86፣ቅድስት ክፍለ- ዮሐንስ - Kidist Kifleyohannes

         የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1980ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia@gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው ይዘከራል፡፡ አሁን ከሚድያ ዘርፍ ታሪኳ የሚቀርብላት ሰው ከ30 አመት በላይ በሙያው ዘልቃለች፡፡ ለመሆን ይህች ሴት ማነች? ቅድስት ክፍለዮሀንስ ፡፡

              መወላለድ ወይም መፈጣጠር

ጋዜጠኝነት ለእኔ ልክ እንደ ዶሮና እንቁላል ነው መወላለድ ወይም መፈጣጠር ነው የምትለዋ ቅድስት ክፍለ- ዮሐንስ ጋዜጠኛው ሚዲያውን ይፈጥረዋል/ ይወልደዋል፤ ሚዲያውም መልሶ ጋዜጠኛውን ይፈጥረዋል፤ በሌላ አነጋገር፣ የሚዲያ ባለሙያ ሙያውን ይፈጥረዋል ሙያውም መልሶ ባለሙያውን ይፈጥረዋል! አንዱ አንዱን ያሳድገዋል የምር ጋዜጠኝነት እንዲህ ነው ብዬ አምናለሁ፤ የጋዜጠኝነት ሙያ ሁሌም ከእድገት ጋር የተቆራኘ ሂደት ነው የሚል እምነት አለኝ! (ብዬ አምናለሁ) በማለት ትናገራለች፡፡

         ቅድስት ማነች?

ቅድስት ክፍለዮሐንስ 1953 ዓ ም አዲስ አበባ አራት ኪሎ ተወልዳ አድጋለች።

በአማርኛ ሥነ-ጽሁፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሁፍ በመስራት ላይ ትገኛለች። የተለያዩ ሥልጠናዎችን በጋዜጠኝነትና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ  ወስዳለች። አሁንም  ከሚዲያ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በግሏ በመሥራት ላይ ትገኛለች። በተጨማሪም  በተለያዩ ቦታዎች በበጎ ፈቃደኝነት በማገልገል ላይ ትገኛለች።

        መንደርደሪያ…..

በ1975-1980ዎቹ ተመሳሳይ ፍላጎት ባላቸውና በፈቃደኝነት በተመሰረተ የንባብ ቡድን ላይ ያቀረብኩት የመጀመሪያ ጽሁፌ ወደ ጋዜጠኝነቱ ለመግባት መንደርደሪያ ሆኖኛል የምትለው ቅድስት ይህ ጽሁፍ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ሰዓሊ የነበረው መስፍን ኃብተማርያም የህይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ ነበር፡፡ ጽሁፉ በቱሪስት ድርጅት ሥር ይታተም የነበረው የቱሪዝም  ጋዜጣ ላይ ታትሟል፡፡ በንባብ ቡድናችን ውስጥ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር፣ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ስዩም ተፈራ፣ ባሴ ሀብቴ፣ አውግቸው ተረፈ፣ ደምሴ ጽጌ፣ አላዛር ሳሙኤል፣ ሰዓሊ መስፍን ሀብተማርያም፣ ስንዱ አበበ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ለእኔ ማንነት አስተዋጽኦ ካበረከቱት መካከል ተጠቃሽ ነው፤ የጋዜጠኝነቴንም በር ከፍቶልኛል፡፡ የኃይለመለኮት "ጉንጉን " እና የደምሴ ጽጌ "ፍለጋ" መጽሀፎች በዚህ ቡድን ውስጥ ተጸንሰው እንደተወለዱና ሌሎች በርካታ ስራዎችም  መሰራታቸውን አስታውሳለች።

‹‹እፎይታ›› መጽሔት የመጀመሪያው እትም ላይ "የምድር ባቡርና የእቱ መላምቺ" የሴቶች እግር ኳስ ቡድንን ለስፖርት ዓምድ አዘጋጅታለች ይህም የመጀመሪያዋ ሴት የስፖርት ጋዜጠኛ ሳያደርጋት አይቀርም፡፡ ይህ ስራ የሴቶችን የእግር ኳስ ቡድን እንደገና እንዲንቀሳቀስ መንገድ ከፍቷል፡፡

