128. አለምሰገድ አበበ
ተወዳጅ ሚድያና
ኮሚኒኬሽን በፊልም ፤ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ
ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ
፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች
እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና
እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ
ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን
እናምናለን፡፡ በ5 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር
ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ከሚድያ ዘርፍ ታሪኩ የሚቀርብለት ሰው
አለምሰገድ አበበ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ብቸኛው የጥናትና ምርምር ፕሮግራም አዘጋጅ
አለምሰገድ አበበ
ተወልዶ ያደገው
በአሰላ ከተማ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1990ዎቹ መጀመሪያ በመግባት በዲግሪ ተመርቋል፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ
የሙዚቃ የድርሰትና የግጥም ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ትልቅ የጥበብ ፍቅር ስለነበረው ይኸው ግፊቱ 12ኛ ክፍል ካጠናቀቀ
በኋላ በልቡ ፍላጎትና ተሰጥኦው መሰረት አዲስ አበባ በመምጣት በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ ክፍል በመግባት በዲግሪ
ተመርቋል፡፡
በአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ይማር በነበረበት ጊዜ አሁን ላለበት ህይወቱ በር እንደተከፈተለትና ወደ ጋዜጠኝነቱ እንዲመጣ እንደረዳው ይናገራል፡፡
በተለይም
በዩንቨርስቲው የባህል ማእከል ውስጥ የተማሪዎች የሙዚቃ ክፍልና የመድረክ የስ-ነፅሁፍ ክፍል ፕሮግራሞች በጣም ቀንደኛ ተሳታፊ
ነበር፡፡
ይህንን ፍላጎቱን ይበልጡኑ በማሳደግ በትምህርት ቤት እያለ በ1993.ዓ.ም
ለህትመት ያበቃት "ማሙሽ መሠከረ" የተሰኘችው መፅሀፍ ብዙዎች ያስታውሷታል፡፡
ይህች መጽሀፍ
በኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ በአምሀ አሰበ "ህብረ-አምሳል ቁጥር-1 ቁጥር-2 እና ቁጥር-3" የቅኔ
መፃህፍት ቀጥላ የተፃፈች የሰምና ወርቅ ቅኔ ግጥም መጽሀፍ ባለቤት ያደርገዋል፡፡
"ማሙሽ
መሠከረ" በወቅቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው መጽሀፍ ካሳተሙ ጥቂቶች ውስጥ አንዱ ያደርገዋል፡፡ ይህ መጽሀፍ፣ የተለያዩ
ግጥሞችን እና 100 ያህል ሰምና ወርቅ የዘለሰኛና የመዲና የቅኔ ስልቶችን ያካተተች ነበረች፡፡
በወቅቱ ተራማጅ
የነበረ አስተሳሰብ ባለቤት የነበረው ጋዜጠኛ አለምሰገድ አበበ በተማሪነት ወደተለያዩ ተቋማት በመሄድ እና ስፖንሰር በማፈላለግ
3200 ቅጂ መጻህፍቶችን እንዳሳተማትና በ4 ብር ከጥቂት መጻህፍት ሻጮች ውጪ ራሱ በቦርሳ በመያዝ አዙሮ ሸጦ እንደጨረሳት
