ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
                                        ሌ/ኮሎኔል ፋንታሁን ተምትሜ     ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በውትድርና ሙያ   ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን   ባለሙያዎች የህይወት ታሪክ እያወጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ወታደራዊ ሳይንስን መሰረት በማድረግ ሀገራቸውን   በእውቀት ያገለገሉ ሰዎች ታሪክ ተሞክሯቸው ለአዲሱ ትውልድ አንድ ነገር ያስተምራል ብለን እናስባለን፡፡ ዋናው ግባችን አዲሱ ትውልድ የቀደሙ የታሪክ ባለውለታዎች በወጉ እንዲያውቅ ማድረግ ስለሆነ እርስዎም ታሪኩ መሰነድ አለበት የሚሉትን ሰው ይጠቁሙን፡፡ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉትን በዚህ ገጽ ላይ እናቀርባለን፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ ታሪካቸው የሚታየው ሌተናል ኮሎኔል ፋንታሁን ተምትሜ ሲሆኑ ከ31 አመት በፊት ነበር ህይወታቸው ባልታወቀ ሁኔታ ያለፈው፡፡     እኒህ በወታደራዊ እውቀት   የካበተ ልምድ ባለቤት የሆኑ ሰው ብዙ የሰሩ ቢሆኑም ብዙ አልተዘመረላቸውም ብለን ስላሰብን ይህን የህይወት ታሪካቸውን አውጥተነዋል፡፡ ወደፊት ከቤተሰቡ ጋር በመነጋገር እና አንድ ላይ በመሆን   በህይወታቸው ዙርያ ተጨማሪ የስነዳ ተግባራትን እናከናውናለን፡፡   ይህን የህይወት ታሪክ ስናሰናዳ ልጃቸው ህይወት ፋንታሁን እና አብሮ አደግ ጓደኛቸው ኮሎኔል አደፍርስ   ታፈሰ ላደረጉልን ትብብር ምስጋናችን...
ምስል
                 አቶ ወርቁ ተገኝ     ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በድርሰትና በጋዜጠኝነት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን   ባለሙያዎች የህይወት ታሪክ እያወጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዋናው ግባችን አዲሱ ትውልድ የቀደሙ የታሪክ ባለውለታዎች በወጉ እንዲያውቅ ማድረግ ስለሆነ እርስዎም ታሪኩ መሰነድ አለበት የሚሉትን ሰው ይጠቁሙን፡፡ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉትን በዚህ ገጽ ላይ እናቀርባለን፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ ታሪካቸው የሚታየው   ጋዜጠኛ ወርቁ ተገኝ ናቸው ፡፡ እኒህ ሰው ከአንድ አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን እዝራ እጅ እና ቤርሳቤህ ጌቴ እንደሚከተለው የህይወት ታሪካቸውን ሰንደውታል፡፡ ልጃቸው ብሌን ወርቁ ይህ ጽሁፍ በዚህ መልኩ እንዲወጣ ላደረገችው አስተዋጽኦ ማመስገን እንወዳለን፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ከተማ በ1941 ዓ.ም የተወለዱት አቶ ወርቁ ተገኝ እናታቸው ወ/ሮ አስካለ   አሸብር እና አባታቸው አለቃ ተገኝ ስመኝ ከወለዷቸው ልጆች መካከል 13ኛው ልጃቸው ሲሆኑ እናታቸው ወ/ሮ አስካለ ብዙ ልጆች ስለሞቱባቸው ''እርሱ እንኳን በህይወት ቢተርፍ'' በሚል አዲስ አበባ አጎታቸው ዘንድ   መጥተው እንዲማሩ ተደርገዋል።     የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም   በአዲስ አበባ ነበር ያጠናቀቁት። አቶ ወርቁ የስራ አለምን የተቀላቀሉት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሬድዮ ክፍል ተለማማጅ ሆነው በመግባት ነበር፡፡ ቀጥለውም በጋዜጠኝነት ለረዥም አመታት ሰርተዋል።በስራቸው በጣም ትጉህ የነበሩት አቶ ወርቁ የጋዜጠኝነት ሙያቸውን ይበልጡን ለማሻሻል ወደ ጀርመን እና አሜሪካ ሲራኩስ ዩኒቨርስቲ ተ...
ምስል
          መዝገቡ አባተ ገብሩ        ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በድርሰትና በጋዜጠኝነት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን   ባለሙያዎች የህይወት ታሪክ እያወጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዋናው ግባችን አዲሱ ትውልድ የቀደሙ የታሪክ ባለውለታዎች በወጉ እንዲያውቅ ማድረግ ስለሆነ እርስዎም ታሪኩ መሰነድ አለበት የሚሉትን ሰው ይጠቁሙን፡፡ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉትን በዚህ ገጽ ላይ እናቀርባለን፡፡ አሁን በዚህ ጽሁፍ ታሪካቸው የሚታየው የደራሲና የጋዜጠኛ መዝገቡ አባተ ነው፡፡ እኒህ ሰው ከ12 አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን እዝራ እጅጉ እንደሚከተለው የህይወት ታሪካቸውን ሰንዶታል፡፡ ልጃቸው ጸሀይ መዝገቡ አባተ ይህ ጽሁፍ በዚህ መልኩ እንዲወጣ ላደረገችው አስተዋጽኦ ማመስገን እንወዳለን፡፡         ትውልድ ልጅነት እና ትምህርት     ደራሲና ጋዜጠኛ መዝገቡ አባተ ከአባቱ ከአቶ አባተ ገብሩና ከእናቱ ከወ / ሮ ቦጋለች ወልደፃድቅ በሀረርጌ ክፍለ-ሀገር በጋራሙለታ አውራጃ ግረዋ ከተማ ህዳር 23,1923 አ . ም ተወለደ፡፡ አባቱ አቶ አባተ ገብሩ የጣልያንን ወረራ በመቃወም በሀረር በኩል የዘመተውን ጦር ተቀላቅለው ሲፋለሙ በጠላት እጅ ተገደሉ፡፡ መዝገቡ አባተ ገና በ5 አመት እድሜው አባቱን በጦርነቱ ቢያጣም እናትም አባትም ሆነው ያሳደጉት እናቱ   እርሱ እንደሚጠራቸው እናዬ ነበሩ፡፡ እድሜው ለትምህርት ሲደርስም   በአካባቢው በሚገኝ የቄስ ትምህርት ቤት ገብቶ ግእዝና አማርኛ ትምህር...