ስለ ኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ አንጋፋውን የፊልም ባለሙያዎች ሚሼል ፖፖታኪስን በማናገር በእለተ- ሰንበት ጋዜጣ እንዲሁም ብርሃኑ ሽብሩን በእፎይታ መጽሔት በተከታታይነት በመስራት ፊልም ማዕከሉን የሚያነቃንቅ ሥራ ሆኖ በመገኘቱ ሰዎች ከስራ እስኪታገዱ አድርሷል፡፡ 

‹‹…..ከሁሉ በላይ የሚያስደስተኝ ስራዬ ግን የሴቶች የጡረታ መብት እንዲከበር በመንግስት ደረጃ ውሳኔ የተሰጠበት እና ለውጥ ያስገኘው ስራዬ ነው›› ብላለች። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ስራዎቿ ሙሉ ለሙሉ ወደ ጋዜጠኝነት ስራ ከመግባቷ በፊት ተጋባዥ ተዋናይ በመሆን የቴአትር ሙያ ውስጥ በነበረችበት ሰዓት የተሰሩ ሥራዎቿ ናቸው፡፡

ለጋዜጠኝነት ሙያ በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ ሬድዮ፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ ፋና በመቋቋም ላይ በነበረበት ሰዓት አብራቸው እንድትሰራ ጥሪ አቀረቡላት፡፡ ይህ ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ በአገሪቱ ላይ በተለይ አዲስ አበባ በወቅቱ የፖርኖግራፊ መጽሔቶችና ፊልሞች እንደ አሸን በዝተው ነበር፡፡ ይህንን የሚቃወም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ቡድን ተቋቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ስለነበር እሷም የእንቅስቃሴው አካል በመሆን ከመሳተፍ አልፎ ከእንቅስቃሴው አባላት ጋር ትልልቅ ህዝባዊ ስብሰባና ሰልፍ በመምራት በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ጋር በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል፤ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለውጥም ተገኝቷል።ይህ እና ለጋዜጣና መጽሔት ትጽፋቸው የነበሩት ጽሁፎች  በእነዚህ ሚዲያዎች አይን ውስጥ እንድትገባ ሳያደርጋት አልቀረም ፡፡ቴሌቭዥን ለሴቶች ፕሮግራም አንድ ሥራ ካሜራ ማን ተመድቦላት ከቀረጹ በኋላ አየር ላይ ሳይውል ፤ በመቋቋም ላይ ያለውንና ገና ስም እንኳን ያልወጣለትን    ራድዮ ጣቢያ ተቀላቀለች። ስም እንድናወጣ ለሁላችንም የቤት ስራ ተሰጥቶን ነበር።  "ፋና" የሚለው ስም ተስማሚ ሆኖ ተገኘና ፋና ተባለ ያለችው ቅድስት ፤ በራድዮ ፋና የቤተሰብ ሰዓት፣ የከርሞ ሰው (የህጻናት ፕሮግራም) ፣ የጤና ፣ የሴቶችና የስነ- ህዝብ ፕሮግራሞች አዘጋጅና አቅራቢ ነበረች።

የቤተሰብ ሰዓት ፕሮግራም የቤተሰብ ህጉ እንዲሻሻል ከህግ ባለሙያዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደጋጋሚ በጋብቻና ፍቺ ዙሪያ በመስራትና የህግ ክፍተቱን በማየት ህጉ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ካደረጉት አካሎች መካከል አንዱ ነው።

የቤተሰብ ሰዐት ፕሮግራምን ለአራት ዓመት ያለማቋረጥ ያዘጋጀችው ዝግጅት ነው። በርካታ ጉዳዮችንም በቤተሰብ ዙሪያ ዳሷል፡፡ ጋብቻና ፍቺን፣  ቤተሰብ አመሰራረትን፣ ተጥለው የተገኙ ህጻናትን ማሳደጊያ አፈላልጎ ማስገባት፣ በሀሰት የተፈረደ ፍርድን ይግባኝ እንዲጠየቅበት በማስደረግ ውሳኔው እንዲለወጥ ያደረገ፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ማገናኘት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጠለፋ፣  ስለ ፍቅር ግንኙነት፣ የልጆች አስተዳደግ ፣የልጆችና ወላጆች ግንኙነት...ወዘተ በዝግጅት ክፍሉ ከተዳሰሱት መሀል ናቸው። ጦር ሜዳ ሳይቀር አድማጮች የነበሩትና ደብዳቤ ይጽፉላት የነበረ ሲሆን ፤  ከስልክና ደብዳቤ አልፎ ሰዎች በአካል በመምጣት አስተያየትና ችግራቸውን የሚያካፍሉበት   ፕሮግራም ነበር፡፡  

