.jpg)
አለም ብርሀኔ ደስታ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያው ዘርፍ ጉልህ አሻራ የነበራቸውን ጋዜጠኞች፣ የቴክኒክ ሰዎች ፣ የሚድያ መምህራን ፣ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሥራ መሪዎችን እያፈላለገ የህይወት ታሪካቸውን እየሰነደ ይገኛል፡፡ ይህ የተሰነደ ታሪክ መዝገበ- አእምሮ መጽሀፍ ቅጽ 2 ላይ የሚወጣ ሲሆን ቅጽ 1 መዝገበ-አዕምሮ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ ታሪኩን የምናቀርብለት ሰው አለም ብርሀኔ ደስታ ይባላል፡፡ በአለም በኢትዮጵያ ሬድዮ በቴክኒክ ዘርፍ ላይ ከማገልገሉ በላይ የጣቢያው የቆየ ታሪካዊ የስቱድዮ እና የመስክ መሳሪያዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረጉ ስሙ ይነሳል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ሬድዮ የሬድዮ ቀንን ባከበረ ጊዜ ለኤግዚቢሽን የሚሆኑ የድሮ እቃዎችን በማሰባሰብ አለም የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ እንደ አለም አይነት ብርቱ ሰዎች ያለፉበት መንገድ ያስተምራል በሚል እሳቤ የህይወት ታሪኩን እዝራ እጅጉ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡ ከልደት እስከ ዕድገት መምህር አለም ከአባቱ ከአቶ ብርሃኔ ደስታ ፣ ከእናቱ ወ/ሮ ሄዋን ተድላ የካቲት 25 1969 ዓ.ም በቀድሞ ትግራይ ክፍለ ሃገር በምስራቃዊ ዞን ደብረ ዳሞ ገዳ...