116. አሊ ሹምባሕሪ ኢብራሂም - Ali Shumbahri
በአፋርኛ የድርሰት ስራዎችን የሰራ
ተወዳጅ ሚድያና
ኮሚኒኬሽን በፊልም ፤ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ
ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም
በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ
እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡
በ5 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው
የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ በሚድያ ዘርፍ በአፋርኛ ልዩ ልዩ የሚድያ እና የጥበብ ስራ የሚያቀርበውን አሊ ሹምባህሪን
እናስተዋውቃለን፡፡
ትውልድ እና ልጅነት
አሊ ሹምባሕሪ ጥር 03 1980 ዓ.ም አላማጣ ተወልዶ ፤ አላማጣና አፋር ክልል ያሎ ወረዳ ነው እድገቱ፡፡
በአላማጣ ከተማ
ምስራቅ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1ኛ-5ኛ ክፍል ድረስ ተምሯል::
በትምህርት ቤቱም
የደረጃ ተማሪ ነበር፡፡
ከ6ኛ-12ኛ ክፍል
በአዲስ አበባ ከተማ እድገት የጎልማሶች ትምህርት ቤት ትምህርቱን
ተከታትሏል፡፡
11ኛ ክፍል ተማሪ
እያለ ነበር ግንቦት 1 ቀን 2002 ጀምሮ በሬድዮ ፋና ስራውን የጀመረው፡፡
2002 የህክምና
ትምህርት ቢጀምርም በስራ ጫና ምክንያት መቀጠል አልቻለም፡፡
በኋላም በአድማስ ዩንቨርሲቲ አይቲ ዲፕሎምና በኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቋል፡፡
የኪነ-ጥበብ ዝንባሌ ወደ ሚድያ ጉዞ
አሊ የ2ኛ ክፍል
ተማሪ እያለ ነበር ወደ ኪነጥበቡ አለም ያዘነበለው ፡፡ በዚህ
ወቅት “አቤት ጊዜ” በሚል ርእስ በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ድራማ ላይ በመሳተፍ ፣ የተለያዩ ግጥሞችን
በትግርኛና በአማርኛ ይፅፍ ነበር፡፡
በ2005 ወደ አዲስ
አበባ በመጣ ጊዜም የተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች በእድገት የጎልማሶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሚኒ ሚድያ ላይ ያቀርብ ነበር፡፡
በትምህርት ቤቱ
አስተማሪ ከነበረውና የወድያነሽና የጉንጉን አንጋፋው ደራሲ
ሀይለመለኮት መዋእል ጋር ለመገናኘትም እድል ፈጥሮለታል፡፡
አሊ ከልጅነቱ ጀምሮ
የመፃፍና የጋዜጠኝነት ሙያ ፍቅር ስላደረበት እንደሚሳካለት ባለሙሉ ተስፋ ነበር፡፡
አንድ ቀን የቅርብ
ጓደኛው መሀመድ አሊ ቢኢዶን አሊ ያገኘዋል፡፡ መሀመድ፣
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሲሆን ከአሊም ጋር
አብረው ተምረው ነበር፡፡ በሬድዮ ፋና የስራ ማስታወቂያ ሰምቶ ይነግረዋል፡፡ መስፈርቱ ደግሞ ዲግሪና ከዚያ በላይ እንዲሁም
የስራ ልምድ ስለሚጠይቅ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሌሎች ጓደኞቹ ቢነግሩትም፡ ጉዳዩን ለደራሲ ሀይለ መለኮት መዋእል አጋርቶት አንተ የሚዲያ ሰው ነህ ተስፋ ሳትቆርጥ ሞክር
ብሎት ነበር፡፡ ወደ ሬድዮ ፋና ሲመጣ በ10ኛ ክፍል ውጤት አንመዘግብም በማለት ይመልሱታል፡፡ አሊ ግን መዝግቡኝና ፈተናውን ከወደቅኩኝ እቀራለሁ፡፡ በዛ ይታይልኝ ብሎ ይጠይቃል፡፡ ከሀላፊዎች ጋር ተነጋግረው፤ በልዩ
እንዲመዘገብ ተደረገ ፡፡ በነገራችን ላይ ስራ ልምድ ስላልነበረው
ለ5 አመት የሰራበትን የሚኒሚድያ ስራ የድጋፍ ደብዳቤ ትምህርት ቤቱ ፅፎለታል፡፡
በአፋርኛ የጻፋቸው የሬድዮ ድራማዎች
አሊ ፋና ሬድዬ በአፋርኛ
ቋንቋ ክፍል ከገባ በኋላ የተለያዩ አጫጭርና ረጃጅም ድራማዎችን ፅፏል፣ አዘጋጅቷል፣
ለምሳሌ ከጻፋቸው ድራማዎች መካከልም ዲፉ፣ቴኬም፣ልኬ፣አብሱማ፣ ዓጎ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ኣጫጭር ድራማዎች ፅፏል፡፡
አሊ በአፋርኛ የማስታወቂያ ስራዎችን በመስራት ግንባር ቀደም የማስታወቂያ ባለሞያ ነው፡፡
አሊ ከአፋርኛ
በተጨማሪም የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን፤ከመናገር አልፎ “ዓሳዲ ራያ” የተሰኘ በራያ ባህል ላይ ትኩረት ያደረገ ለፊልም
የሚሆን ድርሰት ፅፎአል
አሊ ሹምባህሪይ
በ2021 እአአ ዲኬቲ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው የጋዜጠኞች
ውድድር ላይ 1ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኗል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