ስኬት

• ቅድስት ከሙያዋ ጋር በተያያዘ ስላስቀመጠቻቸው አሻራዎችና ስኬቶች ስታስብ ሰው ላሳካ ብሎ ከተነሳ የህልሙን እውን እንደሚያደርግ ከራሷ ተነስታ ታስረዳለች፡፡ ያመጣችውንም ስኬት አንድ በአንድ በእንዲህ መልክ ዘርዝራ አስቀምጣለች:

• የሴቶችን የጡረታ መብት እንዲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣ ላይ የወጣ ዜና ትልቅ የውይይትና የንቅናቄ መንፈስ በመፍጠሩ በመንግስት ደረጃ የጡረታ መብታቸው ተከብሮ ማየቴ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ 

• "ተስፋ ጎህ "የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለ ሰዎች ማህበርን ዘውዱ ጌታቸውና ጓደኞቹ በሚያቋቁመበት ጊዜ አብሬ ማህበሩ እንዲቋቋም የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረጌና ብዙዎች ሲገለገሉበት በማየቴ ደስታ ይሰጠኛል፡፡

• በተመሳሳይ ሁኔታ “አዲስ ምዕራፍ” በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ በተለይ ለባለሃብቱና ባለስልጣኑ እንዲሁም በተለያየ ከፍተኛ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች የምክር አገልግሎት የሚያገኙበት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከዘውዱ ጌታቸውና እና ቴዎድሮስ ተሾመ ጋር በመሆን አቋቁመናል- ተሳክቶልናልም፡፡

• ፈርሶ የነበረውን የምድር ባቡርና የእቱ መላምቺ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾችን በእፎይታ መጽሔት የስፖርት ዓምድ ላይ እነ በለጥሽ ገ/ማርያምን በማነጋገር ታሪካቸውን (በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ 16 የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በየክፍለ ሀገሩ ነበር፡፡) በመስራት የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ተነቃቅቶ እንደገና ለምስረታ መብቃቱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡

• ሬድዮ ፋና የቤተሰብ ሰዓት ፕሮግራም ላይ ቀርቦ የነበረ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ እየተንከባለለ የቤተሰብ ጉዳይ በልደታ ከፍተኛ በፍርድ ቤት የተወሰነ ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነና  ሬጅስትራር ጽ/ቤት ኃላፊን በማነጋገር እንደገና ጉዳዩ እንዲታይና  ሚስት ይግባኝ ጠይቃ ለእሷና ለልጆቿ  መወሰኑ ለሥራዬም ለተበተነው ቤተሰብም ትልቅ ስኬት ነበር፡፡ ይህ የቤተሰብ ሰዓት ፕሮግራም በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን የሰራና ለማህበረሰቡ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ነው፡፡ እንደ ሶሻል ወርከር ሁሉ ሆኜ የወደቁ/የተጣሉ ህጻናትን ማሳደጊያ አፈላልጌ እስከማግባት ድረስ እሰራ ስለነበር ስኬታማ ነኘ ብዬ አምናለሁ።

• በርካታ ቤተሰቦችን በማወያየት እንደገና አብሮነታቸው እንዲቀጥል ምክንያት በመሆኔ ከስኬት እቆጥረዋለሁ፡፡ እዚህ ሁሉንም መዘርዘር የሚቻል አይመስለኝም፡፡የስነ ልቦና እና የስነ አእምሮ ፣ የጤና ፣የሕግ የሶሲዮሎጂ ወዘተ ባለሙያዎችን ሬድዮ ፋና ለእኔ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉ በመሆናቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

