ሰሎሞን ሞገስ Jump to navigation Jump to search በደብረብርሀን ከተማ የተወለደው ነገር ግን የህጻንነት እና የወጣትነት እድሜውን ከወላጅ እናቱ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈው ገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ / ፋሲል / በተለይም በሀገር ጉዳይ ላይ ባተኮሩ መሳጭ ግጥሞቹ ይታወቃል፡፡ ባለፉት 26 አመታት በገጣሚነቱና በጋዜጠኝነቱ የሚታወቀው ሰሎሞን 4 የግጥም መጽሀፎችን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በተጨማሪም በቪሲዲ ‹‹የሀገር ልጅ ጨዋታ›› የተሰኘ የኮሜዲ ስራንም ለተመልካቾች አቅርቧል ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ በመይሳው ፣ በገናናው፣በሩህ ፣በኔሽን እና በአውራ አምባ ታይምስ ጋዜጦች ላይ የሰራ ሲሆን በ2007 አ.ም ዳሸን ቢራ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ ውድድር በስነ-ግጥም ዘርፍ ተወዳድሮ አንደኛ ለመሆን የቻለ ነው፡፡በወቅቱም‹‹ ህልሞቻችሁን ፈልጉ!›› በተሰኘው ግጥሙ ከዳሸን ቢራ የአንድ መቶ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በ2001 አ.ም‹‹እውነትን ስቀሏት!››፤ በ2004 አ.ም ‹‹ከፀሀይ በታች››፤በ2006 አ.ም ‹‹ጽሞና እና ጩኸት›› ፣በ2009 አ.ም ‹‹የተገለጡ አይኖች›› የተሰኙ የግጥም መጽሀፍትን አሳትሞ ለንባብ ያበቃ ነው፡፡ሰሎሞን እነዚህም ስራዎቹ በአንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የቻሉ ነበሩ፡፡ሰሎሞን ሞገስ በስነ-ግጥምና በጋዜጣ ጽሁፎቹ የህዝቡን እውነት በመናገር ፤ ማህበራዊ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት ይታወቃል፡፡ በዚህም በወቅቱ በነበረው የኢህአዴግ ስርአት ከፍተኛ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም፣ በ2010 አ.ም ከሚወዳት ሀገሩና ከሙያው ተለይቶ በስደት ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰአት ገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ በጀርመን ሀገር ኑሮውን በስደት እየገፋ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ምንጭ ተወዳጅ ሚድያ...
ልጥፎች
ከኦገስት, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ብርሀኑ ዘሪሁን 1960ዎቹ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ‹‹መዝገበ-አዕምሮ›› በሚል ርዕስ የ180 የሚድያ ሰዎችን ታሪክ በመጽሀፍ አሳትሞ ማስመረቁ ይታወቃል፡፡ በቀጣይ ደግሞ መዝገበ-አእምሮ ቅጽ ሁለት በሚል ርእስ በቅጽ 1 ያልተካተቱ ሰዎች በቅጽ 2 ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህም አንዱ ብርሀኑ ዘሪሁን ነው፡፡ ስለ ብርሀኑ ዘሪሁን ታምሩ ከፈለኝ አጠር ያለ መጣጥፍ አዘጋጅቷል፡፡ “…ስጦታ ኖሮኝ ያቺ መጀመሪያ የፃፍኳት ጽሁፍ ባትታም ወይም ጋዜጣ ላይ ገብቼ ባልጽፍ ስጦታው ላይወጣ ይችላል፡፡ ተደብቆ ይቀር ነበር፡፡” ብርሃኑ በአንድ ወቅት ተናገረው ውልደትና እድገት ጣልያን ዳግም ጦሯን አደራጅታ ከመምጣቷ 2 አመት ቀድሞ በ1926ዓ.ም ጎንደር ከተማ ነው ደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን የተወለደው፡፡ አባቱ ዘሪሁን መርሻ የቤተክህነት ሰው ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያንን በዜማ ከማገልገል በተጨማሪ የብራና መፅሃፍትንም ይገለብጡ ነበር፡፡ እናቱ ወይዘሮ አልጣሽ አግደህ የቤት እመቤት እንደነበሩ መዛግብት ያመክላታሉ፡፡ ብርሃኑ ለቤተሰቦቹ የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ከእርሱ በፊት 5 እህትና ወንድሞች አሉት፡፡ ስድስት አመት ሲሆነው ብርሃኑ በዘመኑ ልማድ ወደአብነት ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ጀመረ፡፡ አባቱ የቤተክህነት አገልጋይ ቢሆኑም በዘመኑም ለቤተክህነት ትምህርት ከፍ ያለ ዋጋ ቢሰጥም ብርሃኑ ለትምህርቱ የሰጠው ዋጋ ከፍ ያለ አይመስልም፡፡ በአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ እስከ አስራ ሁለት አመቱ ድረስ ቢዘልቅም እውቀቱ እምብዛም ነበር ይላሉ፡፡ የግእዝ እውቀቱም ወንዝ የሚያሸግር አልሆነም፡፡ የአብነት ትምህርቱን ከመማር ጎን ለጎን ቤተሰቦቹን በስራ ያግዝ ነበር፡፡ ቤት ውስጥ ያሉትን እንስሳት እያገደ ውሎ ሲመለስም እንጨት ለቅሞ ይመጣ ነበር፡፡ ከ...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች

ይድነቃቸው ሹመቴ በአዲስ አበባ ከተማ ከሐብተጌዎርጊስ ድልድይ ገባ ብሎ በሚገኘው ሮዛ ሰፈር 1973 ዓ . ም ተወለደ። ይድነቃቸው ለፊልም ፍቅርና ቅርበት የነበረው ገና በልጅነት ዕድሜው ሲሆን እንደዛሬው በየቤቱ ቴሌቪዥን ባልገባበት ወቅት ከታናናሾቹ ጋር በመሆን ቴሌቪዥን እና PCR ባላቸው ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ቤት እየሄደ የፊልም ስራዎችን ይመለከት ነበር። በተጨማሪም የስዕል ዝንባሌ ስለነበረው ትኩረቱን በስዕሉ ላይ አድርጎ ሰርቷል።እንደ ፑሽኪን ባሉ እና በትምህርት ቤት በኩል የሚሰጡ የስዕል ስልጠናዎች ወስዷል ። ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የቪዲዮ ትምህርት የተማረ ሲሆን ዩኒቨርሳል ኦዲዮ ቪዥዋል በሚባል ትምህርት ቤት ደግሞ አጠቃላይ ከካሜራና ካሜራ ኦፕሬሽን ጋር የተያያዘ ትምህርትን ተምሯል። በቀለም ትምህርቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአፍሪካ አንድነት አትክልት ተራ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ ከተማ ሲማር በእንጦጦ አጠቃላይ የሙያ ትምህርትቤት በጀነራል መካኒካል ዲፓርትመንት ጠቅላላ የብረት ስራ ለ 3 ዓመታት ተምሯል። በ ቶም ቪዲዮና ፊልም ማሰልጠኛ ገብቶ በትምህርትቤቱ የሚሰጡ ስልጠናዎችን ወስዷል። የፊልም አፍቃሪው ይድነቃቸው ፊልም / ቪዲዮ ማከራያ ቤት ከፍቶ ከሚወደው ሙያ ጋር የበለጠ ቁርኝት ለመፍጠር እንዲያስችለው የእናቱን እገዛ በመጠየቅ ለ...