ይናገራል፡፡
ይህችን መጽሀፍ
ከወላጅ እናቱ ከወ/ሮ አፀደ 400 ብር በመቀበል፣ ከብሎ ቶፕስ ሬስቶራንት ባለቤት ከነበረው ለአቶ አንተነህ ተጫኔ 2000 ብር
ከባለዛፍ መጠጥ ኢንደስትሪ (ከአቶ በላይ) 500 ብር እና ከዳታኮም ኮምፒውተር ዋና ስራ አስኪያጅ ከነበሩት ከአቶ ግዛቸው ዋና
ስ/አስኪያጅ 500 ብር በማሰባሰብ ኤስ.አይ.ኤም ማተሚያ ቤት ነበር ያሳተማት፡፡ አሁንም የቅኔ ስራዎቹን ‹‹የእኔ ቅኔዎች››
የተሰኘ የቴሌግራም ገጽ በመክፈትም እያቀረበ ይገኛል፡፡
በትምህር ቤት እያለ
በሀሌታ ኮምቲውተር፤በሳብ ፔጅ የማስታወቂያ የሎ ፔጅ፤ በዳታኮም ኮምፒውተርና በሻሎም ቪዲዮ ውስጥ በማርኬቲንግ መስራቱ ትልቅ
የስራ ልምድ እንዲያገኝ ያደረገው ነበር፡፡
አንድ ቀን የሳብ
ፔጅ ማስታወቂያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃደ ስላሴ ከበደ አንድ ነገር ይጠይቀዋል፡፡ ሙዚቃ መስራት ትችላለህ? ብሎ፡፡ በወቅቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ60ኛውን ዓመት ይከበር ነበርና፡፡ ወቅቱ 1996 ዓ.ም ነበር፡፡
በማግስቱ በቴፕ
ቀርፆና ግጥሙን ፅፎ ያመጣለት የአንድ ቀን ስራው እጅግ የተደነቀና የ60ኛ አመት ባንኩ ክብረ በአል ማድመቂያ ሆኖ ነበር፡፡
ከዛም ፀረ- ሙስና
ኮሚሽን የሰራው "ሙስና የእድገት ጠንቅ ነው" የተሰኘው ስራው ጥሩ ማስተማሪያና የሙዚቃ ችሎታው ያሳየበት
ነበር፡፡
በተጨማሪም
አለምሰገድ በልጅነት ዘመኑ ውስጥ ከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪም ወደ ጋዜጠኝነት ህይወት እንዲገባ ያደረገው የዛሚ 90.7 ሬድዮ
መከፈት ነበር፡፡ የጋዜጠኝነት ስራ መጀመሪያ ሀሁ የቆጠረውም እዛ ነበር፡፡
ዛሚ ሬዲዮ ሲከፈት
ወደ ጋዜጠኝነት ህይወት በመቀላቀል ከ1999 ዓ.ም እስከ 2001 ዓ.ም ድረስ በመስራት ያገለገ ለሲሆን፤ ወዲያው አጸድ
የማስታወቂያ ስራ የተሰኘ ድርጅት በመክፈት ከ96.3 ሬዲዮ የአየር ሰዓት በመውሰድ ከ2001 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ 2006
ዓ.ም ድረስ መክሊት የተሰኘ የቢዝነስ ፕሮግራም ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡
በዚህ ፕሮግራሙ ላይ
የተለያዩ የሚያነቃቁ ሀሳቦችን የሥራ ጥቆማዎችን የሥራ ፈጠራዎችን በማንሳት ሊሰራ ችሎአል፡፡ የቢዝነስ ሀሳቦችን ከባለቤቱ
ከጋዜጠኛ ትዝታ ክንዴ ጋር በማፍለቅም በበርካቶች ዘንድ የሚወደድ መሰናዶ ሊሰራ ችሏል፡፡
በዚህ ፕሮግራሙ ላይ የሚያቀርባቸው የሀገራችን ታላላቅ የቢዝነስ ሠዎች
/የሥራ ፈጠራ ባለቤቶች ልምዳቸውን እና ተሞክሮአቸውን ያካፍሉ ነበር፡፡ ፕሮግራሙም ላይ ከ270 በላይ ቃለ- ምልልስ የሰራ ድንቅ ጋዜጠኛ ነው፡፡
2006 ዓ.ም ላይ
ጋዜጠኛው እና ተመራማሪው አለምሰገድ አበበ የአዲአበባ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ሲመረቁ ያይና ይሄ ሁሉ ተማሪ
የሚሰራው ምርምር የትነው ያለው? የትኛው ነው ፍሬ ያፈራው? ብሎ በመጠየቅ የምርምር ፕሮግራም ለማዘጋጀት ፕሮፖዛል በመጻፍና
ለብስራት ሬድዮ በማቅረብ፤በ2007 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከብስራት 101.1 ሬዲዮ የአየር ሰዓት በመውሰድ "ከሼልፍ