• ከሁሉ በላይ ሁለት ልጆች ብቻዬን አሳድጌ ለቁምነገር እንዲበቁ ማድረግ ትልቁ ስኬቴ ነው፡፡ ዓለም አቀፉ የዮጋ አሰልጣኝ፣ ተጋባዥ ተናጋሪ ( guest Speaker) እና (Motivational trainer) የክሁል ሁለንተናዊ ማዕከል መሥራችና ዳይሬክተር ዮፍታሄ ማንያዘዋል እና የአራት ልጆች እናት የሆነችው ሜሮን ግርማ ሁለቱም ልጆቼ ያሉበት ደረጃ እንዲደርሱ ማድረግ ትልቅ ሃላፊነትን ይጠይቃል፡፡ የህይወቴ ትልቁ ስኬት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡በነሱም ደስተኛ ነኝ!!

• በጉዲፈቻ ምክንያት የተለያዩ እናትና ልጅን ማገናኘት ፤

• በጉዲፈቻ ልጆች ወደ ውጪ አገር ሲሄዱ እዚህ ያለው ዶክመንት በአግባቡ ባለመያዙ ምክንያት ልጆች አድገው ወላጆቻቸውን/ቤተሰቦቻቸውን ፍለጋ ሲመጡ ለመገናኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡ በዚህ ዙሪያ ተከታታይ ዝግጅት በማዘጋጀት ዶክመንት አያያዛቸው እንዲሻሻል ለማድረግ ጥሬያለሁ፡፡

• የቤተሰብ ሰዓት ፕሮግራም የተጠፋፋ ቤተሰቦችን አገናኝ ሆኖም ሰርቷል፡፡ በኋላ ብዙ ባለጉዳዮች መምጣት ሲጀምሩ ማስታወቂያ በነጻ እንዲነገርላቸው ሬድዮ ጣቢያው ፈቅዶ ነበር በዚህ ሬድዮ ፋና ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ብዙዎችም በሚያስታውሱትና በያዙት  መረጃ አማካይነት ተገናኝተዋል ከጉዲፈቻ ውጪ ለልመናና ለተለያየ ምክንያት የተሰረቁ ልጆች ከረጅም ጊዜ በኋላ  ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

• ሬድዮ ፋና  አሁን ያለው ደረጃ ላይ ደርሶ ማየቴ ትልቅ ስኬት ነው የእኔም አስተዋጽኦ አለበትና! 1986 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ፋና እስኪሆን ድረስ የነበረው ሬድዮ ላይ የተወስንን ሰዎች እየሰራን ቆይተናል፡፡ ጎን ለጎን ፋናን እያስተዋወቅን የጋዜጠኝነት ስልጠና እየወሰድን ነው ያቋቋምነው፡፡ ስለዚህ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ በማየቴ ደስተኛ ነኝ።

• ቴርዴዞም በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ-ሰናይ ድርጅት  በካውንስሊንግ አገልግሎት ውስጥ የቡድን ውይይቶችን በማመቻቸትና (Case Study and Group Dissection facilitator) ሆኜ ሰርቻለሁ። እርዳታ በሚሰጡ ፈረንጆች በተደፈሩ ህጻናት ወንዶች ላይ የሰራሁት ሥራ/case ፍርድ ቤት እንደ መረጃ በመቅረቡ ከደፋሪዎቹ መካከል አንዱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትራንዚት ሲያደርግ ተይዞ እንዲፈረድበትና እንዲታሰር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

• የኃይሌ ገሪማ " ጤዛ" ፊልምን ለማስመረቅ የኮሚኒኬሽንና የፕሮሞሽን ሥራ በመሥራትና መጽሔት በማዘጋጀት አብረን የሰራን ሰዎች ትልቅ ስኬትን አግኝተናል። እነዚህ ከስኬቶቼ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ብላለች።

