ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
          175.  መሰለ መንግስቱ -   ህልሙን ያሳካ ታላቅ ሰው ለሁለት አመታት ‹‹ ስካይ ስፖርት ›› የምትል ጋዜጣን ሲያሳትም የቆየ አንድ ጉጉ ወጣት፣ ወደ ሸገር ኤፍ ኤም ተሻግሮ በ 102.1 አየር ሞገድ ድምፁን ሲያንቆረቁር፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ አድርጎት በፊት ገፁ ምስሉን ይዞ ወጣ። በቃለ - መጠይቁ መሃል " የወደፊት ህልምህ ምንድን ነው ?" የሚል ጥያቄ ተነሳለት፤ መለሰ፦ "24 ሰዓት የሚሰራ የስፖርት ሬዲዮ ጣቢያ መክፈት " ከአመታት በኋላ አፍላው አንጋፋ ሁኖ ህልሙ ሰመረና በነሃሴ 2007 ዓ . ም በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 በኩል " ኦያያያ ... አስደናቂ ነበር " ሲል ተደመጠ። መሰለ መንግስቱ።   መሰለ መንግስቱ እግር ኳስን በሬዲዮ ተመልከቱ ይህች በሁለት መስመር ግጥም ልክ ተሰፍታ የተቆረጠች ስንኝ ለዓመታት አየር ሞገድ አቆራርጦ በሬዲዮ ለሚደርሰን ቀጥታ የእግር ኳስ ስርጭት ስም ሁና አገልግላለች።   እግር ኳስን ቀጥታ ሲያስተላልፍልን የምናውቀው መሰለ ጥሩ እግር ኳስ ተጫዋች እንደነበር ራሱም ይናገራል። ታምረኛ እግሩ ጎል ብቻ ሳይሆን ሚስትም እንዲያገባም አግዞታል። በመጋቢት 5 ፣ 1958 ዓ . ም አዲስ አበባ " በቅሎ ቤት " በተባለ ሰፈር በኩል ነው ወደ እዚች ምድርብቅ ያለው። በአቶ መንግስቱ ገ / ስላሴ እና በወ / ሮ አቻምየለሽ መኩሪያ ቤት የነበረና ራሱ " ጣፋጭ "   ሲል የሚገልፀውን ልጅነቱንም በዚያው ...