87. ብርሀኑ አየለ አክሊሉ-Birhanu Ayele
Aklilu
የማስታወቂያ
ሰው-ብርሀኑ አየለ
የዚህ ታሪክ
አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ
፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ
እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ
የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን
እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia@gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ
ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ
የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር
ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል
ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም
ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው
ይዘከራል፡፡ በማስታወቂያ እና ዶክመንተሪ ዘርፍ ባለፉት 15 አመታት የራሳቸውን አሻራ ካስቀመጡ ባለሙያዎች አንዱ ነው፡፡
ብርሀኑ አየለ፡፡ ብርሀኑ አየለ ማነው?
ትውልድ እና ትምህርት
ብርሃኑ አየለ
አክሊሉ ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺ ኩምሳ ሰኔ 12 1965 ዓ/ም ተወለደ።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በኢትዮጵያ እርምጃ እና
ፈለገ- ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ተማረ።የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ተምሯል።ከቅድሰተ
ማርያም ዩኒቨርስቲ በማርኬቲን የመጀመሪያ ዲግሪውንም አግኝቷል።
ወደ ጽሁፍ አለም ጉዞ
ከልጅነት ጀምሮ
የተለያዩ ፅሁፎችን ለቤተሰቡ እና ለጓደኞቹ በማንበብ ነበር ወደ ስነፅሁፉ ዓለም የገባው ።በፈለገ- ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት
ወስጥ የተለያዩ መፅሐፍትን በመተረክ ደግሞ ከአማርኛ መምህሮቹ ሙገሳን ማግኘት ጀመረ።ይህ የመምህሮቹ ሙገሳ ብርታት ሆኖት
የተለያዩ መፅሐፍትን ለእናቱ እና ለጓደኞቹ መተረኩን ተያያዘው።ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እየተማረ ለሰፈሩ ልጆች ጋዜጣ ሲያነብ
የሰማው አላፊ መንገደኛ ትምህርት መገናኛ ዘዴዎች( ለገዳዲ )ራዲዮ ጣቢያ በመሄድ እንዲወዳደር ጠቆመው።ጥቆማውን ሰምቶ ሄዶ ተወዳደረ
በፍሪላንስ ለመስራት ከተመዘገቡ እኩዮቹ ሁሉ የተሻለ ነጥብ በማምጣት ማንነቱን የበለጠ ወደሚያገኝበት ፈፅሞ ወደተቃኘበት ጣቢያ ተቀላቀለ።
"ቅዳሜን
ከእኛ ጋር እና እሁድን ለአንድአፍታ" በትምህርት አምባ እና ከማስታወሻ ደብተራችን ላይ በንባብ እና በትረካ መሳተፍ
ጀመረ።
የማስታወቂያ እና የዶክመንተሪ ስራ
በ1993 ዓ/ም ላይ
የመጀመሪያውን ማስታወቂያ " ከአንበሳ" ማስታወቂያ ጋር ሰራ ።ሌላ ዓለም ተጀመረ በዚህ የማስታወቂያ ስራ
መነሻነት :–
ከሜጋ
ማሳታወቂያ፣ከሀሌታ ማስታወቂያ፣ከ MT ፣ከሻሎም፣ከሶራ፣ከካክተስ፣ከማንጎ፣ ሞፒክቸርስ፣ከዘኩራ፣ጄሎርድ… እና ከረሱ B2
ማስታወቂያ ጋር እጅግ በርካታ ማስታወቂያዎችን ሰርቷል ለአብነት ያህል
የዳሽን ባንክ
"ዳሽንቫን"፣ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ጉና የንግድ ስራዎች፣አምባሰል ንግድ ስራዎች፣ሐረር ቢራ፣አዋሽ