ልጆቿ

ቅድስት ወንድ ልጇን ዮፍታሄ ማንያዘዋልን ለቁምነገር ለማብቃት ገና በልጅነት ጥሩ አድርጋ አሳድጋዋለች፡፡ አሁን 32 አመቱን እያከበረ ያለው ዮፍታሄ ማንያዘዋል እንደሻው በአለም አቀፍ ደረጃ የሰብእና ትምህርት አሰልጣኝኛ አነቃቂ ተናጋሪ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ መልካም ስምን መጎናጸፍ የቻለ ነው፡፡ የራሱን ማእከል ከፍቶ እየሳራ ያለው ዮፍታሄ በተለይ ኢትዮጵያን ለመርዳት ህልም የሰነቀ በበርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር ቃለ-መጠይቅ የሰጠ ሲሆን ለዚህ ስኬቱ በዋናነት የእናቱ የቅድስት ክፍለ-ዮሀንስ ድርሻ ትልቅ ነበር፡፡ ዛሬ የዮፍታሄ ን የስኬት ጉዞ ስናጤን የእናቱን ጠንካራነት እናያለን፡፡ ቅድስትም ብትሆን ስለ ልጇ ስኬት አውርታ አትጠግብም፡፡ ልጅን ጓደኛ አድርጎ ማቅረብ ፣ በማንኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየትና የልጆችን ዝንባሌ ማጤን በአስተዳደግ ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ናቸው ትላለች ። ሴት ልጇም ሜሮን በልጆች አስተዳደግ የእናቷን መንገድ በመከተል ከልጆቿ ጋር በማንኛውም ጉዳይ ላይ የምትወያይና ከልጆቿ ጋር ጓደኝነትን የፈጠረች ናት።  ልጆቼ ዛሬም ድረስ ጓደኞቼ ናቸው ። ደስተኛ ቤተሰብ አለን ትላለች ቅድስት::

ቅድስት ወንድ ልጇን ዮፍታሄ ማንያዘዋልን ለቁምነገር ለማብቃት ገና በልጅነት ጥሩ አድርጋ አሳድጋዋለች፡፡ አሁን 30 አመቱን እያከበረ ያለው ዮፍታሄ ማንያዘዋል እንደሻው በአለም አቀፍ ደረጃ የሰብእና ትምህርት አሰልጣኝኛ አነቃቂ ተናጋሪ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ መልካም ስምን መጎናጸፍ የቻለ ነው፡፡ የራሱን ማእከል ከፍቶ እየሳራ ያለው ዮፍታሄ በተለይ ኢትዮጵያን ለመርዳት ህልም የሰነቀ በበርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር ቃለ-መጠይቅ የሰጠ ሲሆን ለዚህ ስኬቱ በዋናነት የእናቱ የቅድስት ክፍለ-ዮሀንስ ድርሻ ትልቅ ነበር፡፡ ዛሬ የዮፍታሄ ን የስኬት ጉዞ ስናጤን የእናቱን ጠንካራነት እናያለን፡፡ ቅድስትም ብትሆን ስለ ልጇ ስኬት አውርታ አትጠግብም፡፡ ልጅን ጓደኛ አድርጎ ማቅረብ ፣ በማንኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየትና የልጆችን ዝንባሌ ማጤን በአስተዳደግ ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ናቸው ትላለች ። ሴት ልጇም ሜሮን በልጆች አስተዳደግ የእናቷን መንገድ በመከተል ከልጆቿ ጋር በማንኛውም ጉዳይ ላይ የምትወያይና ከልጆቿ ጋር ጓደኝነትን የፈጠረች ናት። ልጆቼ ዛሬም ድረስ ጓደኞቼ ናቸው ። ደስተኛ ቤተሰብ አለን ትለለች ቅድስት::

ስለ ዮፍታሄ ማንያዘዋል በሌላ የዊኪፒዲያ ገጽ በዝርዝር እናወራችኋለን፡፡

     የበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች 

• የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያ ሴቶችን ማህበር ከመሰረቱት መካከል አንዷ ነኝ፡፡ በተለያዩ ኮሚቴዎች አገልግያለሁ፡፡ የቦርድ አባል በመሆንም ሁለት ጊዜ ተመርጫለሁ፡፡ አሁንም በቦርድ አባልነት በፈቃደኝት እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡

• የብሔራዊ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር /ወወክማ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሥርዓተ ጾታና ሥነ ተዋልዶ ክፍል ሰብሳቢ በመሆን አገልግያለሁ በዚህም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ስብሰባዎችና ስልጠናዎች  ላይ ተሳትፌያለሁ።

