ልጥፎች

ከዲሴምበር, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
                 ዳይሬክተር አለሙ ቶሎሳ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያው ዘርፍ የጎላ አሻራ ያኖሩ ባለሙያዎችን የህይወት ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ብዙዎቹ ከሀገር በሙያቸው አንድ ቁምነገር ሰርተው ነገር ግን ያልተሰነደላቸው ወይም ያልተነገረላቸው   ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ቃለ-ምልልስ እንኳን ሰጥተው አያውቁም፡፡ በዚህ ምክንያት የሰሩት ስራ ይደበቃል፡፡ የሀገር ታሪክም እንደዋዛ ተረስቶ ይቀራል፡፡ ይህ ክፍተት እንዳይኖር ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሙሉ ፍቅር ፤ መሰጠትና ፍላጎቱ ተግባሩን እየተወጣ ይገኛል፡፡ የህይወት ታሪካቸው በዚህ ጽሁፍ የምናይላቸው አቶ አለሙ ቶሎሳ በኢቲቪ ያገለገሉ ሰው ናቸው፡፡ ለዚያውም 44 አመት ፡፡ እዝራ እጅጉ ታሪካቸውን እንደሚከተለው ሰንዶታል፡፡ በህዳር ወር በ 23 ኛው ቀን 2015 ላይ ጠዋት 4:40 በብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ከአቶ አለሙ ቶሎሳ ጋር ተገናኝተን ባደረግነው ቆይታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ 44 ዓመታት ሲያገለግሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ   ብዙ ነው፡፡ ከልጅነት ከጀመረው የህይወታቸው መልክ አንድ ብለን እንጀምራለን፡፡           ትውልድ እና ልጅነት   በቀድሞው አጠራር አዲስ ዓለም በአሁኑ ደግሞ ኤጀሬ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በ 1948 ዓ . ም ነበር የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እስከ 4 ኛ ድረስ ብቻ እዚያው የትውልድ ስፍራቸው ላይ ተምረዋል፡፡ ከ 4 ኛ ክፍል በኋላ እስከ 2 ...