ወይንጠጅ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ፣አምቦ ውሃ ፣የኢትዮጵያመብራት ኃይል፣የፌደራል የፀረ- ሙስና ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ
ቴሌኩሙዩኒኬሽን፣ዶን ዴታል፣ሮፓክ ኢንተርናሺናል ፣ላይፍ ቦይ ሳሙና
፣ዲኤስቲቪ፣ሕብረት
ባንክ፣ክኖር ዶሮ፣ሶፊ ቡና ማልት፣የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሳተላይት መምጠቅን አስመልክቶ የተሰራው ማስታወቂያ፣ሎሬንዜቲ የውሃ
ማሞቂያ፣አቢሲንያ ስቲልስ፣አቢሲኒያ ፕሮፋይል፣ኦሜጋ የጤና ኮሌጅ፣መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ኬቤ ኢንተርናሺናል፣ትሪፕልኤ
ወረቀት፣ቱሬ የጤፍ ዱቄት ፣የኮካ ምርቶች ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
በዶኪዩመንተሪ
ፊልሞችም ሁሉንም መጥቀስ አሰልቺ ቢሆንም የተወሱነትን ለማሳያ እነሆ
ከሀሌታ ማስታወቂያ
ጋር፣የኢየሩሳሌም ህፃናት ማሳደጊያ፣ኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ፣ኢትዮ ቱሪዝም የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕርግሮግራም ፣አዋሽ
ወይንጠጅ፣የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣
ከሜጋ ማስታወቂያ
ጋር:–
የሶማሌ ክልል
ኢንቨስትመንት ቢሮ፣ትራንስ ኢትዮጵያ፣ጉና ንግድ ስራዎች፣ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣
ከዋልታ ቴሌቪዥን
ጋር በርካታ እና ታላላቅ አገራዊ አጀንዳ ያላቸው ዘጋቢ ፊልሞችን
የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብሔረሰቦች የኑሮ ዘይቤን የሚዳስሱ ሰርግን፣ሃዘንን፣የህግ ስርዓትን፣የአምልኮ
ሂደትን፣የግጭት አፈታትን በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ይቀርብ የነበረው " ሀገሬ" የተሰኘው ሳምንታዊ
ፕሮግራም ላይ ከቀረቡት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
የቦረና ሞገሳ መቃ
ባሳ፣የሶፍ ዑመር ዋሻ፣የግልገል ጊቤ ሁለት የ26 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ ዋሻን ያካተተ ዘመናዊ ስራን የተመለከተ
"ነጩ ቤኒዚን"የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም፣ኮአሜ፣ሺናሻ፣ዛይ፣የጋምቤላ ኢንቨስትመንት፣
የኮንሶ ባህላዊ
የእርከን ስራ፣የአፋር ኮሪደር፣የአትሌቲክሱ መንደር፣
ከሶራ ማስታወቂያ
ጋር :–
የአውስኮድ የመስኖ
ስራ፣የአርጎባ ባህል፣ልማት፣እና የቱሪዝም እንቅስቃሴ፣የኢትዮጵያ የሴቶች ማኅብር፣የአፋር ክልል የልማት፣የቱሪዝም
እንቀስቃሴ፣የባህል ሂደት የሰርግ፣ የሀዘን፣እንዲሁም ጎጂ ባህልን( የሴት ልጅ ግርዛትን) ማስወገድ የተመለከተ
ከኢትዮጵያ ዜና
አገልግሎት ጋር:– የሰላም ሚኒስቴር፣የሲዳማ የተፈጥሮ ገፅታ፣የሶማሌ ክልል መብራት ኃይል፣የፓርኮች ገፅታ ከሰው አንፃር፣
በግል የተሰሩ:–
የሰሜን እዝ
መከላከያ "ጠንካራው ምሽግ" የተሰኘ፣የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የአስረኛ ዓመት የሥራ ጉዞ፣የፋሲካ በዓል አከባበር
በአክሱም ፂዮን፣የሰበታ ከተማ ኮሙኒዩኬሽን ቢሮ
ከካክተስ ማስታወቂያ
ጋር:–
ለመጀመሪያ ጊዜ
የወደ ጨረቃ የመጠቀችውን ኢቲስ1 የተሰኘችውን ሳተላይት የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም
እንዲሁም ከጠቅላይ
ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጋር ተያይዞ የተሰራው:–
