.jpg)
165. አላዛር አስገዶም ---የታላቆቹ እኩያ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን፣ በቅርቡ መዝገበ - አእምሮ / ኢንሳይክሎፒዲያ / በሚል ርእስ የሚድያ እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን ታሪክ በጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ አሳትሞ ያስመርቃል፡፡ ታሪካቸው በመጽሀፉ ውስጥ ከሚሰነድላቸው አሻራ ካኖሩ የሚድያ ሰዎች አንዱ ጋዜጠኛ አላዛር አስገዶም ነው፡፡ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን እስከ አሁን ታሪካቸውን ከሰነደው የሚዲያ ሰዎች በእድሜ ትንሹ እርሱ ነው። ከልቡ መሻት ጋር የገጠመ የጋዜጠኝነት ስራው የታላቆቹ እኩያ እንዲሆን ስለበቃው በልዩ መስፈርት ታሪኩን እንደሚከተለው እንሰንዳለን። ጋዜጠኛ አማረ ደገፋውና ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ የአልአዛርን ግለ ታሪክ እንደሚከተለው አጠናክረውታል፡፡ በሁሉም ዋጋ ጋዜጠኛ መሆን አለብኝ የ 2005 ዓ . ም መስከረም ከጠባ ጥቂት ከራርሞ .... የሙዚቃው ሰው ሰርፀ ፍሬስብሃት ለፋና ኤፍኤም አንድ ሰው ጠቆመ። " ይህን ወጣት ብትቀጥሩት ታተርፋላችሁ " አለ። ፋናዎች ሰርፀን ሰሙና ለወጣቱ የ 20 ቀናት የሙከራ ጊዜ ሰጡት። ተሞካሪው እነዚህን 20 ቀናት በትጋት ሁኖ ፈፀመ። ሞካሪዎቹ ዝም አሉ፤ እርሱ ግን ትጋቱን ቀጠለ። ከተቀጣሪ ሰራተኞች እኩል ስራም ስምሪትም ይሰጠዋል፤ በብቃት ይሰራል .... አሁንም ዝም...