85. ተስፋ ካሣ ተፈራ - tesfa kassa teffera
“ጌምቤሮ” ---ተስፋ ካሣ
የዚህ ታሪክ
አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ
፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ
እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ
የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን
እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia@gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ
ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ
የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር
ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል
ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም
ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው
ይዘከራል፡፡ አሁን ከቴአትር ዘርፍ ታሪኩ የሚዘከርለት ሰው
በፓንቶ ማይም ዘውግ የሚታወቅ ነው፡፡ ጊምቤሮ በተሰኘው ገጸ -ባህሪው ይታወቃል፡፡ ተስፋ ካሳ፡፡
ስም- ተስፋ ካሣ
ተፈራ
የትውልድ ጊዜ-
12/10/1970
የትውልድ ቦታ-
ጎንደር /ሰሜን ጎንደር/
የትዳር ሁኔታ-
ያገባ/ የሶስት ልጆች አባት/
የትምህርት ቤት
ዳራ ታሪክ
ተስፋ ካሣ
የተወለደው በጎንደር ከተማ ከእናቱ አስካል ወንዴና ከአባቱ ካሳ ተፈራ ነው፡፡ ፊደል መቁጠር የጀመረው የተረትና የቅኔ አዋቂው
“የንታ” ብሎ ከሚጠራቸው ቄስ ት/ቤት ነው፡፡አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በሰሜን ጎንደር ህብረት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ተማረ ፡፡
ሁለተኛ ደረጃና
ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተማረው ፋሲለደስ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን በጊዜውም የሶሻል ሳይንስ ተማሪ
ነበረ፡፡
ክፍተኛ ሁለተኛ
ደረጃ ት/ት- መልቀቂያ ፈተና ወስዶ በዲፕሎማ ውጤት በ1990 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኤጁኬሽን ትምህርት ክፍል
ቀጠለ፡፡
በ1996 ዓም
በማታው ፕሮግራም የፍልስፍና ትምህርት ክፍል አንድ አመት ከተማረ በኋላ የቴአተር አርት ትምህርት ክፍል የማታ ፕሮግራም
ስለጀመረ ተዘዋውሮ መማር ጀመረ፡፡ በ2000 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪውን በቴአትር አርትስ ያዘ፡፡
የስራና የሙያ ሁኔታ
አርቲስት ተስፋ ካሳ
የሚወደው ሙያ ቴአተር ሲሆን በተለይም የትወና ዘርፉ ላይ እጅግ ፍቅር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በጎንደር ፋሲለደስ ት/ቤት
ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር የመጀመሪያ አጭር የቴአተር ስልጠና ወስዶ ዩኒቨርሲቲ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ “ ዞብል”
የኪነጥበብ ክብብ አባል በመሆን አጫጭር ተውኔቶችን፤የሙሉጊዜ ተውኔቶችንና ድምጽ አልባ ተውኔቶችን በመተወን በአማተርነት
ሰርቷል፡፡ የድምጽ አልባ ተውኔት (mime/pantomime) ተውኔት ኪህሎቱንም ያዳበረው በዚህ ወቅት ነበረ፡፡ የመጀመሪያ
ድምጽ አልባ ተውኔትም “ጸጉር አስተካካዩ” ይባላል፡፡
አዲስአበባ
ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ኤጁኬሽን ዲፕሎማውን ሲማር ግን ከትወና ፤ባጠቃላይ ከኪነጥበብ ጋር የነበረው ግንኙነት
ተቋርጧል፡፡በዩኒቨርሲቲው ባህል ማእከል በነበረው ክበብ ሊሳተፍ ቢሞክርም በተለያዩ ምክንያቶችአልተሳካለትም፡፡
በዲፕሎማ ከተመረቀ
በኋላ ሠሜን ጎንደር ደባርቅ ወረዳ ማህበራት ጽ/ቤት በኦዲተርነት ለአራት አመታት ሰርቷል፤፤ነገር ግን የስራ ባልደረቦቹ
በትወና ሙያ እንዲቀጥል ይገፋፉት እንደነበር ያስታውሳል፡፡
አንድ ቀን ጠዋት
በህይወቱ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ፡፡ ይህም ስራውን ለቆ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የልጅነት ህልሙና ምኞቱ የሆነውን ቴአትር ለመማር
ነው፡፡ ከዛም አዲስ አበባ በመምጣት በየካ ክ/ከተማ ማህበራት ኦዲተር በመሆን በማታ ቴአተር ትምህርት ስላልነበር በፍልፍስፍና
ት/ክፍል ለአንድ አመት ከተማረ በኋላ በ1997ዓ.ም ወደቴአትር
ትምህርት ተዘዋውሮ መማር ጀመረ፡፡
በዚህ ጊዜ የነበረውን
ስራ ለቆ አዲስ ብድርና ቁጠባ የንኡስ ቅርንጫፍ ስራ እስኪያጅ ሆኖ ቀንቀን እየሰራ ማታ ቴአትር ይማር ነበረ፡፡ከተመረቀ በኋላም
በዚሁ ተቋም የኦዲዮ ቪዥዋል ባለሙያና የኮሚኒኬሽን ኤክስፐርት ሆኖ እያገለገለ ቆየ፡፡ ማታ ደግሞ በአቢሲኒያ የኪነጥበብና
ሞዴሊነግ ተቋም በትወና፤ዝግጅትና በተውኔት አጻጻፍ ያስተምር ነበረ፡፡ በዚህም ለ11 አመታት ያስተማረ ሲሆን አሁንም በስራው
ላይ ቀጥሏል፡፡
አሁን የቢዝነስና
ሌሎች ስራዎችን ትቶ በሙሉ ጊዜው የራስ ቴአተር ተዋናይና በአቢሲኒያ መምህር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡በተጨማሪም በህዝብ ዘንድ
በተለይ በህጻናት ያሳወቀውን “ጌምቤሮ” የተባለውን የማይም ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ጌምቤሮ- የፓንቶ
ማይም ዘውግ ያለው ድምጽ አልባተውኔት ገጸ-ባህሪይ ሲሆን ከሁለት አመት በላይ በኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ቻናል የቀረበ ሲሆን
በዚህ አይነት አቀራረብና በቁጥር ብዛት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው፡፡
ለወደፊት በኢትዮጵያ
ሲኒማ ፊልሞች በዝግጅትና በስክሪፕት ጽሁፍ ላይ የራሱን ሥራዎች ለመስራት እቅድ እንዳለውና እየሰራም እንደሆነ ይናገራል፡፡
የሰራቸው
ሙያዎችዝርዝር
• የሂሳብ ኦዲትር
• ኦዲዮቪዥዋል
ባለሙያ
• ኮሚዩኒኬሽን
ባለሙያ
• የሬዲዮና
የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ
• የቴአትር መምህር
• ተዋናይ
• ድምጽ አልባ
ተውኔቶች ጸሀፊና ተዋናይ
በህዝብ
ያሳዎቁትናየሰራቸው ስራዎች
• ደንብ 5 -
ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ-
• አለቃ ገ/ሃና
እና ጥቁር ደም- የሬዲዮ ትረካ
• ተከታታይ የኢት.
ሬዲዮ ድራማዎች
• የተለያዩ አስተኔ
የፊልም ገጸባህሪያት ወዘተ…..
• ቅዳሜናእሁድ
ተከታታይ ቲቪ ድራማ
• ጌምቤሮ-
pantomime
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