27. አብርሀም ግዛው ገብረወልድ  Abreham Gizaw G/wold

 

አብርሀም ግዛው ገብረወልድ 30ዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ወጣት ነው፡፡ ግን ትጉህ ነው፡፡ ራሱን በስራ ለማሳደግ ብዙ ጥረት ያደርጋል፡፡ በተለይ በሚድያ ፕሮሞሽን ዝግጅቶችን በማቀናበር እና በማዘጋጀት በራሱ ድርጅት አማካይነት ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው፡፡ አብርሀም የራሱንም መጽሄት እያዘጋጀ ለአንባቢ ያደርሳል፡፡ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን  በፕሮሞሽን ዘርፍ ከተሰማሩት ታታሪ ባለሙያዎች መሀል አንዱ የሆነውን አብርሀም ግዛውን  እንደሚከተለው ያስተዋውቃል፡፡

 አብርሀም ግዛው 1981 . ተወለደ፡፡ በመዲናችን አዲስ አበባ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በአፄ ቴዎድሮስ ተማሪ ቤት ተማረ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ቤት አጠናቀቀ፡፡ በአዲስ ኮሌጅ በቢውሊድንግ ኮንስትራክሽን ተማረ፡፡ በመቀጠል ወጋገን ኮሌጅ ገብቶ በትያትር በዲኘሎማ ከተመረቀ በኋላ አቧሬ ቴክኒክና ሙያ በሲቪል ሰርቪስ የጋዜጠኝነት ኮርሶችን ወሰደ፡፡

አብርሀም ቀደም ሲል በኤፍ ኤም 96.3 የጥበብ ሀበሻ ኘሮግራም አዘጋጅ ነበር፡፡ በመቀጠል በብስራት  ኤፍ.ኤም 101.1 የመዝናኛና የመረጃ ኘሮግራም አዘጋጅ ሆኖ ሲሰራ ነበር፡፡ 2006 . ጀምሮ "ስንቅ" መፅሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነው፡፡   የበዓል ፕሮግራሞችንም ላለፉት 8 ዓመታት ከተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር አዘጋጅቷል፡፡ አጠቃላይ  16 በላይ የበዓል ኘሮግራሞችን   በማዘጋጀት  የሚድያ ፕሮሞሽን ስራን በብቃት አከናውኗል፡

ከቅርብ ጊዜት ወዲህ በተለይም በጋዜጠኝነት ሞያ እና በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ነው፡፡ ጋዜጠኛና ፕሮሞተር ብለን ልንጠራውም እንችላለን፡፡

 አብርሀም  በአሁን ሰአት የተለያዩ መርሀ-ግብሮችን ያዘጋጃል፡፡ አልበሞችና ሙዚቃ ምርቃቶችንም  በተሳካ ሁኔታ በማስተባበር አደራውን ይወጣል፡፡

ጋዜጠኛና ፕሮሞተር አብርሃም ግዛው በአሁኑ ወቅት በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ የሚተላለፈውን ‹‹የጥበብ ብልጭታ›› የተሰኘውን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሆኖ እየሰራ ነው፡፡

  300 በላይ የሆኑ አማርኛ ፊልሞችን ፕሮሞት በማድረግ አስመርቋል፡፡

  አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች የሀገር ውስጥ ፊልም ፌስቲቫሎች ሙሉ የማስተባበር ሃላፊነት በመውሰድ ሰርቷል፡፡

  የተለያዩ የምርቃት ፕሮግራሞች የመጽሀፍና ሆቴሎች እንዲሁም ሌሎች ፕሮግራሞች በተዋጣላቸው መልኩ እንዲመረቁ አድርጓል፡፡

  የባዛርና የሙዚቃ ዝግጅቶች አዘጋጅቷል፡፡

 

  በሀገራችን ለሚገኙ የሜሪጆይ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ሜቄዶንያ የአዕምሮ ህመምተኞች በጎ አድራጎት፣ የወደቁትን አንሱ በጎ አድራጎት፣ ፣እንዲሁም ሙዳይ በጎአድራጉት፣ መሰረት በጎ አድራገት፣ጌርጌሶኒያን በጎ አድራጎት፣ ስለእናት በጎ አድራጎትን፣  በማስተዋወቅ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

