53. ከንፋስ ስልክ እስከ አሜሪካ
እሱባለው መዓዛ ማሞ -Esubalew Meaza Mamo
ተወዳጅ ሚድያ እና
ኮሚኒኬሽን በቅርቡ ደረጃውን የጠበቀ ለቤተ-መጽሀፍት አገልግሎት የሚውል በጠንካራ ሽፋን የተጠረዘ የኢትዮጵያ ኢንሳይክሎፒዲያ
አሳትሞ ያቀርባል፡፡ እስካሁን በዚህ ገጽ ያወጣናቸውን በጥራዝ መልክ አድርገን ለታሪክ የምናስቀምጥ ሲሆን ታሪካቸው በዚህ መልክ
በክብር ከሚሰነድላቸው አንዱ እሱባለው መአዛ ይሆናል፡፡ እሱባለው
አሜሪካ ሀገር ከ30 አመት በላይ ሲኖር አንድ ጠቃሚ ነገር በማከናወኑ ለዚህ ዊኪፒዲያ እንዲበቃ አድርገነዋል፡፡
ልጅነት
እሱባለው መዓዛ
እንደ ኢሮጵያውያን አቆጣጠር በ1971 በአዲስ አባባ ከተማ ልዩ ስሙ ንፋስ ስልክ በሚባል ሰፈር ተወለደ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በፍሬህይወት ቁጥር ሁለት ትምህርት ቤት ፣
የ9ኛ ክፍል ትምህርቱን በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቆ የ10ኛ ክፍልን እንደጀመረ ባገኘው የትምህርት እድል መሰረት ወደ አሜሪካ ተጓዘ።
ኳስ ፊደሉ
እሱባለው በልጅነት
እድሜው ከሚታወቅባቸው ነገሮች ሁሉ ጎላ ብሎ የሚታወሰው የእግር ኳስ ጨዋታ ፍቅርና ብቃቱ ነው። ችሎታው ከእኩዮቹ ብቻ ሳይሆን ከእሱ በላይ ካሉ ልጆች እንዲጫወት እድሉን
ስለሰጠው “ኳስ ፊደሉ” የሚል የሰፈር ስም አሰጥቶታል። የኳስ
ችሎታው አሜሪካም ከመጣ በኋላ ትምህርት ቤቱን ወክሎ እንዲጫወትም
አድርጎታል።
አሜሪካ- ከሁለተኛ ደረጃ እስከ ኮሌጅ
እሱባለው እንደ
ኢሮጵያውያን አቆጣጠር ኦክቶበር 1987 ወደአሜሪካ ሲገባ
ኒውጀርሲ በምትባል ክፍለ ሀገር ውስጥ የምትኖረው እህቱ ሰናይት መዓዛ እና ቤተሰቧ ጋር ነበር ያረፈው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም በዛው በኒውጀርሲ በሚገኘው
Englewood Dwight Morrow High School በሚባል ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ከትምህርቱ ጎን ለጎን በከተማው ውስጥ ከሚገኘው የህዝብ መጽሐፍ ቤት
ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ከጨረሰ በኋላ ሜሪላንድ ክፍለ ሀገር የሚኖረው ወንድሙ ጋር ተጉዞ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን በ
University of District of Colombia (UDC) ተምሮ እንድ ኢሮጵያውያን አቆጣጠር በ1990 በማእረግ
ካጠናቀቀ በኋላ በዩንቨርሲቲው ውስጥ ተቀጥሮ የኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን እና በዋሽንግተን አካበቢ ለሚገኙ
ታዳጊዎች በNASA በተመቻቸው ፕሮግራም ላይ የዲጂታል ኢንጂነሪንግ ትምህርት አስተምሯል።
የሥራ ዓለም
እንደ ኢሮጵያውያን
አቆጣጠር በ1997 EDS በሚባል በወቅቱ ትልቅ የሶፍትዌር
መሥሪያቤት ተወዳድሮ ባሳየው ብቃት መሰረት ተቀጥሮ ስራ ጀመረ።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮም አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ብዙ የሶፍትዌር ካምፓኒዎች ሠርቷል። SRA, EXODUS, Anderson Consulting, እንዲሁም
iWorks በሚባሉ ኩባንያዎች Vice President እስከመሆን ድረስ አገልግሏል። በሥራ በነበረበት ዘመን በትርፍ ጊዜው እየተማረ የማስተርስ ዲግሪውን
በ2010 ከ Colorado Technical University በ
Enterprise Information Systems (MSEIS) በማእረግ ተመርቆ ይዟል።
እሱባለውና ኢትዮጵያ
እሱባለው በሥራ
ዓለምና በቤተሰብ ማስተዳደር ተወጥሮ ባለበት ዘመኑ የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ህልሙን በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች
በመጓዝና ታሪኳን በመመዝገብ Ethiopia: Inspiring journey የሚለውን የመጀመሪያ መጽሐፉን በ2012 ለአንባቢዎች
አቀረበ። ከዚያም ቀጠል በማድረግ የትውልድ ሀገሩን ዋና ከተማ
የአዲስ አበባን ገፅታዎች በጥሩ መልኩ በፎቶና በጽሑፍ Addis
Ababa: the new flower of Africa በሚል ርእስ በ2015 አሳትሞ ለንባብ አቀረበ። እሱባለው ቀጠል አድርጎ በ 2019 ከ 6ኛው ክፍለ- ዘመን እስከ 17ኛው
ክፍለ- ዘመን የተፈለፈሉትንና የተሰሩትን፥ በትግራይ፥ በጎጃም፥ በጎንደር፥ በወሎ ከሚገኙት ከ40 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት እና ቤተክርስቲያናትን ያካተተ
Ascending to heaven: Ancient churches and monasteries of Ethiopia የሚለወን ሦስተኛ
መጽሐፉን ለአንባቢያን አቅርቧል። የእሱባለውን ሥራዎች ለየት
ከሚያደጋቸው ነገሮች አንዱና ትልቁ በጥራት መሰራታቸው እና
በመጽሐፎቹ ላይ የተካተቱትን ቦታዎች በሙሉ ራሱ ሄዶ በማየትና በጥሩ ሁኔታ መመዝገቡ ነው።
አንጋፋው የቱሪዝም
አባት አቶ ሀብተስላሴ ተስፋዬ እና ታላቁ የጥበብ ሰው ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ስለ እሱባለው መዓዛ መፅሐፎች እንዲህ ብለዋል
“The book is
not only quaint, but also highly informative. It is noteworthy contribution to
the effort of promoting Ethiopia’s tourist attraction properties.”
Hapte-Selassie
Tafesse
“Ascending
to Heaven, a stunning collection of photography by Engineer Esubalew Meaza, is
beautiful
and aptly
titled book. “Ascending to [Debre Damo] Heaven” is a wax and gold qinie, a
poetic expression
composed in
the traditional style of Geez poetry. And indeed, the breathtaking images in
the book,
together
with the clear, succinct text descriptions that accompany them, chart the road
to heaven, the path of Ethiopian Christianity. They also bring ancient Ethiopia
to life. “
Professor
Getatchew Haile
የአማርኛ ድርሰት
እሱባለው ከዚህ
በፊት ከተገለፁት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከጻፋቸው መጽሐፎች ለየት ባለ መልኩ የአማርኛ ድርሰት ችሎታውን “ልቃቂት እና ሌሎች
ወጎች” በሚል 11 አጫጭር ታሪኮችን ያዘለ የልብ- ወለድ መፅሐፍ በ2021 ለአንባቢዎች አድርሷል። የእሱባለውን የሀገር ውስጥ ጉዞና የልብ ወለድ አቅም ቁልጭ አድርጎ ያሳየ
ይህ መጽሐፍ በአንጋፋው የጥበብ ሰው ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ
ተወድሷል፡
“…የኢትዮጵያንና
የአዲስ አበባን ልዩ ልዩ ገፅታዎች በካሜራው አይን ቀርፆ አሳትሞ አቅርቦልናል፡፡ አሁን ደግሞ በአይነ- ህሊናው ዓይን ተመልክቶ
የኢትዮጵያን ሕዝብ በየዓይነቱ በምናቡ ቀርፆ አቅርቦልናል፡፡ አስቸጋሪውን የአጭር ልብ ወለድ አፃፃፍ በቅልጥፍና ለዛ ባለው
ቋንቋ ለአንባቢ በማቅረቡ ደራሲ እሱባለውን እንኳን ወደ አማርኛ ሥነፅሑፍ ዓለም መጣህ ስለው ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፡፡”
ልቃቂት የአጫጭር
ልብወለዶችና አጫጭር ትረካዎች (ShortStories) ጥርቅም ነው። በአብዛኛው ጉዞ ወለድ ሲሆን
እሱባለው በህይወት
ጉዞው ውስጥ ያያቸውን ገጠመኞች፣ ተመልክቶ፣ አዳምጦ፣ አሽትቶ፣ ሰምቶ፣ ነክቶና አጣጥሞ ያቀረበው የድርሰት ግብዣ ነው።
መዝጊያ ÷ እሱባለው በልጅነት ወደ ምድረ- አሜሪካ ቢገባም የኢትዮጵያ
ፍቅር ግን አብሮት ያደገ ነው፡፡ በመሆኑም በሙያ ደረጃ በአይቲው ዘርፍ ላይ ቢሰራም እርሱን ግን ስለ ሀገሩ በመጽሀፎች ማስተዋወቅ ስራ ላይ ተጠምዷል፡፡ አሜሪካን
ሀገር በአይቲው ዘርፍ ሰርቶ ከሚከፈለው ገንዘብ ላይ ለመጽሀፍት ማሳተሚያ በማዋል ሀገሩን በአንድ በኩል ለመርዳት ሀሳብ
እያደረገ ነው፡፡ 4 መጽሀፎችን ሲያሳትም አንዳች ርካታ
ይሰማዋል፡፡ አሁንም ስለ ሀገሩ አውቆ ማሳወቁን እንደቀጠለ ነው፡፡ ለረጅም አመት ባህር ማዶ መኖሩ ስለሀገሩ እውቀት
እንዳይኖረው አላገደውም፡፡ ይልቁንም ሀገር ቤት መጥቶ በገዳማት
እየዞረ ኢትዮጵያን ለቀሪው ማህበረሰብ ለማሳወቅ ታግሏል፡፡ ባህር
ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እሱባለው እንደአርአያ የሚቆጠር
ነው፡፡ ሀገሩን አልረሳም፡፡ ሀገሩን አልተወም፡፡ ቀንም ያስባታል፡፡ ማታም ስለ እምዬ ማሰላሰሉን ይቀጥላል፡፡ እንዲህ አይነት
ሰዎች በዚህ ዊኪፒዲያ አዘጋጆች ይበረታታሉ-ይከበራሉ፡፡ ስለእሱባለው ታሪክም ስንሰራ አዲሱ ትውልድ ምን እንዳደረገ እንዲያውቅ
በማሰብ ነው፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