• አሁንም የአራት ኪሎ ወወክማን ለማስመለስ በበጎ ፈቃደኝነት የወወክማ ልጆች በጋራ እየተንቀሳቀስን ነው።

• Sanvee Majr Carlos Secretary General for the Global YMCA Alliance ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው የቀድሞ የአፍሪካ አሊያንስ General Secretary እንዲሆን ሲመረጥ በአስመራጭ ኮሚቴነት Africa Alliance ጋብዞኝ ኢትዮጵያን ወክዬ አስመራጭ ኮሚቴ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡

• 14ኛው የአፍሪካ የጠረጴዛ ኳስ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ በመሆን በበጎ ፈቃደኝነት ሰርቻለሁ፡፡

• ተስፋ ጎህ ማህበርን  ዘውዱና ጓደኞቹ በሚያቋቋሙበት ጊዜ በፈቃደኝነት አብሬ  የበኩሌን አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ፡፡ ይህም ብዙዎች ሲገለገሉበት በማየቴ ደስታ ይሰጠኛል፡፡

• በተመሳሳይ ሁኔታ አዲስ ምዕራፍ የተባለውንም በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ የሚሰራ ማህበር እንዲሁ ከማቋቋም ጀምሮ በበጎ ፈቃደኝነት አገልግያለሁ፡፡

• ኢትዮ- ስዊድሽ ህጻናት ማሳደጊያና መልሶ ማቋቋሚያ ግብረ- ሰናይ ድርጅት መስራችና የቦርድ ፀሐፊ በመሆን በፈቃደኝነት አገልግያለሁ፣ የቦርዱ ፕሬዚዳንት ታላቁ የሙዚቃ ባለሙያ ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ነበር፡፡ 

• መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠናዎችን ለኩሽ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተማሪዎች በነጻ ሰጥቻለሁ፡፡

• በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር እና አ/አ ዩኒቨርስቲ በጋራ ባዘጋጁት ዲላ፣ሐዋሳ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የሚዲያ ግዴታና ኃላፊነት ምን መሆን አለበት? በሚል ርዕሰ ጉዳይ  ላይ ለውይይት መነሻ በማዘጋጀትና በማቅረብ ፣እንዲሁም የሥራ ልምዴን በማካፈል ተሳትፌያለሁ  ብላለች።

በቴአትርና ፊልም ስራ

• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፣ የቴአትር ትምህርት ክፍል በተዋናይነት

• ራስ ቴአትር፣ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ባህልና ቴአትር አዳራሽ በተጋባዥ ተዋናይነት፣

• የተለያዩ የቴአትር ቡድኖች ውስጥ ተሳትፌያለሁ፡፡

• በፊልም ማዕከል የተዘጋጀው በህይወት ዙሪያ የብርሃኑ ሽብሩ ፊልም ላይ በትወና

• አንድ የውጭ ሀገር ፊልም (የእንግሊዝ) ላይ በአጃቢነት ተሳትፌያለሁ

• የሳሌም መኩሪያ የወንዞች ማዕበል ዶክመንተሪ (ዘጋቢ) ፊልም ላይ በረዳት አዘጋጅነት ተሳትፌያለሁ፡፡

የፖለቲካ ተሳትፎ

• 1997 ቅንጅት ፓርቲን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት (ማዘጋጃ ቤት) ተመርጫለሁ፡፡

የጋዜጠኝነት ስራ

• ሬድዮ ፋና፣ እለታዊ አዲስ ጋዜጣ፣ ነጋድራስ ጋዜጣ ከመስራችነት ጀምሮ እንዲሁም ኢትዮ ፖስት ጋዜጣ፣ ሰርቻለሁ፡፡ 

• ኢትዮጵያ ሬድዮ የተለያዩ ድራማዎችና “አጉል ጸባይ” ጭውውቶች ላይ ተሳትፌያለሁ፡፡

• ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ማህበር “ብሩህ ተስፋ” ፕሮግራም በአዘጋጅና አቅራቢ  ኢትዮጵያ ሬድዮ

• በብሔራዊ ሎተሪ “እድል” በኤፍ ኤም 97.1 አዘጋጅና አቅራቢ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች