የሚድያ መሪ ፍሰሀ ይታገሱ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ለሚድያ እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለውለታዎችን እያፈላለገ የህይወት ታሪካቸውን ሲሰንድ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የአንድን የሚድያ ሰው ታሪክ መሰነድ የሀገር ታሪክ ጠብቆ እንደማቆየት ነውና ይህን ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ለአንድ ሚድያ በእግሩ መቆም ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር እና ባለሙያ ሚና ይኖረዋል፡፡ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ባለፈው ሀምሌ 30 2014 የ180 በሚድያ ውስጥ አሻራ ያኖሩ ሰዎችን ታሪክ መዝገበ-አእምሮ በሚል ርእስ አሳትሞ ማስመረቁ ይታወቃል፡፡ አሁን በቅጽ 2 ‹‹የስነጽሁፍ እና የሚድያ አሻራ ያኖሩ›› በሚል የጎላ አሻራ ያስመዘገቡ ሰዎችን እናያለን፡፡ በሚድያው ዘርፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ አምጥተው በብዙዎች እየተመሰገኑ ያሉት የኢቢሲ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ ትጋትን በተግባር ያሳዩ ናቸው፡፡ ትንሽ የሰራ አይዞህ መባል አለበት ጅምሩን አይቶ በክፍተቱ መቆም ግድ ነው በሚለው የመዝገበ አእምሮ የቦርድ አባላት እምነት የአቶ ፍሰሀ ይታገሱን አበርክቶ ለትውልዱ ልናስቀምጠው ወደናል፡፡ ሊነገር የሚችል የጎላ አሻራ ያላቸው የሚድያ መሪዎችን እያመጣን ምስጋናችንን እንገልጽላቸዋለን፡፡ እስካሁን 16 የኢትዮጵያ የሚድያ መሪዎች ፈቃደኛ ሆነው ታሪካቸውን ለመስጠት እሺታቸውን የገለጹ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ ነው፡፡ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ በአሁኑ ሰአት የ36 አመት ወጣት ባለትዳር እንዲሁም የ2 ልጆች አባት ነው፡፡ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ ፈቃደኛ ሆኖ የስራ ታሪኩን ስላካፈለን ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ እዝራ እጅጉ በርካታ ሰዎችን በማነጋገር የአቶ ፍሰሀን ታሪክ እነሆ ብሏል፡፡ ...
ልጥፎች
ከጁላይ, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች

ስመኝ ቴሶ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያ ዘርፍ የተሻለ አሻራ ያኖሩ ባለሙያዎችን በተወዳጅ ዲጂታል ሚድያዎች በመጽሀፍ እና በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ግለሰብን እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሀገር ያለፈችበት እና እያለፈችበት ያለው ታሪክ ስለሆነ ባለ ታሪክ የሆኑ እና በእኛ ቦርድ ታሪካችሁን ትሰጡ ዘንድ የተጠየቃችሁ ትብብር ታሳዩ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡ ዛሬ የሚጻፈው ታሪክ ነገ ለሚጀመረው ስራ መነሻ ይሆናልና እባካዎ ታሪክዎ አንድ ዋጋ አለውና ይተባበሩን፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ የህይወት እና የስራ ታሪኳን የምታሳየን የሚድያ ሰው በአፋን ኦሮሞ የሚድያ ስራ ላይ ላለፉት 31 አመታት ተግታ የሰራች ነች፡፡ በተለይ በኢቢሲ ለ13 አመታት ‹‹ዳንጋ በተሰኘው የመዝናኛ መሰናዶ የራሷን ትልቅ አሻራ አኑራለች፡፡ ይህች ድንቅ ለኢትዮጵያ ፍቅር ያላት የሚድያ ሰው ስመኝ ቴሶ ትባላለች፡፡ እዝራ እጅጉ እና ቦጋለ ተስፋዬ ታሪኳን እንደሚከተለው አጠናክረውታል፡፡ ልጅነት ውልደቷ ሚያዝያ 27 1959አ.ም በያኔው በወለጋ ክፍለ ሀገር በቤጊ ከተማ ነበር።ከሁለት የቤተሰቦቿ ሴት ልጆች መካከል የመጀመርያዋ ልጅ ህፃኗ ስመኝ ቴሶ፤ አባቷ አቶ ቴሶ_ዲሳሳ____ ቤጊ ከተማ የሚገኘውን ትምህርት ቤት ከመመስረታቸው ባሻገር፤በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በጎበዝ መምህርነታቸው የታወቁ እንደ ነበር ይወሳላቸዋል። ስመኝ፣ በልጅነት ከአሁኗ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር አብሮ አደግ እና የልጅነት ወዳጆች እንደነበሩም ታሪኳ ያስረዳል። ልጅነትና ሙዚቃ በልጅነቷ ለሙዚቃ የጠለቀ ፍቅር የነበራት ስመኝ ከትምህርቷ ጎን ለጎን ሙዚቃንም ከማንጎራጎር አልፋ ያለችበትንም ክፍለ...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች

ሀቢባ ፋሪስ ጀማል ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ሰዎችን የህይወት እና የስራ ታሪክ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም የ180 የሚድያ ሰዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ አሳትመን ማስመረቃችን ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ቅጽ 2 እያዘጋጀን ስለሆነ የሚድያ ሰዎች የሚድያ መሪዎች የስነ-ጽሁፍ ሰዎች የህይወት ታሪካችሁን በመስጠት ወይም ፈቃደኛ በመሆን ትብብር እንድታሳዩ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን፡፡ በዚህ ጽሁፍ የህይወት ታሪኳን የምናይላት የሚድያ ሰው ወይዘሮ ሀቢባ ፋሪስ ትባላለች፡፡ በሚድያ ስራ 24 አመት የቆየች ሲሆን በአሁኑ ሰአት የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን እያገለገለች ትገኛለች፡፡ በነገራችን ላይ ይህን የሚድያ ባለሙያ ሀቢባ ፋሪስን የህይወት ታሪክ እንድንሰራ የመጀመሪያውን ጥቆማ ለሰጠን ለዲፕሎማት እና የሚድያ ሰው አቶ አማኑኤል አብርሀም ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን፡፡ ሌሎች ባለሙያዎችም የስራ ታሪኩ ያስተምራል ብላችሁ የምታምኑበትን ሰው ብትጠቁሙን ደስታችን ወደር የለውም፡፡ ሀቢባ ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰራች ሲሆን በዋልታ ቲቪ እና በኤልቲቪ ላይ በስራ ሃላፊነት ሙያዊ አደራዋን ተወጥታለች፡፡ እዝራ እጅጉ ታሪኳን እንደሚከተለው ያቀርበዋል፡፡ ትውልድ እና ልጅነት ወቅቱ የደርግ መንግስት ወደ ስልጣን የመጣበት አብዮት በአል በደማቅ የሚከበርበት፤ ክረምቱም ተጠናቆ አዲሱ አመት በአዲሰ ተስፋ በአል የሚደምቅበት እለት ነው፡፡ መስከረም 1 ቀን 1968 ዓ.ም ድንገት የመጀመሪያ የሆነ አንድ እንግዳ በአቶ ፋሪስ ጀማልና ወይዘሮ ፋጡማ ጀማል ቤት መወለዱ ይበሰራል ፡፡ በጋንዲ ሆስፒታል የነበረው የውልደት የምስራች ዜና ለበአላት በተንቆጠቆጠው አበባ ታጅቦ ፣ ይህችስ ልጅ አበባ ናት የሚል የቤት ...