ገበታ
ለሃገር ወንጪ፣ጎርጎራ፣ኮይሻ ይጠቀሳሉ።
በሬዲዮ ሥራ የቅዱስ
ጊዮርጊስ የስፖርት ክለብ የሬዲዮ ፕሮግራም በብስራት ራዲዮ ላይ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ጀምሮ ለአንድ አመት አብሮ ሰርቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ
ከኢትዮጵያ በመውጣት ኬኒያ ናይሮቢ በመሄድ" ፍሪ ስታይል" ከሚባልየማስታወቂያ ድርጅት ጋር "
"ኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ የተሰኘ" በአሉበት አገር ኮከብ ይሆናሉ የተባሉ ሙዚቀኞችን የሚያበረታታ በአፍሪካ ባሉ
አገሮች በተመረጡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የተላለፈ የአመት ፕሮግራም በጋራ ሰርቷል።
የበጎ ስራ ላይ
ተሳትፎ:–
ለትምህርት የደረሱ
ግን መማር ያልቻሉ ልጆችን ሙሉ ወጪ ሸፍኖ አስተምሯል፣ ለአቅመ -ደካማ ወገኖች (ጡረተኞች) የበኩሉን ድጋፍ አድርጓል።የዘመኑ
ወረርሺኝ ኮቪድ–19 ባመጣው ችግር ሳቢያ ገቢያቸው ላሽቆለቆለና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖችን ከአብሮ አደጎቹ ጋር በመሆን ድጋፍ
አድርጓል።
እንደ ብርሀኑ እምነት ፤ማስታወቂያም ሆነ ዶክመንተሪ ፊልም
የራሳቸው ዘዬ አላቸው።
የማስታወቂያ ፅሁፍ
አጭር ግልፅ እና የማያሻማ ሊሆን ግድ ነው።የቃላት መደጋገም እና ርዝመት አድማጩን ያሰለቻል።ከጥቂት መንደርደሪያ በስተቀር
ቀጥታ የታለመውን ዒላማ ሊመታ ይገባል።የማስታወቂያ ፅሁፍ ስለ ሚተዋወቀው ምርት፣እቃ፣አገልግሎት አጭር፣ግልፅ፣ሲነበብ አድማጭን የሚመስጥ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች
አስተዋዋቂውም ሆነ ሻጩ እኩል ይጠቀማሉ።.›› በማለት ብርሀኑ ስለ ማስታወቂያና ዶክመንተሪ ያለውን እይታ አብራርቶ ተናግሯል፡፡
‹‹…….እኔ ይህን
ሙያ ያሰጀመሩኝ " የማስታወቂያው ንጉስ" የሚባሉት ጋሽ ውብሸት ወርቃለማሁ ናቸው።በሙያው ይበልጥ የተማርኩት
ሜጋ ማስታወቂያ ሲሆን ልምዱ የዳበረው ሀሌታ ማስታወቂያ ነው።›› በማለትም ይህን ሙያ የቀሰመበትን ስፍራ እንደ አንድ በጎ
ስፍራ ይገልጸዋል፡፡
ብርሀኑ ዶኩዩመንተሪ( ዘጋቢ) ፊልም አተራረክን ከለገዳዲ ራዲዮ ጣቢያ ጀምሮ ነው የተማረው።በተለይ
" ከማስታወሻ ደብተራችን" አዘጋጅ የነበሩት አቶ ገበየሁ እና ወ/ ሮ ዓለምፀሐይ በብርሀኑ የአነባበብ መገራት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡
እንደ ብርሀኑ እይታ የድምፁ ፍጥነት ፅሁፉን ሊከተል ይገባዋል።ፍጥነት እና
እርጋታ የሚወሰነው ፅሁፉ በተፃፈበት እሳቤ መሆን ይኖርበታል። ሲል ከልምድ ያገኘውን እውቀት ተንትኖ ያቀርባል፡፡
‹‹……አንድ ተራኪ
የራሱን የአተራረክ ስልት ሊከተል ይገባዋል።ሌሎችን መምሰል የራስን ችሎታ ያሳጣል፤በሌሎች ድምፅ ተነተርሶ መጓዝ መጨረሻው ኪሳራ ነው።ዋናው የድምፁ ባለቤት አለና።ትረካው ሲተረክ
ከንባብ መለየት አለበት።አድማጭ ከቴሌቭዢኑ መስኮት ሳይነሳ ፊልሙ ሊጠናቀቅ ይገባዋል።ተራኪው ፊደላቱን በጥንቃቄ እና በእርጋታ
እየተከተለ ሲተርከው፣የፅሁፉን ዓላማ ተረድቶ ለተመልካች ያካፍላል ማለት ነው።.›› ምልከታውን ያጋራል፡፡
ስነ ፅሁፍን በተመለከተ :–
አልፋ ከተሰኘ የሥነ
-ፅሁፍ ክበብ ጋር የተለያዩ ሥነ- ግጥም፣አጫጭር ልብ-ወለዶችን አቅርቧል።ሁኔታዎች ሲመቻቹ የግጥም መድብል እና በእጁ ያሉ
ፅሁፎችን አሳትሞ በሌላው መንገድ ከአንባቢዎች ጋር ለመተዋወቅ ምቹ ጊዜን ይጠብቃል
ብርሃኑ አየለ ባለ
ትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