ልጥፎች

ከሜይ, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
                 178.ጣሰው ተፈራ ዘለቀ         የለጌው ባለሟል ጣሰው ተፈራ ፣ መምህርና ጋዜጠኛ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት መኖሪያውን በአሜሪካ ያደረገ ሲሆን ለ20 አመታት በለገዳዲ ሬድዮ በቅዳሜና እሁድ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ ያገለገለ ባለሙያ ነው፡፡ ብዙዎች ገና በተማሪነት ዘመናቸው የለገዳዲ ደጃፍ የረገጡ ሲሆን በትህትና እነዚህን ወጣቶች ካሳተፉ ባለውለታዎች አንዱ ጣሰው ተፈራ ነው፡፡ የመዝገበ-አእምሮ የሚድያ ሰዎች ታሪክ አዘጋጅ  እዝራ እጅጉ ገና በታዳጊነቱ የመጀመሪያውን ተሰጥኦ እንዲያወጣ በር የከፈተለት ጣሰው ተፈራ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ለብዙዎች ስኬታማ መሆን ምክንያት የሆነ ሰው ማነው? የሚለውን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡       ትውልድ እና እድገት ጣሰው ተፈራ የተወለደው በአሩሲ ከሁሩታ ከተማ 12 ኪ.ሜ ያህል ርቃ በምትገኘው ሎዴ ጫንጌ በምትባል ቦታ ነው ።ጊዜውም ጥቅምት 27 ፤1950 ዓ.ም ነበር ። የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጁ ጣሰው የአርሶ አደር ልጅ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአርብ ገበያ በአሁኑ ሎዴ ጫንጌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል ። የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለ የመምህር ብርሃኑን እና የመምህር አሰፋን ውለታ የሚረሳ አይደለም ።ፊደል እንዲለይ ከማድረግ ጀምሮ እስከ ወስጄው ላስተማረው ድረስ ከፍተኛ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ስድስተኛ ክፍል ሲደርስ የምንጊዜም የማይረሳው የህብረተሰብ ትምህርት መምህሩን መምህር ተክለብርሃን ነው።መምህሩ በሚያምር ድምጹ ከጠረጴዛው ላይ በመቀመጥ ስለሜሶፖታሚያ ታሪክ የሚያነብላቸውን ዛሬው ድረስ አይረሳውም ። መምህር...
ምስል
                         177.እዝራ እጅጉ በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ የ ህትመት ሚዲያው ፈርጣማ ክንዱን ባሳየበት 1980 ዎቹ መጨረሻ፣ ትታተም በነበረች “ ኩኩሉ ” የልጆች መጽሔት ላይ አንድ የ 15 ዓመት ብላቴና የወደፊት ምኞቱን አሰፈረ። በየትኛው የትምህርት ተቋም ምን መማር እንደሚፈልግ፣ ምን ዓይነት መጽሐፍ ማሳተም እንደሚሻ፣ “ እግዚአብሔር ብሎለት ” ሃብታም ቢሆን መክፈት ስለሚፈልገው ድርጅት ... የመሻቱን ሁሉ መጽሔቷ ላይ በዝርዝር አሰፈረ። ምንም እንኳ   የዚህ ጽሁፍ አቅራ ቢበዘመኑ ለአቅመ ንባብ ባልደርስም ምኞቱን ያነበቡ አዋቂዎች ግን “ ያሳድግህ ” ከማለት አልፈው “ የምኞቱን ቢያሳካስ ” ብለው ያሰቡ አይመስለኝም። ይህ ከሆነ ከሶስት አስርታት በኋላ፣ የያኔው ብላቴና አሁን ባለው ዘመኑ የሆነውንና በለጋ እጁ ከትቦ የልጆች መጽሔት ላይ ያኖረ የልጅነት ምኞቱን ብናስተያይ መስመር በመስመር ይገጥማሉ። የፈለገውን ተምሮ፣ ያሻውን ጽፎ፣ ያሰበውን ድርጅት ከፍቷል።   ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ተመርቆ፣ የተፈጥሮ ውበት ስለሆነው የሰው ልጅ መጽሐፍትን ጽፎ፣ የሥነ ጽሑፍ ፍቅርና ችሎታ ላላቸው ልጆች የስራ እድልን የፈጠረ “ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ” ን አቁሟል፦ እዝራ እጅጉ። የስራ እድሉ በረከት ከደረሳቸው አንዱ ነኝ   እኔ አማረ ደገፋው፤ ዛሬ ሌላ እድል ደር...