   አብርሀም 2011 . ከጄ ቲቪ ጋር በመተባበር መስቀልን በልዩ ጉራጌ ባህል እንዲሁም ባህላዊ ሃይማኖታዊ ጥናት ሰርቷል፡፡ በመቀጠል ከልጆች ጋር በተያያዘ የገና በአል በአይነቱ ለየት ያለ አቀራረብ ልጆችን ያሳተፈ የገና በአል ዝግጅት  አቅርቧል፡፡

   ላለፉት 11 ዓመታት በሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል የኪነጥበብ ዝግጅቶችን አዘጋጅቷል፡፡ 

   የመጽሐፍ ምረቃ ዝግጅቶች

በደራሲ ተዘራ ለማ የተደረሰው ‹‹የሚስጥር መንትዮች›› መጽሀፍ፣በደራሲ ከተማ ኬሬታ ‹‹አልበም›› የተሰኘ የመጽሀፍ ምርቃት በደራሲና ተርጓሚ አፈወርቅ በቀለ ከልካይ የተዘጋጀው ‹‹ደም በደም›› በደራሲ ፀሀፊ ተውኔት እና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱ ያሳተማቸው መፅሀፎች እንዲሁም በርካታ የስነ ጽሁፍ ምሽቶች ሌሎችም የግጥምና ልብ ወለድ መጽሀፎችን አብርሀም አስመርቋል፡፡

    አብርሀም ስለ እቅዱ ምን ይላል?

የአጭር ጊዜ  እቅዴ የያዝኩት ያውን አጠንክሬ መያዝ ነው፡፡ በጋዜጠኝነቱ ሞያውን ለህብረተሰቡ የማስተላለፍ ትኩስና ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችን ወደ ህዝብ የማድረስ ተግባሬ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከነዚህም ጋር የፕሮሞሽን ስራውን በስፋትና በተደራጀ መልኩ ማከናወኔን እቀጥላለሁ ፡፡ የረጅም ጊዜ እቅዴ ብዙ ነው፡፡ የራሴን የሬዲዮ ጣቢያ እስከመክፈት የሚደርስ እቅድና አላማ ነው ያለኝ፡፡ የጋዜጠኝነት /ቤት ከፍቼ ብዙ ብቁ ባለሞያዎችን እንዲፈጠሩ እድል የማመቻቸት አላማ ሰንቄአለሁ፡፡

 በሀገራችን እየሰራሁ ያለውን ፕሮሞሽንና ኢቨንት ስራ   በአለም አቀፍ  ደረጃ እንዲሆን ህልም አለኝ ፡፡ዎች በውጪ አለም ማለት በቱርክ በዱባይ እና በቻይና በጀርመን ሀገር ካሉ ፕሮሞተሮች ጋር በጋራ በመሆን እዛው ሀገር ድረስ በመሄድ ልምድ አይቼ ስልጠናም ወስጄ መጥቻለሁ፡፡ የተለያዩ መርሀ-ግብሮችንም ለመስራት እንቅስቃሴ ጀምሬአለሁ ፡፡ ሌላም የቴሌቪዥን ቶክ ለማዘጋጀት እንዲሁም የሚቀጥለውን አመት ሁሉንም የሞያ ዘርፎች ያካተተ በኪነ-ጥበብና በመዝናኛ ብዙሀን የሽልማት ፕሮግራም አዋርድ ለመስራት እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡ አሁን በሀገራችን ያለውን መነቃቃት በተለይም // / አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እያየን ያለነው ለውጥ ሀገራዊ መግባባትና ኢትዮጵያዊ ስሜት እራስን የለውጡ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያነሳሳ ሞራል የሚሰጥ ስለሆነ እራሴን በተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረግ እያነቃቃው ነው፡፡

የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነው ፈጣሪ አምላኬን አመሰግናለሁ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በፈጣሪ ድጋፍ ስለሆነ ላደረገልኝ ሁሉ ፈጣሪ ይመስገን፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች