ዛሬ በእኛ
ኢትዮጵያውያን ዘንድ ባለውየሚዲያ /ማህበራዊ ሚዲያም ጭምር/ አጠቃቀም ዙሪያ ብዙ ምክክር ማድረግ ይገባናልም ትላለች።
ጋዜጠኝነት እና ተዛማጅ ግልጋሎቶች
ቅድስት እንደምትለው
የጋዜጠኝነት ሙያ ሁለገብ ያደርጋል፣ በኢትዮጵያ ራዲዮ በነበራት
ቆይታ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች በቀላሉ እንድትሳተፍ አግዟታል። ሴት የሚዲያ ሙያተኞችን በማብቃት በተለያየ ሀገራት
የልምድ ልውውጥ ማድረግን በትልቁ፣ ሙያዊ ስልጠናዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመስጠት ጉልህ ሚና የተጫወተው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ሴት ባለሙያዎች ማህበርከምስረታ ጀምሮ ፣
በአባልነት
በኢትዮጵያ ራዲዮ
እና ቴሌቪዥን ድርጅት የፀረ- ኤችአይቪ/ኤድስ ፅ/ቤትሰብሳቢ/ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያውቁ ፣ ስለ በሽታውም ግንዛቤም
እንዲኖራቸው ያስቻለ ስራ የተሠራበት/
በኢትዮጵያ ራዲዮ
የሀገርህን እወቅ ማህበር ሊቀመንበር በመሆን ፣ ሠራተኞች ስለ ሀገራቸው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ግንዛቤው እንዲኖራቸው
የሚሠሩበትን ተቋም እንዲወዱ፣ የእርስ በርስ ቤተሰባዊ ትስስር እንዲፈጠር ያስቻለ ስብስብ ከባልደረቦቿ ጋር መፍጠር መቻሏ በተቋሙ ውስጥ ከነበራት ቆይታ የማትረሳው መሆኑን ታሠምርበታለች። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2002
ዓም ማብቂያ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ራድዮና ቴሌቪዥን የተሰናበተችው ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ፣ ለ4
ለ4 አመታት በቤት
ከተቀመጠች በኋላ “Vision on Africa” በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በምክትል ስራ አስኪያጅነት ለ አንድ አመት
ካገለገለች በኋላ ፣ በአዲስ አበባ ሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ በኮምዩንኬሽን ዲፓርትመንት ፣ ምክትል የኮሙዩንኬሽን
ኋላፊ በመሆን እየሠራች እያለች ወደ አውሮፓ ጉዞ በማድረግ ከ2006 ዓም ጀምሮ ኑሮዋንበአውሮፓዊቷ ስዊዘርላንድ መጀመሯን
ትገልፃለች። በአሁኑ ሰዓት የምትኖርበትን ሀገር የስራ ቋንቋ
ከመማር ባሻገር ፣ ጣሊያንን ጨምሮ ሌሎች ስካንድኒቪያን ሀገራትን
ባቀፈው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት የሚዲያ ክፍሉን በኃላፊነት
እየመራች ትገኛለች ።
ስለ ሀገሬ ብዙ
አስባለሁ፣ እፀልያለሁ፣ አብዝቼም ወደ ፈጣሪ አለቅሳለሁ፣ የምትለው ቅድስት በላይ ፣ በሀገራችን ጉዳይ በትዕግስትማየት የሚገቡን
በርካታ ጉዳዮች አሉን፣ የሰከነ የሙህራን ውይይትም ያሻናል
ትላለች፣ በኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘናት የምትገኙ የሀገሬ ወጣቶች፣ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ ለመመርመር መሞከር ይገባችኋልና ነገ
ከእናንተ በኋላ ለሚተኩ የዛሬ ህፃናት በጎ ምግባርን ማሻገር የሚያስችሉ በርካታ ሀብቶችአሉንና ሀገርን፣ ቤተሰብን እና
ማህበረሰብን ወዳድ፣ አገልጋይ ትሆኑ ዘንድም በእግዚአብሔር ስም እጠይቃችኋለሁ ስትል ትማፅናለች።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