ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
           1 37.   ተፈራ   ሻውል  - Teferra Shiawl- Kidanekal           አምባሳደር ተፈራ ሻውል     ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኑኬሽን ለሀገር ያገለገሉ ሰዎችን ታሪክ እየከተበ ለትውልዱ እያስቀመጠ ይገኛል፡፡ አሁን ታሪካቸው የሚነገርላቸው ሰው በአንድ በኩል በጋዜጠኝነት ያገለገሉ ሲሆን ረጅም ዘመናቸውን ደግሞ በዲፕሎማሲ የሰሩ ናቸው፡፡ ብስራተ ወንጌል ከዛሬ 59 አመት በፊት ሲጀመር ይህ ብስራተ ወንጌል ነው የሚለውን መክፈቻ ያሰሙ ናቸው፡፡ በጀርመን ፤ በካርቱም ፤ እንዲሁም በቼክ ሪፖብሊክ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡  በተባበሩት መንግስታት ለረጅም አመታት የሰሩ ናቸው፡፡ የቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር ተፈራ ሻውል ፡፡ራሳቸው በአምባሳደርነት ከማገልገላቸው በላይ ልጃቸውም ወደዚህ ክቡር ሙያ እንዲሳብ በር የከፈቱ ናቸው፡፡ ልጃቸው ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሄኖክ  ተፈራ በአሁኑ ሰአት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው፡፡ እነሆ አቶ ተፈራ ሻውልን ታውቁ ዘንድ ይህን ጽፈናል፡፡ ይህንን አጭር ዘገባ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉና አማረ ደገፋው እንደሚከተለው አሰናድተውታል፡:  1     እንደ ኢትዮጵያ የዘመን ቀመር 1950 ዎቹ አጋማሽ ..... በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ታሪክ ከማሟሻዎቹ አንዱ የሆነው የብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ተመርቆ ስራውን ሲጀምር የተሰማው የመጀመሪያ ድምፅ የእርሳቸው ነው፦ የአምባሳደር ተፈራ ሻውል። " ይህ የብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ነው " ። ከግማሽ ከፍለ ዘመን በላይ ወደ ኋላ መለስ ብለው ወቅቱን ሲያስታውሱ ' ንጉሰ ነገ...