ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
      አስናቀች ጸጋዬ/ ከመጀመርያዎቹ የኢቲቪ የቪድዮ ኤዲተሮች አንዷ     ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሚድያ ሥራ ውስጥ የጎላ ሚና የነበራቸውን ባለሙያዎች የህይወት ታሪክ በመሰነድ ለታሪክ እያስቀመጠ ይገኛል፡፡ ቲቪ ሲነሳ የቪድዮ ኤዲቲንግ ዘርፍ ባለሙያዎች ፤ የማሰራጫእና የቴክኒክ   ትጉሀን ባለሙያዎች ሚናቸው ጉልህ ነው። ከጋዜጠኛው እኩል በሚባል ደረጃ ለስራው መሳካት አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡ በመሆኑም መዝገበ አእምሮ ላይ የቲቪ እና የሬድዮ እና የኤዲቲንግ ባለሙያዎችን ከጋዜጠኛው ታሪክ ጎን ለጎን እያወጣን እንገኛለን፡፡ ከዚህ ቀደም መዝገበ-አእምሮ ቅዳሜ ሀምሌ 30 2014 ታትሞ መመረቁ ይታወቃል፡፡ በቀጣይ መዝገበ-አእምሮ ቁጥር 2 ላይ ታሪካቸው ከሚሰነድላቸው ጠንካራ የቲቪ የቪድዮ ኤዲተሮች አንዷ አስናቀች ጸጋዬ ናት፡፡ አስናቀች በዚህ ሙያ ከ1974 ጀምሮ የሰራች ስትሆን አጠቃላይ በሙያው ላይ የ40 አመት ልምድ ካካበቱ ጥቂት ጉምቱ ወይም ከመጀመርያዎቹ የቲቪ የቪድዮ ኢዲተሮች አንዷ ነች፡፡ የህይወት ታሪኳ ተግተው ለሚሰሩ ባለሙያዎች የሚጠቅም   ሆኖ ስላገኘነው ትውልድ እንዲያነበው ስንል ሰንደን አስቀምጠነዋል፡፡ ታሪኩን እዝራ እጅጉ እንደሚከተለው ያቀርበዋል፡፡   አስናቀች ፀጋዬ ነሲቡ   በ 1953 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ወረዳ ተወለደች፡፡ ትምህርቷን በእቴጌ መነን እና በተፈሪ መኮንን ተምራ በ አካውንቲንግ ተመረቀች፡፡ በ 1971 ዓም አቡነ ጴጥሮስ በሚገኘው የሬድዮና   ዜና አገልግሎት ግቢ   በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሂሳብ ክፍል ተመደበች ። በተፈጥሮዋ ፈጣን እና ቀልጣፋ ስለሆነች...