ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
             148. ኡመር አሊ ከይሪ -የአፋርኛ ጋዜጠኛ   ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣ በቅርቡ ክምችተ-አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ አሳትሞ ያስመርቃል፡፡ ታሪካቸው በመጽሀፉ ውስጥ ከሚሰነድላቸው አሻራ ካኖሩ የሚድያ ሰዎች አንዱ   ኡመር አሊ ከይሪ ናቸው፡፡   እኒህ ሰው   በተለይ በአፋርኛ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካኖሩት ውስጥ ናቸው፡፡ ግለ-ታሪካቸው እንደሚከተለው ተጠናክሯል፡፡           የሚድያ ሰው ኡመር አሊ ከይሪ 1942 ዓ . ም በቀድሞ አዳልና ኢሳ አውራጃ ከድሬዳዋ 30 ኪ . ሜ ትር ርቀት ላይ በምትገኝ ኤሬር በምትባል ቦታ ተወለዱ፡፡ ኡመር እንደማንኛውም የአፋር አርብቶ አደር ልጆች ፍየል፣ ከብትና ግመል በመጠበቅ ነው ያደጉት፡፡ በዚህ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው አዳሪ ትምህርት ቤት የመማር እድል አግኝተው በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርታቸው ተከታትለዋል፡፡ 12 ኛ ክፍል እንደጨረሱ ተንዳሆ፣መልከወረር እርሻ ምርምር ተቀጥረው ለ2 አመታት ሰርተዋል፡፡ እዚህ እየሰሩ ባለቡት ጊዜ ነበር የኢትዮጵያ ሬድዮን ማስታወቂያ ከጋዜጣ አንብበው፣ ከልጅነታቸው ጀምረው የህዝብ ጉዳይ በጋዜጠኝነት ሙያ ህዝቤን የማገልገል ፍላጎት ስለነበራቸው ሳይውሉ ሳያድሩ በፍጥነት አመልክተው የፈተናውን ቀን መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ከጣቢያው ለፈተና ተጠርተው ብቸኛ ተወዳዳሪ ስለነበሩ አስፈላጊው ጥያቄና...