ላይ" የተሰኘ የጥናትና የምርምር ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ፡፡ በዚህም ያገኘውን መልካም አስተያየት በመጠቀም ፕሮግራሙን
ወደ ቴሊቪዥን በማሳደግ LTV በማምጣት ፕሮግራሙ መቅረብ
እንደጀመረና ለብዙ የጥናትና የምርምር ሰዎች መታወቅ ሊሆን እንደቻለ ይናገራል፡፡
ከዛም ወደ አሀዱ
ሬዲዮና ቴሌቭዥን በመምጣትም የተመራማሪዎች አፍ መሆን ቀጠለ፡፡
እሱ እንደሚገልፀው
ከሆነ እስከ ዛሬ በፕሮግራሜ ያልተነኩ የምርምር ሀሳቦች የሉም ይላል፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ የሚለው ጋዜጠኛ አለምሰገድ
አበበ፤እስከዛሬዋ ቀን ድረስ 195 ፕሮግራሞችን የምርምር ውጤቶችን በማቅረብ እና ተመራማሪዎችን በመጋበዝ አንድ የዲሲሜኔሽን
መስመር ለመሆን እንደቻለ ይገልፃል፡፡ በጥናትና ምርምር ፕሮግራሙ ላይ ምርምሮች የቀረበላቸው ተቋማት
• የኢትዮጵያ ብዝሀ
ህይወት ኢንሰቲቲውት
• የኢትዮጵያሥራ
አመራር ኢንስቲትዩት
• የኢትዮጵያ
ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ባለስልጣን
• የኢትዮጵያ ግብርና
ምርምር
• ደቡብ ግብርና
ምርምር
• የኢትዮጵያ የደን
ምርምር ኢንስቲቲዩት
• ደብረ.ዘይት
ግብርና ምርምር
• የሳይንስና
ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (የቀድሞ)
• የፖሊስ ጥናትና
ምርምር ኢንስቲቲዩት
• መቀሌ ዩንቨርሲቲ
• ሀሮማያ
ዩኒቨርሲቲ
• ጎንደር
ዩኒቨርሲቲ
• ቅ.ማርያም
ዩንቨርሲቲ
• የባዮ ቴክኖሎጂ
ኢንስቲትዩት
• አዲስ አበባ
ዩንቨርሲቲ
• ሪፍት ቫሊ
ዩንቨርሲቲ
• አርባምንጭ
ዩንቨርሲቲ
• ደብረ ብርሃን
ዩኒቨርሲቲ
• ጅማ ግብርና
ምርምር
• አማራ ግብርና
ምርምር እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
በእዚህ ስራው
ምርምሮች እንዲታወቁ ተመራማሪዎች እውቅና እንዲሰጣቸው እና የምርምር መሰራረቅ እንዳይከሰት፤ ተደጋጋሚነት እንዳይኖርም ጥሬያለሁ ብዬ አምናለሁ ይላል፡፡
በቀጣይነትም
በምርምሩ ዘርፍ የምርምር ሽልማት ፕሮግራሞችንና የምርምር ኮንፈረንሶችን በሃገር ደረጃ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡
‹ከሼልፍ ላይ››
በተሠኘው ፕሮግራሜ ያቀረብኳቸው የምርምር ውጤቶችና ተመራማሪዎች ሁሉ የምደነቅባቸው ናቸው፤ ሆኖም ግን በጣም ያስደነቁኝ
ብገልጻቸው ደስ ይለኛል የሚለው ጋዜጠኛ አለምሰገድ
1/ ‹‹The
impact of white settlement policy in Kenya›› /ገርማሜ ነዋ በ1948 በኮሎንቢያ ዩነቨርስቲ የሰራው
የመመረቂያ ስራው /ከዳንኤል ማሞ ጋር/
2/
Encyclopedia Etopica የኢትዮጵያ የ14 አመታት የኢንሳይክሎፒዲያ ዝግጅት በጀርመናውያን ተመራማሪዎች አነሳሽነት
በኢትዮጵያውያንና በርካታ የአለም ተመራማሪዎች የተሳተፉበት በአምስት ቮሉም/መጻፍ ታተመ /ከዳንኤል ማሞ ጋር/
3/ ዶ/ር አበራ
ሞላ እ.ኤ.አ በ1980ቹ መጀመሪያ የግእዝ ፊደላትን ከኮምፒውተር
ያስተዋወቁ ተመራማሪ
4/ Dr Abrham
Belay INSA ም/ዳሬክተር የነበሩ /2008/ አሁን MiNT የሚንስቴር ‹‹Integrated safety and security
management platform ››
5/ Dr Adisu
Fekadu (Arba-Minch university Bio
technologist ) የእንሰት የእርሾ ዝግጅትና ግኝት እንዲሁም አዲስ የእንሰት ማዘጋጃ የኢንጂነሪንግ የቴክኖሎጂ ሽግግር ፤
6/ Dr
Fantahun Abebe ደመና መፍጠሪያ ማሽን (G2-5/15
Cloud weapon) ደመና መፍጠሪያ ማሽን (G2-5/15
Cloud weapon) እና ከኢትዮጵያ ቡና ዝርያዎች ላይ ጥናት በማድረግ ለስኳር ህሙማን ተዛማጅ ህመሞችን ማስታገሻ
7/ Dr kefena
Effa /Holota EIAR/ ‹‹Feral hours of Kundudo mountain›› የቁንዱዶ ተራራ የዱር ፈረሶች አመጣጥና
ዝርያ
8/ Professor
Birhanu Andualem (Gonder university) የጠጅ ስታንዳርድ (Honey wine standardization
research )
9/ Professor
Ensermu kelbesa (AAU) The Flora of Ethiopia & Eritrea /የኢትዮጵያና የኤርትራ እጽዋት
ጥናት በምርምር የተሳተፉ ከ90 በላይ ተመራማሪዎች የ30 አመታት በላይ ጊዜ የወሰደ ከ6017 በላይ የኢትዮጵያ እጽዋትን
የለየና ከ10 ጥራዞች እንዲታተሙ ያደረገ ምርጥ ጥናት
10/ Dr Alemu
Abebe (በደርግ ዘመን ምክትል ጠ/ሚንስትር ነበሩ እና የፕሮጀክቱ የበላይ ኃላፊ የነበሩ)
‹‹Tana
Belese 1977-1983 Melti purpose project/ የጣና በለስ ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክት›› this is alemseged 5
ጋዜጠኛ አለምሰገድ
አበበ ተጨማሪም ‹‹የድለላ ቢዝነስ የተሰኘ›› የድለላ ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረና ለተለያዩ ተቋማት የማስታወቂያ ስራዎችም የሰራ
ሰው ነው፡፡
እንዲሁም "
ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅ/ቤቱ ጋር በመሆን" ከ2003 -2005 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ አመታት
"የአዕምሯችን ውጤት" የተሰኘ የፈጠራ ሥራ አውደ- ርዕይ ያዘጋጀና ያስተዋወቀም ሰው ነው፡፡
ጋዜጠኛና ተመራማሪ
የሀገራችን ብቸኛው የጥናትና ምርምር ፕሮግራም አዘጋጅ አለምሰገድ አበበ በ2002 ዓ.ም ካገባት ውድ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ትዝታ
ክንዴ ጋር ላለፉት 11 በትዳር የኖሩ ሲሆን በእነዚህ አመታትም መክሊት አለምሰገድ እና አቤኔዘር አለምሰገድ የተባሉ ቆንጆ
ቆንጆ ልጆችን አፍርቷል፡፡
ስራውም በፍሬ
እንዲታጀብለት እንመኛለን፡፡ ይህ ሰው በስራ አለም ባሳለፋቸው አመታት አቅሙን ለአንዲትም ደቂቃ ሳይቆጥብ አሁን ድረስ እየሰራ
ይገኛል፡፡ ከዚህ በላይ መስራት እንዳለበት የሚያምነው አለምሰገድ ለንባብ ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የመንፈሰ -ጠንካራው
ቴክኖሎጂስ የአቶ ዳንኤል መብራሀቱን ግለ-ታሪክ የሰራው ጋዜጠኛ አለምሰገድ አበበ ኢትዮጵያ ታላላቅ ባለውለታዎች አሏት ብሎ
ያምናል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