ልጥፎች

ከጁላይ, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ምስል
                ሁለገቧ አርቲስት አዳነች ወ / ገብርኤል                            ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በኪነጥበብ እና በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ያልተነገረላቸው ባለሙያዎችን በአማርኛ   ኢንሳይክሎፒዲያ ላይ ሲያወጣ ነበር፡፡ ሀገር የምታድገው የሰራ ሰው ልምድና ታሪኩን ሲያካፍል ብለን እናምናለን-እንደ ተወዳጅ፡፡ ያለ አንዳች እረፍት የሰራ ሰው ለብዙዎች አርአያ እንደመሆን ስለሚታመን ታሪኩ ይሰነዳል፡፡ ከእነዚህ ታሪካቸው ከሚሰነድላቸው ሰዎች መካከል ሁለገቧ አርቲስት አዳነች ወልደገብርኤል ናት፡፡ ማስረሻ መሀመድ የጻፈውን ጽሁፍ ከተጨማሪ ምስክርነቶች ጋር አክለን የአዳነችን የህይወት ገጽ መፈተሸ እንጀምራለን፡፡ ይህ ጽሁፍ ባለታሪኳን በማስፈቀድ ይሁኝታ በማግኘት የተሰራ ነው፡፡ በተጨማሪም ባለታሪኩዋ ከሰጠችን ብዙ ካልታዩ ምስሎች ጋር የህይወት ታሪኳን አሰናድተናል፡፡መልካሙ ሁሉ ለአዲ.. እናከብርሻለን፡፡   አርቲስት አዳነች ከአባቷ ወ / ገብርኤል ገብረ ማርያም እና ከእናቷ ፋና አምባው በ 1952 ዓ . ም ይህችን አለም ‹‹ ሀ ›› በማለት ይፋትና ጠሞ በሚባል አውራጃ ካራቆሬ በተባለ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተወለደች፡፡ እንደማንኛውም ልጅ እናትና አባቷን በቤት ውስጥ በማገልገል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በዚህችው ካራቆሬ በተባለች ትንሽ ከተማ ውስጥ ...