
187ክብሬ ተስፋዬ አበበ በታላላቅ ሁነት አዘጋጆች የምትመረጥ ባለሙያ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያ ዘርፍ ለሀገራቸው አንድ አሻራ ያኖሩ ሰዎች እየሰነደ ለመጪው ትውልድ እያስቀመጠ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከ1950 ጀምሮ በየዘመኑ በሀገሪቱ የሚድያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ገብተው የራሳቸውን ቀለም ፈጥረው የተገኙ ሰዎችን ከያሉበት ፈልገን የህይወት ታሪካቸው እንዲታወቅ ፤ ራሳቸውም ራሳቸውን እንዲያውቁ ወደ ኋላ መለስ ብለው ምን አበርክቼ ይሆን እንዲሉ መንገዱን እያመቻቸን ነው፡፡ መዝገበ-አእምሮ የ180 የሚድያ ሰዎች ታሪክ የሚለው ባለ 600 ገጽ መጽሀፋችንም ሀምሌ 30 2014 በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ ታሪካቸው በዊኪፒዲያ፤ በተወዳጅ ሚድያ ድረ-ገጽና በልዩ ልዩ መንገድ ከሚሰነድላቸው ብርቱ የሚድያ ሰው ፤ የመድረክ መሪ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆነችው ክብሬ ተስፋዮ ናት ፡፡ ክብሬ ተስፋዬ በመድረክ መሪነት ትታወቃለች፡፡ በጦቢያ ዝግጅትና በቀደመ ስሙ ጣይቱ እና በአሁኑ ስሙ የእቴጌ እልፍኝ በተሰኙ ሁለት ሴቶችና ሃገር ላይ በሚያተኩሩ ፕሮግራሞቿ ተመልካች በደንብ ያውቃታል፡፡ በሬዲዮ ፋና እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? በተሰኘው ተወዳጅ ፕሮግራምም የመጀመሪያዋ ሴት አወያይ በመሆን በሩን ለሴቶች ከፍታለች፡፡ ትውልድ ልጅነትና ትምህርት ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ ህዳር 27 ቀን 1972 ዓ.ም ከአባቷ ከመምህር ተስፋዬ አበበ እና ከእናቷ ከወ/ሮ መሰለች ፈለቀ በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ...