
ጋዜጠኛ አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ሰዎችን ታሪክ እያፈላለገ ለትውልድ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም በሐምሌ 30 2015 ዓ . ም ‹‹ መዝገበ - አእምሮ ›› በሚል ርእስ መጽሐፍ አሳትሞ ማስመረቁ ይታወቃል፡፡ በቅጽ ሁለት ታሪካቸው ከሚሰነድላቸው የሚድያ ሰዎች አንዱ አማኑኤል አብርሃም ነው፡፡ አማኑኤል በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ከምስረታ አንስቶ ከነበሩ ባልደረቦች አንዱ ነው፡፡ ዜና በብዛት በመስራት የሚታወቀው አማኑኤል አብርሃም 2 መጽሐፎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡ የአማኑኤልን ታሪክ አንተነህ ደመላሽ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡ የሚድያ ሰው አማኑኤል አብርሃም ÷ በወርሃ ግንቦት በዕለተ - እሁድ ምሽት 12 ሰዓት በ 1961 ዓ . ም በቀድሞው አጠራር ዎላይታ አውራጃ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ቡጌ በምትባል መንደር ተወለዱ፡፡ ምጣኔ እድገታቸው ለአቅመ - ትምህርት ሲደርስም በመንደራቸው ወደሚገኘው ቡጌ ትምህርት ቤት ከ 1 ኛ እስከ 6 ኛ ክፍል ተማሩ፡፡ በመቀጠል 5 ኪ . ሜ ርቆ በሚገኘው ‹‹ ጋቼኖ ›› በሚባል መንደር በማምራት የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ በየ 2 አመት ልዩነት ትምህርት ቤት እየለወጡ የሚማሩት የ 9 ኛ እና 10 ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ...